2010–2019 (እ.አ.አ)
ወደ ጌታ ዙሩ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ወደ ጌታ ዙሩ

በዚህ የሟች ህይወት ኑሮ፣ እኛ የሚደርሱብንን በሙሉ ለመቆጣጠር አንችልም፣ ነገር ግን፣ እኛ በህይወታችን ላሉ ፈተናዎች የምንመልስበትን ለመቆጣጠር ፍጹም ቁጥጥር አለን።

በጸደይ 1998 (እ.አ.አ) ኬሮል እና እኔ ለስራ የምንጓዝበትን ከሽርሽር ጋር አጣመርን እና አራት ልጆቻችንን በቅርብ ባለቤቷ የሞተባት አማቴን ይዘን ወደ ሀዋዪ ለትንሽ ቀናት ሄድን።

ወደ ሀዋዪ ከመብረራችን ምሽት በፊት፣ እድሜው አራት ወር የነበረው ወንድ ልጃችን ጆናተን ሁለት ጆሮዎቹን አመመው፣ እናም ለሶስት ቀን ለመጓዝ እንደማይችል ተነገረን። እኔ ከቀሩ ቤተሰቦች ጋር ለመጓዝ እናም ኬሮል ከጆነተን ጋር በቤት መቆየት እንደሚያስፈልጋት ተወሰነ።

ይህ ጉዞ በአዕምሮዬ ያሰብኩት እንዳልሆነ የመጀመሪያው ምልክት ያየሁት ወዲያው በዚያ እንደደረስን ነው። ባህርን በምንመለከትበት ዛፎች በሚገኙበት በጨረቃ ብርሀን በሚበሩበት መንገድ ላይ እየሄድኩኝ እያለሁ፣ ስለደሴቱ ወብት ለመናገር ስዞር፣ እና በዚያ የፍቅር ስሜት ጊዜ፣ ኬሮልን ሳይሆን የአማቴ አይኖች ነበር ያየሁት። ይህ የጠበቅኩት አልነበረም። ኬሮልም ከታመመው ህጻን ልቻችን ጋር በብቻዋ በቤት ውስጥ የሽርሽር ጊዜአችንን ለማሳለፍ አትጠብቅም ነበር።

ራሳችንን በማንጠብቀው፣ በተበጠበጠ ሽርሽር በላይ የሆኑ ጉዳዮች በሚያጋጥሙ መንገድ ላይ የምንገኝበት ጊዜ ይኖራል። ጉዳዮች፣ ልንቆጣጠራቸው የማንችላቸውንም፣ ተስፋ የነበረንን እና ያቀድነውን ህይወት ሲቀይሩ እንዴት መልስ እንሰጣለን?

ምስል
ሀይረም ስሚዝ ሻምዌይ

በሰኔ 6 ቀን 1944 (እ.አ.አ)፣ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር የነበረው ሀይረም ሻምዌይ በኦማሀ ባህር ዳር በዲ-ቀን ወደራ ተሳታፊ ነበር። በባህር ዳር ላይ በደህና ደረሰ፣ ነገር ግን በሀምሌ 27 ቀን፣ ሰራዊት ወደ ፊት በሚገፉበት ጊዜ ታንክ የሚያፈነዳ ፈንጂ በሚያሳቅቅ ሁኔታ አቆሰለው። ወዲያውም፣ ህይወቱ እና ለሀኪምነት የነበረው የስራ እቅድ በጣም ተጋጨ። ከብዙው ቁስሉ እንዲድን ከረዱት ከብዙ ቀዶ ጥገናዎች በኋላ፣ ወንድም ሻምዌይ አይነ ስውር ሆነ። ምላሹ ምን ነበር?

ራሱን ማቋቋም ከሚችልበት ሆስፒታል ለሶስት አመት ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቤቱ ወደ ለቬል፣ ዋዮሚንግ ተመለሰ። ሀኪም የመሆኑ እቅዱ የማይሆን እንደሆነ አወቀ፣ ነገር ግን ወደፊት ለመሄድ፣ ለማግባት፣ እና ቤተሰቡን ለመደገፍ ውሳኔ ነበረው።

በመጨረሻም በቦልቲሞር፣ ሜሪላንድ ውስጥ አይነ ስውር የሆኑት ራስ በሚያቋቁሙበት መካሪ እና ስራ በማግኘት ረጂ ሆነው። ራሱን በሚያቋቁምበት ጊዜም፣ አይነ ስውሮች ከሚያውቀው በላይ ችሎታ እንዳላቸው ተማረ፣ እናም በዚህ ስራ ውስጥ ለስምንት አመት ሲያገለግልም፣ በሀገሯ ከነበሩ አማካሪዎች በላይ ብዙ አይነ ስውር ሰዎችን ስራ እንዲያገኙ ረድቶ ነበር።

