ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
አባሪ ሐ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች


“አባሪ መ፦ የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች”ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ፦መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ መ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

ምስል
ልጆች እና አስተማሪ እየዘመሩ

አባሪ ሐ

ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች

የመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ልጆቻችሁ ስለ ሰማይ አባት የደስታ እቅድ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መሰረታዊ እውነቶችን እንዲማሩ ለመርዳት ሃይለኛ መሳሪያዎች ናቸው። ልጆች ስለ ወንጌል መርሆዎች ሲዘምሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ እውነትነታቸው ይመሰክራል። ቃላቱ እና ሙዚቃው በልጆቹ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ በመላ ህይወታቸው ይቀመጣል።

ወንጌልን በሙዚቃ አማካኝነት ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ የመንፈስን መመሪያ እሹ። ስለምትዘምሯቸው እውነቶች ያላችሁን ምስክርነት አካፍሉ። ልጆቹ፣ ሙዚቃው በቤት እና በመጀመሪያ ክፍሎች ውስጥ ከሚማሩት እና ከሚያጋጥሟቸው ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲመለከቱ እርዷቸው።

በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ለሚቀርብ ፕሮግራም መመሪያዎች

በኤጲስ ቆጶሱ አመራር፣ ልጆች በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ የሚያቀርቡት ፕሮግራም በተለምዶ በአመቱ ውስጥ በአራተኛው ሩብ አመት ነው። እንደ የመጀመሪያ ክፍል አመራር እና የሙዚቃ መሪ ዝግጅቱን ለማቀድ የመጀመሪያ ክፍልን በበላይነት ከሚቆጣጠረው የኤጲስ ቆጶስ አማካሪ ጋር አብራችሁ ስሩ።

ፕሮግራሙ ልጆቹ እና ቤተሰቦቻቸው በዓመቱ ውስጥ የዘመሯቸውን የመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮችን ጨምሮ በቤት እና በመጀመሪያ ክፍል ከመፅሐፈ ሞርሞን የተማሩትን እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ መሆን አለበት። ዝግጅቱን ስታቅዱ ተሰብሳቢዎቹ በአዳኙ እና በትምህርቶቹ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ሊረዳ ስለሚችልባቸው መንገዶች አስቡ።

ክፍሎቹ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆችን የያዙ ከሆነ የቤተሰብ አባላት ከልጆቻቸው ጋር መሳተፍ የሚችሉባቸውን መንገዶች ሊያስቡ ይችላሉ። አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ስብሰባውን አጠር ባለ ንግግር ሊያጠናቅቅ ይችላል።

ፕሮግራሙን ለማቅረብ ስትዘጋጁ፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች አስታውሱ፥

  • በልምምዶች ጊዜ ከመጀመሪያ ክፍል ወይም ከወላጆቻቸው ርቀው የሚቆዩበት አላስፈላጊ ጊዜ መኖር የለበትም።

  • የእይታ ማስተማሪያዎችን፣ አልባሳትን፣ እና ሚዲያዎችን በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ላይ መጠቀም ትክክል አይደለም።

አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ 12.2.1.2ይመልከቱ።

የመዝሙር ጊዜ መመሪያዎች

አምስት ደቂቃ (የመጀመሪያ ክፍል አመራር)፦ መክፈቻ መዝሙር፣ ቀዱሳት መጻህፍት ወይም የዕምነት አንቀጾች እና አንድ ንግግር

20 ደቂቃ(የሙዚቃ መሪ)፦ የመዝሙር ጊዜ

የመጀመሪያ አመራር እና የሙዚቃ መሪው፣ ልጆች በትምህርት ክፍል እና በቤት እየተማሯቸው ያሉትን መርሆዎች ለማጠናከር የሚረዱ ለያንዳንዱ ወር የሚሆኑ መዝሙሮችን ይመርጣሉ። እነዚህን መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ዝርዝር በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካተዋል።

መዝሙሮችን ለልጆቹ በምታስተምሩበት ጊዜ፣ መዝሙሮቹ ስለሚያስተምሯቸው ታሪኮች እና ትምህርታዊ መርሆዎች የተማሩትን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። በመዝሙሮቹ ውስጥ ስለሚገኙት እውነቶች ያላቸውን ሃሳቦች እና ስሜቶች እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ መዝሙርን በተመለከተ መሰረታዊ ግብአት ነው። በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች እና በጓደኛ ውስጥ ያሉ ሙዚቃዎች ተገቢ ናቸው። ማንኛውንም ሌላ ሙዚቃ በመጀመሪያ ክፍል ለመጠቀም ከአኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ፈቃድ መገኘት አለበት( አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፣ 12.3.4)።

