2010–2019 (እ.አ.አ)
መልካምን ለማድረግ አትፍሩ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


መልካምን ለማድረግ አትፍሩ

በእለቱ በእምነት ስንቆም፣ ጥርጣሬ የሚቀነስ፤ መልካም የማድረግ ፍላጎትም የሚጨምር እንደሚሆን ጌታ ነግሮናል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጌታ መንፈስ እኔ ንግግሬን ሳቀርብ ከእኛ ጋር እንዲሆን በትሁት እጸልያለሁ። ይህች ቤተክርስቲያኑ ለሆነችው፣ በዚህ ጉባኤ ውስጥ በጥልቅ ጸሎቶች፣ በተነሳሱ ሰበካዎች፣ እና በመላእክታዊ መዘመር ለተሰሙን ስሜቶች ለጌታ ባላኝ ምስጋና ልቤ የተሞላ ነው።

ባለፈው ሚያዝያ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በአለም አቀፍ ልቦችን የነካካ መልእክት ሰጥተውን ነበር። ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ኃይል ተናገሩ። የዚህን ትምህርት እንድናጠና፣ እንድናሰላስል፣ እና እንድንጠቀምበት ገፋፉን። በእያንዳንዱ ቀን ለማጥናትና ለማሰላሰል ጊዜ መሰዋት ካደረግን እንዲሁም መጽሐፈ መርመን የያዘውን ትዕዛዛት ከጠበቅን፣ ስለእውነታው በጣም ጠቃሚ የሆነ ምስክርነት እንደሚኖረን እናም የሕያው ክርስቶስ ምስክርነት ውጤት በችግር ወቅት እንደሚያወጣን ቃል ገባ። (“የመፅሐፈ ሞርሞን ሀይል,” Liahona፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 86–87 ተመልከቱ።)

እንደ ብዙዎቻችሁ፣ የነብዩን ቃላት ጌታ ለእኔ እንደተናገረው ድምፅ ነው የሰማሁት። እናም እንደ ብዙዎቻችሁ፣ እነዛን ቃላት ለመታዘዝ ወሰንኩኝ። አሁን፣ ትንሽ ልጅ ከሆንኩኝ ጊዜ ጀምሮ፣ መጽሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፣ አብና ወልድ ለጆሴፍ ስሚዝ እንደተገለጡና እንዳወሩት፣ እናም የጥንት ሐዋርያቶች የክህነት ቁልፎችን ለጌታ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ወደ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደመጡ ምስክነትን አግንቻለሁ።

በዛ ምስክርነት፣ መጽሐፈ ሞርሞንን በእየቀቡ ለ50 ዓመታት አንብቤአለሁ። ስለዚህ ምናልባት የፕሬዘዳንት ሞንሰን ቃላት ለሌላ ሰዎች ይሆናል ብዬ ማሰብ እችላለሁ። ነገር ግን፣ እንደ አብዛኞቻችሁ፣ የነብዩን ማበረታቻ እና ቃል-ኪዳን የበለጠ ጥረትን እንዳደርግ ሲጋብዘኝ ተሰምቶኛል። ብዙዎችችሁ ያደረኩትን ነገር አድርጋችኋል፣ በከፍተኛ መነሳሻ ጸልያችኋ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከልባችሁ አሰላስስላችኋል እናም ጌታን ሌሎችን ለእርሱ ለማገልገልየበለጠ ሞክራችኋል።

ለእኔ እና ለብዙዎቻችሁ አስደሳቹ ውጤት፣ ነብዩ የገባው ቃል-ኪዳን ነው። የተነሳሳውን ምክራቸውን ወደ ልባችን ለወሰድን ሰዎች መንፈስ በተለየ ሁኔታ ተሰምቶናል። ፈተናን ለመቋቋም ታላቅን ኃይል አግኝተናል እናም ትንሳኤ ባደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በወንጌሉ፣ እናም በሕያው ቤተክርስቲያኑ ታላቅ እምነትን ተሰምቶናል።

