ምዕራፍ ፲
ሌሂ አይሁዶች በባቢሎናውያን በምርኮ እንደሚወሰዱ ተነበየ—ከአይሁዶች መካከል መሲህ፣ አዳኝና፣ መድኃኒት እንደሚመጣ ተናገረ—እንዲሁም ሌሂ የእግዚአብሔርን በግ የሚያጠምቀው እንደሚመጣ ተናገረ—ሌሂ የመሲሁን ሞትና ትንሣኤ ተናገረ—እርሱም የእስራኤልን መበተንና መሰባሰብ ከወይራ ዛፍ ጋር አነፃፀረ—ኔፊ ስለእግዚአብሔር ልጅ፣ ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታና፣ ስለፅድቅ አስፈላጊነት ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እና አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ ሀበእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ የእኔን ድርጊትና ንግስና አገልግሎት ታሪኬን በመፃፍ እቀጥላለሁ፤ ስለዚህ፣ በእኔ ታሪክ ለመቀጠል፣ የአባቴን ደግሞም የወንድሞቼን ነገሮች በመጠኑ መናገር አለብኝ።
፪ እነሆም፣ እንዲህ ሆነ አባቴ ሀስለህልሙ መናገሩን፣ እናም እነርሱን በሙሉ ትጋት መምከር ከጨረሰ በኋላ፣ አይሁዶችን በተመለከተ ተናገራቸው—
፫ እነርሱም ከጠፉ በኋላ፣ እንዲሁም ያቺ ታላቂቷ ከተማ ሀኢየሩሳሌምና ብዙዎች ሕዝቦቿ በምርኮ ወደ ለባቢሎን ሐከተወሰዱ በኋላ፣ ጌታ በጊዜው መሰረት እንደገና መይመለሳሉ፣ አዎን፣ ከምርኮ ወጥተው ይመለሳሉ፤ እናም ከምርኮም ወጥተው ከተመለሱ በኋላ፣ እንደገናም የርስት ምድራቸው ባለቤት ይሆናሉ።
፬ አዎን፣ አባቴ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ሀከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ፣ ጌታ እግዚአብሔር ከአይሁዶች መካከል ለነቢይን፣ እንዲሁም ሐመሲሁን ወይም በሌላ አነጋገር የዓለምን መድኃኒት ያስነሳል።
፭ እናም፣ ደግሞ እርሱ ነቢያትን በተመለከተ፣ እርሱ ስለተናገረበት መሲህን ወይም ይህ የአለም አዳኝን በሚመለከት ስለእነዚህ ነገሮች እንዴት ታላቅ ቁጥር ያላቸው ሀእንደመሰከሩ ተናገረ።
፮ ስለዚህ በዚህ መድሐኒት ካልታመኑ በስተቀር ሁሉም የሰው ዘር በመሳትና ሀበውድቀት ላይ ነበሩ፣ እናም ለዘለአለምም ይሆናሉ።
፯ እናም ደግሞ እርሱ ከመሲሁ፣ በፊት የጌታን መንገድ ለማቅናት ስለሚመጣው ሀነቢይ ተናገረ—
፰ አዎን፣ ወደ ምድረበዳው ሄዶ እንዲህ በማለት ይጮሃል፥ የጌታን መንገድ ሀአቅኑ፣ ጥርጊያውንም አዘጋጁ፣ እናንተ የማታውቁት አንዱ ከመካከላችሁ ቆሟልና፤ እናም እርሱም የጫማውን ጠፍር ለመፍታት ብቁ ያልሆንኩ ከእኔ የበረታ ነው። እናም ይህንን ነገር በተመለከተ አባቴ ብዙ ተናገረ።
፱ እናም አባቴ ከዮርዳኖስ ባሻገር ሀቤተ ባራ ውስጥ እርሱ እንደሚያጠምቅ ተናገረ፣ ደግሞም እርሱ በውሃ ለእንደሚያጠምቅ ተናገረ፤ መሲሁንም ቢሆን በውሃ ያጠምቀዋል።
፲ እናም እርሱ መሲሁን በውሃ ካጠመቀ በኋላ፣ የዓለምን ኃጢያት የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን ሀበግ ማጥመቁን እርሱ እንዲሁም ይመሰክራል።
፲፩ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ በአይሁዶች መካከል ስለሚሰበከው ወንጌል፣ ደግሞም ስለአይሁዶች ሀእምነት በማጣት ለመመንመን ለወንድሞቼ ነገራቸው። እናም ዳግም የሚመጣውን መሲሕ ሐከገደሉ በኋላና እርሱም ከተገደለ በኋላ፣ ከሞት መይነሳል፣ እናም እራሱን ሠበመንፈስ ቅዱስ ለአህዛብ ይገልጣል።
