የሞርሞን ቃላት
ምዕራፍ ፩
ሞርሞን የኔፊን ትልቁን ሰሌዳ አሳጠረ—ትንሹን ሰሌዳ ከሌላኛው ሰሌዳ ጋር አስቀመጠ—ንጉስ ቢንያም በምድሪቱ ውስጥ ሰላምን መሰረተ። በ፫፻፹፭ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም አሁን እኔ ሀሞርሞን ለልጄ ሞሮኒ የፃፍኩትን ታሪክ ለመስጠት እየተዘጋጀሁ እያለሁ፣ እነሆ፣ የህዝቤን የኔፋውያንን በሙሉ የመጥፋትን ምስክር ሆኛአለሁ።
፪ እናም እነዚህን መዛግብት ለልጄ የሰጠሁት ክርስቶስ ከመጣ ሀከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ነው፤ እርሱም የህዝቡን ፈፅሞ መጥፋት ይመሰክራል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን አንድ ቀን እነርሱን ለእንዲጠቅማቸው ዘንድ፣ እነርሱን በተመለከተ እናም ክርስቶስን በተመለከተ ጥቂት ይፅፍ ዘንድ እግዚአብሔር ከእርሱ እንዲድን ይፍቀድ።
፫ እናም አሁን፣ የፃፍኩትን በተመለከተ በመጠን እናገራለሁ፤ አማሌቂ ስለተናገራቸው ሀከኔፊ ሰሌዳዎች ጀምሮ እስከ ንጉስ ቢንያም ድረስ፣ ያሉትን ለአሳጥሬ ከፃፍኩ በኋላ፣ የተሰጠኝን ሐመዝገብ መረመርሁ፣ እናም ከያዕቆብ እስከ ንጉስ መቢንያም ንግስና ድረስ ትንሹን የነቢያት ታሪክ የያዙትን እነዚህን ሰሌዳዎችና ደግሞ ብዙዎቹን የኔፊን ቃላት አገኘሁ።
፬ እናም በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ ያሉት ነገሮች እኔን ሀያስደስቱኛል፣ ምክንያቱም የክርስቶስን መምጣት ስለሚተነብዩ፤ እናም አባቶቼ ብዙዎቹ እንደተፈፀሙ ያውቃሉ፤ አዎን፣ እናም ደግሞ እስከአሁን ድረስ ብዙ ነገሮች እኛን በተመለከተ የተተነበዩት እንደተፈፀሙና ከዚያ በኋላ የሚሆኑትም ብዙዎችም በእርግጥ መፈፀም እንዳለባቸው አውቃለሁ—
፭ ስለሆነም፣ በእነርሱ ላይ ምዝገባዬን ለመጨረስ ሀእነዚህን ነገሮች መረጥሁ፣ ቀሪውን ታሪክ ለከኔፊ ሰሌዳዎች ላይ እወስዳለሁ፣ እናም ህዝቤን በተመለከቱ ነገሮች ሐመቶኛውን መፃፍ አልችልም።
፮ ነገር ግን እነሆ፣ ትንቢቶችንና ራዕዮችን የያዙትን እነዚህን ሰሌዳዎች እወስዳለሁ፣ እናም ከቀሪው ፅሁፌ ጋር አስቀምጣቸዋለሁ፣ ለእኔ ምርጥ ናቸውና፤ እናም ለወንድሞቼ ምርጥ እንደሚሆኑ አውቃለሁ።
፯ እናም ይህን ሀለብልህ ዓላማ አደርገዋለሁ፤ በእኔ ውስጥ ያለው የጌታ መንፈስ በዝግታ ድምፅ ተናግሮኛልና። እናም አሁን፣ ሁሉንም ነገሮች አላውቅም፤ ነገር ግን ጌታ የሚመጡትን ነገሮች ሁሉ ለያውቃል፤ ስለሆነም፣ እንደፈቃዱ ለማድረግ በእኔ ይሰራል።
፰ እናም ወደ እግዚአብሔር ሀየምፀልየው ወንድሞቼን በተመለከተ ነው፣ ይኸውም እነርሱ አንዴ እንደገና እግዚአብሔርን ወደማወቅ፣ አዎን፣ በክርስቶስ ቤዛነት ይመጡ ዘንድ፤ አንዴ እንደገና ለየተወደዱ ህዝቦች ይሆኑ ዘንድ ነው።