በዚህ እየጨመራ ባለ በጫጫታማ ዓለም እነዛ የምስክርነት መጨመር ጥርጣሬንና ፍርሀትን አባረው የሰላም ስሜትን አምጥተውልናል። የፕሬዘዳንት ሞንሰንን ምክር መስማት ሌሎችሁለት መንስኤዎችን በእኔ ላይ አሳድሮብኛል። መጀመሪያ፣ ቃል-የገቡት መንፈስ ወደ ፊት ስላለው ነገር ቀና ሃሳብነትን አመንጭቷል፣ ምንም እንኳን በዓለማችን ውስጥ ያለው ብጥብጥ እየጨመረም ቢሄድ። እናም፣ ሁለተኛ፣ ጌታ ለእኔ እና ለእናንተ ምንም እንኳን ጭንቀት ውስጥ ብንሆን የፍቅሩን ታላቅ ስሜትን ሰጥቶኛል። ልሎችን በማድን ስራ ላይ የጨመረ ፍላጎትን ተሰምቶናል። ያ ፍላጎት በፕሬዘዳንት ሞንሰን መአከላዊ አገልግሎትና ትምህርት ላይ ነው።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ኳድሪ ከፊታቸው ያሉት ስራዎች ከባድ መስለው ሲታያቸው ጌታ ለሌሎች ሰዎች ፍቅርን እና ብርታትን እንደሚሰጣቸው ቃል ገባ። የሚያስፈልጋቸው ብርታት እርሱን እንደ አለታቸው በመውሰድ በእርሱ ላይ በሚኖራቸው እመነት እንደሚመጣ ጌታ ተናገረ፤

“መልካምን ለማድረግ አትፍሩ፣ ልጆቼ፣ የዘራሃችሁትን ታጭዳላችሁና፤ ስለሆነም፣ መልካምን ከዘራችሁ፣ ለሽልማታችሁ መልካምን ታጭዳላችሁና።

“ስለሆነም፣ አትፍሩ፣ መልካምን አድርጉ፣ ሰማይና ምድር በእናንተ ላይ ይጋጠሙ፣ ምክንያቱም በአለቴ ላይ ከተገነባችሁ፣ መውደቅ አይችሉምና።

“እነሆ፣ አልኮንናችሁም፣ ወደ መንገዳችሁ ሂዱ እና ሃጢያት አትስሩ፤ ያዘዝኳችሁን ስራ በክብር ተግብሩ።

“በሁሉም አስተሳሰባችሁ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩም፣ አትፍሩም።

“ጎኔን የወጋኝ ቁስል እና በእጆቼና በእግሮቼ ላይ ያሉትን የሚስማር አሻራዎች ተመልከቱ፤ አማኞች ሁኑ፣ ትዕዛዛቴን ጠብቁ እናም የሰማይን መንግስት ትወራሳላችሁ” (ት. እና ቃ. 6፥33–37)።

ጌታ በተመለሰው ጊዜ ያሉ መሪዎቹን ነገራቸው እና ለእኛም በእምነት በአለቱ ላይ ስንቆም፣ ጥርጣሬና ፍርሃት እንደሚቀንሱ፤ መልካምን የማድረግ ፍላጎት እንደሚጨምሩ ነገረን። የፕሬዘዳንት ሞንሰንን በልቦቻችን ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት የመትከል ግብዣን ስንቀበል፣ ስለእኛ ፍላጎት ሳንጨነቅ ሌሎችን የማዳን ስራ ላይ ኃይልን፣ ፍላጎትንና ብርታትን እናገኛለን።

ያንን እምነትና ብርታት ብዙ ጊዜ አማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች አስፈሪ ፈተናዎችን በተጋፈጡበት ጊዜ አይቻለሁ። ለምሳሌ፣ የቲታን ግድብ በሰኔ 5፣ 1976 (እ.አ.አ) ሲፈርስ በአይዳሆ ነበርኩኝ። የውኃ ግድግዳ ወረደ። በሺዎች የሚቆጠሩ ከቤታቸው ሸሹ። በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችና ንግዶች ወደሙ። በተአምር በሆነ ሁኔታ፣ ከ15 ሰዎች ያነሱ ተገደሉ።

እዛ ያየሁት፣ የኋኛው ቀን ቅዱሳኖች በኢየሱስ ክርስቶስ የምስክርነት አለት ላይ በጥንካሬ ሲቆሙ ነው። ምክንያቱም እርሱ እንደሚጠብቃቸው ምንም ጥርጣሬ ስላልነበራቸው ፍርሃት አልባ ሆኑ። ወደ ሌሎች እርዳታ ለመሄድ የገዛ ፈተናቸውን ችላ አሉት። ምንም ካሳ ሳይጠይቁ ይህን ያደረጉት ለጌታ ካላቸው ፍቅር ነው።

