ክፍል ፻፳፰
ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስለሙታን ጥምቀት ተጨማሪ መመሪያን የያዘ፣ በመስከረም ፮፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.) በናቩ የተጻፈ ደብዳቤ።
፩–፭፣ የአካባቢ እና አጠቃላይ መዛግብት ስለሙታን መጠመቅ መከናወን ማረጋገጥ አለባቸው፤ ፮–፱፣ ዘገባዎቹም የሚያስተሳስሩ ናቸው እና በምድር እናም በሰማይ የተመዘገቡ ናቸው፤ ፲–፲፬፣ የማጥመቂያ ገንዳው የመቃብር ተምሳሌት ነው፤ ፲፭–፲፯፣ ኤልያስ ከሙታን ጥምቀት ጋር ተዛማጅነት ያለውን ሀይልን ዳግም መለሰ፤ ፲፰–፳፩፣ ያለፉት ዘመናት ቁልፎች፣ ሀይላት፣ እና ስልጣናት ሁሉ ዳግም ተመልሰዋል፤ ፳፪–፳፭፣ አስደሳች እና የከበረ ምስራች ለህያው እና ለሙታን ታውጇል።
፩ ስፍራዬን ትቼ ከመሄዴ በፊት ከጊዜ ወደጊዜ እንደምፅፍላችሁ እና ብዙ ርዕሶችን በሚመለከት መግለጫዎች እንደምሰጣችሁ እንዳመለከትኳችሁ፣ በጠላቶቼ እየተሰደድኩኝ እያለሁ፣ ርእሱ በአዕምሮዬ ውስጥ ስላለ እና በስሜቴ ላይ በብርቱም ስለሚገፋፋኝ፣ ስለሙታን ሀመጠመቅ ርዕስ እቀጥላለሁ።
፪ ዘጋቢውን በሚመለከት ጥቂት የራዕይ ቃላትን ፅፌላችኋለሁ። ይህን ርዕስ በሚመለከት አሁን የማረጋግጣቸው ጥቂት ተጨማሪ አስተያየቶች አሉኝ። ያም፣ ከዚህ በፊት በደብዳቤዬ እንደገለፅኩት፣ የአይን ምስክር የሚሆን፣ እና በጆሮዎቹ ሰምቶ በጌታ ፊት እውነትን ይመዝገብ ዘንድ ሀዘጋቢ ማስፈለጉን ነው።
፫ አሁን፣ ከዚህ ጉዳይ ጋር በሚገናኝም፣ ለአንድ ዘጋቢ በሁሉም ጊዜያት ለመገኘት እና ሁሉንም ስራዎች ያከናውን ዘንድ አዳጋች መሆኑን ነው ይህን ችግር ለማስወገድ፣ በእያንዳንዱ ከተማው ዎርዶች የስብሰባ መዛግብትን ያለስህተት ለመጻፍ ብቁ የሆነ ዘጋቢ ለመመደብ ይቻላል፤ እና ቃል ጉባኤውን ለመጻፍም፣ በአይኑ እንዳያቸውና በጆሮዎቹ እንደሰማቸው፣ ቀናትን፣ ስሞችን፣ እና ሌሎችን፣ እና የጉዳይን ሁሉ ታሪኮችን በመመዝገብ፣ መዝገቡን በማረጋገጥ በጣም ጥንቁቅ እና ትክክለኛ ይሁን፤ እሰጣችኋለው፤ በሁለት ወይም በሶስት አንደበት ሀምስክርነት ሁሉም ቃል ይጸና ዘንድ በዚያ ከነበሩም፣ በሚጠሩበት በማንኛውም ጊዜ ይህን ለማረጋገጥ የሚችሉ የነበሩትን ሶስት ግለሰቦችን ስም ይጻፍም።
፬ ከዚያም፣ ዘገባው እውነት እንደሆነ የሚያስረዳ የፈረመባቸውን የምስክር ወረቀቶች የሚቀበል አጠቃላይ ዘጋቢም ይኑር። ከዚያም የ ቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ዘጋቢ በአጠቃላይ በ ቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥ ከምስክር ወረቀቶች እና ከነበሩት ምስክሮች ጋር በቤተክርስቲያኗ የተመደቡትን ሰዎች አጠቃላይ ጸባይ እውቀቱን በመጠቀም የተጻፈውን መዝገብ እውነትኛነት እና መዛግብቱም እውነት እንደሆኑ እንደሚያምንም ሊፅፋቸው ይችላል። እና ይህም በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥ ሲደረግ፣ መዝገቡም ቅዱስ ይሆናል፣ እና ስነስርዓቱም ልክ በአይኖቹ እንዳያቸው፣ በጆሮዎቹ እንደሰማቸው፣ እና በአጠቃላይ በቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥም እንደመዘገባቸው ይሆናል።
