ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 28–ህዳር 3፦“ [ሁላችሁም] ንሰሃ እንድትገቡ…ለማሳመን እፈልጋለሁ።” ሞርሞን 1–6


“ጥቅምት 28–ህዳር 3፦‘[ሁላችሁም] ንሰሃ እንድትገቡ…ለማሳመን እፈልጋለሁ።’ ሞርሞን 1-6፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ጥቅምት 28–ህዳር 3 ሞርሞን 1-6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ሞርሞን በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ እየፃፈ

Mormon Abridging the Plates [ሞርሞን ሰሌዳዎቹን አሳጥሮ እየፃፈ፣ በቶም ሎቬል

ጥቅምት 28–ህዳር 3፦“ [ሁላችሁም] ንሰሃ እንድትገቡ…ለማሳመን እፈልጋለሁ።”

ሞርሞን 1–6

ሞርሞን በኔፋውያን መካከል ስላያቸው “አሰቃቂ” ክፋቶች እና ርኩሰቶች “ሙሉ ታሪክ” ሰጥቶናል (ሞርሞን 2:185:8)። ሆኖም በሞርሞን 1–6 ውስጥ የመዘገበው ብቻ በአንድ ወቅት ጻድቅ የነበሩ ሰዎች ምን ያህል ሊወድቁ እንደሚችሉ ለማስታወስ በቂ ነው። እንደዚህ ክፋት በተንሰራፋበት ሁኔታ በጣም ቢደክመው ብሎም ተስፋ ቢቆርጥ ማንም ሞርሞንን ሊወቅሰው አይችልም። ሆኖም ባየው እና ባጋጠመው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ታላቅ ምሕረት እንደሆነ እና መቀበል የሚቻለውም በንስሐ መንገድ እንደሆነ ያለውን እምነት ፈጽሞ አላጣም። እንዲሁም፣ ምንም እንኳን የራሱ የሞርሞን ህዝቦች ንስሃ እንዲገቡ ያቀረበላቸውን የተማፅኖ ግብዣዎች ባይቀበሉም የሚያሳምናቸው ብዙ አድማጮች እንደነበሩት ያውቅ ነበር። “እነሆ፣ ለሁሉም ለዓለም እፅፋለሁ” ሲል ተናግሯል። በሌላ አነጋገር ለእናንተ ነው የጻፈው (ሞርሞን 3:17–20 ይመልከቱ)። እናም ዛሬ ለእናንተ ያለው መልዕክት ኔፋውያንን በዘመናቸው ሊያድናቸው ይችል የነበረው ያው መልዕክት ነው፦ “የክርስቶስን ወንጌል ታምኑ ዘንድ… ንሰሃ እንድትገቡና በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ለመቆም እንድትዘጋጁ ነው” ሞርሞን 3:21–22

በተጨማሪም “ ”(ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞርሞን 1–6

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ሌሎች ሰዎች ምንም ነገር ቢያደርጉ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል እችላለሁ።

ሞርሞን ዕድሜው ገና 10 ዓመት ገደማ እያለ በዙሪያው ካሉ ሰዎች በሚያስደንቅ ሁኔታ የተለየ ነበር። ሞርሞን 1–6ን በምታነቡበት ጊዜ ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለው እምነት እርሱን ልዩ ያደረገበትን እንዲሁም ሌሎችን እንዲያገለግል እና እንዲባርክ እድሎችን የሰጠባቸውን መንገዶች ፈልጉ። ለማስጀመሪያ ያህል የሚሆኑ ጥቂት ጥቅሶች ቀጥሎ ቀርበዋል፦

ሞርሞን 1:2–3፣ 13–17በሞርሞን እና በሕዝቡ መካከል ምን ልዩነቶች ታያላችሁ? እንዲህ ባለ አስቸጋሪ ጊዜ በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ የረዱት ምን ባሕርያት ነበሩት?

ሞርሞን 2:18–19ሞርሞን ይኖርበት የነበረውን ዓለም ለመግለፅ ምን ቃላትን ተጠቅሟል። የአካባቢው ሁኔታ ባይፈቅድለትም ተስፋውን ይዞ የቆየው እንዴት ነው?

ሞርሞን 3፥12በዙሪያው ስለነበሩት ሰዎች ሞርሞን ምን ተሰማው? እርሱ የነበረውን ዓይነት ፍቅር ለማዳበር ምን ማድረግ ትችላላችሁ።

ሞርሞን 1–6 ውስጥ የሚገኙ ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት የሚያጎሉ ሌሎች ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? ታማኝ ሆኖ ለመቆየት በመፈለጉ ምን ዓይነት ዕድሎች ተሰጡት?

የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ጎልተው እንዲወጡ ወይም እንዲለዩ አስፈላጊ የሆነባቸውን ምክንያቶች እየፈለጋችሁ “Be an Example and a Light” (ሊያሆና፣ ሕዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 86–88)፣ የሚለውን የፕሬዚዳንት ቶማስ ኤስ.ሞንሰንን መልዕክት ማጥናትን አስቡ። እንደነዚህ ያሉትን ዓረፍተ ነገሮች እንዴት ታሟላላችሁ? “ [እርሱ ወይም እርስዋ] ለእኔ ምሳሌ ነበር/ች ። ይህ እንድፈልግ ረድቶኛል

ሞርሞን የእርሱ ምሳሌ በህዝቡ ላይ ለውጥ እያመጣ እንዳልሆነ ሊሰማው ይችል ነበር። ከሞርሞን ጋር ለመነጋገር እድል ቢኖራችሁ ኖሮ የእርሱ ምሳሌ በእናንተ ላይ ስላመጣው ለውጥ ምን ትነግሩት ነበር?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “Quick to Observe፣” ኤንዛይን ታህሳ. 2006 (እ.አ.አ)፤ 30–36፣ ወይም ሊያሆና፣ ታህሳ. 2006 (እ.አ.አ)፣ 14–20፤ “Something Different about Us: Example” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “Living the Gospel of Jesus Christ,” ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ሌሎች የተማሩትን እንዲያካፍሉ እርዷቸው። ሰዎች የተማሩትን ነገር በሚያካፍሉበት ጊዜ የራሳቸውን እና የሌሎችን እምነት ያጠናክራሉ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88:122 ይመልከቱ)። ቤተሰባችሁ እና የክፍል ተማሪዎች የእግዚአብሄርን ቃል እያጠኑ በነበረበት ጊዜ ምን ዓይነት ተሞክሮዎች እንደነበሯቸው ለመጠየቅ ሞክሩ።

ምስል
ኔፋውያን እና ላማናውያን እየተዋጉ

Battle[ጦርነት፣ በጆርጅ ኮኮ

ሞርሞን 2:10–15

እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሃዘን ወደ ክርስቶስ እና ወደ ዘላቂ ለውጥ ይመራኛል።

ሞርሞን የህዝቡን ሃዘን በተመለከተጊዜ ንሥሐ እንደሚገቡተስፋ አደረገ። ሆኖም ሀዘናቸው ለንሥሐ አልነበረም (ሞርሞን 2:13)—እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሃዘን ሳይሆን ዓለማዊ ሃዘን ነበር። ልዩነቱን ለመገንዘብ በሞርሞን 2:10–15 ውስጥ የምትማሩትን በሚከተለው ዓይነት ቻርት መመዝገብን አስቡ።

እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሃዘን

ዓለማዊ ሃዘን

ወደ ኢየሱስ ይመጣል (ቁጥር 14)

እግዚአብሄርን ይሰድባል (ቁጥር 14)

ሃዘናችሁ ከእግዚአብሄር ፈቃድ የሆነ ይሁን ዓለማዊ እንዴት ታውቃላችሁ? ዓለማዊ ሃዘን እየተሰማችሁ ከሆነ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ወደ ሆነ ሃዘን የምትለውጡት እንዴት ነው?

በተጨማሪም 2 ቆሮንቶስ 7:8–11፤ ሚሼል ዲ. ክሬግ፣ “Divine Discontent,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2018(እ.አ.አ)፣ 52–55።

ሞርሞን 3፥3፣ 9

“ጌታ እንዳዳናቸው አልተረዱም [ነበር]።”

ኔፋውያን፣ ጌታ እነርሱን የባረከባቸውን መንገዶች እውነታ እንዳልተቀበሉ ሞርሞን ተመልክቷል። በሞርሞን 3:3, 9 በምታነቡበት ጊዜ እግዚአብሄር በህይወታችሁ ውስጥ ያሳደረውን ተፅእኖ እውነታ እንዴት እየተቀበላችሁ እንደሆነ ልታሰላስሉ ትችሉ ይሆናል። የእርሱን ተፅዕኖ እውነታ ስትቀበሉ ምን በረከቶች ይመጣሉ? የእርሱን ተፅእኖ ያለመቀበል ውጤቶች ምንድን ናቸው? (ሞርሞን 2:26ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59:21 ይመልከቱ)።

በተጨማሪም ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “O Remember, Remember,” ሊያሆና፣ህዳር 2007 (እ.አ.አ)፣ 66–69 ይመልከቱ።

ሞርሞን 5:8–246:16–22

ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ለመቀበል እጆቹን ከፍቶ ይቆማል።

በኃጢአታችሁ ምክንያት ተስፋ የቆረጣችሁ ከሆነ አዳኙ “አናንተን ለመቀበል እጆቹን ከፍቶ ስለመቆሙ” ሞርሞን የሰጠው መግለጫ ማረጋገጫ ሊሰጥ ይችላል። ሞርሞን 5:8–24 እና 6:16–22፣ ስታነቡ ኃጢአት ብትሰሩም እንኳን የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ለእናንተ ስላላቸው ስሜት ምን ትማራላችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እጆቹን ከፍቶ ከእናንተ ጋር ስለሚገናኝ እንዴት ተሰማችሁ? በውጤቱ ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም “Come unto Jesus,” መዝሙር፣ ቁጥር. 117።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞርሞን 1:1–32:1፣ 23–243:1–3፣ 12፣ 17–22