ምስል
የሻምዌይ ቤተሰብ

ለቤተሰቡ እርዳታ ለመስጠት እንደሚችል ልበ ሙሉ ሆኖ፣ ሀይረም ለሚወዳት “ደብዳቤዎችን፣ ካነበብሽ፣ ካልሲዎችን በትክክል ከደረደርሽ፣ እና መኪናውን ከነዳሽ፣ እኔ ሌላውን አደርጋለሁ” በማለት እንድታገባው ጠየቃት። በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ተሳሰሩ እና በመጨረሻም በስምንት ልጆች ተባረኩ።

በ1954 (እ.አ.አ)፣ ወንድም ሻምዊይ ለ32 አመት ለደንቆሮዎች እና አይነ ስውር ሰዎች ትምህርት የክልል መሪ በመሆን ወዳገለገለበት ወደ ዋዮሚንግ የሻምዌይ ቤተሰብ ተመለሱ። በዚያም ጊዜ፣ ለሰባት አመት በሻያን የመጀመሪያ አጥቢያ ውስጥ እንደ ኤጲስ ቆጶስ አገለገለ፣ በኋላም ለ17 አመት እንደ ፓትሪያርክ አገለገለ። ጡረታ ከወጣ በኋላ፣ ወንድምና እህት ሻምዌይ በለንደን ደቡብ ሚስዮን የአዛውንት ጥንዶች ሚስዮኖች በመሆን አገለገሉ።

ሀይረው ሻምዌይ ለትልቅ ልጆች፣ የልጅ ልጆች፣ እና የልጅ ልጅ ልጆች ትውልዶች በአስቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን የእምነትን እና በጌታ የማመን ቅርስ በመተው፣ በመጋቢት 2011 ሞተ።1

የሀረም ሻምዌይ ህይወት በጦርነት ቢቀየርም፣ መለኮታዊ ፍጥረቱን እና የዘለአለም ችሎታውን አልካደም። እንደ እርሱም፣ እኛ የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ነን፣ እናም “ስጋዊ አካልን [አግኝተን] ምድራዊ አጋጣሚዎችን በማግኘት ወደፍጹምነት ለመሻሻል እና በመጨረሻም [እኛ] እንደ መለኮታዊ [እጣችን] ዘላለማዊ ህይወትን ወራሽ [እንድንሆን] የሚያደርገውን አላማውን [ተቀብለን] ነበር።”2 ምንም ያህል ለውጥ፣ ፈተና፣ ወይም ተቃራኒነት ዘለአለማዊ መንገድን ለመቀየር አይችሉም—የነጻ ምርጫችንን በምንጠቀምበት ምርጫዎቻችን ብቻ ነው የሚችሉት።

በሟች ህይወት ውስይ የሚያጋጥሙን ቅያሬዎች፣ እናም በዚህ የሚመጡት ፈተናዎች፣ በተለያዩ መንገዶች እና አይነቶች ይመጣሉ እናም እያንዳንዳችንን በተለያዩ መንገዶች ይነኩናል። እንደ እናንተም፣ ጓደኞች እና ቤተሰቦች በሚቀጥሉት ምክንያቶች ፈተናዎች ሲያጋጥሟቸው ተመልክቻለሁ፥

  • የውድ ሰው መሞት።

  • መጥፎ ፍቺ።

  • ለማግባት ምንም እድል አለማግኘት።

  • አሰቃቂ ህመም ወይም ቁስለት።

  • እንዲሁም በቅርብ በአለም አቀፍ እንዳየናቸውም፣ የተፈጥሮ አደጋዎች።

ዝርዝሩም ይቀጥላል። ምንም እንኳን እነዚህ “ለውጦች” ለእያንዳንዳችን ሁኔታዎች ልዩ ቢሆኑም፣ በፈተናዎቹ ውጤት ውስጥ አንድ የሆነ ክፍል አለ—ተስፋ እና ሰላም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት በኩል ሁልጊዜም ይገኛል። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ለቆሰለው ሰውነት፣ ለተጎዳው መንፈስ፣ እና ለተሰበረው ልብ በመጨረሻ የሚያስተካክል እና የሚፈውስ ሁኔታ ይሰጣል።

ማንም ሊረዳው በማይችለው መንገድ፣ በለውጥ መካከል ወደፊት ለመግፋት እርሱ በግል ምን እንደምንፈልግ ያውቃል። እንደ ጓደኞቻችን እና እንደምናፈቅራቸው ሳይሆን፣ አዳኝ ከእኛ ጋር አብሮ ማዘን ብቻ ሳይሆን፣ ግን እርሱ በነበርንበት ስለነበረ የእኛን ችግር እንደራሱ አድርጎ ያዳምጣል። ለኃጢያታችን ዋጋን ከመክፈል እና ከመሰቃየት በተጨማሪ፣ እና በሟች ህይወት ካጋጠሙን ሁሉ በላይ ኢየሱስ ክርስቶስ በእያንዳንዱ መንገድ ተራምዷል፣ በእያንዳንዱ ፈተና ተፈትኗል፣ እያንዳንዱን የሰውነት፣ የስሜት ወይም የመንፈስ ጉዳትን ተቋቁሟል።

ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዳስተማሩት፥ “የኢየሱስ ክርስቶስ ምህረት እና ጸጋ ኃጢያት በሚሰሩት ላይ ብቻ የተመጠነ አይደለም … ፣ ነገር ግን እርሱን ለሚቀበሉና ለሚከተሉ ሁሉን የሚያቅፍ የዘለአለም ተስፋ ቃል ኪዳን ገብቷል። … የእርሱ ምህረት ታላቅ ፈዋሽ ነው፣ በልዩም የዋህ ለሆኑት ለቆሰሉት።”3

በዚህ የሟች ህይወት ኑሮ፣ እኛ የሚደርሱብንን በሙሉ ለመቆጣጠር አንችልም፣ ነገር ግን፣ እኛ በህይወታችን ላሉ ፈተናዎች የምንመልስበትን ለመቆጣጠር ፍጹም ቁጥጥር አለን። የሚያጋጥሙን ችግሮችና ፈተናዎች ምንም ውጤት የሌለው እና በቀላል መፍትሄ የሚገኝበት ነው ማለት አይደለም። ከሀዘን እና ከልብ ህመም ነጻ እንሆናለን ማለት አይደለም። ለተስፋ ምክንያት አለ እናም ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ወደ ፊት ለመግፋትና የተሻሉ ቀናትን፣ እንዲሁም በደስታ፣ በብርሀን፣ እና በደስታ የተሞሉ ቀናት ለማግኘት እንችላለን ማለት ነው።

በሞዛያ ውስጥ የንጉስ ኖሀ የድሮ ካህን ስለነበረው አልማ ታሪክ እናነባለን፣ እርሱም “ከጌታ ማስጠንቀቂያ በማግኘቱ፣ … ከንጉስ ኖህ ወታደሮች ፊት ወደ ምድረበዳው ሸሹ።” ከስምንት ቀናት በኋላ፣ “በጣም ቆንጆና መልካም ምድር የንፁህ ውሃ ምድር ወደሆነች መጡ፣” በዚያም “ድንኳናቸውን ተከሉና፣ ምድሪቱን ማረስ ጀመሩ፣ እናም ህንፃን መገንባት ጀመሩ።”4

አሁን ጉዳያቸው የተሻለ መሰለ። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ተቀብለዋል። ጌታን እንደሚያገለግሉና ትእዛዛቱን እንደሚያከብሩ ቃል በመግባት ተጠምቀዋል። እናም “በምድር ተባዙ እጅግም በለፀጉ።”5

ነገር ግን፣ ሁኔታቸው ወዲያው ተቀየረ። “የላማናውያን ወታደሮች በምድሪቱ ዳርቻ ነበሩ።”6 አልማ እና ህዝቡ በባርነት ነበሩ፣ እናም “ስቃያቸው ታላቅ ስለነበር ወደ እግዚአብሔርም በኃይል መጮህ ጀመሩ።” በተጨማሪም፣ በምርኮ የያዟቸው ጸሎትን እንዲያቆሙ አዝዘዋቸው፣ አለበለዚያም፣ “እግዚአብሔርን የሚጠራ ማንም ሰው እንዲገደል ነበር።”7 አልማ እና ህዝቡ አዲሱ ሁኔታቸውን እነርሱ ባደረጉት የሚገባቸው አልነበረም። ምላሻቸው ምን ነበር?

እግዚአብሔርን ሳይወቅሱ፣ ወደ እርሱ ዞሩ እናም “ልባቸውን ወደ እርሱ አፈሰሱ።” ለእምነታቸው እና ጸሎታቸው መልስ በመስጠትም፣ ጌታ እንዲህ አለ፥ “መልካም መፅናኛ ይኑራችሁም … በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፣ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልልላችኋለሁ።” ወዲያውም፣ “ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትዕግስት ለጌታ ፈቃድ ተቀባይ እንዲሆኑ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል።”8 ከባርነት ነጻ ባይሆኑም ወደ ጌታ በመመለስ፣ እና ከጌታ ባለመዞር በፍላጎታቸው መሰረት እና በጌታ ጥበብ በኩል ተባርከው ነበር።

ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳስተማሩት፥ “የሚፈውስ በረከት በብዙ መንገዶች ይመጣሉ፣ ከሁሉም በላይ በሚያፈቅረን እንደሚታወቁት፣ እያንዳንዱም ለግል ፍላጎታችን ብቁ የሆኑ ናቸው። አንዳንዴ ‘ፍወሳው’ ህመማችንን ያድናል ወይም ሸከማችንን ከፍ ያደርጋል። ነገር ግን እንዳንዴ ያለብንን ሸከም በጥንካሬ ወይም በመረዳት ወይም በትዕግስት ‘እንፈወሳለን’።”9

በመጨረሻም፣ “እምነታቸውና ትዕግስታቸው ታላቅ በመሆኑ፣” አልማ እና ህዝቡ በጌታ ዳኑ፣ “ምስጋናቸውን ለእግዚአብሔር አበረከቱ፣…፣ በባርነት ስር ነበሩ እናም ጌታ አምላካቸው ካልሆነ በቀር ማንም ሊያስለቅቃቸው አይቻለውምና።”10

የሚያሳዝነው ቢኖር፣ በብዛት እርዳታ የሚፈልጉት ለእርዳታ ፍጹም ምንጭ ከሆነው፣ ከአዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይዞራሉ። የምናውቀው “የነሀስ እባብ”ታሪክ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ምርጫዎች እንዳሉን ያስተምረናል። ብዙ የእስራኤል ልጆች “በሚበሩ መርዛም እባብ”11 ከተነደፉ በኋላ፣ “ምሳሌ የሆነው… ተሰቅሎ ነበር … ማንም ሰው ከተመለከተ … በህይወት ይኖር ዘንድ። [ነገር ግን ይህም ምርጫ ነበር።] እና ብዙዎች ተመለከቱ እናም ኖሩ።

… ነገር ግን ብዙ ልበ ጠጣሮች ስለነበሩ አልተመለከቱም፣ ስለዚህም ጠፉ።”12

እንደ ጥንት እስራኤላውያን፣ ወደ አዳኝ እንድንመለከትና እንድንኖር ተጋብዘናል፣ ቀንበሩ ቀላል እናም ሸከሙም የማያስቸግር ነውና።

ታናሹ አልማ ይህን ቅዱስ እውነት እንዲህ ሲል አስተምሯል፣ “እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ በፈተናቸውና፣ በችግራቸው፣ እናም በስቃያቸው እንደሚደገፉና፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ እንደሚደረጉ አውቃለሁ።”13

በእነዚህ በኋለኛው ቀናት፣ ጌታ ብዙ የመረዳት ምንጭ፣ የራሳችን “የነሀስ እባብ” ሰጥቶናል፤ ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንድንመለከት እና እምነታችንን በእርሱ ላይ እንድንጥል እንዲረዱን የተነደፉ ናቸው። የህይወት ፈተናዎችን መጋፈጥ እውነትን ችላ ስለማለት አይደለም ግን በምን ላይ ለማተኮር መምረጣችን እና ለመገንባት ምን መሰረት መምረጣችን አስፈላጊ ነው።

እነዚህም ምንጮች ተጨማሪ እንጂ በዚህ የተገደቡ አይደሉም፥

  • በየጊዜው ቅዱሳት መጻህፍትን እና የህያው ነቢያትን ትምህርት አጥኑ።

  • ሁልጊዜም፣ በቅንነት ጸልዩ እናም ጹሙ።

  • በብቁነት ቅዱስ ቁርባንን ተቀበሉ።

  • ሁልጊዜም ወደ ቤተመቅደስ ሂዱ።

  • የክህነት በረከቶች።

  • በሰለጠኑ ባለሙያዎች የጥበብ ምክሮችን ማግኘት።

  • እና እንዲሁም፣ በትክክል እና ስልጣን ባለው መድሀኒቶች ሲሰጡም።

በህይወት ጉዳይ ምንም ለውጥ ቢመጣ፣ እናም ባልታሰበበት መንገድ ብንጓዝ፣ ምላሽ የምንሰጥበት መንገድ ምርጫ ነው። ወደ አዳኝ መዞር እና ከእርሱ የተዘረጉት እጆችን መቀበል የእኛ መልካም ምርጫ ነው።

ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት ይህን ዘለአለማዊ እውነት አስተምረዋል፥ “እውነት፣ ከጥንካሬ ጋር የተጣመረ የሚጸና ደስታ፣ ብርቱነት፣ እና ከሁሉም በላይ አስቸጋሪ የሆኑትን ፈተናዎች መቋቋሚያ ችሎታ የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በተመሰረቱ ህይወት ነው። … ወዲያው የሚመጣ መፍትሄ የለም፣ ነገር ግን በጌታ ጊዜ መፍትሄ እንደሚመጣ፣ ሰላም እንደሚያሸንፍ፣ እና ባዶነት እንደሚሞላ ፍጹም ማረጋገጫ አለ።”14

ስለእነዚህ እውነቶች ምስክርነቴን እካፈላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።