2010 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ በረከቶች
ኦክተውበር 2010


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2010 (እ.አ.አ)

የቤተመቅደስ በረከቶች

ቤተመቅደስ ለህይወታችን አላማ ይሰጣል። ይህም—በሰው የተሰጠ ሰላም ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ” በሚልበት ጊዜ ቃል በገባበት ቃል ኪዳን ለነፍሶቻችን ሰላም ያመጣል።

በቤተመቅደስ ውስጥ ወደጌታ መቅረብ ይሰማናል።

በቅዱስ ቤተመቅደሶች ውስጥ ወደ ጌታ መቅረብ እንደሚሰማኝ በአለም ውስጥ፡የሚገኝ ምንም ቦታ እንደሌለ አስባለሁ። ግጥሙን በሌላ መልክ ለመግለፅ፧

ሰማይ ምን ያህል ይርቃል?

በጣም ሩቅ አይደለም።

በእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች

እኛም እዚያ ነን ያለነው።

ጌታ እንዳለው፧

“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤

“ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤

“መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።”1

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባላት፣ ቤተመቅደስ በምድር ላይ ከሁሉም በላይ የተቀደሰ ቦታ ነው። ይህም የጌታ ቤት ነው፣ እናም በቤተመቅደሱ ውጪ የተጻፈው እንደሚገልጸው፣ ቤተመቅደስ “የጌታ ቅድስና ነው።”

ቤተመቅደስ ያነሳሳናል እናም ከፍ ያደርገናል።

በቤተመቅደስ ውስጥ የእግዚአብሔር ውድ አላማ ትምህርት አለ። በቤተመቅደስ ውስጥ፡ነው ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን የሚገባው። ቤተመቅደስ ከፍ ከፍ እንድንል፣ ሁሉም እንደሚያዩአቸው ምልክቶች እንድንቆም ያደርገናል፣ እና ወደ ሰለስቲያል ግርማም እንድንሄድ ይጠቅሙልናል። ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረጉት ድርጊቶች ሁሉ ከፍ ከፍ የሚያደርጉና የሚያስከብር ነው።

ቤተመቅደስ ለቤተሰቦች ነው፣ በስጋዊ ህይወት ውስጥ ካሉን ሀብቶች ሁሎ ታላቅ የሆነውም ነው። ጌታ ለእኛ ለአባቶች ሚስቶቻችንን በልቦቻችን ሁሉ ለማፍቀር እና ለእነርሱና ለልጆቻችን እርዳታ ለመስጠት ሀላፊነት እንዳለብን በማመልከት በግልፅ ተናግሯል። እኛ ወላጆች ከምናደርጋቸው ስራዎች ሁሉ ታላቅ የሆነውን የምናከናውነው በቤት ውስጥ እንደሆነ፣ እና ጋብቻችን በእግዚአብሔር ቤት የታተሙ ሲሆኑ፣ ቤቶቻችን ሰማይ ለመሆነ እንደሚችሉ አመልክቷል።

የአስራ ሑለቱ ሐዋሪያት ቡድን የድሮው ካህን ማቲው ካውሊ አንድ አያት የሴት የልጅ ልጁን እጇን ይዞ—የዱር እንስሣት ለሚታዩበት ሳይሆን ወደ ቤተመቅደስ ስለወሰዳት የቅዳሜ ከሰዓት በኋላ አጋጣሚ አንድ ጊዜ ተናግረው ነበር። የቤተመቅደስ ምድርን ከሚጠብቀው ሰው ፈቃድ አግኝተው፣ ሁለቱ ወደ ቤተመቅደሱ በሮች ሄደ። በጠንካራው ግድግዳ ላይ እና በትልቁ በሮች ላይ እጆቿን እንድታሳርፍ ጠየቃት። በእቅፍ እንዲህ አላት፣ “በዚህ ቀን ቤተመቅደስን እንደነካሽ አስታውሺ። አንድ ቀን ወደውስጥ ትገቢአለሽ።” ለትንሿ ልጅ የሰጣት የከረሜላ ወይም የአይስክሬም ስጦታ ሳይሆን ለጌታ ቤት አድናቆት እንዲኖራት ታላቅ ቁም ነገር ያለውና ዘለአለማዊ የሆነ አጋጣሚነት ነበር የሰጣት። ቤተመቅደስን ነክታለች፣ እና ቤተመቅደሱም ነክቷታል።

