የቤተክርስቲያን ታሪክ
የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባዎች


ምስል
በዛፎች መካከል የሚያልፍ የጸሃይ ብርሃን

የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባዎች

ማጠቃለያ

ጆሴፍ ስሚዝ እግዚያብሄር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በዌስተርን ኒው ዮርክ ስቴት በሚገኘው የወላጆቹ ቤት አቅራቢያ ባለ የዛፎች አፀድ ውስጥ እድሜው 14 ዓመት ገደማ ሲሆነው እንደተገለጡለት መዝግቧል፡፡ ጆሴፍ ስለሃጢያቱ ስለተጨነቀ እና የትኛውን መንፈሳዊ መንገድ መከተል እንደሚገባው እርግጠኛ ባለመሆኑ፣ ስብሰባዎችን በመካፈል፣ ቅዱሳን ጽሁፎችን በማንበብ እና በመጸለይ መመሪያ ለማግኘት ፈለገ፡፡ በመልሱም፣ ሰማያዊ መገለጫን ተቀበለ፡፡ ጆሴፍ የመጀመሪያው ራዕይ በመባል የሚታወቀውን በተለያዩ አጋጣሚዎች አካፍሏል እንዲሁም መዝግቧል፤ አራት የተለያዩ የራዕዩን ዘገባዎች ጽፏል ወይም ጸሃፊዎች እንዲጽፉት መድቧል፡፡

ጆሴፍ ስሚዝ በህይወት ዘመኑ የመጀመሪያውን ራዕይ ሁለት ዘገባዎች አሳትሟል፡፡ ከእነዚህ የመጀመሪያው፣ ዛሬ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ በመባል የሚታወቀው በታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ ታትሟል ስለዚህም ይበልጥ የታወቀ ዘገባ ሆኗል። በጆሴፍ ስሚዝ ከሁሉ የሚቀድም ግለ‑ታሪክ ውስጥ እና በኋላም በማስታወሻ ደብተር ውስጥ የተመዘገቡት ሁለቱ ያልታተሙ ዘገባዎች ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚሰሩ የታሪክ አጥኚዎች እንደገና እስካገኟቸውና በ1960ዎቹ እስካሳተሟቸው ድረስ በአጠቃላይ የተረሱ ነበሩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ አነዚህ ሰነዶች በቤተክርስቲያኗ መጽሄቶች ውስጥ፣ የቤተክርስቲያኗ ንብረት በሆኑ እና የቤተክርስቲያኗ ደጋፊዎች በሆኑ ፕሬሶች የታተሙ ስራዎች ውስጥ እና በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ምሁራን ህዝባዊ ውይይቶች ላይ በተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎባቸዋል።1 ከመጀመሪያ ዘገባዎቹ በተጨማሪ፣ በእሱ ዘመን በነበሩ ሰዎች የተመዘገቡ አምስት የጆሴፍ ስሚዝ ራዕይ ገለጻዎችም አሉ።2

ምንም እንኳን በአጽንኦት እና በዝርዝር መለያየታቸው ተፈጥሯዊ ቢሆንም የተለያዩ የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባዎች ወጥ የሆነ ታሪክ ይናገራሉ። አንድ ግለሰብ ለበርካታ አመታት በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እና ለተለያዩ አድማጮች አንድን ተሞክሮ ሲገልጽ እያንዳንዱ ዘገባ በተሞክሮው የተለያዩ ገጽታዎች ላይ አጽንዖት እንደሚሰጥ እና ልዩ ዝርዝሮችን እንደሚይዝ የታሪክ ምሁራን ይጠብቃሉ። በርግጥ ከመጀመሪያው ራዕይ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ልዩነቶች ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ ላይ ያየውን ራዕይ እና በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ሃዋርያት የነበራቸውን ተሞክሮ በዘገቡ ብዙ የቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ ይገኛሉ።3 ነገር ግን ልዩነቶች ቢኖሩም፣ በሁሉም የመጀመሪያ ራዕይ ዘገባዎች ውስጥ ያለው መሠረታዊ ወጥነት እንደተጠበቀ ነው፡፡ አንዳንዶች ታሪኩን ድጋሚ በመግለጽ ላይ ያለ ማንኛውም ልዩነት የፈጠራ ስራ ለመሆኑ ማስረጃ እንደሆነ በተሳሳተ መንገድ ተከራክረዋል። በተቃራኒው፣ ውዱ ታሪካዊ መዝገብ አሁን ካለበት ባነሰ ደረጃ ተመዝግቦ ቢሆን ኖሮ ልናውቅ ከምንችለው በላይ ስለዚህ የሚደነቅ ክስተት ይበልጥ ለመማር ያስችለናል።

የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባዎች

በጆሴፍ ስሚዝ እና በእሱ ዘመን በነበሩት ሰዎች የተሰጠው እያንዳንዱ የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባ ክስተቱ የታወሰበት፣የተነገረበት እና የተመዘገበበት የራሱ የሆነ ታሪክ እና አውድ አለው። እነዚህ ዘገባዎች ቀጥለው ተብራርተዋል።

የ1832 (እ.አ.አ) ዘገባ። ከሁሉም በፊት የሚታወቀው የመጀመሪያው ራዕይ በጆሴፍ ስሚዝ በራሱ እጅ የተፃፈው ብቸኛው ዘገባ በ1832 (እ.አ.አ) ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ጆሴፍ ስሚዝ ባዘጋጀው አጭር፣ ያልታተመ ግለ-ታሪክ ውስጥ ይገኛል። በዘገባው ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ህሊናው ስለራሱ ሃጢያት የሚለውን እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካነበበው ጋር የሚመሳሰል ወደ መዳን የሚመራው ቤተክርስቲያን ማግኘት ባለመቻሉ ስላጋጠመው ብስጭት ገልጿል። በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ እና እሱ ባቀረበው የግል ቤዛነት ላይ አጽንዖት ሰጥቷል። “ጌታ” እንደተገለጠለት እና ሃጢያቶቹን ይቅር እንዳለለት ጽፏል። ምንም እንኳን እንዳመለከተው ዘገባውን የሚያምን አንድም ሰው ባያገኝም እንኳን ጆሴፍ በራዕዩ ምክንያት ደስታን እና ፍቅርን አግኝቷል። የ1832ቱን ዘገባ እዚህ ያንብቡ።

የ1835 (እ.አ.አ) ዘገባ። በ1835 (እ.አ.አ) በልግ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕዩን ከርትላንድ ኦሃዮን ሊጎበኝ ለመጣው ለሮበርት ማቲውስ ጠቀሰለት፡፡ በጆሴፍ የማስታወሻ ደብተር ውስጥ በጸሃፊው ዋረን ፓሪሽ የተመዘገበው የድጋሚ ትረካ የትኛው ቤተክርስቲያን ትክክለኛ እንደሆነ ለማግኘት ባደረገው ሙከራ ላይ ፣ሲጸልይ በተሰማው ተቃውሞ እና አንድ መለኮታዊ አካል ወዲያውም ሌላው ተከትሎት በመከሰታቸው ላይ አጽንዖት ያደርጋል። ይህ ዘገባ በራዕዩ ውስጥ የመላአክትን መከሰትም ይጠቁማል። የ1835ቱን ዘገባ እዚህ ያንብቡ

የ1838 (እ.አ.አ) ዘገባ። ዛሬ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን በጣም የታወቀው የመጀመሪያው ራዕይ ትረካ የ1838ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ ነው። መጀመሪያ በ1842 (እ.አ.አ) የቤተክርስቲያኗ ጋዜጣ በሆነችው በ ታይምስ ኤንድ ሲዝንስ፣ በናቩ፣ ኢሊኖይ የታተመው ዘገባ ጆሴፍ ስሚዝ የተፋፋመ ተቃውሞ ውስጥ በነበረበት ጊዜ የተናገረው ረዘም ያለ ታሪክ ክፍል ነበር። የ1832ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ ጆሴፍ ስሚዝ በወጣትነቱ ስለፈለገው ይቅርታ የግል ታሪክ ይበልጥ አጽንዖት ሲሰጥ የ1838ቱ ዘገባ ራእዩ “የቤተክርስቲያኗ አነሳስ እና እድገት” ጅማሬ ስለመሆኑ አጽንዖት ይሰጣል። እንደ 1835ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ የትረካው ማዕከላዊ ጥያቄ የትኛው ቤተክርስቲያን ነው ትክክል የሚለው ነው። የ1838ቱን ዘገባ እዚህ ያንብቡ

