2010–2019 (እ.አ.አ)
ጌታ ቤተክርስቲያኑን ይመራል
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ጌታ ቤተክርስቲያኑን ይመራል

የጌታ ቤተክርስቲያን አመራር በምድር ላይ ከሚያገለግሉት ሁሉ ታላቅ እና ጽኑ እምነት ይጠይቃል።

የእግዚአብሄርን ክህነት ለያዙ ውድ ወንድሞቼ፣ ዛሬ ምሽት ጌታ በምድር ያለውን መንግስተ ስለሚመራበት መንገድ መናገር እፈልጋለሁ። መሠረታዊ ነገሮችን ታውቋቸዋላችሁ። መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ለእናንተ እንዲያረጋግጥላችሁ እጸልያለሁ።

በመጀመሪያ፣ በምድር ላይ ላሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ አናት ነው።

ሁለተኛ፣ በተጠሩ ሰዎች በኩል በመናገር ዛሬ ቤተክርስቲያኑን ይመራል፣ ይህን የሚያደርገውም በራዕይ ነው።

ሦስተኛ፣ ከረጅም ጊዜያት በፊት ለነቢያቱ ራእይን ሰጠ፣ እና አሁንም ይቀጥላል።

አራተኛ፣ በነቢያቱ አመራር ስር ለሚያገለግሉ ሰዎች የማረጋገጫ መገለጥን ይሰጣል።

ከነዚህ መሰረቶች በመነሳት፣ የጌታ ቤተክርስቲያን አመራር በምድር ላይ ከሚያገለግሉት ሁሉ ታላቅ እና ጽኑ እምነት እንደሚጠይቅ እንረዳለን።

ለምሳሌ፣ ከሞት የተነሳው ጌታ ስለ መንግሥቱ በየዕለቱ ዝርዝሩን እንደሚመለከት ለማመን እምነት ይጠይቃል። ፍጹምነት የሚጎድላቸው ሰዎችን ታማኝነትን ወደሚጠይቁ ቦታዎች እንዲጠራ ለማመን እምነትን ይጠይቃል። የሚጠራቸውን ሰዎች፣ ያላቸውን ችሎታ እና አቅማቸውን በሚገባ እንደሚያውቅ እምነትን ይጠይቃል፣ እናም በሚሰጠውም ጥሪ ምንም ስህተት አይሠራም።

ይህም በዚህ አድማጮች ላይ ፈገግታን ወይም የጭንቅላት መነቅነቅን ሊያመጣ ይችላል— የአገልግሎት ጥሪያቸው በስህተት የተሰጣቸው ሊሆን ይችላል ብለው የሚያስቡ እንዲሁም የሚያውቋቸው ሰዎች በጌታ መንግስት ውስጥ በደካማ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ የሚመስላቸው ናቸው። ለሁለቱም ቡድኖች የምሰጠው ምክር፣ ጌታ እንደሚመለከተው በተሻለ ሁኔታ ለማየት እስኪችሉ ድረስ እነዚህን ፍርዶች እንዲያዘገዩ ነው። በምትኩ መስጠት ያለባቸሁ ፍርድ እናንተ ራዕይ ለመቀበል እና በድፍረት ለመተግበር አቅም አላችሁ።

ይህን ማድረግ እምነት ያስፈልገዋል። ጌታ እናንተን ይመራችሁ ዘንድ ፍፁም ያልሆኑ አገልጋዮችን እንደጠራ ማመኑ የበለጠ እምነት ይጠይቃል። የዛሬ ምሽት አላማዬ እግዚአብሔር ለእርሱ አገልግሎት አናንተን እንደሚመራ እምነታችሁንን መገንባት ነው። ከሁሉም በላይ፣ የእኔ ተስፋ የእናንተ መሪዎች እንዲሆኑ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ጌታ እንደሚያነሳ ያላችሁን እምነት መገንባት ነው።

