ለወጣቶች ጥንካሬ
ዳግም ከመምጣቱ በፊት በክርስቶስ ማመን
ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)


“ዳግም ከመምጣቱ በፊት በክርስቶስ ማመን፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ)

ጄረም

ዳግም ከመምጣቱ በፊት በክርስቶስ ማመን

ኔፋውያን አዳኙ ከመምጣቱ በፊት እምነት ነበራቸው፣ እኛም እርሱ ዳግም ከመምጣቱ በፊት እምነት ሊኖረን ይችላል።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ኔፋውያንን እየጎበኘ

ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በአዳኙ ማመን ምን ሊመስል እንደሚችል አስባችሁ ታውቃላችሁን? የጥንታዊ ኔፋውያን እንዲሁ ማድረግ ነበረባቸው—“ወደ መሲህ ወደፊት [መመልከትና] እርሱ እንደመጣም አይነት እንደሚመጣ [ማመን]” (ጄረም 1፥11)።

በአሁን ጊዜ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ኖረ፣ እንደሞተ እና እንደተነሳ የሚመሰክሩ የቅዱሳት መጻህፍት እና የታሪክ መዛግብት አሉን። እኛ አስቀድሞ በመጣው አዳኝ እናምናለን። ግን ደግሞ ዳግም በሚመጣው አዳኝም እናምናለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ኔፋውያን ለሚከተሉት እምነት ነበራቸው፦

ምስል
ንጉሥ ቢንያም እና ሚስቱ እየጸለዩ

ለኃጢአታቸው ይቅርታ እንደሚያገኙ።

“ማንኛውም ክርስቶስ ይመጣል በማለት የሚያምን ለኃጥያቱ ስርየት ያገኛል እርሱም በመካከላቸውም እንደመጣን አይነት በታላቅ ደስታ ሃሴት ይሆናሉ” (ሞዛያ 3፥13፤ አጽንኦት ተጨምሮበታል)።

ምስል
ኢኖስ

ራሳቸውን ይቅር እንደሚሉ።

“እናም ድምፅ ወደእኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፦ ኢኖስ ኃጢያትህ ይቅር ተብሎልሃል። … ስለሆነም፣ በደሌ ተወግዶልኛል። እናም ጌታ፣ ይህ እንዴት ሆነ? አልኩት። እናም እርሱም አለኝ፦ ባላየኸውና ሰምተህ በማታውቀው በክርስቶስ ባለህ እምነት ምክንያት ነው። እናም እራሱን በአካል ከመግለፁ በፊት ብዙ አመታት ያልፋሉ፤ … ሂድ እምነትህ አድኖሃል” (ኢኖስ 1፥5–8 አጽንኦት ተጨምሮበታል)።

ምስል
ያዕቆብ እየሰበከ

ተአምራትን እንደሚያደርጉ።

“ስለክርስቶስ ማወቃችን እናም እርሱ ከመምጣቱ ከብዙ መቶ አመታት በፊት በክብሩ ተስፋ [ነበረን] …። በእውነት በኢየሱስ ስም ስንገስፅ ያም ዛፉ፣ ወይንም ተራራው ወይም የባህሩ ሞገድ ይታዘዝልናል” (ያዕቆብ 4፥4፣ 6 አጽንኦት ተጨምሮበታል)።

ምስል
ሞሮኒ በሰሌዳዎች ላይ እየጻፈ

መገለጥን እንደሚቀበሉ።

“ክርስቶስ ከመምጣቱም በፊት እንኳን በእምነታቸው እጅግ የበረቱ ብዙዎች ነበሩ፤ እነርሱም በመጋረጃው ስር ሊጠበቁ አልተቻሉም፤ ነገር ግን በእውነትም በእምነት አይን [አዩቸው]” (ኤተር 12፥19፤ አጽንኦት ተጨምሮበታል)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት፣ እኛ ለሚከተሉት እምነት ሊኖረን ይችላል፦

ስርየትን ለማግኘት፣ እራሳችንን ይቅር ለማለት፣ ተአምራትን ለማድረግ እና መገለጥን ለመቀበል (ልክ እንደ ኔፋውያን)።

ምስል
አንድ ወጣት በቤተክርስቲያን ውስጥ እየዘመረ

ለእርሱ ዳግም ምፅዓት እራሳችንን ማዘጋጀት።

ቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ ስንጥር፣ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ለመኖር እየተዘጋጀን ነን። “እነሆም፣ ይህ ጊዜ ለሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የዝግጅት ወቅት ነው፤ አዎን፣ እነሆ የዚህ ህይወት ቀናት ሰዎች ስራቸውን የሚያከናውኑባቸው ቀናቶች ናቸው” (አልማ 34፥32)።

ምስል
ወጣቶች ከቤተመቅደስ ፊት ለፊት

ዓለምን ለምጸዓቱ አዘጋጁ።

“በምድር ላይ ካሉት በላይ ታላቅ በሆነው [እስራኤልን የመሰብሰብ] ሥራ” አካል እንድንሆን በፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ተጋብዘናል። “የሰማይ አባታችን ብዙዎቹን ክቡር መናፍስቶቹን፣ ምናልባትም ምርጦቹን ቡድን፣ ለዚህ መጨረሻ ደረጃ በማዘጋጀት አስቀምጦ ነበር። እነዚያ ክቡራን መናፍስት—ምርጦቹ ተጫዋቾች፣ እነዚያ ጀግኖች— እናንተ ናችሁ!”1

ምስል
ወጣት ሴቶች እየተቃቀፉ

በአስቸጋሪ ጊዜያት ተስፋ ይኑራችሁ።

አዳኙ ዳግም ሲመጣ ጻድቃን በሰላም ይኖራሉ። አዳኙ ይነግሣል፣ ኢፍትሐዊነትም ይስተካከላል። “ጌታም ከእነርሱ መካከል ይገኛልና፣ እናም ክብሩም በእነርሱ ላይ ያርፋል፣ እናም እርሱም ንጉሳቸውና ህግ ሰጪአቸው ይሆናል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥59)።

ምስል
ወጣት ሴት

ከሞት በመነሳት እመኑ።

የሰው ዘር በሙሉ ከሞት ይነሳል። ፍጹም፣ የማይሞት አካል ይኖረናል። በሞት የተለዩንን የምንወዳቸውን ሰዎች ዳግም ማየት እንችላለን። “መንፈስም ከስጋ ጋር ፍፁም በሆነ ሁኔታ በድጋሚ አንድ ይሆናል፣ እግርና እጅ እናም መገጣጠሚያዎች ተገቢ በሆነ ሁኔታ፣ እኛ አሁን ባለን አምሳል ይመለሳሉ” (አልማ 11፥43)።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔፋውያን ተገልጦ

ጥንታዊ ኔፋውያን አዳኙ ከመምጣቱ በፊት እምነት ነበራቸው። እኛም አዳኙ ዳግም እንደሚመጣ እምነት ሊኖረን ይችላል—“[እኛም] በሀይልና በሰማይ ደመና፣ በታላቅ ክብር [ተሸፍኖ እናየዋለን]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥44፤ በተጨማሪም የሐዋርያት ሥራ 1፥11 ይመልከቱ)። ዳግም እንደሚመጣ ማወቃችሁ ዛሬ በምታደርጉት ነገር ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

ማስታወሻ

  1. Russell M. Nelson, “Hope of Israel [የእስራኤል ተስፋ]” [worldwide youth devotional [የአለም አቀ የወጣቶች ትመንፈስ ስብሰባ]፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ Gየወንጌል ቤተመጻህፍት።