2010–2019 (እ.አ.አ)
አምላክ እና የደህንነት እቅድ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


አምላክ እና የደህንነት እቅድ

ስለአምላክ እና ከእነርሱ ጋር ስላለን ግንኙነት እውነት ስላለን፣ እኛ በሟች ህይወት ጉዞአችን ውስጥ የመጨረሻው ካርታ አለን።

፩.

የእኛ የመጀመሪያ የእምነት አንቀጽ እንደሚያውጀው፣ “በዘለአለማዊ አባት እግዚአብሔር፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን።” ሌሎች ክርስቲያናት አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስን በማመን አንድ ነን፣ ነገር ግን ስለእነርሱ የምናምነው ሌሎች ከሚያምኑት የተለየ ነው። የክርስቲያን አለም ስላሴ ብለው የሚጠሩትን አናምንም። በመጀመሪያም ራዕይ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ሁለት የተለያዩ ሰዎችን፣ ሁለት ህያው ፍጡር አየ፣ በዚህም በዚያ ጊዜ በሁሉም ስለእግዚአብሔር እና ስለአምላክ ይታመንበት የነበረው ግልጽ አደረገ።

እግዚአብሔር ለመረዳት የማይቻል እና የማይታወቅ ሚስጥር ከሆነው እምነት ጋር በማነጻጸር፣ ስለእግዚአብሔር ፍጡር እና ከእርሱ ጋር ስላለን ግንኙነት ያለ እውነት የሚታወቅ እንደሆነ እና በትምህርታችን ውስጥ ለሁሉም ነገሮች ዋና እንደሆነ እናምናለን። የኢየሱስን በምልጃ ጸሎት እንዲህ ያወጀው በመፅሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፥ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” (ዮሀንስ 17፥3)።

ምስል
መፅሐፍ ቅዱስ

እግዚአብሔርን እና ስራውን ለማወቅ የተጀመረው ከሟች ህይወት በፊት ነበር እናም የሚፈጸመው በዚህ አይደለም። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ “በመጋረጃው በኩል ካለፋችሁ ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው [የዘለአለማዊነት መርሆዎችን በሙሉ] የምትማረት።”1 ከህይወት በፊት በመንፈስ አለም ውስጥ ባገኘነው እውቀት ላይ ነው የምንገነባው። በዚህም፣ እስራኤላውያንን ስለእግዚአብሔር ፍጡር እና እርሱ ከልጆቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስተማር፣ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ አወጀ፥

“እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? …

“አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?” (ኢሳይያስ 40፥18፣ 21)።

የአምላክ ሶስት አባላት የተለያዩ ህያው ፍጡር እንደሆኑ ኣውቃለን። ይህን የምናውቀው በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በተሰጠው ትምህርት ነው፥ “አብ እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል የስጋ እና አጥንት አካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የስጋ እና አጥንት አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ አካል ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ለመኖር ባልቻለ ነበር።” (ት. እና ቃ. 130፥22)።

እግዚአብሔር አብ በአምላክ ውስጥ ምን ከፍተኛ ቦታ እንዳለው፣ እንዲሁም እያንዳንዱ የሚያከናውኑትን ሀላፊነት፣ ነቢዩ ጆሴፍ እንዲህ ገልጿል፥

ምስል
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ

“ሰማይ ሲከፈት ያየ ማንም ሰው በሰማይ ውስጥ የሀይል ቁልፍ የያዙ ግለሰቦች እንደሚገኙ ያውቃል፣ እናም አንዱ በእነርሱ መካከል መሪ ነው። …

“… እነዚህ እነዚህ ግለሰቦችም … ተብለው የሚጠሩት፣ የመጀመሪያው እግዚአብሔር፣ ፈጣሪው፤ ሁለተኛው እግዚአብሔር፣ አዳኙ፤ እና ሶስተኛው እግዚአብሔር፣ ምስክር ወይም መስካሪው።

“[ይህም] የአብ ሀላፊነት እንደ ፕሬዘደንት ወይም አልቃ መምራት፣ የኢየሱስም አማላጅ፣ እና መንፈስ ቅዱስም ምስክር ወይም መስካሪነት ነው።”2

፪. እቅድ

ከአምላክ ጋር ያለን ግንኙነት ያለን መረጃ የሚመጣው ስለደህንነት እቅድ በተገለጸው ነው።

“ከየት ነው የመጣነው?” ለምን በዚህ አለን? እና የት ነው የምንሄደው? የሚሉት ጥቄዎች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ “የደህንነት እቅድ፣” “የደስታ እቅድ፣” ወይም “የቤዛነት እቅድ” ተብለው በሚጠሩት ይመለሳሉ (አልማ 42፥5፣ 8፣ 11)። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የዚህ እቅድ ዋና ክፈል ነው።

