2010–2019 (እ.አ.አ)
ብርሀናችን ለሀገሮች ምልክቶች እንዲሆኑ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


ብርሀናችን ለሀገሮች ምልክቶች እንዲሆኑ

የአዳኝ ወንጌልና በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያኑ ብርሀናችን ለሀገሮች ታላቅ መሰረቶች እንዲሆኑ ብዙ እድሎች ይሰጡናል።

ከብዙ አመቶች በፊት፣ እንደ ሰምነሪ አስተማሪ እያገእገልኩኝ እያለሁ፣ አብሬአቸው ከምሰራው አንዱ ተማሪዎቻቸውን በዚህ ጥያቄ እንዲያሰላስሉ ጠየቋቸው፥ በአዳኝ ቀን ብትኖሩ፣ እርሱን እንደ ደቀመዛሙርቱ ለምን ትከተሉት ነበር? እርሱን በዚህ ቀን የሚከተሉት እና ደቀመዛሙርቱ ለመሆን የሚጥሩት በዚያም ቀን እንዲሁ ያደርጉ እንደሚሆኑ እነርሱም ውሳኔ አድርገዋል።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ በዚያ ጥያቄና በነርሱ ውሳኔ ላይ አሰላስል ነበር። በተራራ ስብከቱ የሚቀጥሉትን በሚልበት ጊዜ አዳኝን ሳዳመጥ ምን ስሜት እንደሚኖረኝ ዙም ጊዜ አስብበታለሁ፥

“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

“መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” (ማቴዎስ 5፥14–16)።

የአዳኝን ድምጽ በመስማት ምን ይሰማችሁ እንደነበር በአዕምሮችሁ ማየት ትችላላችሁን? በእርግጥም፣ በአዕምሮችን ማየት የለብንም። የአገልጋዩን ድምፅ በምንሰማበት ጊዜ የጌታን ድምፅ እንደመስማት ስለሆነ፣ ይህም የሁልጊዜ ልምምድ ሆኖልናል።

በ1838 (እ.አ.አ)፣ በተራራ ስብከት ውስጥ ተሰጥቶ እንደነበረው አይነት መልእክት በመስጠት፣ ጌታ የሚቀጥለውን በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል አወጀ፥

“በመጨረሻዎቹ ቀናትም ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው በዚህ፣ እንዲሁም በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስም ነው።

“ለሁላችሁም እውነት እላችኋለሁ፥ ለህዝቦች መመሪያ ትሆኑ ዘንድ ተነሱ እና አብሩ” (ት. እና ቃ 115፥4–5)።

ቀናችን በጣም አስደናቂ ሆነው ለነቢዩ ኢሳይያስ በራዕይ ታይተው ነበር፤ ስ በዳግም ስለተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና አላማዋ እርሱም አየና ተነበየ፣ እንዲህም አለ፣ “ “ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል” (ኢሳይያስ 11፥12)።

በቅዱስ መጻህፍት አግባብ፣ ምልክት፣ ወይም መሰረት፣ ሰዎች በአንድ አላማ የሚሰበሰቡበት ሰንደቅ ነው። በጥንት ጊዜ፣ ምልክት ወታደሮች ለጦርነት የሚሰበሰቡበት ቦታ ነው። በምሳሌ በመናገር፣ መፅሐፈ ሞርሞን እና በዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለሁሉም ሀግሮች ምልክቶች ናቸው። (See Guide to the Scriptures, “Ensign,” scriptures.lds.org.)

