2023 (እ.አ.አ)
ወደ እርሱ ኑ
መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)


“ወደ እርሱ ኑ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)።

ወርኃዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልእክት፣ መጋቢት 2023 (እ.አ.አ)

ወደ እርሱ ኑ

አዳኙ ሸከማችንን በእርሱ ላይ እንድናሳርፍ ይጋብዘናል።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

ምስል በአኒ ሄንሪ ኔደር

ወደ እኔ ኑ

ወንጌሉን በመማር፣ በእርሱ በማመን፣ ንስሀ በመግባት፣ ቃል ኪዳኖችን በመፈጸም እና በመጠበቅ እና የእርሱን ምሳሌ በመከተል ወደ አዳኙ መምጣት እንችላለን።

የጉልበት ሥራ … ከባድ ሸክም

የጉልበት ሥራ እና ከባድ አካላዊ ሸክሞች ሊያደክሙን ይችላሉ፣ ነገር ግን አእምሯዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ የሆኑትም እንዲሁ ሊያደክሙን ይችላሉ። ምንም አይነት ሸክም ብንሸከም አዳኙ ሰላሙን ይሰጠናል።

ቀንበር

ቀንበር እንደ ማረሻ ወይም ጋሪ ያሉ ሸክሞችን አንድ ላይ እንዲጎተቱ ሁለት እንስሳትን በአንድ ላይ የሚያጣምር መሣሪያ ነው። ቀንበሩ ብዙውን ጊዜ ክብደቱን በማከፋፈል በእያንዳንዱ እንስሳ የትከሻ ጉብታ ላይ የሚያርፍ የእንጨት ምሰሶ አለው።

ተማሩ

ትምህርቶቹንና ምሳሌውን በማጥናትና እነርሱን ለመከተል በመሞከር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መማር እንችላለን።

እረፉ

የአዳኙ እረፍት አእምሮአችንን እና መንፈሳችንን የሚያረጋጋው የእርሱ ሰላም ነው። እሱ ዓለማዊ ጭንቀትን እንድናሸንፍ ይረዳናል እናም ድካም ሲሰማን መንፈሳዊ ጥንካሬን ይሰጠናል።

ልዝብ … ቀሊል

የአዳኙን ቀንበር በላያችን መውሰድ ማለት በቃል ኪዳኖች አማካኝነት እራሳችንን ከእርሱ ጋር ማጣመር ማለት ነው። ልባችንን ለእርሱና ለሥራው መስጠት ማለት ነው። ይህን ስናደርግ ሸክሞቻችን ቀላል የሆኑ ያህል ይሰማናል ምክንያቱም እሱ እየረዳን ስለሆነ ነው።