ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 18–24 ፦ “መንገዱ ይህ ነው።” 2 ኔፊ 31–33


“መጋቢት 18–24 (እ.አ.አ)፦ ‘መንገዱ ይህ ነው።’ 2 ኔፊ 31–33፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 18–24 2 ኔፊ 31–33፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምር

ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን እያስተማረ፣ በጀስትን ኩንዝ

መጋቢት 18–24 ፦ “መንገዱ ይህ ነው”

2 ኔፊ 31–33

ከተመዘገቡት የኔፊ የመጨረሻ ቃላት መካከል፣ “ጌታ እንዲህ አዞኛልና፣ መታዘዝ አለብኝ” (2 ኔፊ 33፥15) የሚለውን መግለጫ እናገኛለን፣። ይህ የኔፊ ህይወት መልካም ማጠቃለያ ነው። የነሃስ ሰሌዳውን ከላባን ለማግኘት ህይወቱን አደጋ ላይ መጣል፣ ጀልባን መገንባት እና ባህርን ማቋረጥ ወይም የክርስቶስን ትምህርት በግልፅ እና በኃይል በአማኝነት ማስተማር ማለት ቢሆንም እንኳን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት ሞከረ፣ በድፍረትም ታዘዘ። “በክርስቶስ ባላችሁ ፅኑነት በመቀጠል” “ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት የሚመራውን ቀጭኑና ጠባቡ ጎዳናን” የመከተልን አስፈላጊነት ኔፊ በአሳማኝነት ሊናገር ይችላል (2 ኔፊ 31፥20፣ 18)፣ ምክንያቱም እሱ የተከተለው መንገድ ያ ነበርና። ይህ መንገድ አንዳንድ ጊዜ ፈታኝ ቢሆንም “ሰው በእግዚአብሔር መንግስት መዳን የሚችልበት ከሰማይ በታች የተሰጠ ሌላ ምንም መንገድም ሆነ ስም [እንደሌለ]” በልምዱ አወቀ (2 ኔፊ 31፥21)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ኔፊ 31

ኢየሱስ ክርስቶስ እና የእርሱ ትምህርት ወደ ዘላለም ህይወት የሚመሩ ብቸኛ መንገዶች ናቸው።

የዘላለም ሕይወት መንገድን በተወሰኑ ቃላት ማጠቃለል ቢኖርባችሁ፣ ምን ትላላችሁ? በ2 ኔፊ 31 ውስጥ ኔፊ እንዴት እንደገለፀው ልብ በሉ። መንገድን መሳል እና በመንገዱ ዳር በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የምታገኙትን መርሆዎች ወይም ደረጃዎች ለመፃፍ አስቡ። ኔፊ ስለ እያንዳንዱ መርህ ያስተማረውን የራሳችሁ ማጠቃለያ በስዕላችሁ ላይ መጨመር ትችላላችሁ።

2 ኔፊ 31፥18–20ን ስታነቡ፣ በወንጌል መንገድ ላይ “በፅኑነት ለመቀጥል” የገዛ ጥረታችሁን ገምግሙ።

በተጨማሪም “በፅኑነት ቀጥሉ ቅዱሳን [Press Forward, Saints]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 81 ይመልከቱ።

ምስል
ቤተሰብ በአንድ ላይ ሲጸልዩ

የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት መከተል ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ይመራናል።

2 ኔፊ 31፥4–13

ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቅ የመታዘዝን ትክክለኛ ምሳሌ አሳይቷል።

ጥምቀታችሁ ትላንትናም ሆነ ከ80 ዓመት በፊት፣ አስፈላጊ ክስተት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብታችኋል። በ2 ኔፊ 31፥4–13 ውስጥ ስለ አዳኙ ጥምቀት ስታነቡ ስለ ጥምቀታችሁ አስቡ። እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን መመለስ ሊረዳ ይችላል፦

  • ክርስቶስ ለምን ነበር የተጠመቀው? ለመጠመቅ ለምን ወሰንኩ?

  • ስጠመቅ የገባሁት ቃል ኪዳን ምንድን ነው? በምላሹ ጌታ ምን ቃል ኪዳን ገባ? (ቁጥሮች 12–13ን፤ በተጨማሪም ሞዛያ 18:10, 13 ይመልከቱ)።

  • ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል አሁንም ቁርጠኛ መሆኔን እንዴት ማሳየት እችላለሁ?

2 ኔፊ 31፥15–20

“እስከመጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል።”

2 ኔፊ 31፥15–20ን ስታነቡ፣ ራሳችሁን የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፣ “እስከ መጨረሻው እንደምጸና እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የሚረዳችሁን ከኔፊ ምን ተማራችሁ?