፭ የእነዚህን ነገሮች ስርዓት በጣም የተለየ ነው በማለት ታስቡ ይሆናል፤ ነገር ግን ይህም የወንጌሉ ሀእውቀት ሳይኖራቸው ለሞቱት ለሙታን ለደህንነት ጌታ ከአለም መመስረት በፊት የሾመውን እና ያዘጋጀውን ስርዓት እና ዝግጅትን በመከተል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማሟላት ብቻ እንደሆነ ልንገራችሁ።
፮ በተጨማሪም፣ በራዕይ ፳፥፲፪ ውስጥ ተመዝግቦ እንደምታገኙት፣ ባለራዕዩ ዮሐንስ ስለሙታን ርዕስ ሲያሰላስል እንዲህ ነበር ያወጀው—ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በእግዚአብሔር ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።
፯ በዚህ ጥቅስ ውስጥም መፅሀፍት ተከፍተው እንደነበርም ታገኛላችሁ፤ እና ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም ሀየሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተፈረደባቸው፤ በዚህም ምክንያት፣ የተነገረላቸውም መፅሀፍት ስራዎቻቸውን ዘገባ የያዙ መሆን አለባቸው፣ እና በምድር ላይ ተጠብቀው ያሉትን ለመዛግብት የሚጠቅስ ነው። እና የህይወት መፅሀፍ የሆነው መፅሀፍም በሰማይ ውስጥ የተጻፈው መዝገብ ነው፤ ይህም መሰረታዊ መርህ ስፍራዬን ትቼ ከመሄዴ በፊት በላኩላችሁ ደብዳቤ ውስጥ የነበረው ትእዛዝ ከሰጣችሁ ራዕይ ጋር በግልፅም ይስማማል—መዛግብቶቻችሁ ሁሉ በሰማይ የተመዘገቡ ናቸው።
፰ አሁን፣ ለዚህ ስነስርዓት መሰረት የሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ አማካይነት የሚገኘው የክህነት ሀሀይል ነው፣ በዚህም በምድር ለየምታስሩት ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ እና በምድርም የፈታችሁ ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። ወይም፣ በሌላ ቃላት፣ የትርጉሙን ሌላ አስተያየት በመውሰድ፣ በምድር የመዘገባችሁት ሁሉ በሰማይ የተመዘገበ ይሆናል፣ እና በምድርም የማትመዘግቡትም ሁሉ በሰማያት አይመዘገብም፤ ሐለደህንነታቸው እግዚአብሔር አለም ከመፈጠሩ በፊት ባዘጋጀው መስርዓት መሰረት፣ ስለሙታናቸው በተጠበቁት መዛግብቶቻቸው መሰረት እነዚህን ስነስርዓቶች ለራሳቸው ወይም በወኪላቸው ቢያከናውኑትም፣ ከመጻህፍቱ መሰረት፣ ሙታናችሁ እንደ ስራቸው ይፈረድባቸዋል።
፱ የተነጋገርንበት—በምድር የሚመዘገበው ወይም የሚያስረው እና በሰማይ የሚያስረው ሀይል ለአንዳንዱ በጣም ደፋር የሆነ ትምህርት ይመስላል። ይሁን እንጂ፣ በአለም ዘመናት ሁሉ፣ ጌታ ለማንም ሰው፣ ወይም ለተለያዩ ሰዎች፣ በእውነት ራዕይ የክህነት ሀዘመንን በሚሰጥበት በማንኛውም ጊዜ ይህ ሀይል ዘወትር ይሰጣል። ከዚህ በኋላ፣ ለበስልጣን፣ በጌታ ስም፣ እነዚህ ሰዎች ምንም ቢያደርጉ፣ እና በእውነት እና በታማኝነት ቢያደርጉት፣ እና የእነዚህን ትክክለኛ እና የታመኑ መዛግብትን ቢጠብቁ፣ በምድር ላይ እና በሰማያት ውስጥ ህግ ይሆናል፣ እና በታላቁ ሐያህዌህ ህግጋት መሰረት ሊሰረዝም አይችልም። ይህም የታመነ አባባል ነው። ማን ይሰማዋል?