ለምሳሌ፣ የቲታን ግድብ ሲፈርስ፣ አንድ የኋኛው ቀን ቅዱሳን ጥንዶች ከቤታቸው በብዙ ማይሎች እርቀው በመጓዝ ላይ ነበሩ። በሬዲዮ ዜናውን እንደሰሙት፣ ወደ ሬክስበርግ በችኮላ ሄዱ። ቤታቸው እንደፈረሰ ለማየት ወደ ገዛ ቤታቸው ከመሄድ፣ ኤጵስ ቆጶሳቸውን ፍለጋ ሄዱ። እንደ ማገገሚያ ጣቢያ ይጠቀሙበት በነበረው ሕንፃ ውስጥ ነበር። በቢጫ የት/ቤት መኪናዎች እየደረሱ ያሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ የፍቃድ እርዳታ ሰጪዎችን ለማሰማራት እያገዘ ነበር።

ጥንዶቹ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ተራመዱና እንዲህ አሉት፣ “አሁን ገና ተመልሰን መጣን። ኤጲስ ቆጶስ፣ ለማገዝ ወዴት እንሂድ?” የአንድ ቤተሰብ ስም ሰጣቸው። እነዛ ጥንዶች ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት በመሄድ ጫቃና ውኃን በማውጣ ቆዩ። ለብዙ ቀናት ከጠዋት እስከ ማታ ሰሩ። መጨረሻ ላይ ቤታቸውን ሄደው ለማየት ዕረፍት ወሰዱ። ምንም የሚፀዳ ነገር ሳይተው በጎርፉ ተጠርጎ ሄዷል። ስለዚህ ወደ ኤጲስ ቆጶሳቸው ለመሄድ በቶሎ ተመለሱ። እንዲህ ጠየቁ፣ “ኤጲስ ቆጶስ፣ ልናግዘው የምንችል ሰው አለህን?”

የብርታትና የልግስና- የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ተአምር ለብዙ ዓመታት በመላው ዓለም እንደገና ተደገመ። በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በመጥፎ ቀናት ስደቶችና ፈተናዎች ወቅት በሚዙሪ ተከሰተ። ብሪግሃም ያንግ ከናቩ ስደተኞችን ሲመሩ እና ለጌታ ፅዮንን ለመገንባት እርስበእርስ እንዲረዳዱ በምስቃማ የተባበሩት መንግስታት በረሃ ቦታዎች ላይ ቅዱሳኖችን ሲጠሩ ተከሰተ።

የእነዛን መስራቾች የዳየሪ መግቢያ ካነበባችሁ፣ የእምነት ተአምር ጥርጣሬንና ፍርሃትን ሲያወጣ ታያላችሁ። እንም ወደ ራሳቸው ጉዳይ ወይም ወደ ያልተጠረገው የበረዶ ስፍራ ከመመለሳቸው በፊት ቅዱሳኖች የራሳቸውን ፈላጎት ትተው ሌሎችን ለጌታ ለመርዳት ሲሄዱ ታነባላችሁ።

ከአውሎ ልናስ ኧርማ በፖርተሪኮ፣ ሴይንት ቶማስ፣ እና በፍሎርዳ ከነበረ በኋላ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ከሌሎች ቤተክርስቲያናት፣ የክልል ህብረተሰባዊ ቡድኖች፣ እና ከሀገራዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የማፅዳት ጥረት ሲጀመር ይህን አይነት ታዕምር ተመልክቻለሁ።

በሬክስበርግ እንደነበሩት ጓደኞቼ፣ በፍሎሪዳ የሚኖሩ አባላችን ያልሆኑ የተጋቡ ሰዎች በራሳቸው ንብረት ላይ ሳይሆን ህብረተሰባቸውን በመርዳት ላይ አተኮሩ። አንዳንድ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጎረቤቶች በቤታቸው ደጃቸውን የዘጋውን የወደቁ ሁለት ትልቅ ዛፎችን ለማውጣት ለመርዳት ሲያቀርቡም፣ የተጋቡት ሰዎች ተጥለቅልቀው እንደነበር እና ጌታ በቤታቸው የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንደሚሰጣቸው እምነት ስለኖራቸው ሌሎችን ለመርዳት እንደሄዱ ገለጹ። ባልየውም የቤተክርስቲያኗ አባላት እርዳታ ለመስጠት ከመምጣታቸው በፊት ይጸልዩ እንደነበር ተካፈለ። እርዳታ እንደሚመጣም መልስ ተቀብለው ነበር። ከዚያ ማረጋገጫ አንድ ሰዓት ሳያልፍም ነበር የመጣው።

