2014 (እ.አ.አ)
ለጸሎቷ መልስ
ማርች 2014


ወጣቶች

ለጸሎቷ መልስ

ጸሐፊዋ በጋውቴንግ፣ ደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ነች።

አንድ ምሽት የሌላ እምነት ተከታይ የሆነ ጓደኛ ጎበኘኝ። ብዙውን ጊዜ ቅዱሳን መጽሐፍቶቼን ለብቻዬ ነው የማጠናው፣ እና በዛም ምሽት ለማጥናት ይዣቸው ወጥቼ ነበር። የቅዱሰ መጽሐፍ ጥናቴን እንድትቀላቀል ለመጋበዝ ተገፋፍቼ ነበር፣ ነገር ግን ፈራሁ እናም በምትኩ ለብቻዬ ማጥናት ጀመርኩ። የመንፈስ ቅዱስን ግፊት ችላ እንዳልኩ አወኩኝ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጥንቃቄ፣ “ከእኔ ጋር ቅዱስ መጽሐፍቶችን ለማጥናት ትፈልጊያለሽ?” ብዬ ጠየኩ። ያል ምንም ማመንታት ጓደኛዬ፣ “አዎ” ብላ መለሰች።

ከዛም ከመጽሐፈ ሞርሞን አነበብን። አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ፣ እናም በምመልስበት ሰአት መንፈስ ቅዱስ ሲመራኝ ይሰማኝ ነበር። ስለ መጽሐፈ ሞርሞን እውነተኛነት ምስክርነቴን አካፈልኩ። ይህንን ካደረኩ በኋላ፣ እንዲህ አለችኝ፣ “ቀኑን ሙሉ ሳለቅስ እና ስፈራ ነበር። ቅዱስ መጽሐፍቶችን ካንቺ ጋር እንዳነብ ስትጠይቂኝ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጸልዬ ነበር። አሁን በጣም የተሻለ ስሜት ይሰማኛል። አመሰግናለሁ።”

ለጸሎት መልስ እና እራዳታ ከሚፈልጉት ልጆቹ መካከል አንዷን ማገልገል እንድችል ጌታ እኔን እንደመሳሪያ ተጠቅሞብኛል። ግፊቶች ከጠቢብ እና ከክቡር አባት የሚመጡ መለኮታዊ መመሪያዎች እንደሆኑ አውቃለሁ። ፍራቻዎቻችንን ከእኛ ስናርቅ፣ በእኛ ታዛዥነት ምክንያት ሀይሉን እንዲገልጽ እንፈቅድለታለን።