2023 (እ.አ.አ)
ቋሚ አጋራችን
ህዳር 2023 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)

ቋሚ አጋራችን

ከዋናው ጽሁፍ የወጣ አጭር ክፍል።

ምስል
alt text

የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ አጋርነት ያስፈልገናል፣ እናንተም ያስፈልጋችኋል። አሁን፣ እንፈልገዋለን፣ ነገር ግን ለማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ከተሞክሮአችን እናውቃለን። መንፈስን የሚያስከፉ ነገሮችን ሁላችንም በየእለት ተእለት ህይወታችን እናስባለን፣ እንናገራለን፣ እናም እናደርጋለን።

ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለን ሊሰማን ይችላል። ብቸኛ እንደሆንን እንዲሰማን ልንፈተን እንችላለን። …

መንፈስ ቅዱስን መስማት ከባድ ሆኖ ካገኛችሁት፣ ንስሃ መግባት እና ይቅርታን መቀበል የሚያስፈልጋችሁ ነገር ካለ ልታሰላስሉ ትችላላችሁ። ለመንጻት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለማወቅ እናም ይበልጥ ቋሚ ለሆነ የመንፈስ ቅዱስ አጋርነት ብቁ ለመሆን በእምነት መጸለይ ትችላላችሁ።

የመንፈስ ቅዱስን አጋርነት መቀበል የምትፈልጉ ከሆነ፣ ለትክክለኛው ምክንያት ልትፈልጉት ይገባል። አላማዎቻችሁ የጌታ አላማዎች መሆን አለባቸው። ምክንያታችሁ በጣም እራስ ወዳድ ከሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስን ማበረታቻዎች ለማዳመጥ እና ለመስማት ከባድ ሆኖ ታገኙታላችሁ።

ለእኔና ለእናንተ ቁልፉ አዳኙ የሚፈልገውን መፈለግ ነው። ምክንያታችን ንጹህ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መነሳሳት አለበት። …

መንፈስ ቅዱስ ለየኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታማኝ የቃል ኪዳን አባላት ለሆኑት እየተላከ ነው። አሁን፣ ልምዶቻችሁ ልዩ ይሆናሉ፣ መንፈስም ለእናንተ እንዲሁም ለምትወዷቸው እና ለምታገለግሏቸው ራዕይን እንድትቀበሉ ለእናንተ እምነት እና አቅም በሚመጥን በተሻለ መንገድ ይመራል። በራስ መተማመናችሁ እንዲያድግ በሙሉ ልቤ እጸልያለሁ።