ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ተጨማሪ ግብዓቶች
አባሪ ሀ፦ ለወላጆች—ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት


“አባሪ ሀ፦ ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ ሀ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

አባሪ ሀ

ለወላጆች—ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት

እርሱ ስለሚወዳችሁ፣ ስለሚያምናችሁ እና ችሎታችሁን ስለሚያውቅ፣ የሰማይ አባት ልጆቻችሁን በእርሱ የቃል ኪዳን መንገድ ማለትም ወደ ዘለአለማዊ ህይወት ወደሚመራው መንገድ ውስጥ እንዲገቡ እና ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ እንድትረዱ እድሉን ሰጥቷችኋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–28 ይመልከቱ)። ይህ እንደ የጥምቀት ቃል ኪዳን እና በቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረጉ ቃል ኪዳኖች የመሳሰሉ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለማድረግ እና ለመጠበቅ እንዲዘጋጁ እነርሱን መርዳትን ያካትታል። በእነዚህ ቃል ኪዳኖች አማካኝነት ልጆቻችሁ እራሳቸውን ከአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያጣብቃሉ።

በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለሚያደርጉት ለዚህ ጉዞ ልጆቻችሁን ለማዘጋጀት ብዙ መንገዶች አሉ፣ እናም እነርሱን ለመርዳት የተሻለውን መንገድ እንድታገኙ የሰማይ አባት ይረዳችኋል። መነሳሳትን ስትሹ የሚሰጡ ትምህርቶች ሁሉ ለትምህርቶቹ በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንደማይከናወኑ አስቡ። በእርግጥ በቤት መማርን በጣም ኃያል ከሚያደርገው ነገር መካከል በቀን ተቀን የህይወት ሂደት በተፈጥሮ የሚከሰት ዓይነት በምሳሌ እና በትንሽ ቀለል ባሉ ወቅቶች የመማር እድል ነው። የቃል ኪዳን መንገድን መከተል ቀጣይነት ያለው የህይወት ሂደት እንደሆነ፣ ስለ ቃል ኪዳኑ መንገድ መማርም ቀጣይነት አለው። (“Home and Family [ቤት እና ቤተሰብ፣” Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር] [2022 (እ.አ.አ)]፣ 30–31።)

ምስል
እናት ከልጅ ጋር

በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለሚያደርጉት ጉዞ ልጆቻችሁን ለማዘጋጀት ብዙ መንገዶች አሉ።

ወደ ተጨማሪ መነሳሳት የሚያመሩ የተወሰኑ ሃሳቦች ከታች ቀርበዋል። ዕድሜያቸው በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ የሆኑ ልጆችን ለማስተማር የሚሆኑ ተጨማሪ ሃሳቦችን በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍሎች ውስጥ ከሚገኘው “ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት” በሚለው ርዕስ ስር ለማግኘት ትችላላችሁ።

ጥምቀት እና ማረጋገጫ

ወደ ቃል ኪዳን መንገድ “የምንገባበት በር፣ ንስሃ እና በውኃ መጠመቅ” እንደሆነ ኔፊ አስተምሯል (2 ኛ ኔፊ 31፥17)። ልጆቻችሁን ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለማግኘት እንዲዘጋጁ የመርዳት ጥረቶቻችሁ እግሮቻቸው በዛ መንገድ ላይ እንዲጸኑ ማድረግ ይችላሉ። እነዚህ ጥረቶች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እና ንስሃን በማስተማር ይጀምራሉ። እንዲሁም በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን በመካፈል የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችንን እንዴት እንደምናድስ ያካትታሉ።

ሊረዷችሁ የሚችሉ ግብዓቶች እነሆ፦ 2 ኔፊ 31፤ ስለ ጥምቀት የሚናገር የጓደኛ መጽሔት ልዩ ዕትም ጓደኛ የወንጌል ርዕሶች፣ “ጥምቀት፣” የወንጌል ላይብረሪ።

  • በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን እምነት የሚያጠነክር ልምድ በሚኖራችሁ ጊዜ ሁሉ፣ ለልጃችሁ አካፍሉ። እምነት እድሜ ልክ እያደገ ሊሄድ የሚችል ነገር እንደሆነ እንዲገነዘብ/እድትገነዘብ እርዱት ወይም እርዷት። ልጃችሁ ከመጠመቁ/ቋ በፊት በክርስቶስ ጠንካራ እምነት እንዲያዳብር/ድታዳብር ማድረግ የምትችሏቸው የተወሰኑ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

  • ልጃችሁ የተሳሳተ ምርጫ ሲያደርግ፣ ስለ ንስሃ ስጦታ በደስታ ተናገሩ። እንዲሁም እናንተ የተሳሳተ ውሳኔ ካደረጋችሁ በኋላ ንስሃ ስትገቡ የሚመጣውን ደስታ አካፍሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሃጢያቶቻችን ስለተሰቃየ እና ስለሞተ የመለወጥ ኃይልን እንደሰጠን መስክሩ። ልጃችሁ ይቅርታን ሲፈልግ፣ በነፃ እና በደስታ ይቅር በሉ።

  • ስለ ጥምቀታችሁ ለልጃችሁ ንገሩ። ፎቶዎችን አሳዩ እንዲሁም ትውስታዎችን አካፍሉ። እንዴት እንደተሰማችሁ፣ የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን የበለጠ እንድታውቁት እንዴት እንደረዳችሁ እና ህይወታችሁን መባረክ መቀጠላቸውን ተናገሩ። ልጃችሁ ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ አበረታቱ።

  • በቤተሰባችሁ ወይም በአጥቢያችሁ ውስጥ ጥምቀት ሲኖር፣ ልጃችሁ እንዲየይ ውሰዱ። ልጃችሁ እና እናንተ ስላያችኋቸው እና ስለተሰማችኋቸው ነገሮች ተነጋገሩ። ከተቻለ፣ ከሚጠመቀው ግለሰብ ጋር ተነጋገሩ እንዲሁም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁ፦ “ይህንን ውሳኔ እንዴት ነው የወሰንከው? እንዴት ነው የተዘጋጀኸው?”

  • ልጃችሁ ለማድረግ ቃል የገባውን ነገር ሲያደርግ ስትመለከቱ፣ ከልብ በሆነ ስሜት አወድሱ። ለማድረግ ቃል በገባናቸው ነገሮች መጽናት ስንጠመቅ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች እንድንጠብቅ እንድንዘጋጅ እንደሚረዳን ጥቀሱ። ስንጠመቅ ለእግዚአብሔር የምንገባው ቃል ምንድን ነው? እርሱስ ለእኛ ቃል የሚገባው ምንድን ነው? (ሞዛያ 18፥8–10፣ 13 ይመልከቱ)።

  • እናንተ እና ልጃችሁ በጋራ ቅዱስ ልምድ ሲኖራችሁ (ለምሳሌ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ ወይም አንድን ሰው ስታገለግሉ) ስለሚሰሟችሁ መንፈሳዊ ስሜቶች ወይም መነሳሳቶች ንገሩት/ሯት። ልጃችሁ ስለሚሰማው/ማት ነገር እንዲያካፍል/እንድታካፍል ጋብዙ። ለእናንተ በግለሰብ ደረጃ የሚናገርባቸውን መንገዶችም ጨምሮ መንፈስ ለሰዎች የሚናገርባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስተውሉ። ልጃችሁ የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ያየበትን/ያየችበትን ሁኔታዎች እንዲያለዩ አግዙ።

  • በወንጌል ላይብረሪ ስብስቦች ውስጥ “እርሱን ስሙት!“ በሚል ርዕስ ስር ያሉትን የተወሰኑ ቪዲዮዎች በጋራ ተመልከቱ። የጌታ አገልጋዮች እርሱን ስለሚሰሙባቸው የተለያዩ መንገዶች ተነጋገሩ። ልጃችሁ የአዳኙን ድምፅ እንዴት እንደሚሰማ/እንደምትሰማ ስዕል እንዲስል/እንድትስል ወይም ቪድዮ እንዲሰራ/እንድትሰራ ጋብዙ።

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን እንዴት እንደባረካችሁ ተናገሩ። ሌሎችን ስታገለግሉ እና ሌሎች እናንተን ሲያገለግሉ ወደ የሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መቅረብ የቻላችሁት እንዴት ነው? እንደ የቤተክርስቲያን አባል ልጃችሁ ሌሎችን ለማገልገል እና ለማጠንከር የሚችልባቸውን መንገዶች እንዲያስብ አግዙ።

  • ቅዱስ ቁርባንን በቤተሰባችሁ ውስጥ የተቀደሰ እና አስደሳች ክስተት አድረጉት። በቅዱስ ቁርባን ወቅት ልጃችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለማተኮር የሚችልባቸውን መንገዶች እንዲያቅድ አግዙ። ቅዱስ ቁርባን ለእኛ ቅዱስ እንደሆነ የምናሳየው እንዴት ነው?