አንዳንዶችቢጫውን የሚረዱ እጆች ሸሚዞችን የለበሱትን የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን እንድ “ቢጫ መላእክት” እንደሚጠሯቸው ሀተታንም ሰምቻለሁ። አንዷ የኋለኛ ቀን ቅዱሳን መኪናዋን ለማሰራት ሄደች፣ እናም የሚረዳትም ሰው ቢጫ ሸሚዝ የለበሱ ሰዎች ከጓሮው የወደቀ ዛፍን ሲያወጡለት ስለነበረው “መንፈሳዊ አጋጣሚ” ገለጸላት እና ገዚያም፣ እንዲህ አለ፣ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንኩኝ መዝሙር ዘመሩልኝ።”

ሌላ የፍሎሪዳ ነዋሪም፣ እርሷም አባላችን አይደለችም፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ወደቤቷ የመጡት በተደመሰሰው ጓሮዋ ውስጥ እየሰራች እያለች እና ተጥለቅልቃ፣ በጣም ሞቋት፣ እና እምባ በመጣባት ጊዜ እንደነበር ተናገረች። እርዳታ የሚሰጡት፣ በእርሷ ቅላት፣ “ንጹህ ታዕምርን” ፈጠሩ። በትጋት ብቻ ሳይሆን በሳቅ እናበፈገግታ፣ ምንም ለመልስ ሳይቀበሉ ነበር ያገለገሉት።

ይህን ትጋት ያየሁት እና ሳቁን የሰማሁት፣ በቅዳሜ ምሽት፣ ከኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ቡድን ጋር ፍሎሪዳን ጎበኘሁ። እርዳታ ሰጪዎቹ የተወሰኑትን ሰዎች እጅ መጨበጥ እንድችል የማፅዳት ስራቸውን አቆሙ። ጆርጂያ ካለው ካስማቸው 90 አባሎች በፍሎሪዳ ውስጥ የማዳን ተልኮን ለመቀላቀል ከዛ ምሽት በፊት ዕቅድ እንደያዙ ተናገሩ።

ከጆርጂያ ከለሊቱ 10 ሰዓት ተነሱ፣ ለሰዓታታት ተጓዙ፣ ቀኑን ሙሉ እንዲሁም ማታም ሰሩ፣ እናም እንደገና በሚቀጥለው ቀን ለመስራት ዕቅድ ያዙ።

ሁሉንም በፈገግታ እና በቀልድ ገለፁት። ሊሰማኝ የቻለው ብቸኛ ጭንቀት ስራቸውን መስራት ይችሉ ዘንድ መመስገናቸው ማቆም እንዳለበት ነበር። ወደ ቀጣዩ የማዳን ስራ ቡድን ለመሄድ ወደ መኪናችን ውስጥ ስንገባ፣ የካስማ ፕሬዘዳንቱ የሰንሰለት መጋዙን እንደገና አብርቶ የወደቀ ዛፍ ላይ ሲሰራ እንዲሁም አንድ ኤጲስ ቆጶስ የዛፍ ቅርንጫፎችን ሲያግዝ አየን።

በዚያ ቀን ቀድሞ፣ ከዛ ወደሌላ ቦታ ስንሄድ፣ አንድ ሰውዬ ወደ መኪናው በመራመድ ኮፊያውን አውልቆ እርዳታ ላቀረቡት ሰዎች አመሰገነን። እንደዚህ አለ፣ “የቤተክርስቲያናችሁ አባል አይደለሁም። ለእኛ ያደረጋችሁትን ነገር ማመን አልችልም። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።” ከጎኑ ቆሞ የነበረ አንድ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እርዳታ አቅራቢ ፈገግ ብሎ ምንም ምስጋና እንደማይፈልግ ለመግለፅ ትከሻዎቹን ከፍ አረገ።