በመጀመሪያ እንዲህ ያለ እምነት ለጌታ ቤተክርስቲያን እና መንግሥት ስኬት አስፈላጊ አይደለም ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ሆኖም ግን፣ ከጌታ ነብይ አንስቶ እስከ አዲስ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ድረስ፣ በየትኛውም የክህነት አገልግሎት ሰንሰለት ላይ ብትሆኑ፣ እምነት አስፈላጊ እንደሆነ ትገነዘቡ ይሆናል።

ለአስተማሪዎች ወይም ለዲያቆን የቡድን ፕሬዚዳንት እምነት ምን እንደሆነ መመልከት እንጀምር። የአስተማሪዎች ደካማ ጎኖች እና ጥንካሬዎችን በማወቅ ጌታ በግል እሱን እንደጠራው ማመኑ በጣም አስፈላጊ ነው። ጥሪውን የሰጠው ሰው በእግዚአብሔር መንፈስ መገለጥን የተቀበለ መሆን ማመን አለበት። የእሱም አማካሪዎች እና የቡድኑም አባላት በድፍረት እንዲተማመኑ አንድ አይነት እምነት ያስፈልጋቸዋል።

አንድ ወጣት ልጅ በአንድ እሁድ ጠዋት ከዲያቆናት አመራሮች ጋር በተቀመጠበት ሰአት እንደዚህ ያለን በራስ መተማመን አየሁ። አዲሱ ፀሐፊያቸው ነበር። እነዛም ወጣት አመራሮች በአንድ ላይ ተማከሩ። ኤጲስ ቆጶሱ በሙሉ የማይከታተለውን ወጣት ልጅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማምጣት ያቀረቡትን ሃላፊነት ሊያሟሉ የሚችሉበትን የተለያዩ መንገዶች ተወያዩ። ከጸሎት እና ውይይት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ወደ ማይመጣው ልጅ ቤት እንዲሄድ እና እንዲጋብዘው ለፀሃፊው ሃላፊነትን ሰጡ።

ፀሐፊው ልጁን አያውቀውም፣ ነገር ግን ከወላጆቹ አንዱ ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትረው የማይመጡና እና ሌላኛው ዋላጅ ደግሞ አባል እንዳልሆኑ እና ጉደኛማ እንዳልሆኑ ያውቅ ነበር። ጸሐፊው ጭንቀት ቢሰማውም ፍርሃት አልነበረውም። የጠፋው በግ ተመልሶ እንዲመጣ የእግዚአብሔር ነቢይ የክህነት ተሸካሚዎችን እንደጠየቁ ያውቅ ነበር። እናም እሱም የአመራሩን ጸሎት ሰምቶ ነበር። ለመዳን የሚረዳውን ልጅ ስም እና የራሱንም ስም ሲስማሙበት ሰምቷል።

ፀሐፊው ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትሮ ወደማይመጣው ትንሽ ልጅ ቤት በመሄድ ላይ እያለ እየተመለከትኩኝ ነበር። ወደ ታላቅ አደጋ የሚሄድ ይመስል ቀስ ብሎ እየተጓዘ ነበር። እሱ ግን በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከልጁ ጋር በደስታ ፈገግ በማለት በመንገዱ ላይ ተመለሰ። በወቅቱ አውቆ እንደሆነ እርግጠኛ ባልሆንም ነገር ግን እሱ በጌታ ሥራ ላይ መሆኑን በመገንዘብ በእምነት ተጓዘ። ያም እምነት በሚስዮናዊነት፣ በአባትነት፣ የወጣት ወንዶች መሪ በሆነበት እና ኤጲስ ቆጶስ በሆነበት ዓመታቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ቆይቷል እናም አድጓል።

