2014 (እ.አ.አ)
የጸሎት ሳንድዊች
ኦክተውበር 2014


ልጆች

የጸሎት ሳንድዊች

ስትፀልዩ ምን እንደምትሉ እንዴት ታውቃላችሁ? ጸሎታችሁን “ውድ የሰማይ አባት ሆይ” በማለት ትጀምራላችሁ እናም “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን” በማለት ትፈጽማላችሁ። በሳንድዊች መካከል ምን እንደሚገባ እንደምትመርጡት፣ በመሀከል የምትሉት የእናንተ ምርጫ ነው።

የሳንድዊች ስዕል ሳሉ፣ በሳንድዊቻችሁ ውስጥ እንዲኖር የምትፈልጉትን የተለያዩ ነገሮች ምረጡ። በዳቦው መካከል በሚገቡት በእያንዳንዱ ስጋ ወይም ተጨማሪ ላይ ለመጸለይ ስለምትፈልጉበት አንድ ነገር ጻፉ። ለበረከቶች፣ “አመሰግናለሁ” ማለት ትችላላችሁ፣ ስለጭንቀታችሁ ተናገሩ፣ ለበረከቶች ጠይቁ፣ ወይም ስለጥያቄዎች ፀልዩ።

የሳንድዊች ስዕላችሁን ቆርጣችሁ ማውጣት ትችላላችሁ። በጸሎቶቻችሁ ምን አይነት ነገሮችን ማለት እንደምትችሉ ለማስታወስ እንዲረዳችሁ በክፍላችሁ ውስጥ ስቀሉት።