ከጆርጂያ የመጡት እርዳታ አቅራቢዎች ለማመን የከበደውን ይህንን ሰውዬ ለመርዳት ሲመጡ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ከዛ ከተጠቃው ከፍሎሪዳ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን በመጓዝ ወደ ሌላ የፍሎሪዳ ክፍል በመሄድ በከፍተኛ ወደተጠቁት ሰዎች ተጉዘዋል።

ያን ቀን፣ የነብዩ ጆሴፍ ስሚዝን የትንበያ ቃላት አስታውስኩኝ እንዲሁም ተረዳሁኝ፥ “አንድ በእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላ ሰው፣ ቤተሰቡን ብቻ በመርዳት አይረካም፣ ነገር ግን ሁሉንም የሰው ዘር ለመባረክ በመጓጓት በዓለም ዙሪያ ይናኛል።” (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007], 426)።

እንደዚህ ዓይነት ፍቅር በሁሉም ቦታ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሕይወቶች ውስጥ እናያለን። በዓለማችን በማንኛውም ቦታ አሳዛኝ ክስተት ሲፈጠር፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ይለግሳሉ እንዲሁም በቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ለማገልገል ፍቃደኛ ይሆናሉ። የይግባኝ ጥያቄ ብዙም አይፈለግን። በዕርግጥ፣ አንድ አንድ ጊዜ በፈቃድ የሚያገለግሉትን ሰዎች ስራውን የሚመሩት ሰዎች ለመቀበል ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ ወደ ጥቃቱ ቦታ ለመሄድ እንዲጠብቁ መጠየቅ አለብን።

ያ የመባረክ ፍላጎት የኢየሱስ ክርስቶስን፣ የወንጌሉን፣ የተመለሰችውን ቤተክርስቲያኑን እና የነብያቶቹን ምስክርነት የሚያገኙ ሰዎች ፍሬ ነው። ለዛ ነው የጌታ ሕዝቦች የማይጠራጠሩት እንዲሁም የማይፈሩት። ለዛ ነው ሚስዮኖች በየዓለም መአዘናት ለማገልገል ፍቃደኞች የሚሆኑት። ለዛ ነው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ለሌሎች የሚፀልዩት። ለዛ ነው መሪዎች ወጣታቸውን የፕሬዘዳንት ሞንሰንን ጥያቄ በመውሰድ እራሳቸውን በምጸሐፈ ሞርሞን ውስጥ መክተትን ከልብ እንዲወስዱት የጋበዙት በመሪዎች በመገፋት ሳይሆን እምነት ላይ ተግባር ባደረጉ ወጣቶች ፍሬው መጣ። እራስ ወዳድ ያልሆነ መስዋትነትን የሚጠይቀው ያ እምነት ተግባር ላይ ውሎ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሰሙ ያደረጋቸውን የልብን መለወጥ አመጣ።

ይሁን እንጂ፣ የነብይን ምክር መከተል ስንቀጥል ብቻ ልቦቻችን እንደተቀየሩ ይሆናሉ። ከአንድ ሙከራ በኋላ መሞከር ካቆምን፣ ለውጡ ይደበዝዛል።

አማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ፣ በመጽሐፈ ሞርሞን እንደ የእግዚአብሔር ቃል ላይ እና በክህነት ቁልፎች በእርሱ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ መመለስ ላይ እምነታቸውን አሳድገዋል። ያ የጨመረው ምስክርነት ታላቅ ብርታትንና ለሌሎች የእግዚአብሔር ልጆች ማሰብን ሰጥቶናል። ነገር ግን ወደ ፊት ያሉት ችግሮችና ዕድሎች የበለጠ ይጠይቃሉ።

ዝርዝር ነገሮቹን መተንበይ አንችልም፣ ነገር ግን ትልቁን ምስል እናውቃለን። በመጨረሻዎቹ ቀናት ዓለም ብጥብጥ ውስጥ እንደምትሆን እናውቃለን። ማንኛውም ዓይነት ችግር ቢመጣም እንኳን፣ አማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለእያንዳንዱ ሃገራት፣ነገዶች፣ ቋንቋዎች እና ሕዝቦች እንዲወስዱ ጌታ እንደሚመራቸው እናውቃለን። ጌታ እውነተኛ ደቀ መዛሙርቶች በድጋሚ ሲመጣ እርሱን ለመቀበል ብቁና ዝግጁ እንደሚሆኑ እናውቃለን። መፍራት የለብንም።