ምስል
ልጆች እየዘመሩ

የመዝሙር ጊዜ የሚሆን ሙዚቃ

ጥር

  • የመጽሃፈ ሞርሞን ታሪኮች,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 118–19

  • Keep the Commandments,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 146–47

  • The Iron Rod፣” መዝሙር፣ ቁጥር 274

የካቲት

  • Nephi’s Courage,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 120-21

  • I Feel My Savior’s Love,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75

  • Choose the Right,” መዝሙር፣ ቁ. 239

መጋቢት

  • I Love to See the Temple,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 95

  • When I Am Baptized,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 103

  • Easter Hosanna,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 68–69

ሚያዝያ

  • A Child’s Prayer,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 12–13

  • Have I Done Any Good?,” መዝሙር፣ ቁ. 223

ግንቦት

  • Love One Another,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 136–37

  • I Will Be Valiant,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 162

  • Help Me, Dear Father,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 99

ሰኔ

  • Testimony,” መዝሙር፣ ቁጥር. 137

  • We’ll Bring the World His Truth,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 172–73

  • Keep the Commandments,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 110-11

ሐምሌ

  • I Want to Be a Missionary Now,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 168

  • My Heavenly Father Loves Me,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29

  • Faith,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 96–97

ነሐሴ

  • As I Search the Holy Scriptures,” መዝሙር፣ ቁ. 277

  • Home Can Be a Heaven on Earth,” መዝሙር፣ ቁ. 298

መስከረም

  • The Still Small Voice,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 106–7

  • Samuel Tells of the Baby Jesus,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 36

  • I’m Trying to Be like Jesus,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79

ጥቅምት

  • Families Can Be Together Forever,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 188

  • The Church of Jesus Christ,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 77

ህዳር

  • Dare to Do Right,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 158

  • I Believe in Christ,” መዝሙር፣ ቁ. 134

ታህሳስ

  • Search, Ponder, and Pray,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 109

  • Away in a Manger,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 42–43

  • He Sent His Son,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 34–35

ትምህርቶችን ለማስተማር ሙዚቃን መጠቀም

የመዝሙር ጊዜ ልጆች የወንጌልን እውነት እንዲማሩ ለመርዳት የታሰበ ነው። በመዝሙሮች እና በመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ውስጥ የሚገኙትን የወንጌል መርሆዎች ለማስተማር የሚያስችሉ መንገዶችን ስታቅዱ የሚከተሉት ሀሳቦች ሊያነሳሷችሁ ይችላሉ።

ተያያዥ ቅዱሳት መጻህፍትን አንብቡ።የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ እና በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ለሚገኙ መዝሙሮችተያያዥ የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችተዘርዝረዋል። እነዚህን አንዳንድ ምዕራፎች እንዲያነቡ እርዷቸው እንዲሁም ቅዱሳት መጻህፍቱ ከመዝሙሮቹ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ተናገሩ። ጥቂት የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችን በሰሌዳው ላይ ልትዘረዝሩ እና ልጆቹ እያንዳንዱን ማጣቀሻ ከአንድ መዝሙር ወይም ከመዝሙሩ አንድ ሥንኝ ጋር እንዲያዛምዱ መጋበዝ ትችላላችሁ።

ባዶውን ቦታ ሙሉ። ብዙ ቁልፍ ቃላት የጎደሉትን የመዝሙሩን አንድ ሥንኝ በሰሌዳው ላይ ጻፉ። ከዚያም ልጆቹን፣ በባዶው ቦታ ውስጥ የሚሞሉትን ቃላት እያዳመጡ መዝሙሩን እንዲዘምሩ ጠይቋቸው። እያንዳንዱን ባዶ ቦታ በሚሞሉበት ጊዜ ከጎደሉት ቃላት ምን ዓይነት የወንጌል መርሆዎችን እንደምትማሩ ተወያዩ።

ምስል
የመዝሙር ጊዜ መሪ

መስክሩ በመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ውስጥ ስለሚገኙ የወንጌል እውነቶች ለልጆቹ አጭር ምስክርነት ስጡ። መዘመር መስክርነት የሚሰጡበት እና መንፈሱ እንዲሰማቸው የሚያደርግ አንድ መንገድ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ልጆቹን እርዷቸው።