፲ ደግሞም፣ አስቀድሞ ስለተፈጸመው፣ ማቴዎስ ፲፮፥፲፰፣ ፲፱፥ እኔም እልሀለሁ፣ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፣ የሲዖል ደጆችም አያሸንፏትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሀለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
፲፩ አሁን የዚህ ጉዳይ ታላቅ እና የከበረው ሚስጥር፣ እና በፊታችን የተዘረጋው እጅግ የላቀው መልካም ነገር የቅዱስ ክህነት ሀይላትን በማግኘት ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ ሀቁልፎች ለተሰጡትም ለእርሱ ስለሰው ልጆች፣ ስለሙታን እና ህያዋን ለደህንነት በሚመለከት ተጨባጭ እውቀትን ለማግኘት ችግር አይኖርም።
፲፪ በዚህም ውስጥ ሀግርማ እና ለክብር፣ ሐህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት አለ—የውሀ ጥምቀት ስነስርዓት፣ በዚህም በሞት ምሳሌነት መመጥለቅ፣ አንዱ መሰረታዊ መርህ ከሌላው ጋር እንዲስማማ፤ በውሀ ውስጥ መጠለቅና ከውሀው መውጣት እንደ ሟች ከመቃብር በትንሳኤ በሚነሱበት ምሳሌ ነው፤ ከዚህ በኋላም፣ ይህ ስነስርዓት የተመሰረተውም እንደ ሞት አምሳል የሆነው የሙታን ጥምቀት ስነስርዓትን ግንኙነት ለመስራት ነው።
፲፫ በዚህም ምክንያት፣ ሀየማጥመቂያ ገንዳው የተመሰረተው በመቃብር ለአምሳል ሲሆን በዝቅተኛ ስፍራም የሚቀመጥ ሆኖ፣ እና አንዱም ከሌላው ጋር ይወያይ ዘንድ ለህያዋንም ሆነ ለሙታን ሁሉም ነገር አምሳያ እንዳለው ለማሳየት ህያዋን እንዲሰበሰቡ የታዘዙበት ስፍራ ነው—ጳውሎስ እንዳወጀውም፣ ምድራዊው ከሰማያዊ ጋር ይስማማ ዘንድ ነው፣ ፩ ቆሮንቶስ ፲፭፥፵፮፣ ፵፯፣ እና ፵፰፥
፲፬ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከምድር ምድራዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የመጣ ጌታ ነው። ምድራዊው እንደ ሆነ ምድራዊ የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያዊ የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው። በእውነትም የተመዘገቡት፣ የዚያንም ሙታናችሁን በሚመለከትም ምድራዊ መዛግብት እንዳሉ ሁሉ፣ የሰማያዊ መዛግብትም ይኖራሉ። ስለዚህ ይህም ሀየሚያትም እና የሚያስተሳስር ሀይል ነው፣ እና ቃሉም በአንድ ትርጉም፣ ለበእውቀት ሐቁልፍ ላይ የተመሰረቱ የመንግስት ቁልፎች ናቸው።
፲፭ አሁንም፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሀደህንነታችንን በሚመለከትም፣ እነዚህ ሙታንንና ህያዋንን የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆች በቀላል እንደማይታለፉ ላረጋግጥላችሁ። ደህንነታቸውም ለእኛ ደህንነት አስፈላጊ እና መሰረታዊ ነው፣ ጳውሎስ ስለአባቶች እንዳለው—ያለ እኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም—ወይም እኛ ያለሙታኖቻችን ለፍጹም ልንሆን አንችልም።
፲፮ አሁንም፣ የሙታን ጥምቀት በሚመለከት፣ ሌላ የጳውሎስን ጥቅስ እሰጣችኋለሁ፣ ፩ ቆሮንቶስ ፲፭፥፳፱፥ እንዲያማ ካልሆነ፣ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ? ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ፣ ስለ እነርሱ የሚጠመቁ ስለ ምንድር ነው?