ያለጥርጥር፣ በእነዚህ በኋለኛው ቀናት ውስጥ ከታላቅ ምልክቶቹ ሁሉ አንዱ፣ “የሰውን አለሟችነት እና ዘላለማዊ ህይወት ማምጣት” (ሙሴ 1፥39) የሆነውን የሰማይ አባትን እቅድ እና ታላቅ ስራ ሁልጊዜም የሚታወጅበት አስደናቂው ታላቅ ጉባኤ ነው።

አጠቃላይ ጉባኤ ሁልጊዜ መሳተፍ እንደ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን “እግዚአብሔር እስካሁን በገለጣቸው ሁሉ፣ አሁንም በሚገልጣቸው ሁሉ እናምናለን፣ እናም የእግዚአብሔርን መንግስት በተመለከተ ወደፊትም እርሱ በሚገልጣቸው ታላቅና አስፈላጊ ነገሮችም እናምናለን” (የእምነት አንቀጾች 1፥9) የሚል እምነት እንዳለን ከሚያሳዩ ታላቅ ምስክሮች አንዱ ነው።

ከዚያስ፣ ብርሀናችንን ለሀገሮች ምልክት በመሆን እንዲቀጥሉ ምን እንደሚያስፈልገን ጌታ በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በኩል ምን ገልጿል? ፅዮንን በመገንባት እና እስራኤልን በመሰብሰብ አስደናቂ ጊዜ መደረግ የሚያስፈልጋቸው አስፈላጉ ነገሮች ምን ናቸው?

ጌታ ፈቃዱን ሁልጊዜ ለእኛ የሚገልጸው “ትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” ነው (2 ኔፊ 28፥30)። ጌታ ፍላጎቱን ሁልጊዜም “በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ”ገልጾልናል፤ስለዚህ በቀላል እና ደጋጋሚ በመሆናቸው መደነቅ የለብንም፣ ምክንያቱም ጌታ እንደመከረን፣ “ምክሬን የሚያደምጡ የተባረኩ ናቸው፣ ጥበብን ይማራሉና፤ ለሚቀበልም ተጨማሪ እሰጣለሁና፤ እና ይበቃናል ለሚሉም፣ ያላቸውም እንኳን ቢሆን ይወሰድባቸዋል።” (2 ኔፊ 28፥30)።

“በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” እና የመሪዎቻችንን ምክር በማዳመጥና በመማር፣ ጌታ እንደሚያዘው ለሌሎች ብርሀን ለመስጠት ለፋኖሳችን ዘይት እንደሚኖረን እመሰክራለሁ።

ለሌሎች ብርሀንና ምልክት ለመሆን ለማድረግ የምንችላቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም፣ እንድንነሳና እንድናበራ በሚያስችሉን ሶስት ነገሮች ላይ ለማተኮር እፈልጋለሁ፥ ሰንበትን ማክበ፤ የደህንነትን ስራ በመጋረጃው ሁለት በኩልም ማፋጠን፤ እና በአዳኝ መንገድ ማስተማር።

የምንነጋገርበት ብርሀን የሚመጣው በሰንበት በምናሳየቅ አምልኮ፣ በቢተክርስቲያንም ይሁን በቤት ነው፤ ይህም ከአለም ራሳችንን ያለእንከን ስንጠብቅ ነው፤ ቅዱስ ቁርባናችንን በቅዱስ ቀኑ ስናቀርብ እና ለሁሉም ሀያል ያለንን አምልኮ በመስጠት የሚመጣ ብርሀን ነው፣ ይህም ሁሉ ሁላችንም ሁልጊዚ ከእኛ ጋር እንዲሆን ያደርጋል። ይህም ባለፈው ጥቅምት ጉባኤ ውስጥ ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እውደ ቤት በምህረት ስሜት በምንመለስበት ጊዜ የሚያስደው እና የሚታየው ብርሀን እንደሆነ እንዲህ በማለት የተናገሩበት ነው፥ “ለመቁጠር ከምንችላቸው በረከቶች ሁሉ መካከል ከሁሉም ታላቅ የሆነው ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል የሚመጣው የምህረት ስሜት ነው። ከኃጢያታችን እንድንጸዳ መጨረሻ የሌለው መስዋዕቱን ለሰጠን ለአዳኝ ታላቅ ፍቅር እና ምስጋና ይሰማናል።” (“Gratitude on the Sabbath Day, Liahona, Nov. 2016, 100)።

የሰንበት ቀንን ቅዱስ ስናደርግ እና ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ የተጸዳን ብቻ ሳይሆን ብርሀናችንን ይጎላል።

