መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
8. የሽማግሌዎች ቡድን


“8. የሽማግሌዎች ቡድን፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“8. የሽማግሌዎች ቡድን፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ሰዎች በንግግር ላይ

8.

የሽማግሌዎች ቡድን

8.1

ዓላማ እና ድርጅት

8.1.1

ዓላማዎች

እድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ብቁ ወንዶች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ሊቀበሉ እንዲሁም በሽማግሌ የክህነት ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ። በዚያ ክፍል የተሾመ ሰው እግዚአብሔር ሥራውን እንዲያከናውን ይረዳው ዘንድ የተቀደሰ ቃል ኪዳን ይገባል (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 84፥33-44 ን ይመልከቱ)።

8.1.2

በሽማግሌዎች ቡድን አባል መሆን

እያንዳንዱ አጥቢያ የሽማግሌዎች ቡድን አለው። የሚከተሉትን ወንድሞች ያካትታል፦

  • በአጥቢያው ያሉትን ሽማግሌዎች በሙሉ።

  • በአጥቢያው ያሉትን እጩ ሽማግሌዎች በሙሉ (8.4ን ይመልከቱ)።

  • በአሁን ሰዓት በካስማ አመራር ውስጥ፣ በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ፣ በከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ ወይም እንደፓትርያርክ በማገልገል ላይ ካሉት በስተቀር በአጥቢያው ያሉትን ሁሉንም ሊቀ ካህናት።

አንድ ወጣት በሽማግሌ ክፍል ገና ባይሾምም 18 ዓመት ከሞላው በሽማግሌዎች ቡድን መሳተፍ ሊጀምር ይችላል። እድሜው 18 ዓመት ሲሆነው ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ወይም በሚስዮን ለማገልገል ከቤት ሲወጣ ብቁ ከሆነ በሽማግሌ ክፍል መሾም አለበት።

ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ባለትዳሮች እጩ ሽማግሌዎች ናቸው፤ እንዲሁም የሽማግሌዎች ቡድን አባላትም ናቸው።

8.2

በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ መሳተፍ

8.2.1

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

8.2.1.2

የወንጌል መማር ማስተማር በቡድን ስብሰባዎች

ስብሰባዎቹ የሚካሄዱት በወሩ በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁድ ላይ ነው። ለ50 ደቂቃዎች ይዘልቃሉ። የሽማግሌዎች ቡድን አመራር እነዚህን ስብሰባዎች ያቅዳል። ከአመራር አባላት አንዱ ይመራዋል።

የቡድን ስብሰባዎች በጣም የቅርብ ጊዜ በሆነ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግሮች ውስጥ በተውጣጡ ርዕሶች ላይ ያተኩራሉ።

8.2.1.3

አክቲቪቲዎች

የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች አክቲቪቲዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። አብዛኞቹ አክቲቪቲዎች ከእሁድ ወይም ከሰኞ ምሽት ውጪ ባሉት ጊዜያት ይካሄዳሉ።

8.2.2

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት

8.2.2.1

አገልግሎት

የሽማግሌዎች ቡድን አባላት የአገልግሎት የስራ ምደባዎችን ከቡድኑ አመራር ይቀበላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ።

8.2.2.2

የአጭር ጊዜ ፍላጎቶች

የአገልግሎት ወንድሞች የሚያገለግሏቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማወቅ እና ምላሽ ለመስጠት ይፈልጋሉ። አባላት በህመም ጊዜ፣ በውልደት ጊዜ፣ በሞት ጊዜ፣ ከስራ መፈናቀል በሚከሰትበት ጊዜ እና ሌሎች ሁኔታዎች በሚገጥሟቸው ጊዜ የአጭር ጊዜ እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ።

አስፈላጊ ሲሆን አገልጋይ ወንድሞች የሽማግሌዎች ቡድን አመራርን እርዳታ ይጠይቃሉ።

8.2.2.3

የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች እና ራስን መቻል

በኤጲስ ቆጶሱ አስተባባሪነት፣ የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች የአባላትን የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች እና ራስን መቻል እውን በማድረግ ይረዳሉ።

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ወይም ሌላ መሪ ግለሰቡ ወይም ቤተሰቡ ራስን የመቻል እቅድ እንዲያዘጋጁ ይረዳል። አገልጋይ ወንድሞች እና እህቶችም እቅዱን በማዘጋጀት ረገድ ሊረዱ ይችላሉ።

8.2.2.4

አንድ የአጥቢያ አባል በሚሞትበት ጊዜ

አንድ የአጥቢያ አባል በሚሞትበት ጊዜ የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች ማፅናኛ እና ድጋፍ ይሰጣሉ። በኤጲስ ቆጶሱ አመራር በቀብር ሥርዓቱ አፈጸጸም ላይ ሊረዱ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ 38.5.8ን ይመልከቱ።

8.2.3

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቱ የአባላትን የሚስዮናዊ ስራ በመምራት እንዲረዳ ከአመራር አባላቱ አንዱን ይመድባል። እነዚህን ጥረቶች ለማስተባበር ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ከተመደበችው አባል ጋር ይሰራል።