፲፪ አዎን፣ አባቴ አህዛቦችን በሚመለከትና የእስራኤልን ቤት በሚመለከት፣ እነርሱንም ልክ ቅርንጫፎቹ እንደወደበቁት ሀወይራ ዛፍ በመነፃፀረና በምድር ላይ ሁሉ ለመበታተን እንደሚገባቸው ብዙ ተናገረ።
፲፫ የጌታ ቃል ይፈፀም ዘንድ፣ በምድር ላይ ሁሉ መበተን አለብን፣ ስለዚህ እኛ ወደ ሀቃልኪዳኑ ምድር በአንድነት ሆነን መሔድ እንደሚያስፈልገን ተናገረ።
፲፬ እናም የእስራኤል ቤቶች ከተበተኑ በኋላ እንደገና በአንድ ላይ ሀመሰብሰብ አለባቸው፤ ወይም ለአህዛብ የወንጌልን ሙሉነት ከተቀበሉ በኋላ፣ ሐየወይራው ዛፍ ተፈጥሮአዊ ቅርንጫፎች፣ ወይም በአጠቃላይ የእስራኤል ቤት ቅሪት ይጣበቃሉ፣ ወይም የእነርሱ መድሐኒትና ጌታ ወደሆነው እውነተኛ መሲሕ እውቀት ይመጣሉ።
፲፭ እናም አባቴ በዚህ አይነት አነጋገር ተነበየ፣ እንዲሁም ለወንድሞቼና በዚህ መፅሐፍ ላይ ያልጻፍኳቸውን ሌሎች ብዙ ነገሮች ተናገረ፣ እኔ ግን ለእኔ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች ሀበሌላኛው የራሴ መፅሐፍ ፅፌአለሁ።
፲፮ እናም እነዚህ ሁሉ እኔ የተናገርኳቸው ነገሮች የተደረጉት አባቴ በልሙኤል ሸለቆ በድንኳን ተቀምጦ ሳለ ነበር።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ የአባቴን ሀቃላት ሁሉ ከሰማሁ በኋላ፣ እርሱ ለበራዕይ ስላያቸው ነገሮችና ደግሞ በእግዚአብሔር ልጅ ባለው እምነት በተቀበለው መንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለተናገራቸው ነገሮች፤ እናም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ሐመሲሁ ነው፤ እኔም፣ ኔፊ ደግሞ መበትጋት እርሱን ለፈለጉት ሁሉ እንደ ሠጥንት ጊዜው አሁንም ቢሆን እራሱን ለሰው ልጆች በሚገልጥበት በእግዚአብሔር ስጦታ ረበመንፈስ ቅዱስ ኃይል እነዚህን ነገሮች እመለከት እንዲሁም እሰማና አውቅ ዘንድ ፈለግሁ።
፲፰ እርሱ ትናንትም ዛሬም እስከዘለዓለም ሀያው ነውና፤ ንስሀ የሚገቡና ወደ እርሱ የሚመጡ ከሆነ፣ መንገዱ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ለሰዎች ሁሉ ተዘጋጅቷል።
፲፱ በትጋት የሚፈልግ ያገኛልና፣ የእግዚአብሔር ሀሚስጥሮች ለእነርሱ እንደጥንቱም ጊዜ ቢሆን በሚመጡትም ጊዜያት ለበመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይገለጥላቸዋል፣ ስለዚህ፣ የጌታ ሐመንገድ አንድ ዘለዓለማዊ ዙሪያ ነው።
፳ ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ አስታውስ፣ ለሥራህ ሁሉ ሀወደፍርድ ትቀርባለህና።
፳፩ ስለዚህ ሀበሙከራ ዘመንህ መጥፎ ነገሮችን ማድረግ ከፈለግህ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት ለሳትፀዳ ትገኛለህ፣ እናም ምንም እርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር አይቻለውም፣ ስለዚህ ለዘለዓለም ትጣላለህ።
፳፪ እናም መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች እናገርና እንዳልደብቃቸው ዘንድ ስልጣን ሰጥቶኛል።