ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ግባችን መለወጥ ነው


“ግባችን መለወጥ ነው፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 (እ.አ.አ)]

“ግባችን መለወጥ ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

ምስል
አባት እና ልጆች በግ እየመገቡ

ግባችን መለወጥ ነው

የሁሉም የወንጌል ትምህርት እና የማስተማር አላማ በጥልቅ እንድንለወጥ እና ይበልጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስል እኛን ለመርዳት ነው። በዚህ ምክንያት፣ ወንጌልን በምናጠናበት ጊዜ፣ አዲስ መረጃን ብቻ የምንፈልግ አይደለንም፤ “አዲስ ፍጡር” ለመሆን እንፈልጋለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17)። ይህም ልባችንን፣ አመለካከታችንን፣ ድርጊቶቻችንን፣ እና ተፈጥሮአችንን ለመለወጥ ይረዳ ዘንድ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መታመን ማለት ነው።

ነገር ግን እምነታችንን የሚያጠናክር እና ወደ ተዓምራታዊ ለውጥ የሚመራው የወንጌል ትምህርት በሙሉ በአንድ ጊዜ አይከሰትም። ከመማሪያ ክፍል በላይ ወደ ግለሰብ ልብ እና ቤት ይሰፋል። ወንጌልን ለመረዳት እና ለመኖር የማይቋረጥ፣ የእለት ጥረታችንን ይጠይቃል። እውነተኛ ለውጥ የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ይፈልጋል?

መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ይመራናል እንዲሁም ስለዚያ እውነት ይመሰክራል ( ዮሐንስ 16፥13 ይመልከቱ)። እርሱ አዕምሯችንን ያበራል፣ በፍጥነት እንድንረዳ ያስችለናል እንዲሁም የእውነት ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር በሥሜቶቻችን አማካኝነት መገለጥን እንድንቀበል ይረዳናል። መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ያነጻል። በእውነት የመኖር ፍላጎትን በውስጣችን ያነሳሳል፣ እንዲሁም ይህን የምናደርግባቸውን መንገዶች በጸጥታ ይነግረናል። በእውነትም፣ “መንፈስ ቅዱስ … ሁሉንም ያስተምረናል” (ዮሐንስ 14፥26)።

በእነዚህ ምክንያቶች፣ ወንጌልን ለመኖር፣ ለመማር፣ እና ለማስተማር በምናደርገው ጥረት፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር የመንፈሱን አብሮ መሆን መፈለግ ነው። ይህ ግብ ምርጫዎቻችንን፣ ሀሳባችንን እና ድርጊቶቻችንን መምራት ይገባዋል። የመንፈስን ተጽዕኖ የሚጋብዘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ መፈለግ እና ከእርሱ ተጽዕኖ ከሚያርቁ ነገሮች መሸሽ አለብን—እኛ ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ብቁዎች ለመሆን ከቻልን፣ እንዲሁ ከሰማያዊ አባት እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን ለመኖር ብቁ ለመሆንም እንደምንችል እናውቃለንና።