፲፯ ደግሞም፣ ከዚህ ጥቅስ ጋር በተገናኘ አይኑን በክህነት ስልጣን ሀዳግም መመለስ ላይ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ለሚገለጡት ክብሮች፣ እና ከሁሉም ርእሶች በላይ የከበረው ይህ፣ እንዲሁም ለሙታን መጠመቅ በዘለአለም ወንጌል ክፍል ስለሆነው ትኩረትን ሰጥቶት ከነበረው ከነብያቱ የአንዱን ጥቅስ እሰጣችኋለሁ፤ በመጨረሻው ምዕራፍ፣ አንቀፅ ፭ እና ፮ ውስጥ ሚልክያስ እንዳለው፥ እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ለኤልያስን እልክላችኋለሁ። መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
፲፰ ለዚህም ሀግልጽ የሆነ ትርጉም ለመስጠት በቻልኩ ነበር፣ ነገር ግን እንዳለም አላማዬን ያሟላ ዘንድ ይህ በቂ ነው። በዚህ ጉዳይ፣ በአባቶች እና ልጆች መካከል በአንድ በተወሰነ ርዕስ ወይም በሌላ፤ አንድ ወይም ሌላ የሚያስተሳስር ለግንኙነት ከሌለ ምድር በእርግማን እንደምትመታ ማወቁ በቂ ነው—እና እነሆ ያ ርዕስ ምንድን ነው? ይህም ለሙታን ሐመጠመቅ ነው። ያለእነርሱ ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ ወይም እነርሱም ያለእኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም። እነርሱም ይሁን እኛ በወንጌሉ ካልሞቱት በስተቀር ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ አሁን መግባት በጀመረው መየዘመን ፍጻሜ መግቢያ ውስጥ ሙላት እና የተፈጸመ እና ፍጹም አንድነት፣ እና ከአዳም ቀናት እስከ አሁን የተገለጡት የዘመናት፣ ቁልፎች፣ እና ሀይላት፣ እና ክብሮች መተሳሰራቸው አስፈላጊ ነውና። እና ይህም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ከዚህ ምድር ሠመመስረት ጀምሮ ያልተገለጡት፣ ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ተሰውረው የነበሩት፣ እነዚያ ነገሮች ረለህጻናት እና ለሚጠቡት በዚህ በዘመን ፍጻሜ ይገለጣሉ።
፲፱ አሁን፣ በተቀበልነው ወንጌል ውስጥ ምን እንሰማለን? የደስታ ድምፅ! የምህረት ድምፅ ከሰማይ፤ እና ከምድር ውስጥም ሀየእውነትን ድምፅ፤ የምስራች ዜና ለሙታን፤ ከህያውና ከሙታን የደስታ ድምፅ፤ የታላቅ ደስታን ለየምስራች ነው። የምስራች የሚናገር፣ ሠላምን የሚያወራ፣ የመልካምን ወሬ የምስራች የሚናገር፣ ስለመዳን የሚያወራ፣ ፅዮንንም አምላክሽ ነግሶአል! የሚል ሰው ሐእግሮቹ በተራሮች ላይ እጅግ እንዴት ያማሩ ናቸው። እንደ ቀርሜሎስ መጠል፣ እንደዚህም የእግዚአብሔር እውቀት በእነርሱ ላይ ያርፋል!
፳ ደግሞም፣ ምን እንሰማለን? ሀከከሞራ የደስታ ዜና! የሰማይ መልአክ ለሞሮኒ የነቢያትን ፍጻሜ—የሚገለጠውን ሐመፅሀፍ ሲያውጅ። የጌታም ድምፅ መበፈየት፣ በሰነካ የግዛት ክፍል ዱር ውስጥ ሶስቱ ምስክሮች ስለመፅሐፉ ሠእንዲመሰክሩ ሲያውጅ! ረየሚካኤል ድምፅም በሰስኳሀና ወንዝ ዳር ዲያብሎስን እንደ ሰብርሀን መልአክ ሲቀርብ በማየት ሲመረምር! ሸየጴጥሮስ፣ የያዕቆብ፣ እና የዮሐንስ ድምፅ በበረሀ ውስጥ በሀርመኒ፣ ሰስኳሀና የግዛት ክፍል ውስጥ እና በኮልስቪል፣ ብሩም የግዛት ክፍል ውስጥ በሰስኳሀና ወንዝ ላይ ራሳቸውን እንደ መንግስት እና እንደ ዘመን ፍጻሜ ቀቁልፎች ያዥ በመግለፅ ሲያውጁ!
