ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ተጨማሪ ግብዓቶች
አባሪ ለ ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜ ልክ እንዲቆዩ ማዘጋጀት


“አባሪ ለ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜ ልክ እንዲሆኑ ማዘጋጀት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ መ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

አባሪ ለ

ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜ ልክ እንዲሆኑ ማዘጋጀት

አምስት እሑዶች ባሏቸው ወራት ውስጥ፣ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዎች በአምስተኛው እሑድ መርሐ ግብር የተያዘለትን የ ኑ፣ ተከተሉኝ መዘርዝር በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የትምህርት አክቲቪቲዎች እንዲተኩ ይበረታታሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መርሆዎች እና ሥርዓቶች

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት እንዴት ወደ እግዚአብሄር እንደምንመለስ ያስተምረናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአሜሪካ ሕዝቦች በተገለጠ ጊዜ ትምህርቶቹን አስተምሯቸዋል። እምነት ቢኖረን፣ ንሥሐ ብንገባ፣ ብንጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስን ብንቀበል እና እስከመጨረሻው ብንፀና ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት እንደምንችል ተናግሯል ( 3 ኔፊ 11:31–40ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:29 ይመልከቱ)። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት አክቲቪቲዎች እነዚህ መርሆዎች እና ሥርዓቶች በመላው ህይወታችን ወደ አዳኙ እንድብቀርብ እንደሚረዱን ልጆቹን ለማስተማር ይረዷችኋል።

ስለ ከርስቶስ ትምህርት የበለጠ ለመረዳት፣ 2 ኔፊ 31 ይመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ማድረግን፣ ንሥሐን፣ ጥምቀትን እና ማረጋገጫ መቀበልን የሚወክሉ ሥዕሎችን ለልጆቹ ስጧቸው (Gospel Art Book፣ ቁጥር 1111103፣ እና 105ን ይመልከቱ)። አራተኛውን የእምነት አንቀፅ ከልጆቹ ጋር አንብቡ ወይም በቃላችሁ ያዙ፣ ከዚያም ያ መርህ ወይም ሥርዓት ሲጠቀስ ስዕሎቻቸውን ከፍ አድርገው እንዲይዙ ጠይቋቸው። ልጆቹ እነዚህ መርሆዎች እና ሥርዓቶች እንዴት የበለጠ እንደ ሰማይ አባታችን እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንሆን እንደሚረዱን እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

  • ልጆቹ እምነት፣ ንሥሐ፣ ጥምቀት እና ማረጋገጫ መቀበል የአንድ ጊዜ ተግባራት ሳይሆኑ በመላው ህይወታችን በመንፈሳዊ እድገታችን ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ እንዲገነዘቡ እንዴት ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ለምሳሌ የአንድን ዘር እና ትልቅ ዛፍ ሥዕል ልታሳዩአቸው (ወይም በሰሌዳው ላይ ልትስሉ) ትችላላችሁ። ዘሩ ወደ ትልቅ ዛፍነት እንዲያድግ ስለሚረዱት እንደ ውሃ፣ አፈር እና የፀሐይ ብርሃን ያሉ ነገሮች እንዲያስቡ እርዷቸው። እነዚህ በመላ ህይወታችን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የምናደርጋቸው በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እንደመግንባት፣ በየቀኑ ንሥሐ እንደመግባት፣ የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችንን እንደ መኖር እና መንፈስ ቅዱስን እንደመስማት ያሉ ነገሮች መሆናቸውን እንዲያዩ እርዷቸው።

  • ስለ ፋየርክራከር የሚናገረውን ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ ያቀረቡትን ታሪክ ከልጆች ጋር ተወያዩ“ How Can Repenting Help Me Feel Happy?” (ጓደኛ፣ ታህሳስ 2017 (2017)፣ 12–13፣ ወይም ሊያሆና፣ ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)፣ 70–71፤ በተጨማሪም “Repentance: A Joyful Choice” የወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

    ሽማግሌ ረንለንድ በታሪኩ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ምን ተሰምቷቸው የነበረ ሊሆን እንደሚችል እንዲያስቡ ልጆቹን ጋብዟቸው። ንሥሐ በምንገባበት ጊዜ ደስታ የሚሰማን ለምንድነው? የሰማይ አባት ይቅር እንዲላችሁ ጠይቃችሁ በነበረበት ጊዜ ተሰምቷችሁ የነበረውን ደስታ እና ፍቅር ለልጆቹ አካፍሉ።

ጥምቀት

ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ለእኔ ምሳሌ ሆኖኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጢያት ያልነበረበት ቢሆንም ለሰማይ አባት ስለመታዘዝ ፍጹም ምሳሌ ይሆን ዘንድ ተጠመቀ (2 ኔፊ 31:6–10 ይመልከቱ)።