  • ብዙ የጓደኛ መጽሔት እትሞች ልጆች ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለማግኘት እንዲዘጋጁ ለመርዳት የታሰቡ ፅሁፎችን፣ ታሪኮችን እና እንቅስቃሴዎችን ያካትታሉ። ልጆቻችሁ የተወሰነ መርጠው ከእናንተ ጋር እዲያነቡ እና እንዲደሰቱ ፍቀዱላቸው። (በተጨማሪም በወንጌል ቤተ መጻህፍት የልጆች ክፍል ውስጥ “ለጥምቀት መዘጋጀት” በሚለው ስር ያሉትን ስብስቦች ተመልከቱ።)

    ምስል
    ወንድ ልጅ እየተጠመቀ

    ወደ ቃል ኪዳን መንገድ “የምንገባበት በር፣ ንስሃ እና በውኃ መጠመቅ” እንደሆነ ኔፊ አስተምሯል (2 ኛ ኔፊ 31፥17)።

የክህነት ሃይል፣ ሥልጣን እና ቁልፎች

ክህነት እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት የእርሱ ስልጣን እና ኃይል ነው። የእግዚአብሔር ክህነት ዛሬ በምድር ላይ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አለ። ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ ሁሉም የቤተክርስቲያን አባላት—ልጆችን ጨምሮ—በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለማጠንከር በእግዚአብሔር የክህነት ኃይል ይባረካሉ (አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል3.5 ይመልከቱ)። ይህ ኃይል አባላቶች በግል እና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን የደህንነት እና በዘለአለም ህይወት ከፍ የመደረግ ስራን ሲሰሩ ይረዳል (አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ2.2 ይመልከቱ)።

በክህነት ስልጣን አማካኝነት ስርዓቶችን እንቀበላለን። ወንዶች እና ሴቶች በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ሲያገለግሉ የክህነት ቁልፎችን በያዙ ሰዎች ምሪት ስር በመሆን በክህነት ስልጣን አማካኝነት ያገለግላሉ። ሁሉም የሰማይ አባት ልጆች—ወንድ ልጆቹ እና ሴት ልጆቹ—ክህነትን የበለጠ ለመረዳት ሲመጡ ይባረካሉ።

ስለክህነት የበለጠ ለመማር፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የክህነት ኃይል ዋጋ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 66–69፤ “Priesthood Principles [የክህነት መርሆዎች]፣” ምዕራፍ 3 በአጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ ውስጥ ይመልከቱ።

  • የክህነት ስርዓቶችን ቀጣይነት ያላቸው የቤተሰባችሁ ህይወት ክፍሎች አድርጓቸው። ለምሳሌ፣ ልጃሁን በየሳምንቱ ለሚደረገው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ በመንፈስ እንዲዘጋጅ እርዱ። ልጃችሁ ሲታመም/ስትታመም ወይም መፅናናት ወይም አቅጣጫ ሲያስፈልገው/ጋት፣ የክህነትን በረከቶች እንዲሻ/እንድትሻ አበረታቱ። ጌታ በክህነት ኃይል ቤተሰባችሁን እየባረከ ያለበትን መንገዶች መጥቀስን ልምድ አድርጉ።

  • ቅዱሳት መጻህፍትን በጋራ ስታነቡ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን በኃይሉ አማካኝነት እንዴት እንደሚባርክ ለመወያየት እድሎችን ፈልጉ። እግዚአብሔር በክህነቱ አማካኝነት እናንተን የባረከበትን ልምዳችሁን አካፍሉ። በክህነት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ስለምንቀበላቸው በረከቶች ምሳሌዎች አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ3.23.5 ይመልከቱ።