እንዲህ ያለው እምነት ለኤጲስ ቆጶስ ምን ማለት እንደሆነ እንነጋገር። ኤጲስ ቆጶስ አንዳንድ ጊዜ በደንብ የሚያውቁትን ሰዎች ለማገልገል ይጠራል። የአጥቢያው አባላት የእርሱን ሰብአዊ ድክመቶችና መንፈሳዊ ጥንካሬያቸውን የሚያውቁ ሲሆን፣ በአጥቢያው ውስጥ ሌሎች ሰዎች የተሻለ የተማሩ፣ የበለጠ ልምድ ያላቸው፣ የበለጠ ማራኪ ወይም የተሻለ መልክ ያላቸው ሰዎች ሊጠሩ ይችሉ ነበር።

እነዚህ አባሎች የኤጲስ ቆጶስ የአገልግሎት ጥሪው ከእግዚአብሔር በራእይ የመጣ እንደሆነ ማወቅ አለባቸው። ያለነርሱ እምነት፣ የተጠራው ኤጲስ ቆጶስ እነርሱን ለመርዳት የሚያስፈልገውን ራዕይ ለማግኘት አስቸጋሪ ይሆንበታል። አባላቱ እሱን ለመደገፍ እምነት ከሌላቸው ስኬታማ አይሆንም።

ደስ የሚለው ግን ይህ በተቃራኒም እውነት ነው። ሕዝቡን ወደ ንስሓ የመራው የጌታን አገልጋይ ንጉስ ቢንያምን አስቡ። ሰብዓዊ ድክመቶች ቢኖሩትም፣ ከእግዚአብሔር የተጠራ መሆኑን እና ቃሎቹም ከጌታ መምጣቱን በማመናቸው ምክንያት የህዝቡ ልብ ሳሳ። ሰዎቹም ምን እንዳሉም አስታውሱ፤ “አዎን፣ ለእኛ የተናገርካቸውን ቃላት በሙሉ እናምናለን፤ እናም ደግሞ ሁሉን የሚገዛው በጌታ መንፈስ አማካኝነት እርግጠኝነታቸውን እና እውነተኝነታቸውን እናውቃለን፣ ታላቅ ለውጥ ለእኛ ወይንም በልባችን ውስጥ በመስራት ከእንግዲህ ኃጢያት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት የለንም፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ።” (ሞዛያ 5:2)።

አንድ መሪ በጌታ ሥራ ላይ ስኬታማ እንዲሆን፣ የህዝቡ በእግዚአብሔር በተጠራው ላይ ያላቸው አመኔታ በህመሞቹ እና በሟች ድክመቶቹ ላይ ያላቸውን አመለካከት መሻር አለበት። ንጉሥ ቤንያም የአመራርነቱን ሚና እንዴት እንዳብራሩ ታስታውሳላችሁ፤

“እኔን እስክትፈሩ ድረስ እኔንም ከሟች ሰው የበለጠ አድርጋችሁ እንድታስቡኝ አላእዝኳችሁም።

“ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ነኝ በሁሉም አይነት የሰውነትና የአይምሮ ጉስቁልና ስር የሆንኩ፣ ይሁን እንጂ በዚህ ህዝብ ተመርጫለሁ፣ እናም በአባቴ ተቀብቻለሁ፣ እናም በዚህ ህዝብ ላይ ገዢ እናም ንጉስ እንድሆን በጌታ እጅ ተፈቅዶልኛል፣ እናም ጌታ በሰጠኝ ሃይል፣ አእምሮ እናም ብርታት ሁሉ እናንተን እንዳገለግል ወደር በሌለው ሃይሉ ተቀምጫለሁ፣ እንዲሁም ተጠብቂያለሁ።” (ሞዛያ 2፥10–11)።

በጌታ ቤተክርስቲያን መሪያችሁ ለናንተ ደካማና ሰው ሊመስል ይችላል ወይም ጠንካራ እና በመንፈስ የተመራ ሊመስል ይችላል። እውነታው ግን እያንዳንዱ መሪ የእነዚህ እና በተጨማሪ የሌሎች ባህሪዎች ድብልቅ ነው። እንዲመሩን የተጠሩትን የጌታ አገልጋዮች የሚያግዛቸው ነገር ጌታ በጠራቸው ጊዜ እንዳያቸው ማየት ስንችል ነው።