እንደ ሞርሞን ኢየሱስ ክርስቶስን እከተላለሁ።

  • ሞርሞን በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት ሲያዳብር በጣም ወጣት ስለነበር በልጆቻችሁ ላይ መነሳሳትን ሊፈጥር ይችላል። ምናልባት ሞርሞን 1:1–3ን ከልጆቻችሁ ጋር ልታነቡና አማሮን ልዩ ተልእኮ በሰጠው ጊዜ ሞርሞን ዕድሜው ስንት እንደነበረ ልጆቻችሁ ማዳመጥ ይችላሉ።። አማሮን በሞርሞን ውስጥ ያያቸውን ባህርያት በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዲፈልጉ ልትረዷቸውም ትችላላችሁ። እነዚህ ባህርያት ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተል የሚረዱን እንዴት ነው?

    ምስል
    ሞርሞን ልጅ እያለ

    Mormon, Age 10 [ሞርሞን፣ ዕድሜ10፣ በስኮት ኤም. ስኖው

  • ሞርሞን ኢየሱስን በመከተሉ ምክንያት ሌሎችን የማገልገል እና የመባረክ ዕድሎች ተሰጥተውት ነበር። ልጆቻችሁ ከሚከተሉት ምንባቦች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ እንዲያነቡ ልትጋብዟቸውና ስለሞርሞን የተማሩትን እንዲያካፍሉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ ሞርሞን 1:1–3፣, 2:1፣ 23–24፤ እና 3:1–3፣ 12፣ 20–22 (በተጨማሪም “Chapter 49: Mormon and His Teachings,” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 138–42)። ኢየሱስ ክርስቶስን የተከተለው እንዴት ነበር? በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እምነት ሌሎችን የረዳው ወይም የባረከው እንዴት ነው? እምነታችን የምናውቃቸውን ሠዎች ሊረዳ የሚችለው እንዴት ነው?

ሞርሞን 2:8–15

እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሃዘን ወደ ክርስቶስ እና ወደ ዘላቂ ለውጥ ይመራኛል።

  • ልጆቻችሁ ሞርሞን 2:8, 10–15 በሚያነቡበት ጊዜ በዓለማዊ እና እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ በሆን ሃዘን መካከል ስላለው ልዩነት እንዲገነዘቡ ለመርዳት ምናልባት “በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች” ውስጥ እንዳለው ዓይነት ቻርተ ልትሰሩ ትችላላችሁ። ንሥሐ “ልባችን…ሐሴት እንድታደርግ የሚያደርግባቸውን ምክንያቶች ለማግኘት ሞርሞን 2:12 ውስጥ መፈለግም ይችላሉ። በኃጢአታችን ምክንያት የሚሰማን ሀዘን እንለወጥ ዘንድ የአምላክን እርዳታ ወደመሻት እንደሚመራን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ሞርሞን 3፥3፣ 9

የሰማይ አባት ብዙ በረከቶችን ይሠጠኛል።

  • ልጆቻችሁ አመስጋኝ የሆኑባቸውን አንዳንድ ነገሮች እንዲዘረዝሩ(ወይም እንዲስሉ) መጋበዝ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ እንዲሆኑ ለመርዳት ጥሩ መንገድ ሊሆን ይችላል። ዝርዝሩን ካዘጋጁ በኋላ ሞርሞን 3:3፣ 9 ልታነቡና የሰማይ አባት ኔፋውያንንም እንደባረካቸው ሆኖም ያንን አምነው እንዳልተቀበሉ ልታብራሩ ትችላላችሁ። ለበረከቶቻችን አመስጋኝ እንደሆንን ለሰማይ አባት ለማሳየት ምን ልናደርግ እንችላለን?

ሞርሞን 3፥12

የሰማይ አባት ሁሉንም እንድወድ ይፈልጋል።

  • ኔፋውያን ክፉዎች የነበሩ ቢሆንም ሞርሞን እነርሱን ከመውደድ ወደኋል አላለም። ልጆቻችሁ በሞርሞን 3፥12 ውስጥ “መውደድ” እና “ፍቅር” የሚሉትን ቃላት እንዲፈልጉ እርዷቸው። ሌሎችን ስለመውደድ የሚናገር እንደ “Jesus Said Love Everyone” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣61) አይነት መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። እግዚአብሄር ለልጆቹ ሁሉ ስላለው ፍቅር መስክሩ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
የወርቅ ሰሌዳዎች

መፅሐፈ ሞርሞን የተፃፈው “የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ታምኑ ዘንድ” ነው (ሞርሞን 3:21)።