ሽማግሌ ዴልጂ. ረንለንድ እንዲህ አስተማሩ፦ “እስከ መጨረሻ መፅናት በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ የተነጠለ ደረጃ —የመጀመሪያ አራቱን ደረጃዎች ጨርሰን፣ ጥርሳችንን ነክሰን ለመሞት መጠባበቅ አይደለም። እስከመጨረሻ መጽናት በንቃት እና ሆን ብሎ ደረጃዎቹን መደጋገም ነው” (“የእድሜ ልክ መለወጥ [Lifelong Conversion]” [ብሬገም ያንግ ዩንቭርሲቲ፣ መስከረም 14፣ 2021 እ.አ.አ]፣ 2፣ speeches.byu.edu)። በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ እንዴት ነው ደረጃዎቹን መደጋገም የምትችሉት (እምነት፣ ንስሃ፣ ጥምቀት እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል)?

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 3233፥2

በክርስቶስ ቃላት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብኝ ያሳየኛል።

በህይወታችሁ ውስጥ ስለ ቀጣዩ እርምጃችሁ እርግጠኛ አለመሆን ተሰምቷችሁ ያውቃል? የኔፊ ሰዎች ተመሳሳይ ችግር ነበራቸው (2 ኔፊ 32:1 ይመልከቱ)። በ2 ኔፊ 32፥2–9 ውስጥ መልስ ፈልጉ። ኔፊ ያስተማረውን በራሳችሁ አባባል እንዴት ታስቀምጡታላችሁ? የኔፊ ቃላት እውነት እንደሆኑ ምን ዓይነት ልምዶች አስተማሯችሁ?

የእግዚአብሔርን ምሪት የምትፈልጉበትን የውሳኔዎችን ወይም የሁኔታዎችን (አሁን እና ወደፊት) ዝርዝር ለመፃፍ አስቡ። ከእርሱ መነሳሳትን ለመቀበል ውጤታማ እንድሆኑ የሚረዳችሁን ከ2 ኔፊ 32 ምን መማር ትችላላችሁ? ሰዎች “በቅዱስ መንፈስ ላይ ልባቸውን [እንዲያጠጥሩ]” የሚያደርጋቸው ምንድነው? (2ኛ ኔፊ 33፥2)።

የኔፊን ምክር ስታሰላስሉ፣ የአዳኙን ቃላት እንዴት እንደምታጠኑ አስቡ። እንደ ጥቂት፣ በቂ ወይም ብዙ መብላት ትገልፁታላችሁ? በእናንተ አስተያየት ልዩነቱ ምንድን ነው? ከአዳኙ ቃላት ጋር ያላችሁን ልምድ ብዙ እንደ መመገብ እንዴት እንደምታደርጉ አስቡ። ምናልባት ከጓደኛ ወይም ከቤተሰብ አባል ሃሳቦችን ማግኘት ትችሉ ይሆናል።

የክርስቶስን ቃላት መመገብ የክርስቶስን ቃላት መመገብ፣ ለመነሳሳት መጸለይን፣ ከጥናት በፊት እና በኋላ ጥያቄዎችን መጠየቅን፣ ቃላትን መተርጎምን፣ ማሰላሰልን፣ ማጣቀስን፣ ማስታወሻ መውሰድን፣ የወንጌል እውነቶችን መፈለግን እና ቅዱሳት መጽሐፍትን በህይወታችሁ ላይ መተግበርን ጨምሮ ብዙ መንገዶች አሉት (1 ኔፊ 19፥23 ይመልከቱ)።

መፈንስ ቅዱስ በህይወታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ ጎብኚ ከመሆን ይልቅ ቋሚ ጓደኛ እንዲሆን የምትጋብዙት እንዴት ነው? የዴቪድ ኤ. ቤድናርን የመንፈስ ቅዱስን ጓደኝነት “ቀጣይነት ያለው እውነታ” ለማድረግ የሰጡትን ሶስት ሃሳቦች በ“መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ [Receive the Holy Ghost]” [ሊያሆና፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 94–97] ውስጥ አንብቡ። ይህን ምክር እንዴት ተግባራዊ ታደርጋላችሁ?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “ራዕይ፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍት፤ “የእለት እንጀራ፦ ንድፍ [Daily Bread: Pattern]” (ቪድዮ) በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ይመልከቱ።

2 ኔፊ 33

መፅሐፈ ሞርሞን ሁላችንም በክርስቶስ እንድናምን ያሳምነናል።

2 ኔፊ 33 ውስጥ፣ ኔፊ ጽሁፎቹን ሲያጠቃልል፣ በመጀመሪያ ለምን እየፃፈ እንደነበረ ገለጸ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ምን ምክንያቶችን ታገኛላችሁ? እስካሁን በ1ኛ ኔፊ እና 2ኛ ኔፊ ውስጥ ያነበባችሁት ታሪኮች እና ትምህርቶች ወደኋላ አስታውሱ። በእናንተ እና በክርስቶስ ላይ ባላችሁ እምነት የትኞቹ ይበልጥ ተፅዕኖ አሳደሩ?