ቤተመቅደስ ለነፍሶቻችን ሰላም ያመጣል።

ቤተመቅደሱን ስንነካ እና ቤተመቅደስን ስናፈቅር፣ ህይወቶቻችን እምነታችንን ያሳያሉ። ወደ ቅዱሱ ቤት ስንሄድ፣ በዚያም ውስጥ የምንሰራውን ቃል ኪዳን ስናስታውስ፣ ሙከራዎችን ሁሉ ለመቋቋም እና ፈተናዎችን ሁሉ ለማሸነፍ እንችላለን። ቤተመቅደስ ለህይወቶቻችን አላማ ይሰጡታል። ይህም—በሰው የተሰጠ ሰላም ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” በሚልበት ጊዜ ቃል በገባበት ቃል ኪዳን ለነፍሶቻችን ሰላም ያመጣል።2

በኋለኛው ቀን ቅዱሳን መካከል ታላቅ እምነት አለ። ጌታ ትእዛዛቱን እንደምንከተል፣ የናዝሬት ኢየሱስ የተከተለውን መንከድ እንደምንከተል፣ ጌታም በሙሉ ልባችን፣ ሀይላችን፣ አዕምሮአችን፣ እና ጥንካሬአችን እንደምናፈቅር፣ እና ጎረቤቶቻችንን እንደ እራሳችን እንደምናፈቅር ለማየት እድል ይሰጠናል።3

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል” በሚለው ምሳሌ አምናለሁ።4

ሁልጊዜም እንደዚህ ነበር፤ ለሁልጊዜም እንደዚህ ይሆናል። ሀላፊነታችንን ካከናወንን እና በጌታ በሙሉ ካመንን፣ የእራሳችንን የስነስርዓት ስራዎችን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ስራዎች ለማከናወን እድል እያገኘን ቤተመቅደሱን እንሞላለን። ባሎችን እና ሚስቶችን እና ልጆችን ለዘለአለም ለማተሳሰር በውክልና በተቀደሰው መሰዊያ አጠገብ እንንበረከካለን። ብቁ የሆኑ 12 አመት እና በላይ የሆኑ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች የጥምቀት በረከቶችን ከማግኘታቸው በፊት ለሞቱት ውኪል ለመሆን ይችላሉ። ይህም ለእናንተ እና ለእኛ የሰማይ አባት ያለው አላማ ነው።

ታምራት መጣ

ከብዙ አመት በፊት፣ ትሁት እና ታማኝ ፔትሪያርክ፣ ወንድም ፐርሲ ኬ ፈትዘር በኮሚኒስት ሀገሮች የሚገኙትን የቤተክርስትያን አባላት የፔትሪያርክ በረከቶችን እንዲሰጡ ተጠርተው ነበር።

ወንድም ፈትዘር ወደ ፖላንድ ምድር በእነዚያ አስቸጋሪ ጊዜዎች ሄዱ። ድንበሩ ተዘግቶ ነበር፣ እና ዜጋዎቹ ለመውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር። ወንድም ፈትዘር ከአለም ሁለተኛው ጦርነት በኋላ ድንበሩ በተቀየረበት እና የሚኖሩበት ምድር የፖላንድ ክፍል በሚሆንበት ጊዜ በዚያ ተይዘው ከነበሩት የጀርመን ቅዱሳን ጋር ተገናኙ።