ምስክር ሆናችሁ ቁሙ ልጆች በየተራ በመቆም እየዘመሩት ካለው መዝሙር ምን እንደተማሩ ወይም መዝሙሩ ስለሚያስተምረው እውነት እንዴት እንደሚሰማቸው እንዲያካፍሉ ጋብዙ። መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ እንዴት እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ እንዲለዩ እርዷቸው ።

ሥዕሎችን ተጠቀሙ። በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ጠቃሚ ቃላት ወይም ሀረጎች ጋር የሚሄዱ ምስሎችን በመፈለግ ወይም በመፍጠር እንዲረዷችሁ ልጆቹን ጠይቋቸው። ሥዕሎቹ ከመዝሙሩ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እና መዝሙሩ ምን እንደሚያስተምር እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ለምሳሌ “The Iron Rod” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 274)፣ የሚለውን መዝሙር እያስተማራችሁ ከሆነ (እንደ iron rodword of Godguidetemptation፣ እና heaven) በመሳሰሉ መዝሙሮች ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ቃላትን የሚያሳዩ ምስሎችን በክፍሉ የተለያዩ ቦታዎች ወይም በወንበሮች ስር ማስቀመጥ ትችላላችሁ። መዝሙሩን በጋራ በምትዘምሩበት ጊዜ ልጆቹ ሥዕሎቹን እንዲሰበስቡ እና በትክክለኛው ቅደም ተከተል እንዲያቆሟቸው ጠይቋቸው።

ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን አካፍሉ። ስለመዝሙሩ ውይይት ለማነሳሳት ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገር መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ “Faith” (Children’s Songbook፣ 96–97) የሚለው መዝሙር ስለትንሽ ዘር ይጠቅሳል። ለልጆቹ አንድ ዘር ልታሳዩዋቸውና ዘር በምንዘራበት ጊዜ እምነት እንዴት እንደምናሳይ መናገር ትችላላችሁ፤ ይህ በመዝሙሩ ውስጥ እንደተገለጸው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዳለን ስለምናሳይባቸው መንገዶች ወደ መወያየት ሊመራ ይችላል።

የግል ተሞክሮዎችን ማካፈልን ጋብዙ። ልጆቹ መዝሙሩ የሚያስተምራቸውን መርሆዎች በእነዚህ መርሆዎች ላይ ካላቸው ተሞክሮዎች ጋር እንዲያዛምዱ እርዷቸው። ለምሳሌ “I Love to See the Temple” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 95) የሚለውን መዝሙር ከመዘመራችሁ በፊት ልጆቹ ቤተመቅደስ አይተው የሚያውቁ ከሆነ እጃቸውን እንዲያወጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በሚዘምሩበት ጊዜ ቤተመቅደስን ሲያዩ ምን እንደሚሰማቸው እንዲያስቡ ጋብዟቸው።

ጥያቄዎችን ጠይቁ። መዝሙሮችን በምትዘምሩበት ጊዜ ልትጠይቋቸው የምትችሏቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ለምሳሊ ልጆቹ በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ከያንዳንዱ ሥንኞች ምን እንደተማሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። መዝሙሩ የሚመልሳቸውን ጥያቄዎች እንዲያስቡ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ይህ መዝሙሩ ስለሚያስተምራቸው እውነቶች ውይይት ወደ ማድረግ ሊያመራ ይችላል።

ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን ተጠቀሙ። ልጆቹ የአንድን መዝሙር ቃል እና መልዕክት ለማስታወስ እንዲረዳቸው ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስቡ ጋብዟቸው። ለምሳሌ፣ “My Heavenly Father Loves Me” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 228–29)፣ ሁለተኛ ሥንኝ በምትዘምሩበት ጊዜ ልጆቹ ወደ ዓይኖቻቸው እንዲጠቁሙ፣ እንደ ቢራቢሮዎች አስመስለው እንዲሰሩ እና የእጃቸውን መዳፍ ከጆሮአቸው ጀርባ እንዲለጥፉ መጋበዝ ትችላላችሁ። “Yes, I know Heavenly Father loves me” የሚለውን መዝሙር በሚዘምሩበት ጊዜ እጆቻቸውን በደረታቸው ላይ እንዲያደርጉ ጠይቋቸው።