2014 (እ.አ.አ)
እንደገና አገለገልኩኝ
ሴፕቴምበር 2014


ወጣቶች

እንደገና አገለገልኩኝ

ደራሲዋ በሪዮ ግራንድ ዶ ኖርቴ፣ በራዚል ነዋሪ ነች።

አንድ ቀን፣ የአገልግሎት የስራ ዕቅድ ከጨረስኩ በኋላ የስብሰባ አዳራሻችንን አልፌ እየሄድኩኝ ነበር እና ሁለት እህቶች ህንፃውን ሲያፀዱ አየሁ። ቃሎቼ ዝም ብለው ወጡ፥ “እህቶች እርዳታ ትፈልጋላችሁ?” አንዷ ፈገግ አለች እና ልክ በሰአቱ እንደደረስኩኝ ተናገረች ምክንያቱም እነርሱ ብቻ ነበሩ ሲያፀዱ የነበሩት እናም በጣም ደክሟቸው ነበር። ጌታ የሚያግዝ ሰው እንዲልክ በጸሎት እንደጠየቀች ተናገረች። ለፀሎቷ መልስ ስለሆንኩኝ በጣም ደስተኛ ነበርኩ። ለሌላ ሰው አገልግሎት ሰጥቼ ጨርሼ እኔም ደክሞኝ ነበር፣ ነገር ግን ልቤን ተከተልኩት እና የበለጠ ለማገልገል እራሴን ሰጠሁ።

በደስታ መስራት ትዕዛዝ ነው (ት. እና ቃ. 24፥7ተመልከቱ)። በሁሉም ሰአት ለማገልገል ፍላጎቱ ሲኖረን፣ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ታምራቶች እንዲከሰቱ መርዳት እንችላለን። ስናገለግል ህይወታችን የበለጠ ትርጉም ያለው ይሆናል። ጌታ በእርግጥ ይወደናል፣ እያንዳንዱን ልጆቹን ይረዳል እና እንድናገለግል ጥንካሬ ይሰጠናል።