፱ እናም አሁን እኔ ሞርሞን፣ ከኔፊ ከወሰድኳቸው ሰሌዳዎች ምዝገባዬን ለመጨረስ እቀጥላለሁ፤ እናም ይህን የማደርገው እግዚአብሔር በሰጠኝ እውቀትና መረዳት መሠረት ነው።
፲ ስለሆነም፣ እንዲህ ሆነ አማሌቂ እነዚህን ሰሌዳዎች ለንጉስ ቢንያም በእጁ ሀከሰጠው በኋላ፣ ወሰዳቸውና ከትውልድ እስከ ትውልድ እስከ ለንጉስ ቢንያም ዘመን ድረስ ለንጉሶች የተላለፉትን ታሪክ ከያዙት ሐከሌሎች ሰሌዳዎች ጋር አስቀመጣቸው።
፲፩ እናም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሀበእጄ እስከሚገቡ ድረስ ከንጉስ ቢንያም ተላልፈዋል። እናም እኔ ሞርሞን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከሚመጣው እንዲጠበቁ ወደ እግዚአብሔር እፀልያለሁ። እንደሚጠበቁም አውቃለሁ፤ ምክንያቱም በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ከውስጣቸው ህዝቦቼና ወንድሞቻቸው በታላቁና በመጨረሻው ቀን ለየሚፈረዱባቸው ብዙ ታላቅ ነገሮች በእነርሱ ተፅፈዋልና።
፲፪ እናም አሁን፣ ይህን ንጉስ ቢንያምን በተመለከተ—በህዝቡ መካከል ጥቂት ፀብ ነበረበት።
፲፫ እናም ደግሞ እንዲህ ሆነ የላማናውያን ወታደሮች ከህዝቡ ጋር ሊዋጉ ሀከኔፊ ምድር ወረዱ። ነገር ግን እነሆ፣ ንጉስ ቢንያም ወታደሮቹን በአንድ ላይ ሰበሰበ እናም ተቋቋማቸው፤ በገዛ ክንዱ ብርታት በላባን ለሰይፍ ተዋጋቸው።
፲፬ እናም በጌታ ኃይል ብዙ ሺህ ላማናውያንን እስከሚገድሉ ድረስ ከጠላቶቻቸው ጋር ተጣሉ። እናም እንዲህ ሆነ ከውርስ ምድራቸው ሙሉ በሙሉ እስከሚያስወጧቸው ድረስ ከላማናውያን ጋር ተዋጉ።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ሀሰተኛ ሀክርስቶሶች ከነበሩና፣ አፋቸው ከተዘጋና፣ እንደ ወንጀላቸው ከተቀጡ በኋላ፤
፲፮ እናም በህዝቡ መካከል ሀሰተኞቹ ነቢያት፣ ሀሰተኛ ሰባኪዎችና መምህራን ከነበሩ፣ እናም እነዚህ ሁሉ እንደ ወንጀላቸው ከተቀጡ በኋላ፤ እናም ከብዙ ፀብና ብዙዎች ተገንጥለው ወደ ላማናውያን የሄዱ ከነበሩ በኋላም፤ እነሆ፣ እንዲህ ሆነ ንጉስ ቢንያም፣ ከህዝቡ መካከል ከነበሩት ቅዱስ ሀነቢያት እርዳታ ጋር—
፲፯ እነሆም ንጉስ ቢንያም ሀቅዱስ ሰው ነበረ፣ እናም በህዝቡም ላይ በፅድቅ ነገሰ፤ ብዙ ቅዱሳን ሰዎች በምድሪቱ ላይ ነበሩም፣ እናም የእግዚአብሔርንም ቃል ለበኃይልና በስልጣን ተናገሩ፤ በህዝብ አንገተ ደንዳናነት የተነሳም ብዙ ሐወሳኝ ቃላትን ተጠቀሙ—
፲፰ ስለሆነም፣ በቅዱሳን ነቢያት ድጋፍ፣ ንጉስ ቢንያም፣ እናም ነቢያት፣ በሰውነቱ ሙሉ ኃይልና በአከላተ ነፍሱ ሁሉ በመስራት፣ በምድሪቱ ላይ አንዴ በድጋሚ ሰላምን መሠረተ።