የ1842 (እ.አ.አ) ዘገባ።ቺካጎ ዴሞክራት ጋዜጣ አዘጋጅ ለጆን ዌንትወርዝ ስለኋለኛው ቀን ቅዱሳን መረጃ ጥያቄ ምላሽ የተጻፈ ሲሆን ይህ ዘገባ በ1842 በ ታይምስ ኤንድ ሲዝንስ፣ ውስጥ ታትሟል። (“የዌንትወርዝ ደብዳቤ፣” በመባል በተለምዶ የሚታወቀው፣ የእምነት አንቀጾች ምንጭም ነው ።)4 ዘገባው፣ የሞርሞን ሃይማኖትን እምነቶች ለማያውቁ አንባቢዎች እንዲታተም የታሰበ አጭር እና ቀጥተኛ ነው። እንደቀደሙት ዘገባዎች ሁሉ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰማውን ግራ መጋባት እና ለፀሎቱ መልስም ሁለት አካላት እንደተገለጡለት ጠቅሷል፡፡ በቀጣዩ አመት፣ ጆሴፍ ስሚዝ ይህንን ዘገባ ትንሽ ማስተካከያ አድርጎበት እስራኤል ዳኒኤል ረፕ ለሚባል የታሪክ አጥኚ ላከው እሱም በመጽሃፉ ውስጥ እንደ አንድ ምዕራፍ አድርጎ አሳተመው He Pasa Ekklesia [The Whole Church]: An Original History of the Religious Denominations at Present Existing in the United States.5 የ1842ቱን ዘገባ እዚህ ያንብቡ

የሰሚ ሰሚ ዘገባ። ጆሴፍ ስሚዝ ራሱ ካቀረባቸው ከእነዚህ ዘገባዎች በተጨማሪ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ስለራዕዩ ሲናገር በሰሙ በወቅቱ በነበሩ ሰዎች አማካኝነት አምስት ዘገባዎች ተጽፈዋል። እነዚህን ዘገባዎች እዚህ ያንብቡ

የጆሴፍ ስሚዝን የመጀመሪያ ራዕይ ዘገባዎች በተመለከተ የሚደረጉ ክርክሮች

የመጀመሪያው ራዕይ ዘገባዎች መለያየት እና ብዛታቸው አንዳንድ ተቺዎች የጆሴፍ ስሚዝ ገለጻዎች በዕውን ካጋጠሙት ተሞክሮዎች ጋር ስለመግጠም አለመግጠማቸው ወደመጠየቅ መርቷቸዋል። የእሱን ታማኝነት የማይቀበሉ ሁለት ክርክሮች ተደጋግመው ይደረጋሉ፦የመጀመሪያው የጆሴፍ ስሚዝ የክስተቶቹ ትውስታ ጥያቄ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በጊዜ ሂደት የታሪኩን ክፍሎች አሰማምሯቸው ይሁን አይሁን የሚጠይቅ ነው።

ትውስታ የጆሴፍ ስሚዝን የመጀመሪያ ራዕይ ዘገባ ትውስታ አስመልክቶ የሚነሳው አንድ ክርክር ታሪካዊ ማስረጃ በፓልማይራ፣ ኒውዮርክ እና አካባቢው በ1820 (እ.አ.አ) የሃይማኖት መነቃቃት ነበረ ሲል ጆሴፍ ስሚዝ ያቀረበውን ገለጻ አይደግፍም ሲል የሚከስ ነው። አንዳንዶች ይህ ጆሴፍ ተከስቷል ያለውን ያልተለመደ ሃይማኖታዊ አድናቆት እንዲሁም ራሱን የራዕዩን ዘገባ ቅቡልነት እንደሚሸረሽረው ይከራከራሉ።