ከሚስቱ እና ከልጆቹ ጋር በእዚያ የሚኖሩት ወንድም ኤሪክ ፒ ኮነትዝ በጀርመን ቅዱሳን ሁሉ መካከል መሪያችን ነበሩ። ወንድም ፈትዘር ወንድም እና እህት ኮነትዝንና በእድሜ የደረሱትን ልጆች የፔትሪያርክ በረከቶችን ሰጡአቸው።

ወንድም ፈትዘር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሲመለሱ፣ ጠሩኝ እና መጥተው ለመጎብኘት እንደሚችሉ ጠየቁኝ። በቢሮዬ ተቀምጠው እያሉ፣ ማልቀስ ጀመሩ። እንዲህም አሉ፣ “ወንድም ሞንሰን፣ በኮነትዝ ቤተሰብ አባሎች ራስ ላይ በምጭንበት ጊዜ፣ የማይሟላ የተስፋ ቃል ሰጠኋቸው። ወንድም እና እህት ኮነትዝን ወደተወለዱበት ጀርመን አገር ለመመለስ እንደሚችሉ፣ በአሸናፊ አገሮች ጭፍን ውሳኔ ምክንያት በምርኮ እንደማይያዙና በጌታ ቤት ውስጥ እንደቤተሰብ እንደሚተሳሰሩ የተስፋ ቃል ሰጠኋቸው። ወንድ ልጃቸውን ሚስዮን ለማሟላት እንደሚችል ቃል ገባሁለት፣ እና ሴት ልጃቸው በእግዚአብሔር ቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ እንደምትጋባ ቃል ገባሁላት። በተዘጋው ድንበሮች ምክንያት የእነዚህ በረከቶች መሟላትን ለመቀበል እንደማይችሉ እኔ እና እርስዎ እናውቃለን። ምን አደረኩኝ?

እኔም እንዲህ አልኳቸው፣ “ወንድም ፈትዘር፣ የሰማይ አባት የፈለገውን እንዳደረክ እስከማወቅ ድረስ አንተን አውቅሀለሁ።” ሁለታችንም በጠረጴዛዬ አጠገብ ተንበረከክን እና መለኮታዊ ለሆኑት ቤተሰቦች ስለእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እና ሌሎች በረከቶች በሚመለከት አሁን የማያገኙትን ቃል ኪዳን እንደተሰጣቸው በማመልከት ወደሰማይ አባት የልባችንን አፈሰስን። ያስፈለገንን ታምራት ማምጣት የሚችለው እርሱ ብቻ ነበር።

ታምራቱ ደረሰ። የፖላንድ መንግስት እና የፈደራል ጀርመን ሪፐብሊክ መሪዎች በዚያ ቦታ የሚኖሩት የጀርመን ዜጋዎችን ወደ ምዕራብ ጀርመን ለመሄድ እንዲችሉ በመስማማት ስምምነትን ፈረሙ። ወንድም እና እህት ኮነትዝ እና ልጆቻቸው ወደ ምዕራብ ጀርመን ገቡ፣ እና ወንድም ኮነትዝ በሚኖሩበት ዎርድ ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ።

የኮነትዝ ቤተሰብ በሙሉ በስዊዘርላንድ ውስጥ ወዳለው ቅዱስ ቤተመቅደስ ሄደ። ነጭ ሱፍ ለብሰው እነርሱን ሰላም ለማለት የሚጠብቋቸው ማን ነበሩ? ያን ቃል ኪዳን የሰጧቸው ፔትሪያርክ ፐርሲ ፈትዘር ነበሩ። በበርን ስዊትዘርላንድ ቤተመቅደስ ፕሬዘደንት ሀላፊነታቸው መሰረት፣ የገቡላቸውን ቃል ኪዳን ለማሟላት፣ እና ባልና ሚስትን እና ልጆችን ከወላጆች ጋር ለማስተሳሰር ወደ ጌታ ቤት እንኳን ደህና መጣችሁ አሏቸው።

ታናሿ ሴት ልጅ በኋላም በጌታ ቤት ውስጥ አገባች። ወጣቱ ወንድ ልጅ ጥሪውን ተቀበለ እና የሙሉ ጊዜ ሚስዮንን አሟላ።

“በቤተመቅደስ ውስጥ እናዮታለን!”