  • በቤተሰባችሁ ውስጥ የአንድ ሰውን የክህነት ስልጣን መስመር እወቁ። (የመልከጸዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች የስልጣን መስመራቸውን ቅጂ ለLineofAuthority@ChurchofJesusChrist.org ኢሜል በመላክ መቀበል ይችላሉ፤ እንዲሁም “Request a Priesthood Line of Authority [የክህነት ስልጣን መስመርን ጠይቁ]” በ ChurchofJesusChrist.org በእርዳታ ማዕከል ውስጥ ይገኛል) የክህነት ስልጣን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ እንደሚመጣ ማወቅ ጠቃሚ የሆነው ለምን እንደሆነ ተናገሩ። እርሱን ለእኛ ይህን የሚያጋራው ለምንድን ነው?

  • ከጥምቀት በኋላ ልጃችሁ የጥምቀትን ቃል ኪዳን በመጠበቅ የክህነት ኃይልን መቀበል እንደሚችል/ምትችል አስተምሩ። የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን መልዕክት የሆነውን “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” (ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79 ይመልከቱ) በጋራ ከልሱ። የክህነት ስርዓቶች የእግዚአብሔርን ሃይል ወደ ህይወታችሁ እንዴት እንዳመጡ ለልጃችሁ ንገሩ። በክህነት ኃይል ስለምንባረክባቸው የተወሰኑ መንገዶች ዝርዝር ለማግኘት አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ3.5 ይመልከቱ።

  • “የጌታ አገልጋይ ምን ዓይነት ነው?” የሚለውን ጥያቄ ተወያዩበት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36–42 በጋራ አንብቡ እና መልሶችን ፈልጉ። ልጆቻችሁ (ወይም ሌላ ሰው) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ካሉት አንዱን መርህ ወይም ባህርይ ተግባራዊ ሲያደርጉ ስትመለከቱ እውቅና ስጡ።

  • እናንተ ወይም ልጃችሁ በርን ለመክፈት ወይም መኪናን ለማስነሳት ቁልፍን ስትጠቀሙ፣ የክህነት መሪዎች ከያዙት ቁልፎች ጋር ለማነጸጸር የአፍታ ጊዜ ውሰዱ። (ለክህነት ቁልፎች ትርጉም አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ3.4.1 ይመልከቱ)። የክህነት ቁልፎች ለእኛ “የሚከፍቱት” ወይም “የሚያስነሱት” ምንድን ነው? በተጨማሪም ጌሪ ኢ. ስቲቭንሰን፣ “የክህነት ቁልፎች እና ስልጣን የት ናቸው?፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 29-32፤ “ቁልፎቹ የት ናቸው?” (ቪዲዮ)።

  • ለጥሪ ስትለዩ የሚቻል ከሆነ ልጃችሁ እንዲገኝ ጋብዙ። ልጃችሁ ጥሪያችሁን ስታሟሉ እንዲያይ አድርጉ። ልጃችሁ ሊያግዛችሁ/ልታግዛችሁ የሚችልበትን/ችልበትን ተገቢ መንገዶች መፈለግም ትችላላችሁ። የጌታ ኃይል በጥሪያችሁ ውስጥ እንዴት እንደሚሰማችሁ ግለፁ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—ለሙታን የሚደረጉ ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው። ሁሉም ነገሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠቁሙበት በቤተመቅደስ ውስጥ፣ በቅዱስ ስርዓቶች ስንሳተፍ ከሰማይ አባት ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እናደርጋለን። የሰማይ አባት በዚህ ህይወት ስርዓቶቹን ያልተቀበሉትን ጨምሮ ሁሉም ልጆቹ ቃል ኪዳኖችን እዲገቡ እና በስርዓቶች እንዲሳተፉ መንገድን ሰጥቷል። ልጃችሁ 12 ዓመት በሚሆንበት/በምትሆንበት የዓመቱ መጀመሪያ ላይ፣ ልጃችሁ በቤተመቅደስ ውስጥ ለሞቱ ቅድመ ዓያቶች ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማድረግ በቂ ነው።