ጌታ አገልጋዮቹን በፍጹም ሁኔታ ይመለከታል። የእነሱን አቅምና የወደፊት ሁኔታቸውን ይመለከታል። እርሱም ተፈጥሮአቸው እንዴት መለወጥ እንደሚችል ያውቃል። እንዲሁም ከሚመሩት ሰዎች ጋር ባላቸው ልምዶች እንዴት ሊለወጡ እንደሚችሉ ያውቃል።

ለማገልገል በተሰጣችሁ ሰዎች የመጠንከር አጋጣሚ ሊኖራችሁ ይችላል። በአንድ ወቅት ላላገቡ ጎልማሳዎች ኤጲስ ቆጶስ እንድሆን ተጠራሁ። የጌታ አላማ በነሱ ውስጥ ለውጥን ለማምጣት ልረዳው ይሆን ወይም በእኔ ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም።

በተወሰነ ደረጃ፣ በዚያ አጥቢያ ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አብዛኞቹ ወጣቶች በእግዚአብሔር ለነርሱ ተጠርቼ እንደሆንኩ አድርገው መቀበላቸውን አልተረዳሁትም። ድክመቴን ቢያዩም ነገር ግን አርቀው ተመልክተዋል።

ስለ ትምህርት ምርጫው ምክርን የጠየቀ አንድ ወጣት አስታውሳለሁ። በጣም ጥሩ በሆነዩንቨርስቲ ውስጥ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነበር። ይህን ምክር ከሰጠሁት አንድ ሳምንት በኋላ፣ ከእኔ ጋር ሌላ ቀጠሮ ያዘ።

ወደ ቢሮ እንደገባ “ቢሾፕ፣ ከማውራታችን በፊት መጸለይ እንችላለን?” ብሎ በመጠየቁ አስገረመኝ። እናም መንበርከክ እንችላለን? እኔ ጸሎቱን ልስጥ?

ጥያቄዎቹ በጣም አስገረሙኝ። ነገር ግን ጸሎቱ አብዝቶ አስገረመኝ። እንዲህም የሚል አይነት ነበር፤ “የሰማይ አባት፣ ባለፈው ሳምንት ቢሾፕ አይሪንግ ምክር ሰጠኝ፣ እናም ያ አልተሳካም። እባክህ አሁን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንዲያውቅ ምሪትን ስጠው።”

አሁን በዚህ ፈገግ ልትሉ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ጌታ ምን ልርምርሥራት እንደሚፈልግ ያውቅ ነበር። ነገር ግን በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአንድ ኤጲስ ቆጶስ ጥሪን አከበረ እናም ምናልባት በዚህ ጥሪ ውስጥ ራዕይ ለመቀበል የበለጠ እድል እንዲሰጠኝ ፈልጎ ይሆናል።

ይህም ሰርቷል። ልክ እንደተነሣን እና እንደተቀመጥን ራዕይ ወደ እኔ መጣ። ጌታ እንዲሰራ ስለሚፈልገው ምን እንደተሰማኝ ነገርኩት። በወቅቱ 18 ዓመት ብቻ የነበረ ቢሆንም በመንፈሳዊ አመቱ የጎለመሰ ነበረ።

