ምዕራፍ ፰
ሌሂ ስለ ሕይወት ዛፍ ራዕይ አየ—ከፍሬውም ተካፈለና ቤተሰቦቹም እንደዚያው እንዲያደርጉ ፈለገ—የብረት በትር፣ የጠበበና የቀጠነ መንገድና ሰዎችን የሚጋርደውን የጨለማ ጭጋግ ተመለከተ—ሳርያ፣ ኔፊና፣ ሳም፣ ፍሬውን ተካፈሉ፣ ላማንና ልሙኤል ግን ተቃወሙ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ ከሁሉም ዓይነት ዘሮች ሁሉንም የእህል ዓይነትና፣ ከሁሉም ዓይነት የፍራፍሬ ዘሮች በአንድነት ሰበሰብን።
፪ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ በምድረበዳ በቆየበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ተናገረን፥ እነሆ ህልምን ሀአልሜአለሁ፣ ወይም በሌላ አባባል፣ ለራዕይን አይቻለሁ።
፫ እናም እነሆ ባየሁት ነገር የተነሳ ሀበኔፊና ደግሞም ስለሳም በጌታ የምደሰትበት ምክንያት አለኝ፣ እና እነርሱና ብዙዎቹ ዘሮቻቸው እንደሚድኑ ለመገመት ምክንያት አለኝ።
፬ ነገር ግን እነሆ ሀላማንና ልሙኤል፣ በእናንተ ምክንያት እጅግ እፈራለሁ፤ እነሆ በህልሜ ውስጥ ጨለማና የማያስደስት ምድረበዳ ማየቴን ተረዳሁ።
፭ እናም እንዲህ ሆነ አንድ ሰው አየሁ፣ ነጭ ሀልብስ ለብሶ ነበር፤ እናም መጥቶ በፊቴ ቆመ።
፮ እናም እንዲህ ሆነ እርሱም ተናገረኝ፣ እናም እንድከተለው ጋበዘኝ።
፯ እናም እንዲህ ሆነ እርሱን እንደተከተልኩት ራሴንም በጭለማ እና በማያስደስት ባድማ ውስጥ እንደነበርኩ ተመለከትኩ።
፰ እናም ለብዙ ሰዓታት በጨለማ ውስጥ ከተጓዝኩ በኋላ እንደምህረቱም ብዛት ጌታ በእኔ ላይ ሀምህረትን ያደርግ ዘንድ ፀለይኩ።
፱ እናም እንዲህ ሆነ ለጌታ ከፀለይኩ በኋላ፣ ትልቅና ሰፊ የሆነን ሀሜዳ ተመለከትኩ።
፲ እናም እንዲህ ሆነ ሀፍሬዋ አንድን ሰው ደስተኛ ለማድረግ መልካም የሆነችን ለዛፍ ተመለከትኩ።
፲፩ እናም እንዲህ ሆነ ሄጄ ሀከፍሬዋ ተካፈልኩ፤ ከዚህ በፊት ከቀመስኩት ሁሉ ጣፋጭ እንደሆነች አየሁ። አዎን፣ ፍሬዋም ከዚህ በፊት ካየሁትም ንጣት ሁሉ በላይ ለነጭ የሆነች ፍሬ እንደሆነች ተመለከትኩ።
፲፪ ከዚህች ፍሬ ስካፈልም ይህም ነፍሴን ሀበደስታ ሞላው፣ ስለሆነም ቤተሰቦቼም ደግሞ ይካፈሉት ዘንድ ለመመኘት ጀመርኩ፤ ከሌላው ፍሬ ሁሉ በላይ ሐአስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁና።
፲፫ እናም ቤተሰቤን ደግሞ ማግኘት እችል ዘንድ በዙሪያው ስመለከት፣ ሀየወንዝ ውሃን ተመለከትኩ፤ ይወርድም ነበር፣ እና እኔ ፍሬውን ከበላሁበት ዛፍ አቅራቢያ ነበር።
፲፬ እናም ከየት እንደመጣም ለማየት ተመለከትኩ፣ ትንሽ ራቅ ብሎም ምንጩን አየሁ፤ እናታችሁ ሳርያን፣ ሳምንና፣ ኔፊን፣ በዚያው በምንጩ አየሁ፤ እነርሱም ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እንደማያውቁ ሆነው ቆሙ።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ጠቆምኳቸው፣ ወደ እኔ እንዲመጡና ከሌሎች ፍሬዎች ሁሉ በላይ መልካም የሆነውን ፍሬ፣ እንዲበሉ በከፍተኛ ድምፅ ነገርኳቸው።
፲፮ እናም እንዲህ ሆነ እነርሱ ወደ እኔ መጡና ደግሞ ፍሬውን በሉ።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ላማንና ልሙኤልም እንዲመጡና ደግሞ ፍሬውን እንዲበሉ ተመኘሁ፣ ስለሆነም እንዳያቸው ዘንድ አይኖቼን ወደ ወንዙ ምንጭ ጣልኩኝ።
፲፰ እናም እንዲህ ሆነ እኔ አየሁአቸው፣ ነገር ግን እነርሱ ወደ እኔ ሀአልመጡም፣ ፍሬውንም አልበሉም።