23.5.1 እና 23.5.3ን ይመልከቱ።

8.2.4

ቤተስቦችን ለዘለዓለም ማጣመር

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቱ የአባላትን የሚስዮናዊ ስራ በመምራት እንዲረዳ ከአመራር አባላቱ አንዱን ይመድባል። እነዚህን ጥረቶች ለማስተባበር ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ከተመደበችው አባል ጋር ይሰራል።

25.2፥2ን ይመልከቱ።

8.3

የሽማግሌዎች ቡድን መሪዎች

8.3.1

የካስማ አመራር እና ኤጲስ ቆጶስ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ተጠሪነቱ በቀጥታ ለካስማ አመራር ነው። መመሪያ ለመቀበለል እና የኃላፊነቱን ሪፖርት ለማድረግ ከአመራር አባላት ጋር በየወቅቱ ይገናኛል።

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቱ በአጥቢያው ውስጥ የበላይ መሪ ከሆነው ከኤጲስ ቆጶሱም መመሪያ ይቀበላል። በየወቅቱ ይገናኛሉ።

8.3.2

ከፍተኛ አማካሪ

የካስማ አመራሩ በእያንዳንዱ የሽማግሌዎች ቡድን የሚወክላቸው አንድ ከፍተኛ አማካሪ ይመድባሉ። ኃላፊነቶቹ በ6.5 ውስጥ ተዘርዝረዋል።

8.3.3

የሽማግሌዎች ቡድን አመራር

8.3.3.1

የሽማግሌዎች ቡድን አመራርን መጥራት

ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ከተማከረ በኋላ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ አንድን ሽማግሌ ወይም ሊቀ ካህን የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ሆኖ እንዲያገለግል ይጠራል።

ክፍሉ ትልቅ ከሆነ የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቱ አማካሪዎቹ ሆነው የሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት ሽማግሌዎችን ወይም ሊቀ ካህናትን ለካስማ ፕሬዚዳንቱ በጥቆማ ያቀርባል።

8.3.3.2

ኃላፊነቶች

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዳንት የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦ አማካሪዎቹ ይረዱታል።

  • በአጥቢያ ምክር ቤት ያገለግላል።

  • ቡድኑ በደህንነት እና በዘለዓማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ ለመሳተፍ የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ይመራል (ምዕራፍ 1ን ይመልከቱ)።

  • የአገልጋይ ወንድሞችን አገልግሎት ያደራጃል እንዲሁም በበላይነት ይቆጣጠራል።

  • በኤጲስ ቆጶሱ አመራር ከአጥቢያው ጎልማሳ አባላት ጋር ይማከራል።

  • የሽማግሌዎች ቡድኑ ያላገቡትን እና ያገቡትን ወጣት ጎልማሳ ወንድሞች ለማጠናከር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ያስተባብራል።

  • ከእያንዳንዱ የቡድኑ አባላት ጋር በግለሰብ ደረጃ ቢያንስ በዓመት አንዴ ይገናኛል።

  • የቡድኑን አባላት ስለክህነት ሃላፊነቶቻቸው ያስተምራል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥89ን ይመልከቱ)። ይህም ሥርዓቶችን እና በረከቶችን በማከናወን ክህነታቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ ማስተማርን ይጨምራል።

  • የቡድኑን መዛግብት፣ ሪፖርቶች እና ገንዘብ በበላይነት ይቆጣጠራል LCR.ChurchofJesusChrist.org)ይመልከቱ።

8.3.3.3

የአመራር ስብሰባ

የሽማግሌዎች ቡድን አመራሩ እና ጸሃፊው በየወቅቱ ይገናኛሉ። ፕሬዚዳንቱ እነዚህን ስብሰባዎች ይመራል። ለቡድኑ የተመደበው ከፍተኛ አማካሪ በየጊዜው ይሳተፋል።

የመወያያ አጀንዳዎቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • እጩ ሽማግሌዎችን ጨምሮ የቡድን አባላትን እና ቤተሰባቸውን እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል ማቀድ።

  • የሚስዮናዊ ሥራን እንዲሁም የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራን ማስተባበር።

  • ከአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባዎች ለሚመጡ የስራ ምደባዎች ምላሽ መስጠት።

  • ከአገልግሎት ቃለ መጠይቅ የሚገኙ መረጃዎችን መገምገም።

  • ወንድሞች በጥሪዎች እና በምደባዎች እንዲያገለግሉ ግምት ውስጥ ማስገባት።

  • የቡድን ስብሰባዎችን እና አክቲቪቲዎችን ማቀድ።

8.3.4

ጸሃፊ

በኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ፣ የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባል አንድን የቡድን አባል የቡድኑ ፀሐፊ እንዲሆን ሊጠራ ይችላል።

8.4

እጩ ሽማግሌዎች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እንዲቀበሉ በማዘጋጀት መርዳት

ዕጩ ሽማግሌ ማለት የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ያልተቀበለ እና (1) ዕድሜው 19 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነው ወይም (2) ከ19 ዓመት ያነሰ እና ያገባ ወንድ የቤተክርስቲያኗ አባል ነው።

እጩ ሽማግሌዎች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እንዲቀበሉ በማዘጋጀት መርዳት የቡድኑ አመራር ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው።