ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 7–13፦ “እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው።” 3 ኔፊ 17–19


”ጥቅምት 7–13፦ ‘እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው።’ 3 ኔፊ 17-19፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ጥቅምት 7–13 3ኔፊ 17–19፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ምስል
አኢየሱስ ለኔፋውያን ታየ

The Light of His Countenance Did Shine upon Them [የፊቱ ብርሃን በራባቸው]፣ በ ጋሪ ኤል. ካፕ

ጥቅምት 7–13፦ “እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው።”

3 ኔፊ 17–19

ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌሉን እያስተማረ፣ ከሞት በተነሳው አካሉ ላይ ያለውን ምልክት ህዝቡ እንዲያዩ እና እንዲዳሡ እያደረገ እንዲሁም እርሱ የተነገረለት አዳኝ እንደሆነ እየመሰከረ ቀኑን በለጋሥ ምድር በማገልገል አሳልፎ ነበር። አሁን የመመለሻ ጊዜ ነው። “ጊዜዬ ቀርቦአል” አለ (3 ኔፊ 17:1)። ወደ አባቱ የመመለሻው ጊዜ ነበር፤ እንዲሁም ለህዝቡ አስተምሯቸው የነበረውን ማሰላሰል ይችሉ ዘንድ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸውም ያውቅ ነበር። ስለዚህ በቀጣዩ ቀን እንደሚመለስ ቃል ገብቶ ህዝቡን ወደየቤታቸው አሰናበታቸው። ሆኖም ማንም አልሄደም ነበር። ምን እየተሰማቸው እንደነበረ አልተናገሩም ነገር ግን “እርሱ ከእነርሱ ጋር ትንሽ እንዲቆይ” ተስፋ አድርገው እንደነበር ኢየሱስ አውቆ ነበር (3 ኔፊ 17:5)። ሌሎች የሚፈፅማቸው አስፈላጊ ጉዳዮች ነበሩት፤ ሆኖም ለእግዚአብሔር ልጆች ርኅራኄ ማሳየት ሁልጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ትንሽ ቆየ። ከዚያ ተከትሎ የመጣው ምናልባት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከተመዘገቡት ሁሉ የሚልቅ በርኅራሄ የማገልገል ምሳሌ ነው። በቦታው የነበሩት ሰዎች በቃላት ሊገለጽ የማይችል ብለውታል (3 ኔፊ 17:16–17 ይመልከቱ)። ኢየሱስ ራሱ ይህንን ያልታቀደ መንፈሳዊ ፍሰት በእነዚህ ቀላል ሆኖም ኃይለኛ በሆኑ ቃላት አጠቃሏል፦ “አሁን፣ እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው” (3 ኔፊ 17:20)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 1718:24–25, 30–32

አዳኙ የአገልግሎት ፍፁም ምሳሌዬ ነው።

አዳኙ በተገለጠ ጊዜ 2,500 የሚያህሉ ሰዎች በቦታው የነበሩ ቢሆንም ሁሉንም አንድ በአንድ የሚያገለግልበትን መንገድ አግኝቶ ነበር። በ3 ኔፊ 17፤18:24–25, 28–32 ውስጥ ባገለገለበት መንገድ ላይ ምን ታስተውላላችሁ? ለምን ዓይነት ፍላጎቶች አገልግሎት ሰጥቷል? አገልግሎቱን ውጤታማ ያደረጉት ምን ዓይነት ባህርያት ናቸው? እናንተን እንዴት እንደሚያገለግላችሁ ልታስቡም ትችላላችሁ። ምሳሌውን መከተል የምትችሉት እንዴት ነው? (በተጨማሪም 3 ኔፊ 18:24–25 እና 28–32 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም “Jesus Christ Has Compassion and Heals the People” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

3 ኔፊ 17:13–2218:15–2519:6–9፣ 15–36

አዳኙ እንዴት እንደምፀልይ አስተምሮኛል።

አዳኙ ሲጸልይላችሁ መስማት ምን ዓይነት ሥሜት ሊፈጥር እንደሚችል አስቡ። እንዲህ ያለው ተሞክሮ በምትፀልዩበት መንገድ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? 3 ኔፊ 17:13–2218:15–25፤ እና 19:6–9, 15–36 በምታጠኑበት ጊዜ ይህንን አሰላስሉ። ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ እና ትምህርቶች ስለፀሎት ምን ትማራላችሁ? እንዴት፣ መቼ፣ የት፣ ለማን እና ለምን መፀለይ እንደሚገባችሁ ግንዛቤዎችን ለማግኘት መፈለግን አስቡ። ከእነዚህ ጥቅሶች ሌላ ምን ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ?

እንዲሁም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 10፥5 10:5 ይመልከቱ።

3 ኔፊ 18፥1–12

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ቅዱስ ቁርባንን በምወስድበት ጊዜ በመንፈሱ ልሞላ እችላለሁ።

አንድን ነገር ደጋግመን ስናደርገው የተለመደ ወይም ተራ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ሳናስብ እንኳን ልናደርገው እንችላለን። በሳምንታዊው የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት ወቅት ያ እንዳይከሰት ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? 3 ኔፊ 18:1–12፣ ስታነቡ በቅዱስ ቁርባን በምትሳተፉበት በእያንዳንዱ ጊዜ እንዴት በመንፈስ መሞላት እንደምትችሉ አሰላስሉ (በተጨማሪም 3 ኔፊ 20:1–9 ይመልከቱ)። በቁጥር 5–7፣ 11መሠረት፣ “ሁልጊዜ” ማድረግ ያሉባችሁ ነገሮች ምን ምን ናቸው? ኢየሱስ የቅዱስ ቁርባን ሥርዓትን ለምን እንደሰጠን —እንዲሁም ቅዱስ ቁርባኑ የእርሱን ዓላማ በህይወታችሁ እያከናወነ ስለመሆኑ ልታሰላስሉ ትችሉም ይሆናል። ቅዱስ ቁርባን ለእናንተ ቅዱስ የሆነውለምንድን ነው?

ፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ “Always Remember Him” (ሊያሆና፣ የካ. 2018ን(እ.አ.አ)፣ 4–6)፣ በሚለው መልዕክታቸው በየሳምንቱ በቅዱስ ቁርባን ቅዱስ ምልከቶች ስትሳፉ ልታስታውሷቸው ስለምትችሏቸው ነገሮች ሦስት ጥቆማዎችን” ሰጥተዋል። ስለጥቆማዎቹ ምን ጎልቶ ይታያችኋል? በቅዱስ ቁርባን ወቅት እና ሳምንቱን ሙሉ አምልኳችሁን ለማሻሻል ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ይበልጥ ትርጉም ባለው መንገድ ለማምለክ ሌላ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ራሳችሁን እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ልትጠይቁ ትችላላችሁ፦“የአዳኙ መስዋዕት በዕለት ተዕለት ህይወቴ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? “እንደ እርሱ ደቀ መዝሙር በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለሁት በምን ላይ ነው ምን ማሻሻል እችላለሁ?”

በተጨማሪም ማቴዎስ 26:26–28፤ ጄፍሪ አር. ሆላንድ፣ “Behold the Lamb of God,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 44–46፤ “As Now We Take the Sacrament,” መዝሙር፤ ቁ. 169፤ “Jesus Christ Introduces the Sacrament” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ቅዱስ ቁርባን፣” ወንጌል ላይብረሪ።

ለማሰላሰል ጊዜ ፍቀዱ። አንዳንድ ጊዜ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት የማንበብ፣ የመፀለይ እና የማሰላሰል ቅይጥ ይሆናል። እየተማራችሁት ስላላችሁት ነገር በጥልቀት ለማሰብ እና ከእግዚአብሄር ጋር ለመነጋገር የጥሞና ጊዜ ሲኖራችሁ፣ የቃሉን ሀይል በህይወታችሁ መጨመር ትችላላችሁ።

3 ኔፊ 18:22–25

የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን “ከፍ ማድረግ” እችላለሁ።

ከእርሱ ተከታዮች አንዱ መሆንህን እንጂ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምንም የማያውቅ ጓደኛ ነበረህ እንበል። ጓደኛችሁ ከምታደርጉት ነገር ተነሥቶ ስለእርሱ ምን ዓይነት ድምዳሜ ላይ ይደርሳል? “ለዓለም ያበራ ዘንድ ብርሃናችሁን ከፍ አድርጉ” ማለት ለናንተ ምን ማላት ይመስላችኋል? (3 ኔፊ18፥24)። አዳኙ በ3 ኔፊ 18:22-25 ውስጥ ያንን ብርሃን ከፍ እንድታደርጉ የሚረዳችሁ ምን ሌላ ግብዣ አስተላለፈ?