እንደዚህ ባለ ችግር ላይ ወደ ኤጲስ ቆጶስ መሄድ እንደማያስፈልገው ቀድሞውኑ አውቆ ነበር። ነገር ግን በእሱ የሟች ድክመቶች ውስጥ የጌታን አገልጋይ መደገፍ እንዳለበት ተምሯል። በመጨረሻም የቃስማ ፕሬዘደንት ሆነ። አብረን የተማርነውን ትምህርት ከእርሱ ጋር አቆይቷል። ጌታ ፍጹማን ባልሆኑበሚጠራቸው አገልጋዮች በራዕይ በኩል ቤተክርስቲያኑን እንደሚመራ እምነት ካላችሁ፣ ጌታ የሰማይ መስኮቶችን ለእነርሱም እንዲሁም ለእናንተም ይከፍታል።

ከዚህ አጋጣሚ፣ የምናገለግላቸውን ሰዎች እምነት፣ አንዳንዴም ከኛ እምነት በላይ፣ በጌታ አገልግሎት ውስጥ ራዕይን የሚያመጣልን እንደሆነ ትምህርት ተማርኩኝ።

ለእኔ ሌላም ትምህርት ነበር። ይህ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሩ ምክር ባለመስጠቴ ቢፈርድብኝ ኖሮ እንደገና ለመጠየቅ ባልመጣ ነበር። እናም በእኔ ላይ ላለመፍረድ በመወሰኑ የሚፈልገውን ማረጋገጫ ተቀብሏል።

ከዚህ አጋጣሚ ሌላም ትምህርትም አግኝቻለሁ። እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ በጥቢያም ውስጥ ለማንም አባላት ጥሩ ምክር እንዳልሰጠሁ አላሳውቅም። ያን ቢያደርግ ኖሮ፣ በጥቢያው ውስጥ ኤቂስ ቆጶሱ በመንፋሳዊ ምሪቱ ላይ እምነታቸው ዝቅ ያለ እንዲሆን ያስችል ነበር።

የጌታን አገልጋዮች ላለመፍረድ ወይም ስለእነሱ ግልጽ ድክመቶች ላለማውራት እሞክራለሁ። እኔም ይህን ለልጆቼ በምሳሌ ለማስተማር እጥራለሁ። ፕሬዚዳንት ጄምስ  ኢ ፎስት የራሴ አድርጌ ለመውሰድ የምሞክረውን አንድ እሴት አካፍለዋል። ለናንተም አደራ እሰጣለሁ፤

“እኛ … የአካባቢያችንን መሪዎችን ማገዝና መደገፍ ያስፈልገናል ምክንያቱም …እነሱ ‘ተጠርተው እናም ተመርጠዋል።’ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ አባል ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዘደንት፣ ከካስማ ወይም ከሚስዮን ፕሬዘደንትና ከቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንት እና ተባባሪዎቻቸው ምክር ሊቀበል ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ጥሪ እንዲሰጣቸው አልጠየቁም። ፍጹም የሆነም የለም። ነገር ግን እነርሱ በእውነቱ የመንፈስ ምሪት የመቀበል ስልጣን ባላቸው የተሾሙ የጌታ አገልጋዮች ናቸው። የተጠሩት፣ ድጋፍ የተሰጣቸው እና ለጥሪው የተለዩ ሰዎች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የማግኘት መብት አላቸው።

“… ለቤተክርስቲያን መሪዎች አክብሮት አለመስጠት ለብዙዎች መንፈሳዊ መድከም እና ማዘቅዘቅ እንዲከሰትባቸው አድርጓል። እኛን እንዲያስተዳድሩ የተጠሩ ሰዎች ፍጹም አለመሆን፣ እያንዳንዱን አቃቂሮሽ በላይ መመልከት አለብን እና እነሱ የሚይዙትን ሃላፊነት ከፍ ማድረግ አለብን” (“Called and Chosen,” Liahona, Nov. 2005, 54–55)።

ይህ ምክር በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ የአምላክ አገልጋዮችን ይባርካል።