ከሟች ህይወት በፊት እንደነበርን እንደ እግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች፣ እኛም የዘለአለም ህይወት እጣ ፈንታችንን ፈለግን ነገር ግን ሰውነት ካለው ያለሟች ህይወት በስተቀር ለማደግ እስከምንችልበት ድረስ ሄደን ነበር። ይህን እድል ለመስጠጥ፣ የሰማይ አባታችን በዚህች አለም መፈጠር ላይ መራ፣ በዚህም ከሟች ህይወት ከመወለዳችን በፊት የነበረን ትዝታ ተወስዶብን፣ የእርሱን ትእዛዛት ለማክበር እና በሟች ህይወት ፈተናዎች በኩል ልምምድን እና እድገትን ልእማግኘት የምንችልበት ነበር። ነገር ግን በሟች ህይወት ልምምድ ውስጥ፣ እና በመጀመሪያ ወላጆቻችን ውድቀት ምክንያት፣ ከእግዚአብሔር ፊት በመወገድ የመንፈስ ሞት፣ በኃጢያት መቆሸሽ፣ እና ለስጋዊ ሞት ተገዢ መሆን ደረሰብን። የአብ እቅድም እነዚህን ሁሉ ገደቦች አስቀድሞ ጠበቀ እናም የምናሸንፍባቸው መንገዶች ሰጠ።

፫. አምላክ

የእግዚአብሔርን ታላቅ እቅድ በማወቅ፣ አሁን የአምላክ ሶስ አባላት በዚህ እቅድ ውስጥ ያላቸውን ሀላፊነት እንመረምራለን።

መጀመሪያ በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውስጥ እንጀምራለን። ለቆሮንቶስ በጻፈው ሁለተኛ ደብዳቤ መጨረሻ ላይ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ደንታ ቢስ በሆነ ሁኔታ ስለአምላክ አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ጠቀሰ። “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት [“ጓደኝነት”3] ከሁላችሁ ጋር ይሁን” (2 ቆሮንቶስ 13፥14)።

ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሰት አምላክን ያመለክታል እናም የእግዚአብሔር አብ ሁሉን ትርጉም የሚሰጥና የሚያነሳሳ ፍቅርን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምህረታዊና አዳኝ ስራ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ይጠቅሳል።

እግዚአብሔር አብ

ሁሉም የሚጀምረው በእግዚአብሔር አብ ነው። ስለእርሱ በጣም ትንሽ የምናውቅ ብንሆንም፣ የምናውቀው የእርሱን ከፍተኛ ቦታ፣ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት፣ እና በደህንነት እቅድ፣ በፍጥረት፣ እና ከዚያም ከተከተሉት ሁሉ ላይ ያለውን ተቆጣጣሪ ሀላፊንትን በውሳኔአዊነት የምንረዳው ነው።

ሽማግሌ ብሩስ አር. መኮንኪ ከሞታቸው በፊት እንደጻፉት፥ “በቃሉ የመጨረሻ አባባል፣ አንድ እውነተኛ እና ህያው እግዚአብሔር ነው ያለው። እርሱም አብ፣ ሁሉን ቻይ ኤሎሔም፣ ከፍተኛ ህያው ፍጡር፣ ፈጣሪና የሁለንተና ገዢ ነው።”4 እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም የሁላችንም፣ እግዚአብሔር እና አባት ነው። ፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ. መኬይ እንዳስተማሩት “በኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያው የተደገፈ እውነት ቢኖር ይህ ነበር፣ ከሁሉም በኋላ፣ ከፍ ብሎ፣ እና ከበላይ የሚገኘው እግዚአብሔር አብ፣ የስማይና የምድር ጌታ ነው።”5

ስለእግዚአብሔር አብ ፍጥረት የምናውቀው ከአንድያ ልጁ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት እና ትምህርት ለመማር ከምንችለው ነው። ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳስተማሩት፣ የኢየሱስ አገልግሎት አላማዎች ውስጥ ዋና የሆነው አንዱ “የዘለአለም አባታችን እግዚአብሔር ምን አይነት እንደሆነ ለመገጽ፣ … የአባታችን፣ የሰማይ አባታችን እውነተኛ ፍጥረት ለእኛ ለመግለፅ እና ግላዊ ለማድረግ ነበር።”6 መፅሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የአባቱ “የባሕርዩ ምሳሌ” (ዕብራውያን 1፥3) ነው በማለት የሐዋርያ ምስክር ሰጥቷል፣ ይህም “እኔን ያየ አብን አይቶአል” (John 14:9) የሚለውን የኢየሱስ ትምህርትን የሚያብራራ ነው።

