ጓደኛ
የሕይወት ዛፍ
ጥር 2024 (እ.አ.አ)


“የሕይወት ዛፍይወት ዛፍ ፣ ጓደኛ ፣ ” ጥር 2024(እ.አ.አ)፣ 26_27።

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2024 (እ.አ.አ)

የሕይወት ዛፍ

ምስል
Alt text

ምስሎች በአንድሪው ቦስሊ

ሌሂ ነቢይ ነበር። እግዚሐብሔር፣ ቤተሰቦቹን ወደቃልኪዳኗ ምድር እንዲወስድ ነገረው። በሚጓዙበት ጊዜም ስለ አንድ መልካም ዛፍ ህልም አይቶ ነበር። የሕይወት ዛፍ ይባል ነበር።

ምስል
alt text

ዛፉም ጣፋጭ ነጭ ፍሬ አፈራ። ሌሂ ከእርሱ በበላ ጊዜ ደስታ ተሰማው። ቤተሰቦቹም እንዲሞክሩት ፈለገ።

ምስል
alt text

ሌሂ ወደ ዛፉ የሚመራውን የብረት በትርም አይቶ ነበር። ሰዎቹም ወደ ዛፉ ለመሄድ እና ፍሬውን ለመብላት በትሩን ያዙ።

ምስል
alt text

በሌሂ ህልም ውስጥ የነበረው የሕይወት ዛፍ የእግዚሐብሔር ፍቅር ነው። በትሩም ቅዱሳት መፃሕፍት ናቸው። ቅዱሳት መጽሃፍትን ስናነብ ወደ ሰማይ አባታችን እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንቀርባለን።

የሚቀባ ገፅ

ቅዱሳት መፃሕፍት ስለኢየሱስ ያስተምራሉ።

ምስል
alt text here

ምስል በ አዳም ኮፎርድ

ስለኢየሱስ የምትወዱት ታሪክ የትኛውን ነው?