በተጨማሪም “ኔፊ የመጨረሻ ምስክትነቱን ጻፈ [Nephi Records His Final Testimony]” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍ ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ማስተማሪያ ሀሳቦች

2 ኔፊ 31፥4–13

ስጠመቅ ኢየሱስ ክርስቶስን እየተከተልኩ ነው።

  • በዚህ ዝርዝር መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ሲጠመቅ የሚያሳይ ምስል አለ። ምናልባት ልጆቻችሁ ስለዚህ ክስተት የሚያውቁትን ለእናንተ ለመንገር ሊጠቀሙት ይችላሉ (በተጨማሪም ማቴዎስ 3፥13–17 ይመልከቱ)። ኢየሱስ እንደ እርሱ እንድንጠመቅ የሚፈልገው ለምንድን ነው? የ2 ኔፊ 31፥4–13ን ክፍል በጋራ ስታነቡ ልጆቻችሁ ምክንያቶችን ማዳመጥ ይችላሉ። በቅርቡ የተጠመቀ/ች ልምዱን/ዷን ቢያካፍል/ብታካፍል ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

2 ኔፊ 31

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ የሰማይ አባት እንዴት እንደምመለስ አስተምሮኛል።

  • 2 ኔፊ 31 ውስጥ ያሉትን ትምህርቶች ልጆች በምናባቸው እንዲመለከቱት ለመርዳት፣ የክርስቶስን ምስል መጨረሻ ላይ በማድረግ መንገድን መሳል ይችላሉ። በዚያ መንገድ ላይ ደረጃዎችን፣ ለምሳሌ በክርስቶስ እምነትን፣ ጸሎትን፣ ጥምቀትን፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እና እስከመጨረሻ መፅናትን የሚወክሉ ምስሎችን እንዲያገኙ ወይም እንዲስሉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። 2 ኔፊ 31፥17–20ን ስታነቡ ምስሎቹ ላይ መጠቆም ይችላሉ።

2 ኔፊ 32፥3–5

የክርስቶስን ቃላት መመገብ እችላለሁ።

  • የክርስቶስን ቃላት “መመገብን” ለማስተማር፣ ልጆች የሚወዱትን ምግብ እንዴት እንደሚመገቡት መተወን ይችላሉ። በ2 ኔፊ 32፥3 ውስጥ ምን መመገብ እንዳለብን ኔፊ ምን አለ? የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ እንዲሁ ከማንበብ በምን ይለያል? ምናልባት ልጆቻችሁ ልዩነቶቹን ሊተውኑ ይችላሉ። ቅዱሳት መጽሐፍትን በመመገባችሁ የተቀበላችሁትን በረከቶች አካፍሉ።

2 ኔፊ 32፥8–9

የሰማይ አባት ሁል ጊዜ እንድጸልይ ይፈልጋል።

  • 2 ኔፊ 32፥8–9ን ካነበባችሁ በኋላ ሰይጣን ለምን እንድንጸልይ እንደማይፈልግ ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋገሩ። እግዚአብሔር “ሁሌ እንድንጸልይ” ለምን ይፈልጋል? ልጆቻችሁ ሊጸልዩ የሚችሉበትን ሁኔታዎች መዘርዘር ወይም ስዕሎችን መሳል ይችላሉ። ከዚያም፣ እንደ “ለመጸለይ አስበሃል ወይ? [Did You Think to Pray?]” አይነት ስለ ጸሎት የሚያስተምር መዝሙርን መዘመር ትችላላችሁ (መዝሙር፣ ቁጥር 40)። በመዝሙሩ ውስጥ ያሉትን አንዳንዶቹን ቃላት በዝርዝራቸው ውስጥ ባሉት መተካት ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ሁሌ ስንጸልይ እንዴት ነው የሚባርከን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
መጥምቁ ዮሀንስ ኢየሱስን ሲያጠምቅ

ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም [To Fulfill All Righteousness]፣ በሊዝ ሌመን ስዊንድል