እግዚአብሔራብ የመንፈሳችን አባት ነው። እኛ ልጆቹ ነን። ይወደናል፣ እናም የሚያደርጋቸው ሁሉ ለእኛ ዘለአለማዊ ጥቅም ነው። እርሱም የደህንነት እቅድ ጸሀፊ ነው፣ እናም በእርሱም ሀይል ነው እቅዱ ለልጆቹ የመጨረሻ ክብር የሆነውን እቅድ ለማከናወን የሚችለው።

ወልድ

ለሟቾች፣ ከአምላክ አባላት ከደንብ ይታይ የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በታላቅ የትምህርት አዋጅ በ1909 (እ.አ.አ) ቀዳሚ አመራር እርሱ “ከእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደ—በመንፈስ የመጀመሪያ ልጅ፣ እናበስጋም አንድያ ልጅ ነው”7 በማለው እንዲህ አወጀው ነበር። ከሁሉም ታላቅ የሆነው ወልድ፣ በአብ የአብነቅድ እንዲያሟላ ተመረጠ—የአብን ሀይል በመጠቀም ቁጥር የሌላቸው አልምን ለመፍጠር (ሙሴ 1፥33 ተመልከቱ) እና የእግዚአብሔርን ልጆች ከሞት በትንሳኤው እና ከኃጢያት በኃጢያት ክፍያው ለማዳን ተመረጠ። ይህ ታላቅ መስዋዕት በእውነትንም እንዲህ ተብሎ ተጠርቷል “በህይወት ታሪክ ውስጥ ከተደረገው ዋናው ስራ።”8

ምስል
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ

እግዚአብሔር አብ በግል ልጁን በሚያስተዋውቅበት በነዚያ ልዩ እና ቅዱስ ጊዜዎች ውስጥ፣ እንዲህ ብሏል፣ “ይህ ውድ ልጄ ነው፥ አድምጠው” (ማርቆስ 9፥7ሉቃስ 9፥35፤ ደግሞም 3 ኔፊ 11፥7ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17 ተመልከቱ)። በዚህም፣ እንደ ያህዌ፣ የእስራኤል ጌታ አምላክ፣ለነቢያት እና በነርሱም በኩል የሚናገረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።9 ስለዚህ ነው ከሞት ከተነሳ በኋላ ኢየሱስ ለኔፋውያን በታየበ ጊዜ “የምድር ሁሉ እግዚአብሔር” ተብሎ ራሱን ያስተዋወቀው (3 ኔፊ 11፥14)። ለዚህም ነው ኢየሱስ ለመፅሐፈ ሞርሞን እና ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ነቢያትን እንደ “አባት እና ልጅ” የሚያነጋግረው፣ ይህም ርዕስ ከ100 አመት በፊት በቀዳሚ አመራር በተነሳሳ የትምህርት መግለጫ ውስጥ የተገለጸው።10

መንፈስ ቅዱስ

የአምላክ ሶስተኛው አባል፣ እንደ ቅዱስ መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ፣ እና እንደ አፅናኝ የሚጠራው መንፈስ ቅዱስ። የግል ራዕይ ወኪል የሆነ የአምላክ ሶስተኛ አባል ነው። እንደ መንፈስ ግለሰብ (ት. እና ቃ. 130፥22)በውስጣችን ለመኖር እና በአብና ወልድ እና በምድር በሚገኙ የእግዚአብሔር ልጆች ጋር የመገናኛ አስፈላጊ ሀላፊነት ነበረው። ብዙ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰቶች ሀላፊነቱ ስለአብና ወልድ መመስከር እንደሆነ ያስተምራሉ (ዮሀንስ 15፥263 ኔፊ 28፥11ት. እና ቃ. 42፥17 ተመልከቱ)። አፅናኚው ሁሉንም ነገሮች እንደሚያስተምር፣ ሁሉንም ነገሮች እንድናስታውስ፣ እና ወደ እውነት እንደሚመራን አዳኝ ቃል ገብቷል (ዮሀንስ 14፥2616፥13 ተመልከቱ)። በዚህም፣ መንፈስ ቅዱስ በእውነት እና በሀሰት መካከል ለመለየት ይረዳናል፣ በታላቅ ውሳኔዎች መመርያዎች ይሰጠናል፣ እናም በስጋዊ ህይወት ፈተናዎቸርዳታ ይሰጠናል።11 እርሱም የምንቀደስበት፣ ያም ማለት፣ ከኃጢአይ መንጸዳበት እና የምንነጠርበት መንገድ ነው (2 ኔፊ 31፥173 ኔፊ 27፥20; ሞሮኒ 6፥4 ተመልከቱ)።

፬.

ስለዚህ፣ ይህን መለኮታዊ የአምላክ እና የደህንነት እቅድ ራዕይን ማወቅ በዛሬ ባሉን ፈተናዎች እንዴት ሊረዱን ይችላሉ?

