2010 (እ.አ.አ)
የሚያድጉትን ትውልዶች ለመንከባከብ ያለን ሀላፊነት
ሴፕቴምበር 2010


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ መስከረም 2010

የሚያድጉትን ትውልዶች ለመንከባከብ ያለን ሀላፊነት

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ምስል

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ከቅዱስ መጻህፍት፧

ምሳሌ 22፧6ኤፌሶን 6፧4ኢኖስ 1፧1አልማ 53፧20–2156፧4757፧27

ያለመንከባከብ፣ የሚያድጉት ትውልዶቻችን በ ሞዛያ 26 ውስጥ እንደተገለጹት ለመሆን አደጋ ላይ ያሉ ለመሆን ይችላሉ። ብዙ ወጣቶች በአባቶቻቸው ባህል አላመኑም እናም በእምነታቸው የተለዩ ህዝቦች ሆኑ፣ ለዘለአለምም እንደዚሁ ሆነው ቀሩ። የእኛ የሚያድጉት ትውልዶች በሰማይ አባት አላማ ውስጥ ያላቸውን ክፍል ካልተደረዱ እንደዚህም የመሆን አደጋ ላይ ናቸው ያሉት።

ስለዚህ ይህን የሚያድግ ትውልድ በደህንነት የሚጠብቅ ምንድን ነው? በቤተክርስትያኗ ውስጥ የሚያድጉትን ትውልዶች ቤተሰብ እንዲመሰርቱ፣ ያንን ቤተሰብ እንዲያስተምሩ፣ እና ያንን ቤተሰብ ለስነስርዓቶች እና ለቃል ኪዳኖች እንዲያዘጋጁ የሚያድኑ መሰረታዊ መመሪያዎችን እናስተምራቸዋለን —እናም የሚቀጥለው ትውልድ ከእነርሱ የሚቀጥለውን ያስተምራሉ እናም እንደዚህም ይቀጥላል፤ እናም እነዚያ መሰረታዊ መመሪያዎች የቤተሰብ መሰረታዊ መመሪያዎች ናቸው።

እንደ ወላጆች፣ መሪዎች፣ እና የቤተክርስትያን አባላት፣ ይህን ትውልድ ለአብራሐም፣ ለቤተመቅደስ፣ በረከቶች እያዘጋጀን ነን። በቤተሰብ አዋጅ ውስጥ በሚገኙት በትምህርት ዋና ነጥቦች ላይ ግልፅ የመሆን ሀላፊነት አለን። እናትነት እና አባትነት ዘለአለማዊ ተጠያቂነት እና ሀላፊነት ናቸው። እያንዳንዳችን ለወንድም ወይም ለሴት የአላማ ግማሽ ሀላፊነት የምንሸከም ነን።

ይህን ትምህርት በማንኛውም ጉዳይ ለማስተማር እንችላለን። ስለጋብቻ እና ስለቤተሰብ በክብር መናገር ይገባናል። ከእኛም ምሳሌነት፣ከምንናገራቸው ቃላት ብቻ ሳይሆን ቤተሰብን በሚመለከት መሰረታዊ መመሪያ ባለን ስሜት እና ጥሩ ምሳሌ፣ የሚያድጉት ትውልዶች ታላቅ ተስፋ እና ግንዛቤ ለማግኘት ይችላሉ።

ጁሊ ቤክ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።

ከታሪካችን

በመስከረም 23፣ 1995 (እ.አ.አ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሆንክሊ እንዲህ አሉ፧ “ያለንበት አለም የተበጠበጠ፣ ምግባረ ጥሩነቱ የሚቀያየር ነው። ጆሮ የሚበጥስ አይነት የሚጮሁ ድምጾች በጊዜ ተመዝኖ የነበረውን የጸባይ መሰረትን በሚክድ አንድ ነገር ወይም ሌላ ይጠራሉ።1 ፕሬዘደንት ሒንክሊ ከእዛም ቀጥለው እህቶችን፣ እና በመጨረሻም በሁሉም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ “ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” የሚባለውን አስተዋወቁ።

በሚቀጥሉትም አመቶች ይህ ነቢያዊ መዝገብ በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሟል እናም ለአለም መሪዎችም ተበትነዋል። የሀገር ዜጋዎችን እና የመንግስት መሪዎችን “ቤተሰብ የማህብረሰብ ዋና መሰረታዊ ክፍል እንዲሆን እና እንዲጠናከር እርምጃዎች እንዲወስዱም” ይጠይቃል።2

አዋጁም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ስለቤተሰብ ያላቸው እምነት መሰረት፣ የምንቀበለው እና ህያው በሆነው አስተያየቱ ቤተሰቦቻችንን እና ቤቶቻችንን ማጠናከር እንደምንችል የምናውቅበት ሆነ።

ማስታወሻዎች

  1. Gordon B. Hinckley, “Stand Strong against the Wiles of the World,” Ensign, ህዳር 1995, 99።

  2. “ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” Liahona, ጥቅምት 2004, 49 ተመልከቱ።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እህቶቼ የሚያድጉትን ትውልዶች ለመንከባከብ “ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅን” እንዲጠቀሙ ለመርዳት እንዴት እችላለሁ? የአዋጁን ግልባጭ ለመካፈል እና እህቶቻችሁ ዋና ትምህርት የሆኑትን ምንባብ ለማወቅ እና ምልክት እንዲያደርጉባቸው ለመርዳት አስቡበት።

  2. የሚያድጉትን ትውልዶች እንዴት ለመንከባከብ እችላለሁ? በዎርዳችሁ፣ በቅርንጫፋችሁ፣ በቤተሰባችሁ፣ ወይም በማህብረሰባችሁ ውስጥ በልዩ ትኩረት እና በፍቅር ጥቅም ለማግኘት የሚችሉትን ለማግኘት አስቡባቸው።