ስለ ጥምቀት የበለጠ ለመማር, ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:37፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ጥምቀት፣” ወንጌል ላይብረሪ ላይ ይመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • የአዳኙን እና የአንድን የሌላ ሰውን የጥምቀት ምሥል አሳዩ (ወይም Gospel Art Book፣ ቁጥር 35 እና ቁጥር 103 ወይም ቁጥር 104)። በሁለቱ ሥዕሎች መካከል ምን ልዩነት እና ምን ተመሳሳይነት እንዳለ እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። ማቴዎስ 3:13–17ን ወይም “Chapter 10: Jesus Is Baptized”ን ከአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 26–29፣ ውስጥ አብራችሁ አንብቡ ወይም በወንጌል ቤተመፃህፍት ውስጥ ተዛማጅ ቪዲዮውን ተመልከቱ።

    ልጆቹ በንባቡ ውስጥ ወይም በቪዲዮው ላይ በተጠቀሱት ሥዕሎች ውስጥ ወዳሉት ነገሮች እንዲጠቁሙ ፍቀዱላቸው። ለአዳኙ ያላችሁን ፍቅር እና ልትከተሉት ያላችሁን ፍላጎት ለልጆቻችሁ ንገሯቸው።

  • ለምሳሌ እንደ “A Child’s Prayer” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 102) ያሉ ስለ ጥምቀት የሚናገሩ መዝሙሮችን ማዳመጥ ወይም መዘመር ትችላላችሁ። ከመዝሙሩ ስለ ጥምቀት ምን እንማራለን? 2 ኔፊ 31:9–10 አንብቡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን እንደተጠመቀ እንዲያዳምጡ ልጆቹን ጋብዙ። የራሳቸውን የጥምቀት ቀን ምስል እንዲስሉ ጋብዟቸው።

ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት መምረጥ እንዲሁም ለመጠመቅ እችላለሁ።

ለጥምቀት መዘጋጀት ለአንድ ፕሮግራም ከመዘጋጀት በብዙ የሚበልጥ ነገርን ይጠይቃል። ቃል ኪዳን ለመግባት መዘጋጀት ከዚያም ያንን ቃል ኪዳን ዕድሜ ልክ መጠበቅ ማለት ነው። ልጆቹ በሚጠመቁበት ጊዜ ለእነርሱ የሰጣቸውን ተስፋዎችና ለእርሱ ገቧቸውን ቃል ኪዳኖች የሚያካትተውን ከሰማይ አባት ጋር የሚገቡትን ቃል ኪዳን ይገነዘቡት ዘንድ እንዴት ለትረዷቸው እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ቃል ኪዳን ሰው እና የሰማይ አባት የሚገቡበት የተስፋ ቃል እንደሆነ አስረዱ። ለእግዚአብሄር የገባናቸውን የተስፋ ቃሎች ለመጠበቅ በምንጥርበት ጊዜ እግዚአብሄር እንደሚባርከን ቃል ገብቷል። በሰሌዳው ላይ ለእግዚአብሄር የገባኋቸው ቃል ኪዳኖች እና እግዚአብሄር ለእኔ የገባለኝ ቃል ኪዳን ብላችሁ ጻፉ። ሞዛያ 18:10፣ 13 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:37፣ አብራችሁ አንብቡ ከዚያም ልጆቹ የሚያገኟቸውን የቃል ኪዳኖች ዝርዝር በተገቢው ርዕስ ሥር እንዲዘረዝሩ አግዟቸው። (በተጨማሪም ዳልን ኤች. ኦክስ፣ “Your Baptism Covenant,” ጓደኛ፣ የካቲ. 2021 (እ.አ.አ)፣ 2–3 ይመልከቱ)። የጥምቀት ቃል ኪዳናችሁን ለመጠበቅ በምትጥሩበት ጊዜ የሰማይ አባት እንዴት እንደባረካችሁ አካፍሉ፡፡

  • ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ያከናወናቸውን ነገሮች የሚያሳዩ ሥዕሎች ለልጆቹ አሳዩ (ለአንዳንድ ምሳሌዎች፣ Gospel Art Book፣ ቁጥር 33–49 ይመልከቱ፡፡ በእያንዳንዱ ሥዕል ውስጥ ኢየሱስ ምን እየሰራ እንደሆነ እንዲናገሩ ፍቀዱላቸው፡፡ ሞዛያ 18:8–10, 13ን አንብቡ እና ልጆች ሲጠመቁ ለማድረግ ቃል የገቡትን ነገሮች እንዲሰሙ ጋብዟቸው (በተጨማሪም “The Baptism Covenant,” ጓደኛ፣ የካቲ. 2019 (እ.አ.አ)፣ 7፤ ሊያሆና፣ የካቲ. 2019 (እ.አ.አ)፣ F3 ይመልከቱ)፡፡ እነዚህ ተስፋዎች በዕለት ተዕለት ድርጊቶቻችን ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ምንድን ነው? ልጆች ኢየሱስ እንደሚያደርገው ሌሎችን እየረዱ የሚያሳይ የራሳቸውን ምስል እንዲስሉ ጋብዟቸው። ልጆቹ የኢየሱስ ስም ያለበት ቀለል ያለ ባጅ እንዲያደርጉ ማድረግ ትችላላችሁ።

    ምስል
    ወንድ ልጅ እየተጠመቀ

    በምንጠመቅበት ጊዜ ለእግዚአብሄር ቃል ኪዳን እንገባለን እርሱም ለእኛ ቃል ኪዳን ይገባልናል።

ማረጋገጫ መቀበል

ማረጋገጫ ስቀበል የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል እሆናለሁ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ልጆች በእግዚአብሄር ሥራ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ እድሎችን ጨምሮ ብዙ በረከቶችን ያመጣል።

ማረጋገጫ ስለመቀበል እና ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የበለጠ ለመማር፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?፣ ”ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 117–20፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “መንፈስ ቅዱስ,” ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • አንድ በቅርቡ የተጠመቀ እና እና ማረጋገጫ የተቀበለ ሰው ወደ ክፍል እንዲመጣና ማረጋገጫ መቀበል ምን እንደሚመስል እንዲያካፍል ጋብዙት። ለዚህ ሰው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን አባል መሆን ማለት ምን ማለት ነው። ልጆቹ እንደ ቤተክርስቲያን አባላት የጥምቀት ቃል ኪዳናቸውን መጠበቅ የሚችሉባቸውን (ለምሳሌ ሌሎችን እንደማገልገል፣ ሌሎች ስለ ኢየሱስ የበለጠ እንዲማሩ እንደመጋበዝ፣ በስብሰባዎች ላይ ጸሎት እንደማቅረብ፣ ወዘተ) ያሉ መንገዶችን እንዲያስቡ እርዷቸው። እነዚህን ነገሮች ማድረግ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን የሚገኘው ደስታ ይሰማችሁ ዘንድ እንዴት እንደረዳችሁ አካፍሉ።

  • በሞርሞን ውሃ አጠገብ የነበሩ ሰዎችን ሥዕል አሳዩ (የወንጌል የአርት መፅሐፍ, ቁ. 76ን ይመልከቱ) እንዲሁም ልጆቹ የሚያዩትን እንዲገልፁ ጠይቋቸው። የአልማን እና የህዝቡን በዚያ የመጠመቅ ታሪክ ተናገሩ (ሞዛያ 18:1–17፤ “Chapter 15: Alma Teaches and Baptizes,” የመፅሃፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 43–44፣ ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በውንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)።

    ሞዛያ 18:8–9 ከልሱ ከዚያም ህዝቡ እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ለማድረግ ፈቃደኛ የነበሩትን ነገሮች እንዲያስታውሱ የሚረዷቸውን ተግባራትን እንዲፈፅሙ ልጆቹን ጋብዟቸው። የቤተክርስቲያን አባላት በእነዚህ መንገዶች ሲያገለግሉ ያያችሁበትን አንድ ተሞክሮ አካፍሉ።

ማረጋገጫ በምቀበልበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እቀበላለሁ።

በምንጠመቅበት እና ማረጋገጫ በምንቀበልበት ጊዜ የሰማይ አባት “የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ [እንደሚኖረን]”ቃል ይገባልናል (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 20:77)። ከእግዚአብሄር የሚመጣው ይህ ኃይለኛ ስጦታ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይባላል።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33:15 አንብቡና በምንጠመቅበት እና ማረጋገጫ በምንቀበልበት ጊዜ የሰማይ አባት ስለሚሰጠን ልዩ ስጦታ እንዲሰሙ ልጆቹን ጠይቋቸው። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዴት እንደሚረዳቸው ይበልጥ እንዲማሩ ለመርዳት ዮሐንስ 14:26ገላትያ 5:22–232 ኔፊ 32:53 ኔፊ 27:20 አብራችሁ ከልሱ። “መንፈስ ቅዱስ … ነው” (ጓደኛ፣ ሰኔ 2019 (እ.አ.አ)፣ 24–25፤ ሊያሆና፣ ሰኔ 2019 (እ.አ.አ)፣ F12–F13) የሚለውን ፅሁፍ ልትከልሱም ትችላላችሁ።

  • የአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆችን ወላጆች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስላላቸው እንዴት እንደተባረኩ በተማሪዎቹ ፊት እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። እንዴት ይረዳቸዋል? ድምፁን የሚሰሙት እንዴት ነው?