ነገር ግን የሰነድ ማስረጃ የሃይማኖት መነቃቃቶች እንደነበሩ የሚገልጸውን የጆሴፍ ስሚዝን ቃላት ይደግፋል። ይኖርበት የነበረው ስፍራ በሃይማኖታዊ አድናቆት ታዋቂ ሆነ እንዲሁም ያለምንም ጥርጥር ከሃይማኖታዊ መነቃቃቶች መነሻ ቦታዎች አንዱ ነበር። (እ.አ.አ) በ1800ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ሰባኪዎች የሚለወጡ ሰዎችን በመፈለግ የተነቃቂ ሰዎችን ካምፕ በመቀለስ መሬቱን በማራቆታቸው ምክንያት የታሪክ ምሁራን ክልሉን “የተቃጠለው አውራጃ” በማለት ይጠሩታል፡፡6 ለምሳሌ፦ በሰኔ 1818(እ.አ.አ) የሜቶዲስት ካምፕ ስብሰባ በፓልማይራ ተደርጎ የነበረ ሲሆን በቀጣዩ በጋም ሜቶዲስቶች ከስሚዝ ቤተሰብ እርሻ 15 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው ቪዬና (አሁን ፌልፕስ ትባላለች) ኒው ዮርክ እንደገና ተሰብስበው ነበር፡፡ የአንድ ተጓዥ ሜቶዲስት ሰባኪ ማስታወሻ ደብተሮች በጆሴፍ መልክዓ ምድራዊ ክልል ውስጥ በ1819 እና በ1820 (እ.አ.አ) የነበሩ ብዙ ሃይማኖታዊ ስሜቶችን በሰነድ አስቀምጠዋል፡፡ ሪቭረንድ ጆርጅ ሌን የተባሉ የመነቃቃት ሜቶዲስት አስተማሪ በእነዚያ ሁለት ዓመታት ውስጥ በእግዚአብሔር ዘዴ ተሐድሶዎችን ለማምጣት” እዚያ እያስተማሩ እንደነበር ሪፖርት አድርገዋል፡፡7 ይህ ታሪካዊ ማስረጃ ከጆሴፍ ገለጻ ጋር የሚጣጣም ነው፡፡ በእርሱ አውራጃ ወይም ክልል ውስጥ ያልተለመደ የሃይማኖት ስሜት “የተጀመረው በሜቶዲስቶች ነው” ብሏል፡፡ በርግጥም፣ ጆሴፍ ወደሜቶዲቶች “በተወሰነ መጠን ያዘነበለ” እንደነበረ ገልጿል፡፡8

ማሰማመር ስለጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ ዘገባ በተደጋጋሚ የሚደረገው ሁለተኛው ክርክር ታሪኩን በጊዜ ሂደት አሰማምሮታል የሚለው ነው። ይህ ክርክር በሁለት ዝርዝሮች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፦ጆሴፍ ስሚዝ አየኋቸው ባላቸው የሰማይ ፍጥረታት ቁጥር እና ማንነት ላይ። የጆሴፍ የመጀመሪያ ራዕይ ዘገባዎች ሰማያዊ አካላቱን በጊዜ ሂደት በላቀ ጥልቀት ይገልጻሉ። የ1832ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ “ጌታ ሰማያትን በእኔ ላይ ከፈተ እና ጌታን አየሁት” ይላል። የ1838ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ “ሁለት አካላትን አየሁ” አንደኛው ሌላውን “የምወደው ልጄ” ሲል አስተዋወቀው ሲል ይገልጻል። በውጤቱም ተቺዎች ጆሴፍ ስሚዝ አንድ አካል—“ጌታን” እንዳየ በመናገር ጀመረ—ከዚያም ሁለቱንም አባትን እና ልጅን አይቻለሁ በማለት ጨረሰ ሲሉ ተከራክረዋል።9