፳፩ ደግሞም፣ በአረጋዊው ሀአባት ዊትመር ቤት ውስጥ በፈየት፣ ሰነካ የግዛት ክፍል ውስጥ እና በተለያዩ ጊዜያት፣ እና በተለያዩ ስፍራዎች በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጉዞዎች እና ፈተናዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ድምፅ! እና ሚካኤል የመላእክት አለቃ ድምፅ፤ ለየገብርኤል፣ ሐየሩፋኤል፣ እና የተለያዩ መመላዕክት፣ ከሚካኤል ወይም ሠከአዳም እስከ አሁን ረዘመን ድረስ፣ በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ ሰበስርዐት ላይ ስርዐትን፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ በመስጠት፤ ወደፊት የሚመጣውን በማወጅ፣ ሸተስፋችንን በማረጋገጥ፣ ማፅናኛ በመስጠት፣ ሁሉም ዘመኖቻቸውን፣ መብቶቻቸውን፣ ቁልፎቻቸውን፣ ክብሮቻቸውን፣ ምስጋናዎቻቸውን፣ እና ክብሮቻቸውን፣ እና የክህነት ሀይሎቻቸውን ሲያውጁ ነው!
፳፪ ወንድሞች፣ ለዚህ ታላቅ ስራ ወደፊት አንሄድምን? ወደኋላ ሳይሆን ወደፊት ሂዱ። በርቱ፣ ወንድሞች፤ እና ወደ ድል ሂዱ! ልባችሁ ይደሰቱ፣ እና በጣምም ተደሰቱ። ምድርም በድንገት ሀትዘምር። ሙታንም ከአለም ፍጥረት በፊት ለተመደበው፣ ለከወህኒም ሐእንድናድናቸው ስላስቻለን ለንጉስ መአማኑኤል የዘለአለማዊ ምስጋና መዝሙርን ይናገሩ፤ እስረኞቹ በነጻ ይሄዳሉና።
፳፫ ሀተራሮችም በደስታ ይጩሁ፣ እና ሸለቆዎች ሁሉ በጎላ ድምፅ አልቅሱ፤ እና እናንት ባህሮች እና ደረቅ ምድራት ሁሉ የዘለአለም ንጉሳችሁን አስደናቂነት ተናገሩ! እና እናንት ወንዞች፣ እና ጅረቶች፣ እና ትንንሽ ወንዞችም በደስታም ፍሰሱ። የሜዳው ጫካዎች እና ዛፎች ሁሉ ጌታን ያመስግኑ! እና እናንት ጠንካራ ለአለቶችም በደስታ አልቅሱ። እና ጸሀይ፣ ጨረቅ፣ እና ሐየአጥቢያ ኮኮቦችም በአንድነት ዘምሩ፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ እልል በሉ። እና ዘለአለማዊ ፍጥረቶችም ስሙን ለዘለአለም ያውጁ። ደግሞም እላለሁ፣ በጆሮዎቻችን ስለክብር፣ እና ደህንነት፣ እና መህያውነት፣ እና ሠስለዘለአለማዊ ህይወት፤ ስለመንግስታት፤ አለቅነትና ስልጣናት የሚያውጀው ከሰማያት የምንሰማው ድምጽ እንዴት የከበረ ነው!
፳፬ እነሆ፣ የጌታ ታላቅ ሀቀን ቀርቧል፤ እና ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን ለመታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን ያቀርቡ ዘንድ፣ እርሱም ብርን ሐእንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ መየሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ሠያነጥራቸዋል። ስለዚህ፣ እንደ ቤተክርስቲያንና እንደ ህዝብ እና እንደ የኋለኛውም ቀን ቅዱሳን የፅድቅ ለጌታ ረመጽዋዕትን እናቅርብ፤ እና በመጨረሻም በቅዱስ ቤተመቅደሱ ውስጥ፣ ለተቀባይነት ሁሉ ብቁ የሆነውን የሙታናችንን ሰመዛግብት የያዘውን መፅሀፍ እናቅርብ።
፳፭ ወንድሞች፣ በዚህ ርዕስ ላይ የምላችሁ ብዙ ነገሮች አሉኝ፤ ነገር ግን ለጊዜው አበቃለሁ፣ እና ርዕሱንም በሌላ ጊዜ እቀጥላለሁ። እኔ፣ እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ትሁት አገልጋያችሁ እና የማይቀየር ባልንጀራችሁ ነኝ፣
ጆሴፍ ስሚዝ።