ስለዚህ፣ በልቦቻችን ውስጥ እምነትንና ብርታትን በገነባነው መጠን፣ ጌታ ከእኛ እና ከእኛ በኋላ ካሉት ትውልዶች የበለጠ ነገርን ይጠብቃል። እኛ ካደረግነው የበለጠ ታላቅና ከባድ ነገሮችን ስለሚያደርጉ ጠንካሮችና ደፋሮች መሆን ይጠበቅባቸዋል። ከነፍሳችን ጠላት ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥማቸዋል።

ወደ ፊት በምንሄድበት ወቅት የቀና ማሰብ መንገድ በጌታ ተሰጥቶናል፥ “በሁሉም አስተሳሰባችሁ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩም፣ አትፍሩም።”(ት. እና ቃ. 6፥36)። ፕሬዘዳንት ሞንሰን ያንን እንዴት ማድረግ እንደምንችል ነግረውናል። መጽሐፈ ሞርሞንን ማሰላሰልና የነብያቶችን ቃላት መተግበር። ሁሌም መጸለይ። አማኞች መሆን። አዳኙን በሙሉ ልባችሁ፣ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁና ጥንካሬአችሁ ማገልገል። ለልግስና - ለክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ስጦታ፣ በሙሉ የልባችን ጉልበት መፀለይ (ሞሮኒ 7፥47–48 ተመልከቱ)። እናም ከሁሉም በላይ የነብይን ምክር በመከተል ቋሚና ተከታታይ መሆን።

መንገዱ አስቸጋሪ ሲሆን፣ ፕሬዘዳንት ሞንሰን ቃል በመግባት የአዳኙን እነዚህን ቃላት በመጥቀስ ያስታወሱንን በጌታ ቃል-ኪዳን ላይ መደገፍ እንችላለን፥ “እናም የሚቀበሏችሁም፣ በእዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁ እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል” (ት. እና ቃ. 84፥88)።

በእርሱ ስራ ላይ በማንኛውም ሰዓት ብትሆኑም ጌታ ከፊታችሁ እንደሚጓዝ እመሰክራለሁ። አንድ አንድ ጊዜ ሌሎችን ከፍ ለማድረግ ጌታ የሚልከው መላዕክ ትሆናላችሁ። አንድ አንድ ጊዜ ከፍ በሚያደርጓችሁ መላዕክቶች የምትከበቡት እናንተው ትሆናላችሁ። ነገር ግን በእያንዳንዱ የቅዱስ ቁርባን አገልግሎት ላይ ቃል እንደተገባላችሁ ሁሌም የእርሱ መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ይኖራችኋል። ትዕዛዛቱን ብቻ ነው መጠበቅ ያለባችሁ።

ለእግዚአብሔር በምድር ላይ መንግስት መልከም ቀናት ወደ ፊት ናቸው። ከነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቀናት ጀምሮ እንዳደረገው ተቃርኖ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት ያጠነክራል። እምነት ሁሌም ፍርሃትን ያሸናፋል። በህብረት መቆም አንድነትን ያመነጫል። ለሚያስፈልጃቸው ሰዎች የምታደርጉት ጸሎታችሁ በአፍቃሪ እግዚአብሔር ይደመጣል እንዲሁምየመለሳል። አያንቀላፋም እንዲሁም አይተኛም።

እግዚአብሔር አብ እንደሚኖር እና ወደ እርሱ ቤት እንድንመጣ እንደሚፈልግ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ይህ እነተኛው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው። ያውቃችኋል፣ ይወዳችኋል፣ እንዲሁም ይጠብቃችኋል። ለእናንተና ለእኔ እና ለመላው የሰማይ አባት ልጆች ሃጢያቶች መስዋትነት ከፍሏል። በሕይወታችሁ እና ለሌሎች ሰዎች በምትሰጡት አገልግሎታችሁ ውስጥ እርሱን መከተል ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያመራ ብቸኛ መንገድ ነው።

በረከቴንና ፍቅሬን እተውላችኋለሁ እንዲሁም እምሰክርላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።