2010–2019 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔር እምባዎችን ሁሉ ይጠርጋል
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


እግዚአብሔር እምባዎችን ሁሉ ይጠርጋል

በአዳኝ እምነታችንን ስንለማመድ፣ ከፍ ያደርገናል እናም በፈተናዎቻችን በሙሉ ይሸከመናል፣ እናም በመጨረሻም በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ያድነናል።

እንደ ሰማይ አባታችን እቅድ ክፍል፣ ሀሰን በስጋዊ ህይወታችን ውስጥ እንዲሰፋ ፈቅዷል።1 አስቸጋሪ ፈተናዎች በእኛ ላይ እኩል ባልሆነ ሁኔታ የሚወድቅብን ቢመስልም፣ በአልድ በኩልም ቢሆን በሌላ፣ ሁላችንም እንደምንሰቃይ እና እንደምንታገል ማረጋጋጫ ለማግኘት እንችላለን። መንፈስ ቅዱስ ይህ ለምን እንደዚህ መሆን እንዳለበት ወደ ታላቅ መረጃ እንዲመራን ጸሎቴ ነው።

የህይወት አስቸጋሪ አጋጣሚዎችን በክርስቶስ እምነት አስተያየት ስንመለከት፣ በስቃያችን መለኮታዊ እቅድ ለመኖር እንደሚችል ለማየት እንችላለን። ታማኞችም የማይስማሙ የሚመስሉትን የጴጥሮስ ምክሮችን እውነት ሊያጋጥማቸው ይችላል። እንዲህም ጻፈ “ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ።”2 “ልብን ወደ መረዳት”3 ስንጠቀምበት፣ ፈተናዎቻችንን ለመጽናት እና ከእነዚህ ለመማር እና በነዚህም ለመነጠር ያለንን ችሎታ ለማሳደግ እንችላለን። ይህ አይነት መረጃም እድሜ ለሌለው “ለምን ነው ለመካም ሰዎች መጥፎ ነገሮች የሚደርሱባቸው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።

ይህን ዛሬ የሚያዳምጥ ሁሉ ከብቸኛነት፣ ከተስፋ መቁረጥ ወይም ከሀዘን ጋር የተዋወቀ ነው።  ያለ “እምነት አይን”4 እና ዘለአለማዊ እውነትን ያለመረዳት፣ በስጋዊ ህይወት የምናገኛቸው መከራና ስቃይ የሰማይ አባታችን ታላቅ እቅድ በእውነት የዘለአለም የደስታ እቅድ እንደሆነ በማወቅ የሚመጣውን ዘለአለማዊ ደስታ በብዛይ እየሸፈኑ እናገኛቸዋለን። የደስታ ሙላይ መቀበያ ሌላ ምንም መንገድ የለም።5

እግዚአብሔር በሌላ መንገድ ለመማር የምይቻሉትን በረከቶችንእና እውቀት እንድናገኝ በራሳችን የግል ልዩ ስቃዮች ውስጥ በእምነት መልስ እንድንሰጥ ይጋብዘናል። በማንኛውም ሁኔታ እና ጉዳይ ትዕዛዛትን እንድንጠብቅ መመሪያ ተሰጥቶናል ምክንያቱም “በችግር ታማኝ የሆነ፣ የዚህም ሽልማት በሰማይ መንግስት ውስጥ ታላቅ ነውና።”6 በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥም እንዲህ እናነባለን፣ “የምታዝን ከሆንክ፣ ጌታ አምላክህን በልመና ጥራ፣ ነፍስህ ደስተኛ ትሆን ዘንድ።”7

ሐዋርያ ጳውሎስ፣ ራሱም ከስቃይ ጋር የማይተዋወቅ ያልሆነው፣ በመልካም ስንጸና እና በትዕግስት፣ ስለሚመጣው ዘለአለማዊ አስተያየት ከራሱ አጋጣሚ በዝልቀት እና በወብት አስተማረ። እንዲህም አለ፣ “ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና።”8 በሌላም አባባል፣ በስቃያችን መካከል እግዚአብሔር ዘለአለማዊ የሚያመዛዝን ሽልማት እንደሚሰጠን ለማወቅ እንችላለን።

