2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ምሳሌ
ጁላይ 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2014 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ምሳሌ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደwww.reliefsociety.lds.org

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ ከአባት ጋር የሚማፀንልን ጠበቃችን ነው“። ቃሉ በእንግሊዘኛ ጠበቃ “ለሌላ የሚለምን ሰው” የሚል የላቲን ትርጉም አለው።1 መረዳትን፣ ፍትህን እና ምሕረትን በመጠቀም አዳኝ ለእኛ ይለምናል። ይህንን ማወቅ ለእሱ የኃጢያት ክፍያ በምስጋና እና በፍቅር ሊሞላን ይችላል።

“ከአብ ፊት ጠበቃ የሆነውን፣ እርሱ ፊትም ስለእናንተ እንዲህ በማለት የሚማፀንላችሁን ስሙ—

“አባት ሆይ፣ ሀኃጢአት ያልሰራውን በእርሱም የተደሰትከውን ስቃይና ሞት ተመልከት፤ የፈሰሰውን የልጅህን ደም ተመልከት፣ ስምህ ይከብር ዘንድ አንተ የሰጠኸውን የልጅህን ደም ተመልከት፤በማለት

“ስለዚህ፣ አባት ሆይ፣ በስምህየሚያምኑትን ወደ እኔም መጥተው ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ እነዚህን ወንድሞቼን አድናቸው” ት. እና ቃ. 45፥3–5

 ስለክርስቶስ አንደኛ ጠበቃነት፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባዬ አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዲህ ብለዋል፥ “በማንኛውም ሰዓትና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በጸሎት በኩል የፀጋ ዙፋንን ለመቅረብ መቻሌ፣ የሰማይ አባቴ አቤቱታዬን መስማቱ፣ ኃጥያት ያልሰራው፣ ደሙ የፈሰሰው፣ ጠበቃዬ የእኔን ችግር መለመኑ፣ ለእኔ በጣም ታላቅ አስፈላጊነት አለው።”2

ከቅዱሳት መጽሐህፍት

ሞዛያ 15፥8–9ሞሮኒ 7፥28ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥5110፥4

ከታሪካችን

በጌታ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሁሉ፣ ሴት ደቀመዛሙርቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ተከትለዋል። አስቴር ታማኝ እና ብርቱ ጠበቃ ነበረች። የአጎቷ ልጅ ማርዶክዮስ አይሁዶች እንዲጠፉ ዘንድ የሚያዝ የንጉሱን የአዋጅ ጽሕፈት ቅጅ ላከላትና “ለሕዝቧ በ[ንጉሡ] ፊት ጥያቄ እንድታቀርብ” አዘዛት። ጨመረ፥ “ደግሞስ ወደ መንግስት የመጣሽው እንደዚህ ላለ ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?” አስቴር 4፥8፣ 14

ለሕዝቧ ጠበቃ መሆን አደጋ ቢኖረውም፣ አስቴር ተስማማች፥ “ምንም እንኳን ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ ብጠፋም፣ እጠፋለሁ።” አስቴር 4፥16).

እናም አስቴር ከንጉሡ ጋር በትህትና ተናገረች “በእግሩም ላይ ወድቃ እያለቀሰች …በአይሁድ ላይ የተተነኰለውን ተንኰል ይሽር ዘንድ ለመነችው። ጨምራም፥ “የዘመዶቼን ጥፋት አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ? (አስቴር 8፥3፣ 5 ተመልከቱ)። የንጉሡ ልብ ሳሳ እናም አቤቱታዋን ሰጣት።3

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Jesus Christ—Our Master and More” (Brigham Young University fireside, የካቲት. 2፣ 1992)፣ 4፤ speeches.byu.edu

  2. ዲ ቶድ ክርስቶፈርሰን “I Know in Whom I Have Trusted” Ensign,ግንቦት 1993፣ 83.

  3. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 51 ተመልከቱ።

ይህንን ተገንዘቡ

የኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃነት ለሌሎች ምሕረትን እና ይቅር ባይነትን እንዴት መዘርጋት እንድንችል ያነሳሳናል?