ሌሎች የበለጠ አስተማማኝ የሆኑ ማስረጃውን የመመልከቻ መንገዶች አሉ። በመጀመሪያ በጊዜ ሂደት ውስጥ በትረካው ውስጥ ያለው መሠረታዊ ስምምነት እውቅና ሊሰጠው ይገባል፦ከአራቱ ዘገባዎች ሶስቱ ሁለት አካላት በመጀመሪያው ራዕይ ለጆሴፍ ስሚዝ እንደተገለጡለት በግልጽ ይናገራሉ። የሚለየው የጆሴፍ ስሚዝ የ1832 ዘገባ ሲሆን ይህም አንድ ወይም ሁለት ሰዎችን ለማመልከት ሊነበብ ይችላል። አንድን ሰማያዊ አካል ለማመልከት ከተነበበ ሃጢያቱን ይቅር ያለለትን ሰው ለማመልከት ይሆናል። እንደኋለኞቹ ዘገባዎች ከሆነ፣የመጀመሪያው መለኮታዊ አካል ሁለተኛውን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን “እንዲሰማ” ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው እርሱም የይቅርታ መልዕክቱን ያካተተውን ዋናውን መልእክት አስተላለፈ።10 ከዚያም የጆሴፍ ስሚዝ የ1832 ዘገባ ይቅርታን ባመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረ ሊሆን ይችላል።

ሌላው የ1832ቱን (እ.አ.አ) ዘገባ የማንበቢያ መንገድ ጆሴፍ ስሚዝ ሁለቱንም “ጌታ” ብሎ የጠራቸውን ሰዎች የሚያመለክት መሆኑ ነው። የማሰማመር ክርክሩ የ1832ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ አንድ መለኮታዊ አካል ብቻ መገኘቱን በሚገልጽ ግምት ላይ የተመሠረተ ነው። ነገር ግን የ1832ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ አንድ አካል ብቻ ተከሰተ አይልም። “ጌታ” ወደሚለው ቃል የሚጠቁሙት ሁለቱ ማጣቀሻዎች በጊዜ የተለያዩ እንደሆኑ አስተውሉ፦በመጀመሪያ “ጌታ” ሰማዩን ከፈተ፤ ከዚያም ጆሴፍ ስሚዝ “ጌታን” አየው። የዚህ ዘገባ ንባብ በመጀመሪያ አንድ አካል ተከሰተ ከዚያ በኋላ ወዲያው ሌላ ተከተለ ከሚለው ከጆሴፍ የ1835ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ ጋር የሚጣጣም ነው። ከዚያም የ1835ቱ (እ.አ.አ) ዘገባ ጆሴፍ ስሚዝ አንድ አካል አየ ከዚያም እሱ ሌላውን ገለጠው ስለዚህም ሁለቱንም “ጌታ” ብሎ ጠቀሳቸው የሚል ትርጉም እንዲኖረው ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ ማንበብ ይቻላል፦“ጌታ ሰማዩን በላዬ ከፈተ፤ ከዚያም ጌታን አየሁት”11

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የሄዱት የጆሴፍ ዝርዝር ገለጻዎች እያደጉ እንደሄዱ ግንዛቤዎች፣ በጊዜ ሂደት እንደተከማቹ፣ በልምድ ላይ እንደተመሰረቱ ተጨማሪ መረጃዎች እያጓጉ ሊነበቡ ይችላሉ። በከፊል፣ በ1832ቱ (እ.አ.አ)ዘገባ እና በኋላ በመጡት ዘገባዎች መካከል ያለው ልዩነት በተጻፈው እና በተነገረው ቃል መካከል ካሉ ልዩነቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የ1832 (እ.አ.አ) ዘገባ ጆሴፍ ስሚዝ ታሪኩን ለመጻፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሞከሩን ያመለክታል። በዚያው አመት፣ “በወረቀት በብዕር እና በቀለም እንዲሁም በተጣመመ በተሰባበረ በተበታተነ እና ፍጽምና በጎደለው ቋንቋ” እንደታሰረ እንደሚሰማው ለጓደኛው ጽፏል። የተጻፈውን ቃል “ትንሽ ጠባብ እስር ቤት” ሲል ጠርቶታል።12 የኋለኞቹ ዘገባዎች ሰፋ ያሉ መሆናቸው ይበልጥ በቀላሉ መገንዘብ የሚቻል ነገር ነው እንዲሁም በቃል የተነገሩ(—ቀላል፣ ለጆሴፍ ስሚዝ አመቺ የሆነ፣ እና ቃላት በቀላሉ እንዲፈሱ የፈቀደ መንገድ) ሊሆኑ የሚችሉ ዘገባዎች እንደነበሩ ስንገነዘብ የሚጠበቅም ነበር።