  • እንደ “The Holy Ghost” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 105) የመሰለ ስለመንፈስ ቅዱስ የሚናገር መዝሙር አብራችሁ ዘምሩ። መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ስለሚችልበት መንገድ መዝሙሩ ምን እንደሚያስተምረን ልጆቹ እንዲገነዘቡ እርዷቸው።።

መንፈስ ቅዱስ በተለያየ መንገድ ሊናገረኝ ይችላል።

የመንፈሱን ድምጽ ማወቅ የሚችሉ ልጆች በመላ ሕይወታቸው ይመራቸው ዘንድ የግል መገለጥን ለመቀበል ይዘጋጃሉ። መንፈስ ቅዱስ ሊያናግረን የሚችልባቸው ብዙ መንገዶች እንዳሉ አስተምሯቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ ሩቅ ከሚኖር ጓደኛ ጋር የምንነጋገርባቸውን እንደ ደብዳቤ መፃፍ፣ ኢሜል መላክ ወይም በስልክ ማናገር የመሳሰሉ የተለያዩ መንገዶችን እንዲያስቡ እርዷቸው። የሰማይ አባት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሊያናግረን እንደሚችል አስተምሯቸው። ልጆቹ መንፈስ ቅዱስ ለአዕምሮአችን እና ለልባችን የሚናገርባቸን የተለያዩ መንገዶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት የፕሬዚዳንት ዳሊን ኤች.ኦክስን መልዕክት የሆነውን How Does Heavenly Father Speak to Us?” (ጓደኛ፣ መጋቢት 2020 (እ.አ.አ)፣ 2–3፤ ሊያሆና፣ መጋቢት 2020 (እ.አ.አ)፣ F2–F3) ተጠቀሙ።

  • መንፈስ ቅዱስ እናንተን በአእምሮአችሁ በሃሳብ ወይም በልባችሁ በስሜት ያነጋገረበትን አንድ ተሞክሮ አካፍሉ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6:22–238:2–3 ይመልከቱ። በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Open Your Heart to the Holy Ghost,” ጓደኛ፣ ነሃሴ. 2019 (እ.አ.አ)፣ 2–3፤ ሊያሆና፣ ነሃሴ 2019(እ.አ.አ)፣ F2–F3) ይመልከቱ። በህይወታችሁ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በተመሳሳይ መንገድ ሊረዳቸው እንደሚችል ለልጆቹ መስክሩላቸው።

  • ልጆቹ መንፈሱ የተሰማቸውን ጊዜ እንዲያስቡ እርዷቸው—ለምሳሌ ስለአዳኙ መዝሙር በሚዘምሩበት ወይም ለሌሎች መልካም ነገር በሚያደርጉበት ጊዜ። መንፈስ ቅዱስ የሚያመጣውን መንፈሳዊ ስሜቶች እንዲያውቁ እርዷቸው። መንፈስ ቅዱስ እነዚያን ስሜቶች የሚያመጣው ለምን ይመስላችኋል? መንፈስ ቅዱስ ሲናገረን ለመስማት እንችል ዘንድ ማድረግ ያሉብንን ነገሮች እንዲያስቡ ልጆቹን እርዷቸው። ድምጹን በበለጠ ጥራት ለመስማት ምን እንደምታደርጉ ተነጋገሩ።

ቅዱስ ቁርባን

ቅዱስ ቁርባንን በምወስድበት ጊዜ የአዳኙን መስዋዕትነት አስታውሳለሁ እንዲሁም ቃል ኪዳኔን አድሳለሁ።

አዳኙ ለእኛ የከፈለውን መስዋዕት እንድናስታውስ እና ቃል ኪዳኖቻችንን ለማደስ እንዲረዳን ቅዱስ ቁርባንን ሰጠን። በዚህ ሳምንታዊ ሥርዓት ምክንያት እድሜ ልካችንን በጥምቀታችን በረከቶች በመደሰት መቀጠል እንችላለን።

የበለጠ ለመማር፣ ማቴዎስ 26:26–30. 3 ኔፊ 18:1–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:77፣ 79 ይመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ “Jesus Introduced the Sacrament to the Nephitesየቅዱሳት መጻሕፍት ታሪኮች ማቅለሚያ መጽሐፍ፡ መጽሐፈ ሞርሞን (2019 (እ.አ.አ)) 26 እንዲቀቡ ጋብዟቸው። በሥዕሉ ውስጥ ሰዎቹ ወደሚያስቡት ነገር እንዲጠቁሙ ጠይቋቸው። 3 ኔፊ 18:1–12 የተወሰነ ክፍል ወይም “Chapter 45: Jesus Christ Teaches about the Sacrament and Prayer,” የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 126–27፣ ለልጆቹ አንብቡላቸው ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በ ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ተመልከቱ። በቅዱስ ቁርባን ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ምን ማድረግ እንችላለን?