  • ሁኔታችሁ በሚፈቅዱላችሁ ጊዜ ሁሉ ደጋግማችሁ በቤተመቅደስ ተሳተፉ። ቤተመቅደስ ለምን እንደምትሄዱ እና ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ እንዴት እንደሚረዳችሁ ለልጃችሁ ተናገሩ።

  • የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ጥያቄዎችን በጋራ ከልሱ እንዲሁም ተወያዩ። በቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ ወቅት ስለሚሆነው ነገር ለልጃችሁ ተናገሩ። ለእናንተ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መያዝ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ አካፍሉ።

  • ሚልክያ 4፥6ን በጋራ አንብቡ። ልቦቻችሁ ወደ ቅድመ ዓያቶቻችሁ እንዴት እንደሚመለስ ተናገሩ። የቤተሰብ ታሪካችሁን በFamilySearch.org ላይ በጋራ በመፈለግ ስለቅድመ ዓያቶቻችሁ የበለጠ ተማሩ። መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል የሚያስፈልጋቸውን የቅድመ ዓያቶችን ፈልጉ። የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪ ሊረዳችሁ ይችላል።

  • በወንጌል ላይብረሪ የልጆች ክፍል ውስጥ “ቤተመቅደስ” በሚለው ርዕስ ስር ካሉት ስብስቦች ውስጥ የተወሰኑትን ግብዓቶች በጋራ ከልሱ። (“ለቤተመቅደስ ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች ልጆቻችሁን ማዘጋጀት” የሚለውን በ ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይመልከቱ።)

የፓትርያርክ በረከትን መቀበል

የፓትርያርክ በረከት የምሪት፣ የመፅናናት እና የመነሳሳት ምንጭ ሊሆን ይችላል። ከሰማይ አባት ለእኛ የተሰጠ የግል ምክርን ይይዛል እንዲሁም የዘለአለም ማንነታችንን እና ዓላማችንን እንድንገነዘብ ይረዳናል። የፓትርያርክ በረከቶችን ጠቀሜታ እና ቅዱስ ተፈጥሮ በማስተማር ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ለመቀበል እንዲዘጋጅ እርዱ።

የበለጠ ለመማር የወንጌል አርዕስቶች፣ “የፓትርያርክ በረከቶች” ይመልከቱ።

  • የፓትርያርክ በረከትን የመቀበል ልምዳችሁን ለልጃችሁ አካፍሉ። ለመቀበል እንዴት እንደተዘጋጃችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር የበለጠ ለመቅረብ እንዴት እንደረዳችሁ እና በረከቱን በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት እንደምትጠቀሙበት የመሳሰሉትን ነገሮች ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ከተቀበሉ ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲነጋገር መጋበዝ ትችላላችሁ።

  • በወንጌል አርዕስቶች፣ “ፓትርያርክ በረከቶች” ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግብዓቶችን በጋራ ለመከለስ ጊዜ ውሰዱ። የፓትርያርክ በረከትን ስለመቀበል ሂደት ለመማር አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ18.17 ይመልከቱ።

  • የፓትርያርክ በረከቶችን የተቀበሉ የቅድመ ዓያቶች ካሏችሁ የተወሰኑትን ከልጃችሁ ጋር ማንበብ የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል። የሞቱ የቅድመ ዓያቶችን በረከቶች ለመጠየቅ ወደ ChurchofJesusChrist.org፣ ግቡና ከላይ በስተቀኝ በኩል ያለውን የአካውንት ምልክት ይጫኑ ከዚያም “የፓትርያርክ በረከቶች” ምረጡ።

  • ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ከተቀበለ በኋላ፣ የተሰማቸውን ስሜት ለመመዝገብ እና ለልጃችሁ ለማጋራት የተገኙ ማንኛውም የቤተሰብ አባሎች ጋብዙ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—የመንፈስ ስጦታ

እግዚአብሔር ሁሉንም ልጆቹን “ከላይ በሚመጣ ኃይል” ሊባርክ ይፈልጋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8)። የግላችንን የመንፈሥ ስጦታ ለመቀበል አንዴ ብቻ ወደ ቤተመቅደስ እንሄዳለን፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርጋቸው ቃል ኪዳኖች እና እንደ መንፈሥ ስጦታ አካል የሚሰጠን መንፈሳዊ ኃይል በህይወታችን ውስጥ በየቀኑ ሊባርኩን ይችላሉ።