መደምደሚያ

ጆሴፍ ስሚዝ ስለእግዚአብሔር አብ እና ስለልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ አስደናቂ የራዕይ ተሞክሮ እንደነበረው ደጋግሞ መስክሯል። የመጀመሪያው ራዕይ እውነትነትም ሆነ በእርሱ ላይ የቀረቡት ክርክሮች በታሪካዊ ምርምር ብቻ ሊረጋገጡ የሚችሉ አይደሉም። የጆሴፍ ስሚዝን ምስክርነት ለማወቅ እያንዳንዱ የእውነት ፈላጊ መዝገቡን እንዲያጠና እና ከዚያም በቅን ልቦና፣ በትሁት ጸሎት እግዚአብሔርን ለመጠየቅ በክርስቶስ ላይ በቂ እምነት ማሳደርን ይጠይቃል። ጠያቂው በመንፈስ ቅዱስ በሚገለጸው መልስ ላይ ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ በትክክለኛ ፍላጎት ከጠየቀ የጆሴፍ ስሚዝ ራዕይ እውነትነት ይገለጻል። በዚህ መንገድ፣ እያንዳንዱ ሰው “ራዕይ አይቻለሁ፣ አውቄዋለሁ፣ እናም እግዚያብሄር እንደሚያውቀውም አውቃለሁ፣ እናም ልክደው አልችልም” ሲል በተናገረ ጊዜ ጆሴፍ ስሚዝ እውነቱን እንደተናገረ ሊያውቅ ይችላል።13

ቤተክርስቲያኗ በዚህ ጽሁፍ ለቀረቡት ታሪካዊ ይዘቶች ምሁራን ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እውቅና ትሰጣለች፤ ስራዎቻቸው የቀረቡት በፈቃድ ነው።

በመጀመሪያ ህዳር 2013 (እ.አ.አ) ታተመ

ተያያዥ ርዕሶች

  • የወንጌል ጥያቄዎችን መመለስ

  • አምላክ

  • እግዚአብሔር አብ

  • ኢየሱስ ክርስቶስ

  • ጆሴፍ ስሚዝ

  • የቤተክርስቲያኗ ዳግም መመለስ

  • የክህነት ስልጣን ዳግም መመለስ

ቅዱሳን መጻህፍት

የቅዱሳን መጻህፍት ማጣቀሻዎች

ቪዲዮዎች

“ዳግም መመለስ”

“ጆሴፍ ስሚዝ፦ የዳግም መመለስ ነቢይ”

“የሚስዮን ዝግጅት ትራክ 14፦ ጎርደን ቢ.ሂንክሊ”

የመማሪያ መረጃዎች

አጠቃላይ መረጃዎች

ታሪክ፣ circa Summer 1832(እ.አ.አ)፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

መጽሄት፣1835–1836(እ.አ.አ)፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

ታሪክ፣ circa ሰኔ 1839(እ.አ.አ)–circa 1841(እ.አ.አ) [ረቂቅ ጽሁፍ 2]፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

‘የቤተክርስቲያን ታሪክ፣’ መጋቢት 1፣1842(እ.አ.አ)፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

‘የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣’ 1844(እ.አ.አ)፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

የጆሴፍ ስሚዝ የአምላክ የመጀመሪያ ራዕይ ቀዳማይ ዘገባዎች፣“ የጆሴፍ ስሚዝ ወረቀቶች

የቤተክርስቲያን መጽሔቶች

ለዳግም መመለሱ መዘጋጀት፣” ኤንዛይን፣ ሰኔ 1999 (እ.አ.አ)

Book of Mormon Personalities Known by Joseph Smith፣” Ensign፣ ታህሳስ 1983(እ.አ.አ)

