2010–2019 (እ.አ.አ)
በሰንበት ቀን ምስጋና
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


በሰንበት ቀን ምስጋና

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ሰንበት የምስጋና ቀን ነው።

በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአለም አቀፍ የምትገኙ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ, ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በዚህ በሰንበት ቀን በጉባኤው ንግግር እንዳቀርብ ስለጠየቁኝ አመሰግንለሁ። መንሰፍ ቅዱስ ቃላቴን ወደ ልባችሁ ይዞ እንዲገባ እጸልያለሁ። መንሰፍ ቅዱስ ቃላቴን ወደ ልባችሁ ይዞ እንዲገባ እጸልያለሁ።

ዛሬ ስለልብ ስሜት ለመናገር እፈልጋለሁ። የማተኩርበት አንዱ ምስጋና ነው–በልዩም በሰንበት ቀን።

ለብዙ ነገሮች ምስጋና አለን፥ ለእንግዳ ሰው ደግነት፣ ሲርበን ለምንበላው፣ ዝናቢ ሲመጣ በበላያችን ለሚገኘ ለደረቀው ጣራ፣ ለሚፈወሰው የተሰበረ አጥንት፣ እና በልብ ለሚያለቅሰው አዲስ ለተወለድ ልጅ። በእንደዚህ አይነት ጊዜዎች ምስጋና ሲሰማን ብዙዎቻችን እናስታውሳለን።

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ሰንበት እንደዚህ አይነት የምስጋና ቀን ነው። በ1831 (እ.አ.አ) በጃክሰን ካውንቲ፣ ምዙሪ ውስጥ ጌታ ቅዱሳንን ጸሎታቸውን እና ምስጋናቸውን ወደሰማይ እንዲልኩት አስተማረ። የመጀመሪያው ቅዱሳን ሰንበትን እንዴት እንደሚጠብቁ እና እንዴት እንደሚጾሙና እንደሚጸልዩ ራዕይ ተሰጥቷቸው ነበር።1

እነርሱ፣ እናም እኛ፣ በጌታ በሰንበት እንዴት እንደምናመልክ እና ምስጋና እንደምንሰጥ ተነግረናል። እንደምታውቁት፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሚሆነው ለስጦታዎች ሰጪው ያለንየፍቅር ስሜት ነው። በዚህም በሰንበት እንዴት ምስጋና እንደምንሰጥ እና እንደምናፈቅር ጌታ የሰጠው ቃላት ናቸው፥

“እንዲህ በማለት ትእዛዛትን እሰጣቸዋለሁ፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አዕምሮህ፣ እና በፍጹም ሀይልህ ውደድ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም አገልግለው። …

“ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች አመስግን።

“የተሰበረ ልብን እና የተዋረደ መንፈስን መስዋዕት አድርገህ ለጌታ አምላካህ በፅድቅ አቅርብ።”2

ከዚያም ጌታ የስጦታ ጸጪዎች የሆኑትን የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለማፍቀርና ማምስገን መውደቅን አስጠናቀቀን። “በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ካለመመስከር እና ትእዛዙን ካለማክበር በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም።”3

የምታዳምጡት ብዙዎቻችሁ የሰንበት ቀንን እንደማስታወሻ እናም እግዚአብሔርን ለበረከቶች እንደምታመስግኑበት ቀን ትደሰትበታላችሁ። የምታውቁትንመዝሙር አስታውሱ፥

በህይወት ነፋሶች ላይ በአውሎ ንፋስ ስትወረወሩ፣

ተስፋ ስትቆሮጡ፣ ሁሉም ጠፍታል ብለን ስናስብ፣

በረከቶቻችሁን ቁጠሩ፤ አንድ በአንድ ስም ስጧቸው፣

እናም ጌታ ምን ያደረገው ያስገርማችኋል።

በረከታችሁን ቁጠሩ፤

አንድ በአንድ ስም ስጧቸው።

በረከታችሁን ቁጠሩ፤

እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ እዩ። …

የህይወት ችግር ሸከም አለባችሁን?

እንድትሸከሙት የተጠየቃችሁት መስቀል ከባድ ይመስላልን?