  • ልጆቹ ሁል ጊዜ ማድረግ እንደሚገባቸው ማስታወስ ያለባቸውን አንዳንድ ነገሮችን እንዲነግሯችሁ ይጠይቋቸው። እነዚህን ነገሮች ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሞሮኒ 4:3 ለልጆች አንብቡ ከዚያም,ቅዱስ ቁርባንን በምንወስድበት ጊዜ ምንን ሁል ጊዜ ለማስታወስ ቃል ኪዳን እንደምንገባ እንዲያዳምጡ ጋብዟቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ልጆቹ የቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ውሃ ኢየሱስ ለእኛ ያደረገልንን እንዴት እንድናስታውስ እንደሚረዳን እንዲገነዘቡ እርዷቸው ( ሞሮኒ 4:35:2 ይመልከቱ)።

  • በሰሌዳው ላይ…” ለማድረግ ቃል እገባለሁ ብላችሁ ፃፉ።የቅዱስ ቁርባኑን ፀሎት ለልጆቹ አንብቡላቸው ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:77፣ 79ይመልከቱ)። ለእግዚአብሔር የገባነውን አንድ ቃል ኪዳን ሲሰሙ፣ ቆም በሉና በሰሌዳው ላይ ያለውን ዓረፍተ ነገር በሰሙት ቃል ኪዳን እንዲያሟሉ እርዷቸው። ቅዱስ ቁርባንን በምንወስድበት ጊዜ ስንጠመቅ የገባነውን ያንኑ ቃል ኪዳን እየገባንን እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ መውሰድ ማለት ምን ማለት ነው? ልጆቹ ይህንን ጥያቄ እንዲመልሱ ለመርዳት ስማችንን በላዩ የምናደርግበትን የአንድ ነገር ምሳሌ አካፍሉ። ስማችንን በእነዚህ ነገሮች ላይ የምናደርገው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙን በእኛ ላይ ማድረግ ለምን ይፈልጋል? የፕሬዚዳንት ራስል አኤም ኔልሰንን ማብራሪያ ማካፈልን አስቡ፦ “የአዳኝን ስም መውሰድንም—በስራዎቻችን እና በቃላቶቻችን—ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ለሌሎች ማወጅን እና መመስከርን ያካትታል” (“The Correct Name of the Church,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 88)።

የክህነት ሃይል፣ ሥልጣን እና ቁልፎች

እግዚአብሄር ልጆቹን በክህነት ሃይል አማካኝነት ይባርካል።

ሁሉም የእግዚአብሄር ልጆች—ሴት እና ወንድ፣ ወጣት እና አዛውንት—ከርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ሲጠብቁ የእግዚአብሄርን ሃይል ይቀበላሉ። እንደጥምቀት ያሉ የክህነት ሥርዓቶችን ስንቀበል እነዚህን ቃል ኪዳኖች እንገባለን ( አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የአኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ማገልገል,፣3.5፣ ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)። የበለጠ ለመማር፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ “Priesthood Principles፣” ምዕራፍ 3 አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ ይመልከቱ።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ልጆቹ በክህነት ምክንያት የሚቀበሉትን በረከቶች እንዲያስተውሉ እርዷቸው፡፡ የተወሰኑ ሃሳቦችን ለመስጠት፣ “Blessings of the Priesthood” (የወንጌል ቤተመፃሕፍት) የተሰኘውን ቪዲዮ ልታሳዩ ትችላላችሁ፡፡

  • እነዚህን በረከቶች በሰሌዳውላይ መዘርዘርን አስቡ። እነዚህ በረከቶች ለእኛ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? እነዚህ በረከቶች ወደ እኛ የሚመጡት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በክህነት ሥልጣኑ እንደሆነ መስክሩ።