በጌታ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ ቀናት ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በቅርብ የሚገኙ መሪዎች ስለ ስህተቶቹ መናገር ጀመሩ። ከጌታ ጋር የነበረውን አቋም ቢያዩምና ቢያውቁም እንኳ፣ የነቃፊነትና እና የቅናት መንፈስ እንደ ወረርሽኝ ተሰራጨ። ከአስራ ሁለቱ አንዱ በጌታ መንግስት ውስጥ ለማገልገል እንድንችል ሊኖረን የሚገቡትን ሁሉንም የእምነት እና ታማኝነት መስፈርቶች አስቀምጦልናል።

የሱም ዘገባ ይኸውና፤ “ብዙ ሽማግሌዎች ዮሴፍ ስሚዝ የተሳሳተ ነቢይ አድርገው ለሚመለከቱ ሁሉ በቤተመቅደስ ውስጥ ይሰበሰቡ ዘንድ ጠሩ። አዲስ የቤተክርስቲያን መሪ እንዲሆን ዴቪድ ዊትመርን ሊሾሙ አሰቡ። … በነብዩ ላይ የቀረቡትን ክርክሮች ካዳመጡ በኋላ፣ ብሬገም [ያንግ] ተነስተው ይህንን መሰከሩ፣ ‘ዮሴፍ ነብይ ነበር፣ እኔም አውቄያለሁ፣ እናም በፈለጉት መንገድም ቢማረሩበትም እና ቢሳለቁበትም፣ የእግዚያብሄርን ነብይ ምርጫን ሊያጠፉ አይችሉም፣ የራሳቸውን ስልጣን ግን ማጥፋት እንዲሁም ከነቢዩ እና ከእግዚያብሄር ጋር የሚያገናኛቸውን ገመድ ሊቆርጡ ይችላሉ፣ እናም እራሳቸውን ወደ ገሃነም ያሰምጣሉ’” (Church History in the Fulness of Times Student Manual [Church Educational System manual, 2003], 2nd ed., 174; see also Teachings of Presidents of the Church: Brigham Young [1997], 79)።

በእኛ አገልግሎት ውስጥ ከጌታ ጋር የሚያስተሳስረን ገመድ አለ። በእኛ በመንግሥቱ ውስጥ በምናገለግልበት ቦታ፣ በክህነት ስልጣን ውስጥ እኛን እንዲያስተዳድሩ በተጠሩት፣ እና ለጌታ በታሰረ ነቢይ ውስጥ የሚዘልቅ ነው። በተጠራንበት ቦታ እንድናገለግል፣ ጌታ እኛንና በእኛ ላይ የሚሾሙትን ለመተማመን እና በሙሉ እምነት ለመደገፍ እምነት እና ትህትና ይጠይቃል።

በኬርትላንድ ዘመን እንደነበረው፣ ልክ እንደ ብሬገም ያንግ እምነት እና ታማኝነት ጌታ በሚጠራን ስፍራ፣ ለነቢያቱ እና ለሾማቸው መሪዎች ታማኝ ሆነን እንድንቆም የምንፈለግበት ጊዜ ይኖራል።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበላይ መሪ እንደሆነ ያለኝን ትሁት እና እጅግ ደስተኛ የምስክርነት ቃል እሰጣችኋለሁ። ቤተክርስቲያኑን እና አገልጋዮቹን ይመራል። ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በዚህ ወቅት በምድር ላይ የቅዱስ ክህነት ቁልፎች ሁሉ የሚይዙና የሚጠቀሙበት ብቻው እንደሆኑ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። እናም እርሱ በግል በሚመራት በእውነተኛዋ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፈቃደኝነት እና በደንብ ለሚያገለግሉ ትሑት አገልጋዮች ሁሉ በረከቶችን እጸልያለሁ። ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሔር አብን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ እመሰክራለሁ። እነሱም አነጋግረውታል። የክህነት ቁልፎች ሁሉንም የሰማይ አባት ልጆች እንዲባርኩ ተመልሰዋል። በቦታችን በጌታችን ስራ ላይ ለማገልገል የእኛ ተልእኮ እና እምነታችን ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።