፲፱ እናም ሀየብረት በትር ተመለከትኩ፣ በወንዙም ዳርቻ፣ እኔ ወደ ቆምኩበት ዛፍ ድረስ እንዲወስድ የተዘረጋ ነበር።
፳ እናም እኔ ወደ ቆምኩበት ዛፍ ከብረት በትሩ ጋር የሚወስድ ሀየጠበበና የቀጠነ መንገድ ተመለከትኩ፣ ይህም ደግሞ በፏፏቴውም ምንጭ፣ ዓለምን ወደሚመስለው ትልቅና ሰፊ ለሜዳ ያመራል።
፳፩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎችን አየሁ፣ እኔ ወደ ቆምኩበት ዛፍ የሚያደርሰውን ሀመንገድ ለማግኘት አብዛኞቹ ወደፊት ይገፉ ነበር።
፳፪ እናም እንዲህ ሆነ መጡ፣ እና ወደዛፉ በሚያመራው መንገድ ወደፊት ተጓዙ።
፳፫ እናም እንዲህ ሆነ የጨለማ ሀጭጋግ ተነሳ፣ አዎን በመንገዱ ጉዞ የጀመሩት መንገዳቸውን እስኪስቱና ተንከራተው እስኪጠፉ ድረስ እጅግ ታላቅ የጨለማ ጭጋግ ተነሳ።
፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ሌሎች ደግሞ ወደፊት ሲጋፉ አየሁ፣ እናም እነርሱም ወደፊት መጡና የብረት በትሩን ጫፍ ያዙ፣ የብረቱን በትር ተጠግተው በጨለማው ጭጋግ ውስጥ ወደፊት መጥተው የዛፉን ሀፍሬ እስኪካፈሉ ድረስ ወደፊት ገፉ።
፳፭ እናም ከዛፉ ፍሬ ከተካፈሉ በኋላ ሀያፈሩ በመምሰል አይኖቻቸውን ወደ እዚህና ወደ እዚያ ጣሉ።
፳፮ እኔም ደግሞ አይኖቼን በዙሪያው ጣልኩኝ፣ እና ከውሃው ወንዝ ባሻገር፣ ትልቅና ሀሰፊ ህንፃን ተመለከትኩ፤ ከምድር ከፍ ብሎ በአየር ላይ የቆመ ይመስል ነበር።
፳፯ እናም በአረጋውያን ጎልማሳም፣ በወንድም በሴትም ሰዎች ተሞልቶ ነበር፣ አለባበሳቸውም እጅግ ያማረ ነበር፤ ፍሬውንም መጥተው ወደበሉት ላይ እጃቸውን እየጠቆሙና ሀእየተሳለቁባቸው ነበር።
፳፰ በእነዚያ በሚያላገጡባቸውም ምክንያት፣ ፍሬውን ሀከቀመሱ በኋላ ለአፈሩ፤ ወደተከለከለውም መንገድ ሐገቡና ጠፉ።
፳፱ እና አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ የአባቴን ቃላት ሀበሙሉ አልናገርም።
፴ ነገር ግን፣ ፅሁፉን ለማሳጠር፣ እነሆ ብዙ ሌሎችም ወደፊት ሲጋፉ አየ፤ መጥተው ሀየብረት በትሩን ጫፍ ያዙ፣ እና ወደፊት መጥተው እስኪወድቁና የዛፉን ፍሬ እስኪካፈሉና እስኪወድቁ ድረስ መንገዳቸውን ወደፊት በመቀጠል ያለማቋረጥም የብረቱን በትር አጥብቀው ያዙ።
፴፩ እና ደግሞ ሌሎችም ሀብዙዎች ወደትልቁና ሰፊው ህንፃ መንገዳቸውን ሲያቀኑ አየ።
፴፪ እናም እንዲህ ሆነ ብዙዎች ወደ ሀፏፏቴው ጥልቅ ሲመጡ፤ እና ብዙዎች ደግሞ በማይታወቅ መንገድ ገብተው ሲቅበዘበዙ ከዕይታው ጠፉ።
፴፫ እና ወደ ማይታወቀው ህንፃ የገቡት ታላቅ ብዛት ነበራቸው። ወደ ህንፃው ከገቡም በኋላ በእኔና ፍሬውን ይካፈሉ በነበሩት ላይ ደግሞ ሀየፌዝ ጣታቸውን ይጠቁሙ ነበር፤ ነገር ግን እኛ አላደመጥናቸውም።
፴፬ እነዚህ የአባቴ ቃላት ነበሩ፥ ሀያደመጡዋቸው በሙሉ ጠፍተዋል።
፴፭ እና አባቴ ሀላማንና ልሙኤል ፍሬውን አልተካፈሉም አለ።
፴፮ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ ብዙ የነበሩትን የህልሙን ወይንም የራዕዩን ቃላት ከተናገረ በኋላ፣ ለእኛ እንዲህ አለን፣ በራዕዩ ባየው ነገር የተነሳ፣ ለላማንና ለልሙኤል በእጅጉ ፈራላቸው፣ አዎ፣ ከጌታ ፊት እንዳይጣሉ ፈራላቸው።
፴፯ እና ምናልባት ጌታ ለእነርሱም መሐሪ እንዲሆንላቸውና እንዳይጥላቸው ዘንድ፣ የእርሱን ቃላት እንዲሰሙ በአፍቃሪ ሀወላጅ ሙሉ ስሜት መከራቸው፤ አዎን፣ አባቴ ለእነርሱ ሰበከላቸው።
፴፰ እናም ለእነርሱ ከሰበከላቸውና፣ ብዙ ነገሮችን ለእነርሱ ከተነበየላቸው በኋላ፣ የጌታን ትዕዛዛት እንዲጠብቁ አዘዛቸው፣ እናም ለእነርሱ መናገርን አቆመ።