ጳውሎስ፣ በወንጌል ዘለአለማዊ የርቀት እይታ የተዋጠውን፣ ስለህይወቱ ስለፈተናዎች፣ መሰደድ፣ እና ስቃዮች እንደ “ቀላል መከራ” ለመናገር ያለው ችሎታ በእውነት የተሰቃየውን ይደብቃል። ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እምነት ሁሉንም ነገሮች እንዲቋቋም እስቻለው። አምስት ጊዜ ተገርፏል፣ ሶስት ጊዜ በዱላ ተመቷል፣ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተደብድቧል፤ ለሶስት ጊዜ የመርከብ አደጋ ደርሶበታል፤ በብዛትም በመጥለቅ፣ በዘራፊዎች፣ እና እንዲሁም በሀሰት ወንድሞች በሞት አደጋ ላይ ነበር፤ ድክመትና በሽታ፣ ራብና ጥማት፣ እናም በብርድ እና በእርቃን መታሰር ደርሶበታል።9

ብዙዎቻችን የስቃያችን ምክንያቶች እንዲነሱልን እግዚአብሔርን እንለምናለን፣ እናም የምንፈልገር እረፍት ሳይመጣም፣ እርሱ እንደማያዳምጥ ለማሰብ ተፈትነናል። በነዚህም ጊዜዎች ጸሎታችንን እንደሚያዳምጥ፣ ስቃያችን እንዲቀጥሉ የሚፈቅድበት ምክንያት እንዳለ፣10 እና እንድንሸከማቸው እንደሚረዳን እመሰክራለሁ።11

ግልጽ እና እንድናስብበሚያደርግ ጽሁፍ፣ ጳውሎስ ስም ስለሌለው በስጋው ውስጥ ስላለ “እሾህ” ተናገረ፣ ይህም ታላቅ ስቃይ አመጣበት እናም ለሶስት ጊዜ በኩልበቱ ወድቆ ጌታ ይህን እንዲወስድለት ለምኖ ነበር። ለጳውሎስ ጸሎት መልስም፣ ጌታ እሾሁን አላወጣውም ነገር ግን ሰላም እና መረዳጃ ለመስጠት በልቡ አናገረም፣ እንዲህም አለ፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና።” በአዲስ መረጃ፣ ጳውሎስ የተሰጠውን እሆሽ ለመቀበል እና ምስጋና ለመስጠት ችሎ ነበር። እንዲህም አለ፣ “የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ … በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።”12

ይህን ዘለአለማዊ አስተያየትን በህይወታችን ስናገኝ፣ እድገትን ለመጽናት ያለን ችሎታ ያድጋል፣ እድራታ የሚያስፈጋቸውን እንዴት ለመርዳት እንደምንችል13 እንማራለን፣ እናም እግዚአብሔር በዘለአለማዊ ህይወት መንገድ እንደአስተማሪ አጋጣሚዎች እንዲኖሩን ለሚፈቅደው ምስጋናን እንሰጣለን።

ራሳችንን በመከራ እየተጓዝን ስናገኝ፣ ፈተናዎቻችን እንደ ደቀመዛሙርትነታችን የግል ፈተና የመንገድ ምልክት እንደሆኑ ለማየት ያስቸግር ይሆናል። ነገር ግን በተስፋ መቁረጥ ሸለቆ ውስጥ የምንጓዝ ወይም በደስታ ከፍተኛ መንገድ ላይ ያለን ብንሆን፣ ከሌሎች ስቃይ እና ለእነርሱም የርህራሄ ስሜት እንዲኖረን በመማር ለመባረክ እንችላለን።