ስለአምላክ እና ከእነርሱ ጋር ስላለን ግንኙነት፣ ስለህይወት አላማ፣ እና ስለዘለአለማዊ እጣ ፈንታችን እውነት ስላለን፣ እኛ በሟች ህይወት ጉዞአችን ውስጥ የመጨረሻው ካርታ እና ማረጋገጫ አለን። ማንን እንደምናመልክ እና ለምን እንደምናመልካቸው እናውቃለን። ማን እንደሆንን እና ምን ለመሆን እንደምንችል እናውቃለን (ት. እና ቃ. 93፥19)። ይህ ሁሉ እንዲቻል የሚያደርገው ማን እንደሆን እናውቃለን፣ እናም በእግዚአብሔር የደህንነት እቅድ በኩል የሚመጡትን በረከቶች እንድንደሰትበታቸው ምን ማድረግ እንዳለብንም እናውቃለን። ይህን ሁሉ እንዲት ነው የምናውቀው? ለነቢዩ እናለእያንዳንዳችን በተሰጡ የእግዚአብሔር ራዕያት ነው።

ሐዋርያ ጳውሎስ “የክርስቶስም ሙላቱ” (ኤፌሶን 4፥13) ብሎ የሚገልጸው ከእውቀት በላይ ያስፈልገዋል። እኛ በወንጌል የታመንን መሆናችን ብቁ አይደለም፤ በዚህ የተቀየርን ለመሆን መስራት እና ማሰብ አልብን። አንድ ነገር እንድናውቅ ከሚያስተምረን ከአለም ድርጅቶች ጋር ሲነጻጸር፣ የደህንነት እቅድ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አንድ ነገር እንድንሆን ያበረታታናል።

ምስል
በፕሬዘደንት ቶማስኤስ. ሞንሰን

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ እንዳስተማሩን፥

“ለእቅዱ ወሳኝ ክፍል የሆነው አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ያለ እርሱ የመስዋእት ክፍያ፣ ሁሉም ነገር ጠፊ ነበር። በእርሱ እና በተልእኮው ማመን ብቻ ግን በቂ አይደለም። መስራት እና መማር፣ መሻት እና መፀለይ፣ ንሰሀ መግባት እና መሻሻል አለብን። የእግዚአብሔርን ህግጋት ማወቅ እና መኖር አለብን። የሚያድን ስርዓቶቹን መቀበል ያስፈልገናል። ይህንን በማድረግ ብቻ እውነተኛ ደስታን እናገኛለን። …

ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳወጁት፣ “ከጥልቅ ነብሴ፣ እና በሙሉ ትህትና፣ ታላቅ ስጦታ ስለሆነው አባታችን ለእኛ ስላለው እቅድ እመሰክራለሁ። በእዚህ እናም በሚመጣው አለም ወደ ሰላም እና ደስታ የሚወስድ ብቸኛው ፍፁም መንገድ ነው።”12

በውድ ነቢያችን ምስክርነትም የራሴን እጨምራለሁ። እኛን በስማችን የሚያውቀን፣ አፍቃሪ የሰማይ አባት እንዳለን እመሰክራለሁ! የሚመራን መንፈስ ቅዱስ እንዳለን እመሰክራለሁ! ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኛችን፣ ሁሉንም እንዲቻል ስላደረገው የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 268.

  2. Teachings: Joseph Smith, 42.

  3. This was a common meaning of communion when that word was chosen by the King James translators (see The Oxford Universal Dictionary, 3rd ed., rev. [1955], 352).

  4. Bruce R. McConkie, A New Witness for the Articles of Faith (1985), 51.

  5. ብሩስ አር መካንኬ፣ in Conference Report, ጥቅምት 1935 (እ.አ.አ.)፣ 100።

  6. Jeffrey R. Holland, “The Grandeur of God,” Liahona, Nov. 2003, 70.

  7. First Presidency, “The Origin of Man,” Ensign, Feb. 2002, 26, 29.

  8. See, for example, Russell M. Nelson, “Drawing the Power of Jesus Christ into Our Lives,” Liahona, May 2017, 40; “The Living Christ: የሐዋሪያት ምስክርነት,” Liahona, ሚያዝያ 2000፣ 2።

  9. See Joseph Fielding Smith, Doctrines of Salvation, comp. Bruce R. McConkie (1954), 1:27.

  10. See First Presidency and Quorum of the Twelve Apostles, “The Father and the Son,” Ensign, Apr. 2002, 13–18.

  11. See Robert D. Hales, “The Holy Ghost,“ Liahona, May 2016, 105–7.

  12. Thomas S. Monson, “The Perfect Path to Happiness,” Liahona, Nov. 2016, 80–81.