  • የሚከተለውን ርዕስ በሰሊዳው ላይ ፃፉ: የእግዚአብሄር ሃይል እና በምድር ለሠዎች የተሰጣቸው የእግዚአብሄር ሃይል እና ሥልጣን. እግዚአብሔር ምድርን በመፍጠር፣ ለኛ ምሪት በመስጠት፣ እንደሚወደን እና እንደሚያውቀን ለእኛ በማሳየት እኛን ለመባረክ ኃይሉን እንዴት እንደተጠቀመ እንድንገነዘብ የሚያግዙንን ሥዕሎች በመጀመሪያው ርዕስ ስር እንዲያስቀምጡ ልጆቹን ጠይቋቸው። (Gospel Art Book፣ ቁጥር 36890፣ 111 ይመልከቱ)። በምድር ላይ ያሉ ብቁ ሰዎች የአምላክን ኃይልና ሥልጣንን የታመሙትን በመባረክ፣ በማጥመቅ፣ ማረጋገጫ በመስጠት፣ ቀዱስ ቁርባንን በማዘጋጀት እና ቤተሰቦችን በማተም እኛን ለመባረክ እንዴት እንደሚጠቀሙ እንድንረዳ የሚያግዙንን ሥዕሎች በሁለተኛው ርዕስ ሥር እንዲያስቀምጡ ጠይቋቸው (Gospel Art Book፣ ቁጥር 46104105107፣ 120 ይመልከቱ)። ለክህነት እና ለሚያመጣችው በረከቶች ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ አካፍሉ።

  • በህይወታችን የእግዚአብሔርን ሀይል በረከቶች ከምንቀበልባቸው ዋና ዋና መንገዶች አንዱ በክህነት ሥርዓቶች በኩል ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84:20 ይመልከቱ)። ልጆቹ ይህንን እውነት እንዲማሩ ለመርዳት የሚከተሉትን የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅሶች በሰሌዳው ላይ መዘርዘር ትችላላችሁ።: 3 ኔፊ 11:21–26, 33 (ጥምቀት)፤ ሞሮኒ 2 (ማረጋገጫ መቀበል)፤ ሞሮኒ 4–5 (ቅዱስ ቁርባን)። ልጆቹ እያንዳንዳቸው ከእነዚህ ፣ምባቦች ውስጥ አንዱን ሊመርጡ እና የሚገልፀውን ሥርዓት ሊለዩ ይችላሉ። ልጆቹ የክህነት ሥርዓቶችን በመቀበላቸው እንዴት በግል እንደተባረኩ እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

  • ልጆቹ በሚጠመቁበት እና የጥምቀት ቃል ኪዳናቸውን በሚጠብቁበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ኃይል እንደሚቀበሉ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ይህ ኃይል ልጆቹን እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ጠይቋቸው።

የእግዚአብሄር ሥራ የሚመራው በክህነት ቁልፎች ሲሆን የሚከናወነውም በክህነት ሥልጣን ነው።

በቁ የሆኑ ወንድ የቤተክርስቲያን አባላት በክህነት ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ አንድ ግለስብ ለአንድ ጥሪ ሲለይ ወይም በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ እንዲረዳ ሲመደብ፣ እሱ ወይም እሷ በውክልና የተሠጣቸውን የክህነት ስልጣን መጠቀም ይችላሉ። በቤተክርስቲያኗ ያለ የክህነት ስልጣን አጠቃቀም ሁሉ እንደ ካስማ ፕሬዚዳንት፣አኤጲስ ቆጶስ እና እና የቡድን ፕሬዚዳንቶች.ባሉ የክህነት ቁልፎችን በያዙ ግለሰቦች ይመራል። የክህነት ቁልፍ የጌታን ስራ በመስራት ሂደት የክህነት አጠቃቀምን ለመምራት የሚያስችል ስልጣን ነው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ማርቆስ 3:14–15፣ ከልጆቹ ጋር አንብቡ እንዲሁም በዚያ የተገለፀውን ክስተት ሥዕል አሳዩዋቸው (ለምሳሌ Gospel Art Book። ቁጥር 38)። አንድ ሰው በክህነት ክፍል ሲሾም ወይም ለጥሪ ሲለይ (ወይም የሏችሁን ተሞክሮዎች ልትነግሯቸው ትችላላችሁ) አይተው ያውቁ እንደሆነ ልጆቹን ጠይቋቸው። ያ አዳኙ ከሐዋርያቱ ጋር ካደረገው ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ልጆቹ ለቤተክርስቲያን አባላት ሊሠጡ የሚችሉ እንደ አስተማሪ ወይም የድርጅት አስተማሪ የመሳሰሉ የክህነት ክፍሎችን እና ጥሪዎችን በሰሌዳው ላይ እንዲዘረዝሩ እርዷቸው። ከእያንዳንዱ ክፍል ወይም ጥሪ አጠገብ በዚያ ክፍል ወይም ጥሪ ያለው አንድ ሰው ምን የማድረግ ሥልጣን እንዳለው ልትፅፉ ትችላላችሁ። በክህነት ቁልፎች አመራር በአንድ ግለሰብ መለየታችሁ ለማገልገል እንዴት እንደረዳችሁ ለልጆቹ ንገሩ።