በረከታችሁን ቁጠሩ፣ ጥርጣሪዎች በሙሉ ይበራሉን፣

እናም ቀኑ ሲቀጥል ትዘምራላችሁና።4

የመንከባከቢያ ሸከም በከበደባቸው ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በደብዳቤ እና በጉብኝት እሰማለሁ። እንዳንዶች፣ ለራሳቸውም ቢሆን፣ ሁሉም የጠፋ ይመስልቸዋል። በሰንበት ስለማመስገን የምለው ጥርጣሪዎች እንዲጠፉ እና በልጅ መዘፈን እንዲጀምር እርዳታ እንዲሰጡ ተስፋዬ እና ጸሎቴ ነው።

ምስጋና ሊሮረን ከምንችለው በረከቶች አንዱ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ መገኘታችን፣ ከደቀመዛሙርቱ አንድ ወይም ሁለት በላይ ከሆኑታ ጋር ለመሰብሰብ መቻላችን ነው። ከመኝታቸው ለመነሳት የማትችል ወይም የማትችል አንዳንድ በቤት ውስጥ ይገኛሉ። እናንተ በምትገኙበት ለሚሆን የሚፈልጉ ግን በሆስፒታል ውስጥ እና በህብረተሰብ ደህንነት እያገለገሉ የሚገኙ ወይም የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል በምድረበዳ ወይም በጫካ ውስጥ የሚገኙ አንዳንዶች አሉ። ከአንድ ሌላ ቅዱሳን ጋር ለመሰብሰብ እና ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል በመቻላችሁ ነው ለእግዚአብሔር ደግነት ምስጋና እና ፍቅር ሊሰማችሁ የሚገባችሁ።

በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝና በዳግም በተመለሰው ወንጌል፣ ሌላ የምንቆጥረው በረከት ቢኖር ስልጣን ባለው የእግዚአብሔር አገልጋይ የተዘጋጀውን፣ የተባረከውን፣ እና የተሰጠውን ቅዱስ ቁርባን በየሳምንቱ ለመቀበል ላለን እድል ነው። ስልጣን ያላቸው የክህነት ተሸካሚ የቀረቡት የቅዱስ ቁርባን ጽሎቶች በሰማይ አባት እንደሚከበሩ በመንፈስ ቅዱስ ሲረጋገጥም ምስጋና ሊኖራችሁ ትችላላችሁ።

ለመቁጠር ከምንችላቸው በረከቶች ሁሉ መካከል ከሁሉም ታላቅ የሆነው ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል የሚመጣው የምህረት ስሜት ነው። ከኃጢያታችን እንድንጸዳ መጨረሻ የሌለው መስዋዕቱን ለሰጠን ለአዳኝ ታላቅ ፍቅር እና ምስጋና ይሰማናል። ዳቦና ውሀንም ስንቀበል፣ ለእኛ እንደተሰቃየ እናስታውሳለን። ላደረገው ምስጋና ሲሰማን፣ ለእኛ ያለው ፍቅር እና እኛ ለእርሱ ያለን ፍቅር ይሰማናል።

የምንቀበላቸው በረከቶች እርሱን “ሁልጊዜ እንድናስታውስ”5 የተሰጠንን ትእዛዝ ለመጠበቅ ቀላል ያደርገዋል። ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ታማኝ ከሆንን የሰማይ አባት ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚገን ቃል የገባውን መንፈስ ቅዱስ የማፍቀር እና የምስጋና ስሜት ይኖረናል። እነዚህን ሁሉ በረከቶች በየሰንበቱ ሊሰማን እና ምስጋናም ሊሰማን እንችላለን።

ሰንበትም የሰማይ አባት ልጆችን ለማፍቀር እና ለማገልገል የገባችሁትን ቃል ኪዳን ለማስታወስ ፍጹም የሆነ ቀን ነው። ይህን ቃል ኪዳን ማሟላትም በተጨማሪ በወንድሞቻችሁ እና በእህቶቻችሁ መካከል እምነት እና ፍቅርን ለመገንባት ከክፍል ወይም ከቡድን ጋር በሙሉ የልብ አላማ መሳተፍም ያስፈልገዋል። ያም ቃል ኪዳን በጥሪአችን መደሰትንም ያካትታል።

በባውንትፉል፣ ዩታ ውስጥ በዲያቆን ቡድን እናም በአይደሆ የሰንበት ትምህርት ክፍል ውስጥ በብዙ እሁዶች ያስተማርኩበትን አሁንም አስታውሳለሁ። ዋናው ሀላፊነቴ መጫወቻዎችን መምረጥ እና መስጠት በሆነበት በህጻናት ክፍል ውስጥ እንደባለቤቴ ረጂ ያገለግልኩበትንም አስታውሳለሁ።