በቅርብ ፍልፒንስ ውስጥ በነበረ የካስማ ጉባኤ በተመደብኩበት፣ ስለወንድም ዳኔል ኤች. አፒልዶ የሚያሳዝን የህይወት አጋጣሚዎች ሳዳምጥ ልቤ ተሰብሮ ነበር። ወንድም አፒልዶ እና ባለቤቱ በ1974 (እ.አ.አ) ተጠምቀው ነበር። በዳግም የተመለሰውን ወንጌል ተቀበሉ እናም በቤተመቅደስ ታተሙ። ስለዚህ፣ በአምስት ቆንጆ ልጆች ተባርከው ነበር። በሀምሌ 7፣ 1997 (እ.አ.አ)፣ ወንድም አፒልዶ እንደ ካስማ ፕሬዘደንት እያገለገሉ እያሉ፣ ትንሹ ቤታቸው በእሳት ነደደ። የወንድም አፒልዶ ታላቅ ወንድ ልጅ፣ ማይክል፣ አባቱን አዳነ እናም ከሚቃጠለው ቤት ጎትቶ አወጣው፣ ከዚያም ሌሎቹን ለማዳኝ ሮጦ ወደ ቤት ውስጥ ገባ። ይህም ወንድም አፒልዶ ልጁን በህይወት ያየበት የመጨረሻ ጊዜ ነበር። በእሳት የሞቱን የወንድም አፒልዶ ባለቤት ዶሚንጋና አምስቱ ልጆቻቸው ነበሩ።

ይህ አሳዛኝ አደጋ ሲደርስ ወንድም አፒልዶ እግዚአብሔርን በሚያስደስት ህይወት የኖረ ቢሆንም ይህን አደጋ አላቆመውም ወይም በዚህ የሚከተለውን ሀዘን ለመቋቋም እንዲችል አላደረገውም። ነገር ግን ቃል ኪዳናቸውን በመጠበቅ እና በክርስቶስ ያላቸውን እምነት በመለማመድ ያላቸው ታማኝነት ከባለቤታቸው እና ከልጆቻቸው ጋር እንደገና እንድሚገናኙ ያለው የተስፋ ቃል ማረጋገጫ ሰጣቸው። ይህም ተስፋ የነፍሱ መህልቅ ሆነ።14

በጉብኝቴ፣ አሁን የካስማ ፓትሪያርክ የሆኑት፣ ወንድም አፒልዶ፣ ከአዲስ ባለቤታቸው ስሞኔት እና ከሁለቱ ወንድ ልጆቻቸው፣ ከራፓዬል እና ዳንኤል፣ ጋር አስተዋወቁኝ። በእውነትም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ “ልባቸው የተሰበረውን ይጠግ[ናል]”15 እናም ለመጠገንም ይችላል።

የወንድም አፒላዶ ታሪክን በመካፈል፣ የእርሳቸው ጉዳት ታላቅነት ብዙዎች የእነርሱ ሀዘን እና ስቃይ ከዚህ ጋር ሲነጻጸሩ ትንሽ እንደሆኑ እንዳይሰማቸው እጨነቃለሁ። እባካችሁ አታነፅሩ፣ ግን በራሳችሁ የስቃይ እሳት ውስጥ ስትሄዱም የዘለአለም መሰረታዊ መርሆችን ለመረዳት እና ለመጠቀም ለመማር ፈልጉ።

በግል ላነጋግራችሁ ከቻልኩች፣ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣”16—የግል ትግላችሁ፤ ማንኛውም የግል ሀዘኖቻችሁ፣ ህመማችሁ፣ መከራችሁ፣ እና እያንዳንዱ አይነት አቅመ ደክምነት፤ ለሰማይ አባትችን እና ለልጁ የሚታወቁ እንደሆኑ ሀሳብ ላቅርብላችሁ። ተበረታቱ! እምነት ይኑራችሁ! እናም የእግዚአብሔር የተስፋ ቃልን እመኑ!