  • የቤተመቅደስን ምስል በቤታችሁ ውስጥ ስቀሉ። በቤተመቅደስ ውስጥ የተሰማችሁን ስሜት ለልጃችሁ ንገሩ። ለጌታ እና ለቤቱ እንዲሁም እዚያ ስለገባችኋቸው ቃልኪዳኖች ያላችሁን ፍቅር በተደጋጋሚ ለልጃችሁ ንገሩ።

  • temples.ChurchofJesusChrist.orgን በጋራ አስሱ። ስለቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ እና ለቤተመቅደስ በረከቶች ተዘጋጁ ያሉ ጽሁፎችን በጋራ አንብቡ። ልጆቻችሁ ስለቤተመቅደስ ያሏቸውን ማናቸውንም ጥያቄዎች እንዲጠይቁ ፍቀዱላቸው። ከቤተመቅደስ ውጪ ስለምን ማውራት እንደምትችሉ ምሪት ለማግኘት የሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልዕክትን “Prepared to Obtain Every Needful Thing” (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ) 101–4፤ በተለይም “Home-Centered and Church-Supported Learning and Temple Preparation [በቤት የተመሰረተ እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ ትምህርት እና ለቤተመቅደስ መዘጋጀት]” የሚለውን ይመልከቱ)።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በሥርዓቶች ውስጥ ስትሳተፉ ወይም ሌላ (እንደ ቅዱስ ቁርባን ወይም የፈውስ በረከት) ሥርዓቶችን ስትመለከቱ በሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ምልክት ለመወያየት ጊዜ ውሰዱ። ምልክቶቹ ምንን ይወክላሉ? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ይመሰክራሉ? ይህ ልጃችሁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን የምልክት ትርጉም ለማሰላሰል እንዲዘጋጅ ሊረዳ ይችላል።

  • ልጃችሁ በሞዛያ 18፥8–10፣ 13 የተገለፀውን የጥምቀት ቃል ኪዳን እየጠበቀ/ቀች ስለመሆኑ/ኗ እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ እርዱ። እንዲሁም ጌታ ልጃችሁን እንዴት እየባረከው/ካት እንዳለ እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ አግዙ። ልጃችሁ ያለውን/ላትን ቃል ኪዳኖችን የመጠበቅ ችሎታ መተማመን ገንቡ።

  • የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቻችሁ ምርጫዎቻችሁን ስታደርጉ እንዴት እንደመራችሁ እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትቀርቡ እንዴት እንደረዳችሁ በግልፅ እና በተደጋጋሚ ተናገሩ። በቤተመቅደስ ውስጥ የምንገባቸውን ቃል ኪዳኖች ለመከለስ አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ27.2ን መጠቀም ትችላላችሁ።

በሚስዮን ማገልገል

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፦ “ለማገልገል የምትዘጋጁበት በጣም ጠቃሚ የሆነው ነገር ቢኖር፣ ወደ ሚስዮን ከመሄዳችሁ ከረዥም ጊዜ በፊት ሚስዮናዊ መሆን ነው። … ጉዳዩ ወደ ሚስዮን መሄድ አይደለም፤ ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ሚስዮናዊ መሆን እና በመላ ህይወታችን ውስጥ በሙሉ ልባችን፣ ሃይላችን፣ አዕምሮአችን፣ እና ጥንካሬአችን ማገልገል ነው። … ለእድሜልክ የሚስዮናዊ ስራ እየተዘጋጃችሁ ነው” (“Becoming a Missionary [ሚስዮናዊ መሆን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2005 (እ.አ.አ)፣ 45–46)። ልጃችሁ ሚስዮናዊ በመሆን ያሉት ልምዶች ሚስዮናዊ በመሆን በሚያገለግልበት/በምታገለግልበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘለአለም ይባርከዋል/ይባርካታል።

የበለጠ ለመማር፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Preaching the Gospel of Peace [የሰላምን ወንጌል መስበክ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 6–7፤ ኤም. ራስል ባላርድ፣ “Missionary Service Blessed My Life Forever [የሚስዮን አገልግሎት ህይወቴን ለዘለአለም ባረከ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 8–10፤ Missionary Preparation: Adjusting to Missionary Life [ለሚስዮን ዝግጅት፦ ህይወትን ሚስዮን ወደመሆን ማስተካከል፣ ይመልከቱ።

