2014 (እ.አ.አ)
የእምነት ጸሎት
ኦክተውበር 2014


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2014 (እ.ኤ.አ)

የእምነት ጸሎት

ምስል
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ

ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ከምንናገራቸው ቃላት በላይ ነው። ይህም በእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል ያለ የሁለት መንገድ ግንኙነት ነው።

ጸሎት እንደሚገባው ሲሰራ፣ የልባችንን ስሜት በቀላል ቃላት እንገልጻለን። የሰማይ አባት በአብዛኛው ከስሜት ጋር የሚመጡ ሀሳባትን በአዕምሮአችን በመ ክተት መልስ ይሰጣል። መልሱ ምንም ቢሆን እና መቼም ቢመጣም፣ ለእርሱ ታዛዥ ለመሆን በመወሰን የምናቀርበውን የልብ ጸሎት ሁልጊዜም ይሰማል።

ጌታ መፅሐፈ ሞርሞንን ለሚያነቡ እና ስለዚህ ለሚጸልዩ ይህን ቃል ኪዳን ይገባል።

“እናም እነዚህንም ነገሮች በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እነዚህ ነገሮች ሀሰት እንደሆኑ ዘለዓለማዊ አብ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም እንድትጠይቁት እመክራችኋለሁ፤ እናም በቅን ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ፍላጎት፣ በክርስቶስ አምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እውነቱን ይገልፅላችኋል።

“እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሁሉንም ነገር እውነታ ታውቁታላችሁ።”(ሞሮኒ 10፥4–5)።

ያም ቃል ኪዳን የተረጋገጠ ነው። ህይወታቸውን በስኬት እና በሚቆይ ደስታ የሚሞላው በረከትን በመቀበል ያን አስደናቂ ቃል ኪዳን የፈተኑ እና ያረጋገጡ ብዙ ሚልዮን ህዝቦች አሉ። ያም ቃል ኪዳን ለእኛ እግዚአብሔር ያለውን አስተያየት እና ፈቃድ ለማወቅ ለምንጸልይበት በሙሉ የሚሆን ነው። መመሪያ እንዲሰጠን ስልጣን ካለው ከእግዚአብሔር አገልጋይ ምክር ስንቀበል ይህንንም ለመጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ፣ በአጠቃላይ ጉባኤ ስብከትን ባዳመጥንበት ጊዜም በዚህ ልንመካ እንችላለን። በህያው ነቢይ በኩል በእግዚአብሔር ከተጠሩት ትሁት ሚስዮኖች ትምህርት ስንቀበልም ይህን ለመጠቀም እንችላለን። ከኤጲስ ቆጶሳችን ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዘደንታችን ምክር ስንቀበልም ይህን ለመጠቀም እንችላለን።

ጸሎት በህይወታችን ውስጥ እንዲሰራ፣ ደንቦቹ ቀላል ናቸው። እውነት ምን እንደሆነ ለማወቅ ወደ አብ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመጸለይ መጠየቅ አለብን። በቅን ልብ መጠየቅም አለብን፣ ይህም ማለት የእግዚአብሔር መልስ እንድናደርግ የሚያስፈልገንን ማንኛውን ለማድረግ እውነተኛ እቅድ ሊኖረን ይገባናል። እውነተኛው ቅንነታችን መምጣት ያለበት በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት ነው።

ከመጠመቁ እና ማረጋገጫ ከመቀበሉ በፊት መጽሐፈ ሞርሞንን የሚያነበው መርማሪ መጽሐፉ እውነት እንደሆነ ማረጋገጫና ዮሴፍ ስሚዝ በእግዚአብሔር ሀይል አማካኝነት እንደተረጎመው ምስክርነትን ያገኛል። እንደ ቤተክርስቲያኗ አባል ማረጋገጫ ከተቀበልን በኋላ፣ ሌሎች እውነቶችን እንዲያረጋግጥልን መንፈስ ቅዱስን እንደ ቅርብ ጓደኛ ለማግኘት እንችላለን። ከዚያም፣ በእምነት በምንጸልይበት ጊዜ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ እግዚአብሔር አብ ህያው እንደሆነ፣ እና እነርሱ እኛን እንደሚወዱን እና የሰማይ አባት ልጆችን በሙሉ እንደሚወድ መንፈስ ቅዱስ እንደሚመሰክርልን መጠበቅ እንችላለን።

መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ምስክር ሲሰጠን በልባችን ልግስና ይኖራል የሚለው የተስፋ ቃል በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኝበት ያም አንድ ምክንያት ነው፥ “ሰው የዋህ እናም በልቡ የሚራራ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ከሆነ እርሱ ልግስና ሊኖረው ይገባዋል” (ሞሮኒ 7፥44)።

በእያንዳንዱ የጾም ሰንበት በመንፈስ ለማደግ ታላቅ እድል አለ። የጾም ሰንበት ላማናውያንን በሀይል፣ በስልጣን፣ እና በፍቅር ለማስተማር ይችሉ ዘንድ ዘለአለማዊ እውነትን ለማወቅ እንደጸለዩት እና እንደጾሙት አልማና የሞዛያ ወንድ ልጆች አይነት አጋጣሚ እንድናገኝ ይረዳናል (አልማ 17፥3፣ 9ተመልከቱ)።

በጾም ሰንበት ጸሎትን እና ጾምን እናገናኛለን። ለድሆች በረከት፣ ያልበላናቸውን ከሁለት የምግብ ጊዜ ዋጋ ጋር እኩል የሚሆኑትን የጾም በኩራትን ለኤጲስ ቆጶስ ወይም ለቅርንጫፍ ፕሬዘደንት በደግነት እንሰጣለን። ሀሳቦቻችንና ፀሎቶቻችን ወደ አዳኛችንና መንፈሳዊ እና ጊዜያዊ ፍላጎታቸውን እንድናገለግላቸው ወደሚፈልገው ሰዎች ይዞራል።

ስንጾም እና በተጨማሪ የዋህ፣ የምንማር፣ እና አፍቃሪ ስንሆን በዚህም ጸሎቶቻችን እና የልብ ፍላጎታችን ወደ አዳኝ ፀሎቶች እና ፍላጎቶች እየቀረቡ ይመጣሉ። እርሱም እንዳደረገው፣ አብ ለእኛ ያለውን ፈቃድ ለማወቅ እና ይህንንም ለማድረግ እንጸልያለን።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘደንት አይሪንግ ጸሎት እና ጾም “ዘለአለማዊ እውነት እንድናውቅ’ እንደሚረዱን አስተምረዋል። የምትጎበኟቸው ሰዎች ምስክርነት የት መጠናከር እንደሚያስፈልገው አስቡበት እናም በዚህ ርዕስም ትምህርትን አዘጋጁ። ለምሳሌ፣ የምትጎበኙት ሰው የቅርብ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል ከሞተባቸው፣ ስለዘለአለማዊ ቤተሰቦች እና ከሞት በኋላ ስላለው እውነት ለመወያየት አስቡበት። የምትጎበኟቸው ስለጾም መሰረታዊ መርህ ምስክርን እንዲያገኙ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመጾም ሀሳብ ለማቅረብ ትችላላችሁ።