የኢየሱስ ክርስቶስ አላማ እና ተልዕኮ “የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ለመውሰድ፣” “ድካማቸውን በራሱ ላይ ለማድረግ፣” “ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ”17 በተጨማሪ የያዘ ነበር።

አዳኝ በነጻ የሰጠን ስጦታ በሙላት ለመቀበል፣ እኛ በዝግታ እምነትን በመለማመድ በኩል በስቃያችን በመማር ካልተካፈልን በስተቀር፣ መሰቃየት በብቻው ለመቆየት የሚችል ዋጋ ሊያስተምረን ወይን እንደሚሰጠን ማወቅ አለብን።

ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዊል ጥቅም ስላለው ስቃይ የተማሩትን በእነዚህ ቃላት ተካፍለዋል፥

“አንዳንድ ስቃዮች፣ በደንብ ከተጽናናን፣ ከፍ ሊያደርገን ይችላል። …

“… በደንብ መፅናት በስቃያችን መካከል ትሁት መሆን፣ … ከአጋጣሚያዎቻችን መማርንም ያካተተ ነው። በእነዚህ ነገሮች በተራ ከማለፍ ሳይሆን፣ በሚቀድሰን መንገድ …በእኛ ውስጥ ማለፍ አለባቸው።”18

በሌሎች ህይወት እና ምሳሌ ውስጥ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ላይ ጠንካራ እና የሚቆይ ተስፋ ሲኖረን ለመመዘን የማይቻል የጥንካሬ እና የሀይል ምንጭ እንደሚሰጥ ተመልክቻለሁ። ይህም የተረጋገጠ ተስፋ ፅኑ እንድንሆን ያደርጋል፣ ለመፅናት የሚያስፈልገንን ጥንካሬና ሀይልም ያመጣል።19 ስቃያችንን ከሟች ህይወት አላም ጋር እና በልዩም በሰማይ ቦታዎች ውስጥ ከሚጠብቁን ሽልማቶች ጋር በማያያዝ፣ በክርስቶስ ያለን እምነት ይጨምራል እናም በነፍሳችን መፅናኛ እንቀበላለን።

ከዚያም በመንገዱ መጨረሻ ላይ ብርሀን ይታየናል። ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳስተማሩት፥ “በእውነትም በመንገዱ መጨረሻ ላይ ብርሀን አለ። ይህም የአለም ብርሀን፣ ብሩህ የሆነና የጠዋት ኮኮብ፣ ‘መጨረሻ የሌለው ብርሀ፣ ለመጨለም የማይችለው’ [ሞዛያ 16፥9]። ይህም ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።”20

የዚህ ህይወት ከባድ አጋጣሚዎች ጊዜአዊ—እንዲሁም ጭለማ የሆኑት ምሽቶች ለታማኞች ወደ ጠዋት እንደሚለወጡ ማወቃችን ጥንካሬ ሊሰጠን ይችላል።

ሁሉም ሲፈጸም፣ ሁሉም ሲከናወን፣ ሁሉንም ነገሮች ወደፊት በሚመጣው ላይ በማመን እና ተስፋ በመጣል ስንጸና፣ ይህም ከሁሉም በላይ የሚሆነው ቃል ኪዳን ይሟላል፥ “እግዚአብሔርም [እንባችንን] ሁሉ ከዓይና[ችን] ያብሳል።”21

እግዚአብሔር አባታችን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ህያው እንደሆኑ እና የቃል ኪዳኖች ጠባቂ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። አዳኝ እንድንመጣ እና የኃጢያ ክፍያውን እንድንቀበል እንደሚጋብዘን እመሰክራለሁ። በእርሱ እምነታችንን ስንለማመድ፣ ከፍ ያደርገናል እናም በፈተናዎቻችን በሙሉ ይሸከመናል፣ እናም በመጨረሻም በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ያድነናል። ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ፣ በእምነት በደንብ እንድትጸኑ፣ እናም በእርሱ ውስጥ ፍጹም እንድትሆኑ፣ እና በእርሱም ፍጹም ደስታ እንድታገኙ እጋብዛችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።