  1. ለምሳሌ የጀምስ ቢ.አለንን “Eight Contemporary Accounts of the First Vision—What Do We Learn from Them?” ይመልከቱ Improvement Era፣ 73 (1970)፦ 4–13፤ ሪቻርድ ኤል. አንደርሰን፣ “Joseph Smith’s Testimony of the First Vision፣” ኤንዛይን፣ ሚያዝያ 1996 (እ.አ.አ)፣ 10–21፤ ሚልተን ቪ. ባክማን፣ Joseph Smith’s First Vision: The First Vision in Its Historical Context (Salt Lake City: Bookcraft፣ 1971፤ ሁለተኛ እትም፣ 1980(እ.አ.አ))፤ ስቲቨን ሲ. ሃርፐር፣ Joseph Smith’s First Vision: A Guide to the Historical Accounts (Salt Lake City: Deseret Book, 2012(እ.አ.አ))።

  2. እነዚህ ሁሉ ዘገባዎች በዲን ሲ.ጀሲ “The Earliest Documented Accounts of Joseph Smith’s First Vision፣” በ ጆን ደብልዩ. ዌልች፣ ed.፣ ከኤሪክ ቢ. ካርልሰን ጋር፣ Opening the Heavens: Accounts of Divine Manifestations, 1820–1844 (Provo and Salt Lake City: Brigham Young University Press and Deseret Book, 2005), 1–33 ውስጥ ታትመዋል።

  3. የሃዋርያት ሥራ 9:3–922:6–2126:12–18ማቴዎስ 17:1–13ማርቆስ 9:2–13ሉቃስ 9:28–36

  4. ሙሉው ደብዳቤ በጆሴፍ ስሚዝ፣ “የቤተክርስቲያን ታሪክ፣” Times and Seasons 3 (መጋቢት 1፣1842(እ.አ.አ))፦706–10 ሊገኝ ይችላል።

  5. ጆሴፍ ስሚዝ፣ “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣” በአይ.ዳኒኤል ረፕ፣ He Pasa Ekklesia: An Original History of the Religious Denominations at Present Existing in the United States ውስጥ (ፊላደልፊያ፦ ጄ. ዋይ. ሃምፍሪስ፣ 1844(እ.አ.አ))፣ 404–10።

  6. ዊትኒ አር. ክሮስ፣ The Burned-Over District: The Social and Intellectual History of Enthusiastic Religion in Western New York, 1800–1850 (Ithaca, N.Y.: Cornell University Press, 1950); ፖል ኢ. ጆንሰን፣ A Shopkeeper’s Millennium: Society and Revivals in Rochester, New York, 1815–1837 (New York: Hill and Wang, 1983)፤ Nathan O. Hatch, The Democratization of American Christianity (New Haven: Yale University Press, 1989).

  7. የቤናጃህ ዊሊያምስ የማስታወሻ ደብተር፣ ሃምሌ 15፣ 1820 (እ.አ.አ) ቅጅ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጽሃፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤የፊደል አጻጻፉ መደበኛ ተደርጓል።

  8. የ1838 ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5፣ 8)።

  9. የ1838 ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ca.1832 በጋ፣ 1832፣3፣ በጆሴፍ ስሚዝ “የደብዳቤ መጽሃፍ A ውስጥ ፣የጆሴፍ ስሚዝ ስብስብ፣የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ሶልት ሌክ ሲቲ፤የ1838 ዘገባ(ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1:17)።

  10. የ1838 ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥17)፤የ1835 ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ፣ “Sketch Book of the use of Joseph Smith, jr.,” መጽሄት፣ህዳር 9–11፣1835፣የጆሴፍ ስሚዝ ስብስብ፣የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ሶልት ሌክ ሲቲ።

  11. የ1832 (እ.አ.አ) ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ca.1832 በጋ፣ 1832፣3፣ በጆሴፍ ስሚዝ “የደብዳቤ መጽሃፍ A ውስጥ ፣የጆሴፍ ስሚዝ ስብስብ፣የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ሶልት ሌክ ሲቲ)።

  12. ጆሴፍ ስሚዝ ለዊሊያም ደብልዩ.ፌልፕስ፣ ህዳር 27፣ 1832 (እ.አ.አ)፣ የጆሴፍ ስሚዝ ስብስብ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤በ www.josephsmithpapers.orgውስጥ ይገኛል።

  13. የ1838 (እ.አ.አ) ዘገባ (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥25)።