ለጌታ የማቀርበው አገልግሎቴ ለሰማይ አባት ልጆች ጠቃሚ እንደነበር በመንፈስ ያወቅኩት ከብዙ አመት በፊት ነበር። በሚያስገርመኝ ሁኔታም፣ አንዳንዶቹ በነዚያ ሰንበት ቀናት መምህርን ለማገልገል የምጥረውን ከብዙ አመቶች በኋላ ያስታውሱ ነበር።

በሰንበት የምንሰጠውን አገልግሎት ውጤት አንዳንዴ እኛ ለማየት እንደማንችልም፣ የሌሎች የጌታ አገልጋዮች የተጠራቀሙ ውጤት ለማየት አንችልም ይሆናል። ነገር ግን ጌታ በጸጥታ እና በትንሽ ትይታ፣ በታማኝ እና ትሁት አገልጋዮቹ፣ መንግስቱን ወደ ወደፊት ግርማዊ ሺህ አመት እየገነባ ነው። የሚያድገውን ታናቅ ድንቁን ለማየት መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገዋል።

በኒው ጀርዚ ቅርጫፍ ውስጥ ከትንሽ አባላት እና አንድ ቤተሰብ ጋር ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ በምሀድበት ነበር ያደግኩትኝ። ከሰባ አምስት አመት በፊት፣ በፔንስልቬኒያ እና በኒው ጀርዚ ውስጥ በቤተክርስቲያኗ በብቻነት በተገነባ የጸሎት ቤት ውስጥ በፊለደልፊያ ነበር የተጠመቅኩት። ግን በፕርስንተን፣ ኒው ጀርዚ ውስጥ አንድ ቅርንጫፍ በነበረበት፣ አሁን ሁለት ትትልቅ የዎርድ ህንጻዎች አሉ። ከትንሽ ቀናት በፊት፣ ብዙ ሺህ ወጣቶች ከፊለዶልፊያ፣ ፔንስልቬንያ ቤተመቅደስ መመሪቂያ በፊት ባለው በአል ተጫውተው ነበር።

እንደ ወጣትነቴ፣ በአልበከርኪ፣ ኒው ሜክሲኮ ውስጥ በምትገኘው ብቸኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ አውራጃ ሚስዮን እንዳገለግል ተጠርቼ ነበር። ዛሬ ቤተመቅደስ እና አራት ካስማዎች ይገኛሉ።

ከአልበከርኪ ወደ ካምብሪጅ፣ ማሳቹሴት ለትምህርት ሄድኩኝ። በዚያም አንድ ቤተክርስቲያን እና ማሳቹሴት እና ሮድአይላንድን በሙሉ ያካተተ አንድ አውራጃ ነበር። በዚያ ወብታማ ከተማ ኮረብታ ላይ እየነዳሁ ወደ ትንሿ ቅርንጫፎች ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እሄድ ነበር፣ አብዛኛዎቹም የኪራ ህንጻዎች ወይም ትትንሽ ቤቶች ነበር። አሁን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ በቤልሞንት፣ ማሳቹሴት እና በሀገሩ የተሰራቹ ካስማዎች ይገኛሉ።

በዚያ ጊዜ በግልጽ ለማየት ያልቻልኩት ጌታ በነዚያ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ውስጥ መንፈሱን እያፈሰሰባቸው እንደነበር ነው። ይህም ይሰማኛል፣ ነገር ግን እንዴት የተስፋፋ እንደነበረ እና ጌታ መንግስቱን ለመገንባት እና ግርማ ለመስጠት ያለመበትን እቅድ ጊዜ አላውቅም ነበር። ነቢይ፣ በራዕይ፣ አሁን ለማየት የምንችለውን አይቶና መዝግቦ ነበር። ኔፊ ቁጥራችን ታላቅ አይሆንም ብሏል፣ ነገር ግን የነዚህ ተጨማሪ ብርሀኖች ለማየት የሚያስደንቁ ናቸው።

“እናም እንዲህ ሆነ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያንን ተመለከትኩ፣ ... ቁጥሯ ጥቂት ነበሩ። …

“እኔ ኔፊ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።”6

በዚህ ዘመን ውስጥም፣ ወደፊት ያለውን የኛን ሁኔታ እና እድል የሚገልፅ እንዲህ አይነት የትንቢት መግለጫ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተመዝግበዋል።

“አብ በእጆቹ ምን አይነት ታላቅ በረከቶች እንዳለው እና ለእናንተም እንዳዘጋጀ ገና አልገባችሁም፤

“እናም ሁሉንም ነገሮች አሁን መሸከም አትችሉም፤ ይህም ቢሆን፣ ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁና። መንግስት የእናንተ ናት እናም በእዚያም ያሉ በረከቶች የእናንተ ናቸው፣ እናም የዘለአለም ባለጠግነትም የእናንተ ናቸውና።

