ምዕራፍ ፳፪
እስራኤላውያን በምድር ሁሉ ገፅ ላይ ይበተናሉ—በመጨረሻው ቀናት አህዛብ እስራኤላውያንን በወንጌል ያጠቧቸዋልም ይመግቧቸዋልም—እስራኤላውያን ይሰበሰባሉ፣ ይድናሉም እናም ኃጢአተኞች እንደአገዳ ይነዳሉ—የዲያብሎስ መንግስት ይጠፋል፣ እንዲሁም ሰይጣን ይታሰራል። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ፣ እኔ ኔፊ ሀበነሀስ ሰሌዳዎች ላይ የተፃፉትን ነገሮች ካነበብኩ በኋላ ወንድሞቼ ወደ እኔ መጡና እንዲህ አሉኝ—እነዚህ ያነበብካቸው ነገሮች ምን ማለታቸው ነው? እነሆ እንደስጋ ሳይሆን በመንፈስ እንደሚሆኑት ነገሮች መሰረት መገንዘብ የሚቻሉ ናቸው?
፪ እናም እኔ፣ ኔፊ፣ እንዲህ ስል ተናገርኳቸው—እነሆ እነርሱ ሀበመንፈሱ ድምፅ ለነቢዩ ለተገልፀዋል፤ ለሰዎች ልጆች በስጋ መሰረት የሚመጡት ሁሉም ነገሮች ሐለነቢያት በመንፈስ እንዲያውቁት ይደረጋሉና።
፫ ስለዚህ ያነበብኳቸው ነገሮች ሀከጊዜያዊና መንፈሳዊ ነገሮች ጋር የተገናኙ ናቸው፤ የእስራኤል ቤት በቅርቡ ወይም በኋላ፣ በምድር ገፅ ላይ ሁሉ እናም ደግሞ በሁሉም ሀገሮች መካከል ለሲበተኑ ይታያል።
፬ እናም እነሆ በኢየሩሳሌም ውስጥ ካሉት እውቀት ብዙዎቹ ጠፍተዋል። አዎን ከሁሉም ሀነገዶች ብዙዎች ለተሰደዋል፤ እናም በባህሩ ሐደሴቶች ላይ ወዲህና ወዲያ ተበትነዋል፤ እንዲሁም የት እንዳሉ ማናችንም አናውቅም፣ ነገር ግን ሁላችንም የምናውቀው እነርሱ መሰደዳቸውን ነው።
፭ እናም ስለተሰደዱ፣ እነርሱን በተመለከተና ደግሞ በእስራኤል ቅዱስ ምክንያት ከእዚህ በኋላ ለሚበተኑትና ከሌሎች ሀገሮች ጋር የሚቀላቀሉትን በተመለከተ እነዚህ ነገሮች ተተንብየዋል፤ ምክንያቱም በእርሱ ላይ ልባቸውን ያጠጥራሉና፤ ስለዚህ በሁሉም ህዝቦች መካከል ይበተናሉ፣ እንዲሁም በሁሉም ሀህዝቦች ይጠላሉ።
፮ ይሁን እንጂ፣ በኋላም ሀበአህዛብ ለያጠቧቸዋል፣ እና ጌታ በአህዛብ ላይ እጁን ያነሳል፤ እንደአርማም ያቆማቸዋል፤ ሐልጆቻቸውንም በክንዶቻቸው ላይ ይሸከሟቸዋል፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም በትከሻቸው ይሸከማሉ፣ እነሆ የተነገሩት እነዚህ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸው፤ ጌታ ከአባቶቻችን ጋር የገባቸው ኪዳን እንደዚህም ናቸውና፤ እናም ይህም በሚመጣው ጊዜ እኛንና፣ ደግሞም የእስራኤል ቤት የሆኑት ወንድሞቻችንን ሁሉ ያመለክታል።
፯ እናም ይህ ሁሉም የእስራኤል ቤት ከተበተኑና ከተቀላቀሉ በኋላ፣ አዎን ጌታ እግዚአብሔርም በዚህች ምድር ገፅ ላይ ሀበአህዛብ መካከል ኃያል ህዝብን የሚያስነሳበት ጊዜ ይመጣል፤ እና በእነርሱም ዘሮቻችን ለይበተናሉ ማለት ነው።
፰ እናም ዘሮቻችን ከተበተኑ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሀበአህዛብ መካከል ለዘሮቻችን ታላቅ ለጥቅም የሚሆኑ ሐድንቅ ስራ መስራቱን ይቀጥላል፤ ስለዚህ ይህም በአህዛብ እንደተጠበቁና በክንዶቻቸውና በትከሻቸው እንደተሸከሟቸው ጋር ተመሳስሏል።
፱ እናም ይህ ደግሞ ለአህዛብ ሀጥቅም ይኖረዋል፣ እናም ለአህዛብ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ለለእስራኤል ሐቤት ሁሉና፣ መበዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ሠይባረካሉ በማለት የሰማይ አባት ከአብርሃም ጋር የገባው ረቃልኪዳኖች ለማሳወቅ ነው።
፲ እናም ወንድሞቼ ጌታ ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ሀካልገለጠ በስተቀር የምድር ወገኖች ሁሉ መባረክ እንደማይችሉ እንድታውቁ እፈልጋለሁ።
፲፩ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን እና ወንጌሉን በእስራኤል ቤት ውስጥ ላሉት በመስጠት ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት መግለጥን ይቀጥላል።
፲፪ ስለዚህ ከምርኮ እንደገና ያወጣቸዋል፣ እናም በአንድ ላይ በርስት ምድራቸው ላይ ሀይሰበሰባሉ፤ ለከጨለማና ከጭጋግም ይወጣሉ፤ እናም ሐጌታ መአዳኛቸውና ቤዛቸው የእስራኤልም ሠኃያል መሆኑን ያውቃሉ።
፲፫ እናም የምድር ሁሉ ጋለሞታ የሆነችው ታላቋና ሀየርኩሰት ቤተክርስቲያን ደም በእራሳቸው ላይ ይመለሳል፤ ምክንያቱም በመካከላቸው ለጦርነት ይሆናል፣ እና ሐበእጆቻቸው ያሉ ጎራዴዎቻቸውም በራሳቸው ላይ ይወድቃሉ፣ በራሳቸውም ደም ይሰክራሉ።
፲፬ እናም የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በአንቺ ላይ ለጦርነት የሚነሳ እይስንዳንዱ ሀሀገር እርስ በራስ ይቃወማሉ፣ እናም እነርሱ የጌታን ህዝቦች ለማጥመድ በቆፈሩት ጉድጓድ ለይወድቃሉ። እናም ፅዮንን ሐየሚዋጉ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ትክክለኛውን የጌታን መንገድ የምታስተው ታላቋ ጋለሞታም፤ አዎን ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን ወደ መአፈር ትወድቃለች፤ እንዲሁም ውድቀቷ ታላቅ ይሆናል።
፲፭ እነሆም ሰይጣን በሰዎች ልጆች ልብ ላይ ኃይል የሚያጣበት ጊዜ በፍጥነት ይመጣል ብሎ ነቢዩ ተናግሯል፤ የሚኮሩ እና ኃጢያትን የሚሰሩ ሁሉ እንደ ሀአገዳ የሚሆኑበት ጊዜ ቀኑ በቅርቡ ይመጣልና፤ እና ለመቃጠል የሚገባቸው ጊዜም ይመጣል።
፲፮ በሰዎች ልጆች ላይ ሁሉ የእግዚአብሔር ሀቁጣ የሚወርድበት ጊዜ በቅርቡ ይመጣል፤ ምክንያቱም ኃጢአተኞች ፃድቃኖችን እንዲያጠፉ እርሱ አይፈቅድምና።
፲፯ ስለዚህ እርሱ በኃይሉ ሀፃድቃንን ለይጠብቃል፣ ምንም እንኳን የቁጣው ሙላት መምጣት ቢኖርበትም እናም ጠላቶቻቸውን እንኳ በእሳት እስከማጥፋት ድረስ ፃድቃኖች ይጠበቃሉ። ስለዚህ ፃድቃኖች መፍራት የለባቸውም፤ ምክንያቱም ከእሳትም እንኳን ቢሆን ይድናሉ ብሎ ነቢዩ ተናግሯልና።
፲፰ እነሆ ወንድሞቼ፣ እነዚህ ነገሮች በቅርቡ መሆን አለባቸው እላችኋለሁ፤ አዎን ደምና እሳት፣ እንዲሁም የጭስ ጭጋግ እንኳን መምጣት አለባቸው፤ እናም ይህ በዚህች ምድር ገፅ ላይ መሆን አለበት፤ እናም እነርሱ በእስራኤል ቅዱስ ላይ ልባቸውን ካጠጠሩ ይህም ለሰዎች በስጋ መሰረት ይመጣል።
፲፱ እነሆ ፃድቃኖች አይጠፉም፤ ከፅዮን ጋር የሚዋጉ የሚጠፉበት ጊዜ በእርግጥ መምጣት አለበት።
፳ እናም ሙሴ፥ ጌታ የእናንተ አምላክ እኔን አይነት አንድ ሀነቢይ በመካከላችሁ ያስነሳል፤ ለእናንተ በሚናገራችሁ በሁሉም ነገሮች እናንተ ስሙት ብሎ የተናገራቸው ቃላት ይሟሉ ዘንድ፣ በእርግጥ ጌታ ለህዝቡ መንገድን ያዘጋጃል። እናም እንዲህ ይሆናል ያንን ነቢይ የማይሰማ ከህዝቡ መካከል ለተለይቶ ይጠፋል።
፳፩ እናም አሁን እኔ ኔፊ እናንተን የምናገራችሁ ይህ ሙሴ ስለእርሱ የተናገረለት ሀነቢይ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ እርሱ በፅድቅ ለይፈርዳል።
፳፪ እናም ፃድቃን መፍራት የለባቸውም፣ ምክንያቱም እነርሱ የሚደባለቁ አይደሉምና። ነገር ግን ይህ በሰዎች ልጆች መካከል የተመሰረተው የዲያብሎስ መንግስት ነው፣ መንግስቱም በስጋ በተሸፈኑት መካከል የተመሰረተው ነው—
፳፫ ሀብትን ለማግኘት የተመሰረቱት ሀቤተክርስቲያኖች ሁሉ፣ የስጋ ኃይልን ለማግኘት የተመሰረቱት ሁሉ፣ እናም በዓለም ዐይናት ለታዋቂ ለመሆን የተመሰረቱትና፣ የስጋቸውን ፍላጎት ለማርካትና የዓለምን ነገሮች ለሚሹ፣ እንዲሁም ሁሉንም አይነት ኃጢያት ለማድረግ ለሚሹ ጊዜው በፍጥነት ይመጣል፤ አዎን በአጠቃላይ በዲያብሎስ መንግስት አባል የሆኑት ሁሉ ሊፈሩ፣ ሊንቀጠቀጡና ሐሊናወጡ ይገባቸዋል፤ እነርሱም መዋረድ ያለባቸው ናቸው፣ እነርሱም እንደአገዳ መመንደድ ያለባቸው ናቸው፣ እናም ይህ እንደነቢዩ ቃላት ነው።
፳፬ እናም ፃድቃኖች እንደሰባ ሀእምቦሳ የሚመሩበትና፣ የእስራኤል ቅዱስ በበላይነት በስልጣንና በኃይል፣ እንዲሁም በታላቅ ክብር የሚነግስበት ጊዜ በፍጥነት ይመጣል።
፳፭ እናም እርሱ ልጆቹን ከአራቱም የምድር ማዕዘናት ሀይሰበስባል፤ እናም በጎቹንም ይቆጥራል፣ እነርሱም ያውቁታል፤ እናም አንድ መንጋና አንድ ለእረኛ ይሆናሉ፤ እርሱም በጎቹን ይመግባል፣ እነርሱም በእርሱ ሐሰማሪያ ያገኛሉ።
፳፮ እናም በህዝቦቹ ፅድቅ ምክንያት ሀሰይጣን ኃይል የለውም፤ ስለዚህ ለለብዙ ዓመታት ሊፈታ አይችልም፤ ምክንያቱም እርሱ በሰዎች ልብ ላይ ስልጣን የለውም፣ እነርሱ በፅድቅ ይኖራሉ፣ እናም የእስራኤል ቅዱስ ሐይነግሳልና።
፳፯ እናም አሁን እኔ ኔፊ እንዲህ እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በስጋ መምጣት አለባቸው።
፳፰ ነገር ግን እነሆ ሁሉም ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና፣ ህዝቦች ሀንስሀ ከገቡ ከእስራኤል ቅዱስ ጋር በደህንነት ይኖራሉ።
፳፱ እናም አሁን እኔ ኔፊ አቆማለሁ፤ ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች በተመለከተ አሁን ከዚህ የበለጠ ለማለት አልደፍርም።
፴ ስለዚህ ወንድሞቼ ሀበነሀስ ሰሌዳዎቹ ላይ የተፃፉት ነገሮች እውነት እንደሆኑ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ እናም እነርሱ ሁሉም ሰው ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት ታዛዥ መሆን እንዳለበት ይመሰክራሉ።
፴፩ ስለዚህ እናንተ እኔና አባቴ ብቻ ይህንን የመሰከርን፣ እናም ደግሞ ስለ እነርሱ ያስተማርን ነን በማለት ማሰብ የለባችሁም። ስለዚህ እናንተ ሀለትዕዛዛቱ ታዛዥ ከሆናችሁና እስከመጨረሻው ከፀናችሁ በመጨረሻው ቀን ትድናላችሁ። እናም እንዲህም ነው። አሜን።