  • እንደ መኪና ወይም በር ያሉ ለመክፈት ቁልፍ የሚያስፈልጋቸው ነገሮችን እንዲያስቡ ልጆቹን ጋብዙ። ቁልፉ ከሌላችሁ ምን ይሆናል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65:2ን አንድ ላይ አንብቡ እና የክህነት ቁልፎችን በምድር ላይ የመኖር አስፈላጊነትን በተመለከተ ምስክርነታችሁን አካፍሉ። “Where Are the Keys?” የሚለውን ቪዲዮ (የወንጌል ላይብረሪ) ተመልከቱ ከዚያም ሽማግሌ ስቲቨንሰን ስለክህነት ቁልፎች ምን እንዳስተማሩ ፈልጉ።

  • አንድ በአጥቢያው ያለ ቁልፎችን የያዘ ሰው ወደ ክፍል እንዲመጣና የክህነትን ሥልጣን መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለልጆቹ እንዲያካፍል ጠይቁት። ኃላፊነቶቹን እንዲገልጽ ጋብዙት። የትኞቹን የጊታ ሥራ ክፍሎች ነው የሚመራው። አዳኙ የሚረዳው እንዴት ነው?

ቤተመቅደስና እና የደስታ እቅድ

ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው። በቤተመቀደስ ከእርሱ ጋር የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን እንገባለን፣ የክህነት ሃይል የመንፈስ ሥጦታን እንቀበላለን፣ መገለጥን እንቀበላለን፣ ለሞቱ ቀድመ ዓያቶቻችን ሥርዓቶችን እናከናውናለን እንዲሁም ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘላለም እንጣመራለን። ይህ ሁሉ የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት ነው።

የምታስተምራቸውን ልጆች ስለጌታ ቤት ቅድስና እንዲገነዘቡ እንዲሁም በቤተመቅደስ ሥርዓቶች ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ እንዲሆኑ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? እነዚህን ግብዓቶ መከለስን አስቡ፦ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97:15–17፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመዝጊያ ነግግር፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 120–22፤ “Why Latter-day Saints Build Temples,” temples.ChurchofJesusChrist.org.

ምስል
ወጣቶች ከአንድ ቤተመቅደስ ውጪ

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቤተመቅደስ ሥዕሎችን አሳዩ። ቤተመቅደስን የተለየ ቦታ የሚያደርገው ምን እንደሆነ ልጆቹን ጠይቋቸው። በእንዳንዱ የቤተመቅደስ መግቢያ ላይ “ቅድስናን ለእግዚአብሔር የእግዚአብሔር ቤት” የሚሉ የተቀረፁ ቃላት እንዳሉ ጥቀሱ። “ቅድስናን ለእግዚአብሔር” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንደሚያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው የተባለው ለምንድን ነው? ይህ ስለ ቤተመቅደስ ምን ያስተምረናል? ከልጆቹ አንዳቸው በቤተመቅደስ ተካፍለው የሚያውቁ ከሆነ እዚያ በነበሩበት ጊዜ እንዴት እንደተሰማቸው ሊያካፍሉም ይችላሉ። በቤተመቅደስ ተሳትፋችሁ የምታውቁ ከሆነ የጌታ መገኘት እንዴት ተሰምቷችሁ እንደነበረ አካፍሉ እንዲሁም ቤተመቅደስ ለእናንተ ለምን የተቀደሰ ሥፍራ እንደሆነ ተናገሩ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥15–17 አብራችሁ አንብቡ። ጌታ ወደ ቅዱስ ቤቱ ከሚገቡ ሰዎች ምን እንደሚጠብቅ እንዲፈልጉ ልጆቹን ጠይቋቸው። ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ መሆን የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? እንደዚህ ውይይት አካል ስለ ቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እንዲሁም እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ከልጆቹ ጋር ተነጋገሩ። የቤተ መቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለመጠይቅ ምን እንደሚመስል እና ስለሚጠየቁት ጥያቄዎች ለእነርሱ እንዲያካፍል አንድን የኤጲስ ቆጶስ አመራር ልትጋብዙ ትችላላችሁ።

በቤተመቅደስ ከእግዚአብሄር ጋር ቃል ኪዳን እንገባለን።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤታችን የሚመልሰንን የቃልኪዳን መንገድ ተከትለን ከሰማያዊ ወላጆቻችንና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንሆን ይጋብዘናል” ሲሉ አስተምረዋል።(“ኑ፤ ተከተሉኝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ) 91)። የቃል ኪዳን መንገድ ጥምቀትን፣ ማረጋገጫ መቀበልን እና ይቤተ መቅደስ የመንፈስ ሥጦታን እና እትመትን እንደሚያካትት እንዲገነዘቡ ልጆቹን እርዷቸው።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • ስንጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባውን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባን በምንወስድበት ጊዜ የምናድሰውን ቃል ኪዳን እንድትከልሱ እንዲረዷችሁ ልጆቹን ጠይቋቸው። (ሞዛያ 18:10ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:77፣ 79 ይመልከቱ)። የቤተመቅደስን ምስል አሳዩ እና የሰማይ አባት በቤተመቅደስ ውስጥ ለእኛ ሊሰጠን የሚፈልጋቸው ተጨማሪ በረከቶች እንዳሉት አብራሩ።

  • ወደ መንገድ የሚያመራ በር ሳሉ። የመሄጃ መንገድ መኖሩ ለምን ጠቃሚ እንደሆነ እንደሚያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ኔፊ የጥምቀትን ቃል ኪዳንን ከበር ጋር የሚያነጻጽርበትንና ከጥምቀት በኋላ በመንገዱ እንድንቀጥል የሚጋብዝበትን 2 ኔፊ31:17–20፣ አብራቸሁ አንብቡ። በቤተመቅደስ የሚገቡትን ቃልኪዳኖች ጨምሮ ከጥምቀት በኋላ የምንገባቸውብዙ ቃል ኪዳኖች አሉ። ፕሬዚዳንት ኔልሰን ይህንን መንገድ “የቃል ኪዳን መንገድ” ብለው እንደጠሩት አብራሩ።

በቤተመቅደስ ውስጥ ለሞቱ ቅድመ ዓያቶቻችን ልንጠመቅ እና ማረጋገጫ ልንቀበል እንችላለን።

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ወንጌልን ሳያውቁ የሞቱ ቢሆኑም እንኳን ከእርሱ ጋር ለመኖር መመለስ እንዲችሉ ያደርጋል። በቤተመቅደስ ልንጠመቅ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን ማረጋገጫ ልንቀበል እንችላለን።

ሊደረጉ የሚችሉ አክቲቪቲዎች

  • አንድ ሰው በራሳችሁ ልታደርጉት ያልቻላችሁትን አንድ ነገር ያደረገላችሁን ጊዜ ተናገሩ። ልጆቹ ተመሳሳይ ተሞክሮዎችን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ ለሌሎች ለሞቱ ሰዎች እንደ ጥምቀት ያሉ ቅዱስ ሥርዓቶችን ማከናወን እንደምንችል ግለፁ። ለሞቱ ሰዎች ሥራ ስንሰራ እንደ ኢየሱስ የምንሆነው እንዴት ነው? በራሳችን ልናደርገው የማንችለውን ምን አድርጎልናል?

  • ለቅድመ ዓያቶቻቸው የተጠመቁ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ውጣቶች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዙ። የቤተመቅደስ ተሞክሯቸው እንዴት እንደነበር ጠይቋቸው። ለቅድመ ዓያቶቻቸው ይህንን ሥራ በመስራታቸው እንዴት እንደተሰማቸው እንዲያካፍሉ አበረታቷቸው።

  • ሥሮቹን እና ቅርንጫፎቹን ጨምሮ በሰሌዳው ላይ አንድ ዛፍ ሳሉ። ቤተሰብ እንዴት እንደ ዛፍ እንደሆነ እንዲያስቡ ልጆቹን ጠይቋቸው። ሥሮቹን ቅድመ ዓያቶች፣ ቅርንጫፎቹን ዘሮች፣ ግንዱን እናንተብላችሁ ሥም ስጡ። ይህንን ዓረፍተ ነገር አብራችሁ አንብቡ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128:18፦“ያለ እነርሱ ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ ወይም እነርሱም ያለእኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም።” እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቂዎችን ጠይቁ፦ “ቅድመ ዓያቶቻችንን የምንፈልጋቸው ለምንድን ነው? ዘሮቻችን የሚፈልጉን ለምንድን ነው? ወላጆቻችን፣ ዓያቶቻችን እና ሌሎች ቅድመ ዓያቶቻችን የረዱን እንዴት ነበር? በቀሪው የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128:18 ውስጥ ቅድመ ዓያቶቻችንን እንዴት መርዳት እንደምንችል የሚገልጽ ሀረግ እንዲፈልጉ ልጆቹን ጋብዟቸው።

  • ልጁ ወደ ቤተመቅደስ የሚወስደውን የቅድመ አያት ስም ለማግኘት ከእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች ጋር መስራትን አስቡ (FamilySearch.org ይመልከቱ)።