መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
36. አዳዲስ ክፍሎችን መፍጠር፣ መለወጠጥ እና መሰየም


“36. አዳዲስ ክፍሎችን መፍጠር፣ መለወጥ እና መሰየም፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]

“36. አዳዲስ ክፍሎችን መፍጠር፣ መለወጠጥ እና መሰየም፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
አንድ ሰው በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርግ

36.

አዳዲስ ክፍሎችን መፍጠር፣ መለወጠጥ እና መሰየም

36.0

መግቢያ

የቤተክርስቲያኗ አባላት በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የአምልኮ መሰብሰቢያ ክፍል አባላት ናቸው(ሞዛያ 25፥17–24ን ይመልከቱ)። እነዚህ የአምልኮ መሰብሰቢያ ክፍሎች በተገቢው የክህነት ስልጣን በመመራት የቤተክርስቲያኗን ስራ ለማደራጀት እና ለመስራት አስፈላጊ ናቸው።

የቤተክርስቲያን የአምልኮ መሰብሰቢያ ክፍሎች (ክፍሎች ተብለውም ይጠራሉ) ካስማዎችን፣ አውራጃዎችን፣ አጥቢያዎቸን እና ቅርንጫፎችን ያካትታሉ። እነርሱም ሲፈለጉ ብቻ ይፈጠራሉ፣ ይለወጣሉ ወይም ይዘጋሉ።

መሪዎች አንድን አዲስ ክፍል ለመፍጠር ወይም የአንድን ክፍል ወሰን ለመቀየር ሃሳብ ከማቅረባቸው በፊት የአባላትን መንፈሳዊ ጥንካሬ ለማሳደግ ይሰራሉ። አዳዲስ ክፍሎች መፈጠር ያለባቸው ነባር ክፍሎቹ በበቂ ሁኔታ ጠንካራ በሚሆኑበት ጊዜ ብቻ ነው።

በዩናይትድ ሰቴትስ እና ካናዳ ውስጥ ድጋፍ ለማግኘት 1-801-240-1007 ይደውሉ። ከዩናይትድ ሰቴትስ እና ከካናዳ ውጪ ድጋፍ ለማግኘት ወደ ዋናው አካባቢው ቢሮ ይደውሉ።