ለእያንዳንዳችን፣ ወደቤተመቅደስ የምንጓዘው ሩቅ ቦታ አይደለም። ለሌሎች፣ ወደ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ከመግባታቸው በፊት ባህርን ማቋረጥ ወይም ለብዙ ኪሎሚትሮች መጓዝ አለባቸው።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ የደቡብ አፍሪካ ቤተመቅደስ ከመፈጸሙ በፊት፣ በሳሊስበርይ ሮዲዥያ ውስጥ የዲስትሪክት ጉባኤን ውስጥ እየተሳተፍኩኝ እያለሁ፣ ከዲስትሪክት ፕሬዘደንት ረጂናልድ ጄ ኒልድ ጋር ተገናኘሁ። ወደቤተክርስትያኑ ስገባ እርሱ፣ ባለቤቱ፣ እና ቆንጆዎቹ ሴት ልጆቹ በበሩ ላይ ተገናኙኝ። ገንዘባቸው እያጠራቀሙና ወደጌታ ቤተመቅደስ ለሚጓዙበት ቀን እየተዘጋጁ እንደነበሩ ገለጹልኝ። ነገር ግን ቤተመቅደሱ ሩቅ ነበር።

በስብሰባው መጨረሻ ላይ፣ አራቱ ቆንጆ ሴት ልጆች ስለቤተመቅደሱ ጥያቄ ጠየቁኝ፧ “ቤተመቅደሱ ምን አይነት ነው?” ያየነው ፎቶዎች ብቻ ነው። “ወደቤተመቅደስ ውስጥ ስንገባ ምን ይሰማናል?” “ከሁሉም በላይ የምናስታውሰውስ ምንድን ነው?” ለአንድ ሰዓት ለሚሆን ለአራቱ ሴት ልጆች ስለጌታ ቤት ልነግራቸው እድል አገኘሁ። ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ስሄድ፣ እጃቸውን አውለበለቡልኝ፣ እናም ታናሿ ሴት እንዲህ አለች፣ “በቤተመቅደስ ውስጥ እናዮታለን!”

ከአንድ አመት በኋላ የኒልድን ቤተሰብ በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ውስጥ ሰላምታ ለመስጠት እድል አግኝቻለሁ። ሰላም በሚገኝበት በመተሳሰሪያው ክፍል ወንድም እና እህት ኒልድን ለጊዜ እና ለዘለአለም ለማተሳሰር እድል አገኘሁ። ከዛም በሮቹ ተከፈቱ፣ እና እነዚያ ቆንጆ ሴት ልጆች ሁሉም ንጹህ የሆነ ነጭ ልብስ ለብሰው ወደክፍሉ ገቡ። እናታቸውን ከእዚያም አባታቸውን አቀፉ። በአይኖቻቸው ውስጥ እምባ ነበር፣ እናም በልቦቻቸው ውስጥ ምስጋና ነበር። በሰማይ አጠገብ ነበርን። እያንዳንድም “አሁን ለዘለአለም ቤተሰቦች ነን” ለማለት ይችሉም ነበር።

ይህም ወደ ቤተመቅደስ ለሚመጡት ሁሉ የሚጠብቃቸው አስደናቂ በረከት ነው። እያንዳንዳችን ቤተመቅደስ ህይወታችንን እና በተሰቦቻችንን እንዲነኩ ዘንድ በንጹህ እጆች እና እና ልቦች በብቁ ህይወት እንኑር።

ሰማይ የት ድረስ የራቀ ነው? ቅዱሱ ቤተመቅደስ እስከዚህም የራቀ እንዳልሆነ እመሰክራለሁ—ምክንያቱም ሰማይና ምድር የሚገናኙት እና የሰማይ አባታችን ለልጆቹ ከሁሉም በላይ የሆኑትን በረከቶች የሚሰጥባቸው በእነዚህ ቅዱስ ቦታዎች ነውና።