2000–2009 (እ.አ.አ)
ነገር ግን እርሱ ባያድነን
ሚያዝያ 2004 (እ.አ.አ)


ነገር ግን እርሱ ባያድነን

እምነትን በመለማመድ ጌታ እንዴት እየቀረጻቸው እንዳለ ሳያውቁም እንኳን ሰዎች በጌታ በመታመን እና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋሉ።

ወጣት እያለሁ ከስምንተኛ ክፍሎች የቅርጫት ኳስ ግጥሚያ ተስፋ ቆርጬ፣ አዝኜ እና ግራ ተጋብቼ እቤት ተመለስኩኝ። “ለምን እንደተሸነፍን አላውቅም—እንደምናሸንፍ እምነት ነበረኝ!” ብዬ ለእናቴ በንዴት ነገርኳት።

እምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዳልገባኝ አሁን ተገንዝቢያለሁ።

እምነት ጉብዝና አይደለም፣ ፍላጎት ብቻም አይደለም፣ ተስፋ ብቻም አይደለም። እውነተኛ እምነት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ እምነት ነው—አንድን ሰው እንዲከተለው በሚያደርገው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ ልበሙሉነት እና መታን።1

ከዘመናት በፊት ዳንዔል እና ወጣት ጓደኞቹ በቅጽበት ከደህንነት ወደአለም ተወርውረው ነበር—እንግዳ እና አስፈረሪ ወደሆነ አለም። ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ በንጉሱ ለተዘጋጀው ወርቃማ ምስል መስገድን እና ማምለክን አሻፈረኝ ባሉ ጊዜ ቁጡው ናቡከደነጾር እንደታዘዙት የማያመልኩ ከሆነ ወዲያውኑ ወደሚነድ እሳት እቶን ውስጥ እንደሚጣሉ ነገራቸው። “ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?“2

ሶስቱ ወጣቶቸም በፍጥነት እና በልበሙሉነት “የምናመልከው አምላካችን ከሚደደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፣ ከእጅህም ያድነናል” ሲሉ መለሱ። ያ ስምንተኛ ክፍል እያለሁ የነበረኝን አይነት እምነት ይመስላል። ነገር ግን ከዚያ በኋላ እምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ እንደተገነዘቡ አሳዩ። እንዲህ ሲሉም ቀጠሉ “ነገር ግን እርሱ ባያድነን፣ … አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምከውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ።”3 ያ የእውነተኛ እምነት መግለጫ ነው፡፡

ምንም እንኳን ነገሮች ተስፋ እንዳደረጉት ባይሆኑም በእግዚያብሄር መታመን እንደሚችሉ አውቀው ነበር፡፡4 እምነት እግዚያብሄር እንዳለ በአእምሮ ከመቀበል፣ እውቅና ከመስጠት የበለጠ እንደሆነ አውቀው ነበር፡፡ እምነት በእርሱ ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር ነው።

እምነት ማለት ሁሉንም ነገሮች መረዳት ባንችልም እርሱ እንደሚችል ማመን ማለት ነው። እምነት ማለት የእኛ አቅም ውስን ቢሆንም የእርሱ እንዳልሆነ ማወቅ ማለት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በእርሱ ላይ ሙሉ ለሙሉ መታመንን ያካትታል።

እቅዱን ያውቁ ስለነበር እና እርሱም ስለማይቀየር ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ሁሌም በእርሱ መታመን እንደሚችሉ ያውቁ ነበር።5 እኛም እንደምናውቀው ሟችነት የተፈጥሮ አጋጣሚ እንዳልሆነ ያውቁ ነበር። ፍቃደኛ ብንሆን እሱ የሚደሰትባቸውን እነዚያን በረከቶች እንድናገኝ ለማስቻል ለእኛ ለወንዶች እና ለሴቶች ልጆቹ ያዘጋጀው የአፍቃሪ የሰማይ አባታችን ታላቅ እቅድ6 አጭር ክፍል ነው።

እኛም እንደምናውቀው በቅድመ ምድር ህይወታችን የስጋዊ ህይወትን አላማ ከእርሱ ተምረን እንደነበር ያውቁ ነበር፦ “እነዚህ ሊኖሩበት የሚችሉትን ምድርን እንሰራለን፤ ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን።”7

ስለዚህ ይህ ፈተና ነው። አለም ለምድራውያኑ ወንዶች እና ሴቶች የፈተና ቦታ ነው። እንድናምነው እና እንዲረዳን እንድንፈቅድለት በሚፈልገው በሰማይ አባታችን የሚሰጥ ፈተና እንደሆነ ስንገነዘብ ሁሉንም ነገር ይበልጥ በግልጽ ማየት እንችላለን።

ስራው እና ክብሩ “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ለማምጣት” እንደሆነ ነግሮናል።8 እርሱ አስቀድሞ መለኮታዊነት ላይ ደርሷል። አሁን ብቸኛው አላማው ወደእርሱ መመለስ እንድንቸል እና እንደእርሱ እንድንሆን እንዲሁም የእርሱን አይነት ህይወት ለዘለለም መኖር እንድንችል እኛን መርዳት ነው።

ይህንን ሁሉ በማወቃቸው ሶስቱ ዕብራውያን ወጣቶች ውሳኔያቸውን ለማድረግ አስቸጋሪ አልነበረም። እግዚያብሄርን ይከተሉታል በእርሱም እምነትን ያደርጋሉ። እርሱ ያድናቸዋል፣ ነገር ግን እርሱ ባያድ[ናቸው]—ቀሪውን የታሪኩን ክፍል እናውቃለን።