በተጨማሪም ቦኒ ኤች. ኮርደን፣ “That They May See፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 78–95 ይመልከቱ።

3 ኔፊ 18:36–3719:6–22

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይፈልጋሉ።

የቅርብ ጊዜ ፀሎቶቻችሁን አስቡ። ፀሎቶቻችሁ ስለእናንተ ውስጣዊ ፍላጎት ምን ያስተምሯችኋል? አዳኙ ባለበት አንድ ቅእን ካሳለፉ በኋላ ሕዝቡ“ይበልጥ ስለሚፈልጉትም ፀለዩ”— የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ። (3 ኔፊ 19:9)። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ይህን ያህል አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህን ምንባቦች በምታነቡበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ጓደኛችሁ እንዲሆን ያላችሁን የራሳችሁን ፍላጎት አሰላስሉ። ያንን ጓደኝነት በትጋት መፈለግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መፅሄቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

3 ኔፊ 17:7፣ 20–25

አዳኙ እያንዳንዱን የሰማይ አባት ልጆች ይወዳል።

  • ልጆቻችሁ በ3 ኔፊ 17ውስጥ ያለውን ዘገባ በዓይነ ህሊናቸው ማየት ይችሉ ዘንድ በዚህ መዘርዝር ውስጥ እንዳሉት ዓይነት ሥዕል ወይም በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ “Jesus Christ Prays and Angels Minister to the Children” የሚለውን ቪዲዮ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። በ3 ኔፊ 17 ውስጥ ጌታ ለህዝቡ ባለው ፍቅር ላይ አፅንዖት በሚሰጡ (እንደ ቁጥር 7 እና 20–25) ያሉ ሃረጎችን እና ጥቅሶችን ማንበብን አስቡ። ልጆቻችሁ ራሳቸውን ከኢየሱስ ጋር ሆነው የሚያሳይ ሥዕል መሳል ይችላሉ። በሚስሉበት ጊዜ ኢየሱስ ለእነሱ ያለውን ፍቅር ያሳየባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ እርዷቸው።

ምስል
ኢየሱስ ህጻናትን ሲባርክ

Behold Your Little Ones [እነሆ ትናንሾቻችሁ]፣ በጋሪ ኤል. ካፕ

3 ኔፊ 18፥1–12

ቅዱስ ቁርባንን በምወስድበት ጊዜ ስለ ኢየሱስ ማሰብ እችላለሁ።

  • በቅዱስ ቁርባን ወቅት ምን እንደሚከናወን እንዲነግሯችሁ ልጆቻችሁን ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ ። ከዚያም 3 ኔፊ18:1–12 ልታነቡ እና ዛሬ እኛ ከምንሰራው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ሲሰሙ ልጆቻችሁ እጃቸውን እንዲያወጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በቅዱስ ቁርባን ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለምን እንድናስታውስ ወይም እንድናስብ ይፈልጋል? (3 ኔፊ 9:7፣ 11 ይመልከቱ)።

3 ኔፊ 18:15–2419:6–9፣ 15–36

አኢየሱስ እንዴት እንደምንጸልይ አስተምሮኛል።

  • A Child’s Prayer” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 12–13) የመሰሉ መዝሙሮችን አንድ ላይ መዘመር ልጆቻችሁ ለምን እንደምንፀልይ እንዲያስቡ ለመርዳት ጥሩ መንገድ ነው። ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ 3 ኔፊ 18:18–21 ልታነቡ እና ኢየሱስ ስለ ጸሎት ምን እንዳስተማረ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በሚጸልዩበት ጊዜ እንዴት እንደሚሰማቸው እንዲነግሯችሁ መጋበዝ ስለፀሎት ያላቸውን ምስክርነት እንዲያካፍሉ ሊረዳቸው ይችላል።

  • አንዳንድ ውድ የሆኑ የጸሎት በረከቶችን ለማግኘት ፍለጋ ማድረግ ለልጆች የሚያስደስት ሊሆን ይችላል። የሚከተሉትን ጥቅሶች በወረቀት ላይ ልትፅፉ እና ልትደብቋቸው ትችላላችሁ፦ 3 ኔፊ18:153 ኔፊ 18:203 ኔፊ 18:213 ኔፊ 19:9፤ እና 3 ኔፊ 19:23። ከዚያም ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ስለፀሎት ያስተማሯቸውን ነገሮች በመፈለግ ወረቀቶቹን ሊያስሡ እንዲሁም ጥቅሶቹን ሊያነቡ ይችላሉ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
መላዕክት ኢየሱስን እና የኔፋውያንን ልጆች ከበው

Angels Ministered unto Them [መላዕክት አገለገሏቸው፣ በዋልተር ሬን