የቅድመ አያቶቻችንን ስም ለማግኘት፣ ስማቸውን ወደ ቤተመቅደስ ለመውሰድ፣ እና ቤተሰባችንን እና ሌሎች እንደዚህ እንዲያደርጉ ለማስተማር ጊዜአችንን የምንቀድስበት እና የምናውልበት ብርሀናችን እንዲጎላ ያደርጋሉ።

የጌታ ቤተመቅደሶች ሲገነቡ በመጋረጃው ሁለቱም ጎን በሚገኙ ቅዱሳን ጋር የምንካፈለው ይህ ቅዱስ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ ከዚህ በፊት ከሚደረገው በላይ ወደፊት እየሄዱ ናቸው። አሁን ቤተመቅደሶች የራሳቸው የቤተሰብ ካርድ ይዘው ለሚመጡት ልዩ ሰረንጠዥ ስለሚሰጡ፣ ባለቤቴና እኔ ከልጆቻችን እና ከልጅ ልጆቻችን ጋር በቤተመቅዳስ ውስጥ በማገልገል የሚያስደስጥ አጋጣሚዎች አሉን።

ስሞችን ስናገኝ እና ወደ ቤተመቅደስ ስንወስድ እናም ሌሎችን እንዴት እንዲህ እንደሚያደርጉ ስናስተምር፣ እንደ ምልክት እየበራን ነን።

ጌታ እንዳስተማረው ማስተማርም ሌላው የምንነሳበት እና የምናበራበት መንገድ ነው። በአዳኝ መንገድ እንዴት ለማስተማር እንደሚችሉ ከሚማሩት ጋር አብሬ እደሰታለሁ። ከአዲሱ የማስተማሪያ መፅሐፍ መግቢያ ውስጥ ካለው ላንብብላችሁ.. “የእያንዳንዱ የወንጌል አስተማሪ—እያንዳንዱ ወላጅ፣ እያንዳንዱ የተጠራ አስተማሪ፣ እያንዳንዱ የቤት ለቤት አስተማሪ፣ እና እያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ—አላማ ንጹህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በመንፈስ ለማስተማር፣ … የእግዚአብሔር ልጆች እምነታቸውን በአዳኝ ውስጥ እንዲገነቡና እንደ እርሱ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው” (Teaching in the Savior’s Way [2016])።

አሁን፣ ብዙ ሺህ ታማኝ አስተማሪዎች እንዴት በአዳኝ መንገድ እንደሚያስተምሩ ሲማሩ ብርሀናቸውን ከፍ እያደረጉ እየያዙ ናቸው። በዚህ አግባብ፣ አዲሱ የአስተማሪዎች ሸንጎ ተማሪዎች በክርስቶስ ትምህርት ምልክት አካባቢ ሲሰበሰቡ ከፍ የሚሉበት እና የሚበሩበት መንገድ ነው፣ ምክንያቱም “እንደ አዳኝ የማስተማር ዋና ቁልፍ አዳኝ እንደኖረበት መኖር ነው” (Teaching in the Savior’s Way, 4)።

በእርሱ መንገድ ስናስተምርና ስንማር እናም እንደ እርሱ ስንሆን፣ ብርሀናችን ይጎላሉ እናም አይደበቁም እናም የአዳኝ ብርሀን ለሚፈልጉት ምልክትም ይሆናል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ብርሀናችንን መደበቅ የለብንም እናም አይገባንም። አዳኝ የሰጠን ትእዛዝ በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ ወይም እንደ ሻልማ ብርሀን እንድናበራ ነው። ይህን ስናደርግ፣ ለሰማይ አባታችንን ክብር እንሰጣለን። የአዳኝ ወንጌልና በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያኑ ብርሀናችን ለሀገሮች ታላቅ መሰረቶች እንዲሆኑ ብዙ እድሎች ይሰጡናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ማንጸባረቅ የሚገባን ብርሀን እንደሆነ እመሰክራለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።