“እናም ሁሉንም ነገሮች በምስጋና የሚቀበል እርሱ የከበረ ይሆናል፤ እናም የምድር ነገሮችም፣ እንዲሁም በመቶ እጥፍ፣ አዎን በብዙ፣ ለእርሱ ይጨመሩለታልና።”7

ለበረከቶች እና ለእግዚአብሔር ፍቅር ያለ የሚቀይር የምስጋና እድገት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሲጨምር ተሰምቶኛል። የእምነታቸው ፈተና ባላበት፣ ወደፊት ለመሄድ እንኳን እግዚአብሔርን በሚለምኑበት ጊዜ ይህ በቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል በፍጥነት የሚያድግ ይመስላል።

የአልማ ህዝብ ለመሸከም የማይችሉትን ሸከም በጣለባቸው በክፉው በአሙሎን ገዢነት ስር እንደነበረው እኛም በታላቅ ችግር ጊዜዎች ውስጥ እያለፍን ነን፥

“እናም እንዲህ ሆነ የጌታ ድምፅ በስቃያቸው እንዲህ በማለት መጣ፥ እራሳችሁን አቅኑም መልካም መፅናኛ ይኑራችሁም፤ ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አውቀዋለሁና፤ ከህዝቤም ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ እናም ከባርነት አስለቅቃቸዋለሁ።

“እናም ደግሞ በባርነት በነበራችሁ ጊዜም ቢሆን፣ በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፣ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልልላችኋለሁ፤ እናም ይህንን የማደርገው ከዚህ በኋላ ለእኔ በምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው።

“እናም አሁን እንዲህ ሆነ በአልማና በወንድሞቹ ላይ የሆነው ሸክም ቀለለላቸው፣ አዎን፣ ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትዕግስት ለጌታ ፈቃድ ተቀባይ እንዲሆኑ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል።”8

እኔ እና እናንተ፣ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም፣ የጌታን ትእዛዛት ስናከብር፣ ለእኛ ላደረገው የምስጋና ጸሎት እንደሰማ እና በታማኝነት ለመፅናት ጥንካሬ እንዲሰጠን ለምንጸልየው መልስ እንደሚሰጥ ምስክሮች ነን። እናም ከአንድ በላይ ለሚሆንም እናንተ አስደሳች እና ጠንካራ አድርጓችኋል።

እናንተ ራሳችሁ ወደፊት ላሉት ፈተናዎች ምስጋና እና ጥንካሬ ለራሳችሁ እና ለሌሎች ለማሳየት እንዴት በዚህ ሰንበት ለመኖር እና ለማምለክ ታስቡም ይሆናል።

ዛሬ በግል እና በቤተሰብ ጸሎት እግዚአብሔር ላደረገላችሁ በሙሉ በማመስገን ለመጀመረ ትችላላችሁ። እርሱን እና ሌሎችን ለማገልገል ጌታ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልጋችሁ ለማወቅ ለመጸለይ ትችላላችሁ። በልዩም፣ መንፈስ ቅዱስ ጌታ እንድትሄዱላቸው የሚፈልጋችሁን ብቸኛ ስለሆነ ወይም እርዳታ ስለሚያስፈልገው ሰው እንዲነግራችሁ ለመጸለይ ትችላላችሁ።

ጸሎታችሁ መልስ እንደሚያገኝ፣ እና በተቀበልችሁት መልስ ስትሰሩም፣ በሰንበት ደስታ እንደምታገኙና ልባችሁ በደስታ እንደሚሞላ እመሰክራለሁ።

እግዚአብሔር አብ ያውቃችኋል እናም ያፈቅራችኋል። አዳኝ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለኃጢያቶቻችሁ ለእናንተ ባለው ፍቅር ምክንያት ክፍሎበታል። ልክ ለእርሱ በታዩበት ጊዜ የነቢዩ ጆሴፍን ስም እንዳወቁት፣ አብ እና ወልድ፣ የእናንተንም ስም ያውቃሉ። ደግሞም ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እና ከእርሱ ጋር የገባችሁትን እና የምታድሱትን ቃል ኪዳን እንደሚያከብር እመሰክራለሁ። ፍጥረታችሁ ራሱ እንደ አዳኝ መሆን ይቀየራል። ከፈተናዎች ስለእውነት ከመጠራጠር ስሜት ተገደባላችሁ። ደስታን በሰንበት ታገኛላችሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።