ጌታ የመምረጥ ነጻነት ሰጥቶናል የመወሰን መብት እና ሃላፊነት።9 በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ በመፍቀድ ይፈትነናል። ለመቋቋም ካለን አቅም በላይ እንድንፈተን እንደማይፈቅድ ያረጋግጥልናል፡፡10 ነገር ግን ከባድ ፈተናዎች ታላላቅ ሰዎችን እንደሚፈጥሩ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ መከራን አንሻም ነገር ግን በእምነት ምላሽ ከሰጠን ጌታ ያጠነክረናል፡፡ ነገር ግን እንደዛ ባይሆን የሚሉት ሁኔታዎች አስደናቂ በረከቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ሃዋርያው ጳውሎስ ይህንን ጉልህ ትምህርት ተምሯል እንዲሁም ከአስርተ አመታት ያልታከተ የሚስዮናዊ ስራ በኋላ እንዲህ ብሏል “መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ፥ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን …ተስፋ አያሳፍርም፡፡”11

“ጸጋዬ ለአንተ ብቁ ነው፤ ጥንካሬዬ በደካማነት ፍጹም ይሆናልና።” የሚል ማረጋገጫ ከአዳኙ አግኝቶ ነበር።12

ጳውሎስም እንዲህም ሲል መለሰ፣ “የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ … በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።… ስለክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፥ ስደክም ያኔ ሃይለኛ ነኝና።”13 ጳውሎስ ችግሮቹን በጌታ መንገድ ሲመለከት እምነቱ ጨመረ።

“አብርሃም በተፈተነበት ጊዜበእምነት ይስሃቅን አቀረበ።”14 አብርሃም በታላቅ እምነቱ የተነሳ ቁጥራቸው ከሰማይ ክዋክብት የበዛ ትውልድ እንደሚኖረው እና ይህም ትውልድ በይስሃቅ በኩል እንደሚመጣ ቃል ተገባለት። ነገር ግን አብርሃም ከጌታ ትዕዛዝ ጋር ወዲያውኑ ተስማማ። እግዚያብሄር ቃሉን ይጠብቃል፣ አብርሃም እንደጠበቀው ሁኔታ ባይሆንም ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ ያምነዋል።

እምነትን በመለማመድ ጌታ እንዴት እየቀረጻቸው እንዳለ ሳያውቁም እንኳን ሰዎች በጌታ በመታመን እና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋሉ።

“ሙሴ … የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባልበእምነት እምቢ አለ።

“ለጊዜው በሃጢያት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚያብሄር ህዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤

“ከግብጽም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቧልና። …

“የንጉሱን ቁጣ ሳይፈራ የግብጽን አገር የተወበእምነት ነበር። …

“በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባህርበእምነት ተሻገሩ።…

“የኢያሪኮ ቅጥርበእምነት ፈረሰ።”15

እነርሱበእምነት መንግስታትን ድል ነሱ፣ …የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፣ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፣

“የእሳትን ሃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፣ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ሃይለኞች ሆኑ።”16

ነገር ግን በተሳታፊዎችቹ ተስፋ በተደረጉ እና በተጠበቁ በእነዚያ ሁሉ ታላላቅ ውጤቶች ውስጥ ሁልጊዜ ነገር ግን ባይሆንስ:የሚሉት ነበሩ።

“ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ፣ … በእስራት እና በወኅኒ ተፈተኑ፦

“በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፦ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ … ዞሩ፤ 17

“ያለእኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚያብሄር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።”18

ቅዱሳን መጻህፍቶቻችን እና ታሪካችን እግዚያብሄር ያድነናል ብለው ባመኑ የእግዚያብሄር ታላላቅ ወንዶች እና ሴቶች ዘገባዎች ተሞልተዋል፤ ነገር ግን ባይሆንስ፣ እንደሚያምኑ እና ታማኝ እንደሆኑ ያሳያሉ።

ኃይሉ አለው ነገር ግን የእኛ ፈተና ነው።

ጌታ ፈተናዎቻችንን በተመለከተ ከእኛ ምን ይጠብቃል? የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ይጠብቃል። የተቀረውን እርሱ ይሰራዋል። ኔፊ እንዲህ ብሏል “ምክንያቱም በጸጋ የምንድነው የምንችለውን ካደረግን በኋላ እንደሆነ እናውቃለንና።”19

እንደሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ ያለ እምነት ሊኖረን ይገባል።

አምላካችን ከመከራ እና ከስደት ያድነናል፣ ነገር ግን እርሱ ባያድነን… አምላካችን ከህመም እና ከበሽታ ያድነናል፣ ነገር ግን እርሱ ባያድነን… እርሱ ከብቸኝነት፣ ከድብርት እና ከፍርሃት ያድነናል፣ ነገር ግን እርሱ ባያድነን፣… አምላካችን ከስጋት፣ ከወቀሳ እና ከደህንነት ማጣት ስጋት ያድነናል፣ ነገር ግን እርሱ ባያድነን፣… እርሱ የምንወዳቸው ሰዎች ሊደርስባቸው ከሚችለው ሞት እና ጉዳት ያድናቸዋል፣ ነገር ግን ባያድ[ናቸው]፣ …በጌታ እንታመናለን።

አምላካችን ፍትህን እና ፍትሃዊነትን ማግኘታችንን ይመለከታል፣ ነገር ግን ባይሆንስ… እርሱ እንደተወደድን እና እውቅና እንደተሰጠን ያረጋግጣል፣ ነገር ግን ባይሆንስ፣… ፍጹም አጋር እንዲሁም ጻድቅ እና ታዛዥ ልጆች እንቀበላለን ነገር ግን ባይሆንስ፣… እኛ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ብናደርግ በእርሱ ጊዜ እና መንገድ እንደምንድን እና ያለውን ሁሉ እንደምንቀበል በማወቅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ይኖረናል።20 ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።