  • ተፈጥሯዊ በሆኑ መንገዶች ወንጌልን በማካፈል ረገድ ምሳሌ ሁኑ። ለሌሎች ስለሰማይ አባት እና ስለአዳኝ እንዲሁም የእርሱ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ ስለተቀበላችኋቸው በረከቶች የሚሰማችሁን ስሜቶች ለማካፈል ለሚገኙት እድሎች ሁሌም ንቁ ሁኑ። በቤተክርስቲያን ውስጥ እና ቤተሰብ ነክ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ሌሎች ሰዎች ከቤተሰባችሁ ጋር እንዲቀላቀሉ ጋብዙ።

  • ቤተሰባችሁ ከሚስዮናውያን ጋር መስተጋብር የሚፈጥሩበትን እድሎች ፈልጉ። ጓደኞቻችሁን እንዲያስተምሩ ጋብዟቸው ወይም ሰዎችን በቤታችሁ ውስጥ እንዲያስተምሩ ፍቀዱላቸው። ሚስዮናውያን ስላሏቸው ልምዶች እና የሚስዮናዊ አገልግሎት እንዴት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እየረዳቸው እንደሆነ ጠይቋቸው። ሚስዮናዊ ለመሆን ለመዘጋጀት ምን እንዳደረጉ (ወይም ይህን አድርገን ቢሆን ኖሮ ብለው የሚመኟቸውን ነገሮች እንዳሉ) ጠይቋቸው።

  • በሚስዮን አገልግላችሁ የምታውቁ ከሆነ ስለልምዳችሁ በግልፅ እና በተደጋጋሚ ተናገሩ። ወይም በሚስዮን ያገለገሉ ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባሎች እንዲናገሩ ጋብዙ። ወንጌልን በመላ ህይወታችሁ ለሌሎች ስላካፈላችሁባቸው መንገዶችም መናገር ትችላላችሁ። ልጃችሁ ወንጌልን የሚያካፍልበት መንገዶች እንዲያስብ አግዙ።

  • ልጃችሁ የወንጌልን መርሆዎች ለቤተሰባችሁ እንዲያስተምር እድሎችን ስጡ። ልጃችሁ እምነቱን/ቷን ከሌሎች ጋር ማካፈልም ይችላል/ትችላለች። ለምሳሌ፣ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን መወያየት ትችላላችሁ፦ “ስለመጽሐፈ ሞርሞን ሰምቶ ለማያውቅ ሰው እንዴት ማስተዋወቅ እንችላለን?” ወይም “ክርስቲያን ላልሆነ ሰው የአዳኝን አስፈላጊነት እንዴት መግለፅ እንችላለን?”

  • ልጃችሁ ከሰዎች ጋር በሚነጋገርበት ወቅት ምቾት የሚሰማው እንዲሆን አርዱ። ንግግርን ለመጀመር አንዳንድ መልካም መንገዶች ምንድን ናቸው? ሌሎች የሚሉትን ለመስማት፣ በልባቸው ውስጥ ያለውን ለመረዳት እና ህይወታቸውን ሊባርኩ የሚችሉ የወንጌል እውነቶችን እንዴት ማካፈል እንደሚችል/እንደምትችል እንዲማር/እንድትማር ልጃችሁን አበረታቱ።

  • ልጃችሁን ስለ ሌላ ባህሎች እና እምነቶች ለማስተማር እድሎችን ፈልጉ። በሌሎች እምነቶች ውስጥ ያሉ መልካም እና ትክክለኛ መርሆዎችን እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ እና እንዲያከብር/እንድታከብር እርዱ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—እትመት

በቤተመቅደስ ውስጥ ባል እና ሚስት ለዘለአለም መጋባት ይችላሉ። ይህ እትመት በሚባል ሥርዓት ውስጥ ይከናወናል። ምንም እንኳን ይህ ሥርዓት ለወንድ ወይም ሴት ልጃችሁ ከብዙ ዓመታት በኋላ የሚከናወን ቢሆንም፣ በእነዚያ ዓመታት ውስጥ በጋራ የምታደርጉት ትንሽ፣ ቀላል፣ ቀጣይነት ያላቸው ነገሮች ለዚህ አስደናቂ በረከት እንዲዘጋጅ/እንድትዘጋጅ ይረዳል።

  • ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅን” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ በጋራ አንብቡ። በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ስለሚገኝ ደስታ እና ስለ ውጤታማ ጋብቻ ይህ አዋጅ ምን ያስተምራል? በአዋጁ ውስጥ ከተጠቀሱት መርሆዎች አንዱን ከልጃችሁ ጋር ለማጥናት ምረጡ ። ከዚያ መርህ ጋር የሚዛመዱ ቅዱሳት መጻህፍትን በየቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ ማየት ትችላላችሁ። ያንን መርህ በህይወታችሁ ውስጥ በይበልጥ ለመተግበር ግቦችንም ማውጣትም ትችላላችሁ። ግቦቻችሁን ለማከናወን ስትሰሩ፣ ያንን መርህ መኖር በህይወታችሁ ላይ ያለውን ተፅዕኖ በጋራ ተወያዩ።

  • የፕሬዚዳንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ መልዕክት “In Praise of Those Who Save” [ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ) 77–80] ከልጃችሁ ጋር አንብቡ። “A Society of Disposables፣” ወደሚለው ክፍል ስትደርሱ በቤታችሁ ውስጥ ሊጣሉ የሚችሉ እና የማይችሉ ነገሮችን መፈለግ ትችላላችሁ። ነገሮች ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ስትፈልጉ ነገሮችን እንዴት በተለየ መልኩ እንደምትንከባከቡ ተናገሩ። ጋብቻን እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን እንዴት መንከባከብ እንደሚገባን ይህ ምን ሀሳብ ያቀርባል? ከፕሬዚዳንት ኡክዶርፍ መልዕክት አዳኙ ጠንካራ ጋብቻን እና ቤተሰቦችን ለመገንባት እንዴት ሊረዳን እንደሚችል ሌላ ምን እንማራለን?

  • ያገባችሁ ከሆነ፣ እንደ ጥንድ መልካም እያደረግን ነው ብላችሁ ስለሚሰሟችሁ ነገሮች፣ እየተማራችኋቸው ስላሉት ነገሮች እና ለመሻሻል ስለምትሞክሩባቸው መንገዶች ለልጃችሁ ግልፅ ሁኑ። እናንተና የትዳር አጋራችሁ በቤተመቅደስ ውስጥ ከታተማችሁ፣ እርስ በእርስ እና ከጌታ ጋር ቃል ኪዳናችሁን ለመጠበቅ እንዴት እንደምትጥሩ ለልጃችሁ በምሳሌ አሳዩ። የሰማይ አባትን እና አዳኙን የግንኙነታችሁ ማዕከል ለማድረግ እንዴት እንደምትጥሩ እና እንዴት እየረዷችሁ እንደሆነ ለልጃችሁ ንገሩ።

  • የቤተሰብ ውሳኔዎች መደረግ ሲያስፈልግ፣ የቤተሰብ ምክክር መድረክ ፍጠሩ እንዲሁም ውይይትን አድርጉ። የሁሉም የቤተሰብ አባላት ሃሳቦች መሰማታቸውን እና ዋጋ መሰጠታቸውን አረጋግጡ። እያንዳንዱ ሰው ነገሮችን በተመሳሳይ መንገድ ባያይም ጤነኛ ንግግርን እና በቤተሰብ ግንኙነቶች ውስጥ በጎነትን ምሳሌ ለማድረግ እነዚህን ውይይቶች እንደ እድሎች ተጠቀሙ።

  • በቤተሰብ ውስጥ አለመግባባት ወይም ግጭት ሲኖር፣ ትህትናን እና ርህራሄን አሳዩ። ልጃችሁ ግጭትን በክርስቶስ መሰል መንገዶች መፍታት እንዴት ለደስተኛ ትዳር እንዲዘጋጅ/ትዘጋጅ ሊረዳው/ዳት እንደሚችል እንዲያይ/ድታይ እርዱ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥41–42ን በጋራ አንብቡ እና በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉ መርሆዎች እንዴት በትዳር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተነጋገሩ።