ምዕራፍ ፳፯
ኢየሱስ ቤተክርስቲያኗን በስሙ እንዲጠሩ አዘዛቸው—ወንጌሉም አገልግሎቱንና የኃጢያት ክፍያውን የያዘ ነው—ሰዎች በመንፈስ ቅዱስም ይነፁ ዘንድ ንሰሃ እንዲገቡና እንዲጠመቁ ታዘዋል—ኢየሱስ እንደሚሆነውም ይሁኑ። ከ፴፬–፴፭ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በተጓዙበት እናም ስለተመለከቱአቸውና ስለሰሙአቸው ነገሮች በሰበኩበትና፣ በኢየሱስ ስም ባጠመቁበት ወቅት፣ እንዲህ ሆነ ደቀመዛሙርቱ ሀበአንድ ላይ ተሰባስበው ነበር፣ እናም በብርቱ ፀሎታቸውና ለፆማቸው አንድ ሆነው ነበር።
፪ እናም ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ ወደ አብ በስሙ በመፀለያቸው በድጋሚ ራሱን ሀአሳያቸው፤ እናም ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆመ፣ እንዲህም አላቸው፥ ምን እንድሰጣችሁ ትፈልጋላችሁ?
፫ እናም እንዲህ አሉት፥ ጌታ ይህንን ቤተክርስቲያን የምንጠራበትን ስም እንድትነግረን እንፈልጋለን፤ ምክንያቱም ይህንን በተመለከተ በህዝቡ መካከል ጥል አለና።
፬ እናም ጌታም እንዲህ አላቸው፥ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ህዝቡ ስለዚህ ነገር ለምን ያጉረመርማል እንዲሁም ይጣላል?
፭ ስሜ የሆነውን፣ ሀየክርስቶስን ስም በእራሳቸው ላይ መውሰድ እንዳለባቸው ቅዱሳን መጻሕፍትን አላነበቡምን? በዚህ ስም በመጨረሻው ዘመን ትጠሩበታላችሁና፤
፮ እናም ስሜን በራሱ ላይ የወሰደና፣ እስከመጨረሻው በዚህ ሀየፀና በመጨረሻው ዘመን እርሱ ይድናል።
፯ ስለዚህ፣ ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ በስሜ አድርጉት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን በስሜ ጥሯት፤ እናም ወደ አብም በስሜ ፀልዩ እርሱም ለእኔም ሲል ቤተክርስቲያኗን ይባርካታል።
፰ እናም በስሜ ካልተጠራ ሀየእኔ ለቤተክርስቲያን እንዴት ሊሆን ይችላል? ቤተክርስቲያኗ በሙሴ ስም ከተጠራች የሙሴ ቤተክርስቲያን ትሆናለች፤ ወይም በሰው ስም ከተጠራች የሰው ቤተክርስቲያን ትሆናለች፤ ነገር ግን በወንጌሌ ላይ የተገነቡ ከሆኑ፣ በስሜ ከተጠራች የእኔ ቤተክርስቲያን ትሆናለች።
፱ እውነት እላችኋለሁ፣ በወንጌሌ ላይ ታንፃችኋል፤ ስለዚህ የምታደርጉትን ማንኛውንም ነገር በስሜ ትጠራላችሁ፤ ስለዚህ ለቤተክርስቲያኗ ወደ አብ በስሜ ከፀለያችሁ አብ ይሰማችኋል፤
፲ እናም ቤተክርስቲያኗ በወንጌሌ ላይ ከታነፀች አብም ስራውን ይገልፅባታል።
፲፩ ነገር ግን በወንጌሌ ላይ ካልታነፀች፣ እናም በሰዎች ስራ ላይ፣ ወይም በዲያብሎስ ስራ ላይ ከታነፀች፣ እውነት እላችኋለሁ ለጊዜው በስራቸው ደስታን ያገኛሉ፣ እናም ከጥቂት ጊዜም በኋላ ፍፃሜአቸው ይመጣልም፣ እናም ሀይፈረካከሳሉም፣ መመለስ በማይቻልበት እሳት ውስጥም ይወድቃሉ።
፲፪ ስራቸው ሀይከተላቸዋልና፣ በስራቸው ምክንያትም ተቆርጠው ወድቀዋልና፤ ስለዚህ የነገርኳችሁን ነገሮች አስታውሱ።
፲፫ እነሆ ሀወንጌሌን ሰጥቻችኋለሁ፣ እናም ለእናንተ የሰጠኋችሁ ወንጌልም ይህ ነው—ወደ ዓለም የመጣሁት የአባቴን ለፈቃድ ለመፈፀም ነው፣ ምክንያቱም አባቴ ልኮኛልና።
፲፬ አባቴም በመስቀል ሀእሰቀል ዘንድ ልኮኛል፤ እናም በመስቀል ላይ ከተሰቀልኩ በኋላ፣ ሰዎችን ሁሉ ወደ ራሴ ለአመጣ ዘንድ፣ እኔ በሰዎች እንደተሰቀልኩ በአብ አማካኝነት ሰዎች ይነሱ ዘንድ፣ መልካምም ይሁኑ መጥፎ በስራቸው ሐእንዲፈረድባቸው በእኔ ፊት ለመቆም ይችሉ ዘንድ፣ ተሰቅያለሁ—
፲፭ እናም ለዚህም ምክንያት ሀተሰቀልኩኝ፤ ስለዚህ፣ በአብ ስልጣን መሰረት ሰዎች በሙሉ በስራቸው ይፈረድባቸው ዘንድ ወደ እኔ እንዲመጡ አደረግሁ።
፲፮ እናም እንዲህ ይሆናል ማንኛውም ሀንሰሃ የገባና በስሜ ለየተጠመቀ ይሞላል፤ እናም እስከመጨረሻው ሐከፀናም እነሆ ዓለምን የምፈርድበት ቀን ስትመጣ በአብ ፊት ከበደል የነፃ አደርገዋለሁ።
፲፯ እናም እስከመጨረሻው ፀንቶ የማይቀጥል ግን በአብ ሀፍትህ የተነሳ፣ ተቆርጦ መጨረሻ ወደሌለው፣ ወደእሳቱ የሚጣል እርሱ ነው።
፲፰ እናም ለሰው ልጆች የሰጣት ይህች ቃል ናት። እናም በዚህ የተነሳ የተሰጠውን ቃላት ይፈፅማል፣ እናም አይዋሽም፣ ነገር ግን ቃሉን በሙሉ ይፈፅማል።
፲፱ እናም በመንግስተ ሰማይ ሀምንም እርኩስ ነገር ሊገባ አይቻለውም፤ ስለዚህ በእምነታቸው እናም ለኃጢአታቸው ሁሉ ንሰሃ በመግባታቸውና እስከመጨረሻው ባላቸው ታማኝነት በደሜ ልብሳቸውን ለካጠቡት በስተቀር ሐበእረፍቱ የሚገባ ማንም የለም።
፳ እንግዲህ ትዕዛዜ ይህች ናት፥ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ሀንሰሃ ግቡ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ለትቀደሱ ዘንድ፤ በመጨረሻው ቀን በፊቴ ሐያለእንከን ትቆሙ ዘንድ ወደ እኔ ኑ፣ እናም በስሜ መተጠመቁ።
፳፩ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ የእኔ ወንጌል ነው፤ እናም በቤተክርስቲያኔም መስራት ያለባችሁንም ነገሮች ታውቃላችሁና፤ እኔ ስሰራው ያያችሁትን ስራ እናንተም ደግሞ ስሩ፤ ስሰራ ያያችሁትን ስራ እናንተም ያን ታደርጋላችሁ፤
፳፪ ስለዚህ፣ እነዚህን ነገሮች ከሰራችሁ የተባረካችሁ ናችሁ፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ ትላላችሁና።
፳፫ ሀከተከለከሉት በስተቀር ስላያችኋቸው እናም ስለሰማችኋቸው ነገሮች ፃፉ።
፳፬ ወደ ፊት የሚሆን የእነዚህን ሰዎች ስራ ቀድሞ እንደነበረው አድርጋችሁ ፃፉት።
፳፭ እነሆም፣ ከተፃፉት እናም ከሚፃፉት መጽሐፍት ይህ ህዝብ ሀይፈረድበታል፣ ምክንያቱም በእነርሱ አማካኝነት ለስራዎቻቸው ለሰዎች ይታወቃሉና።
፳፮ እናም እነሆ፣ ሁሉም ነገሮች በአብ ሀተጽፈዋል፤ ስለዚህ በተፃፉት መጽሐፍት መሠረትም ዓለም ይፈረድበታል።
፳፯ እናም ጻድቅ በሚሆነው ለእናንተ በሰጠኋችሁ ፍርድ መሰረት በዚህ ህዝብ ሀእንደምትፈረዱባቸው ታውቃላችሁ። ስለዚህ፣ እናንተ ምን ለዐይነት ሰዎች መሆን ይገባችኋል? እውነት እላችኋለሁ ሐእንደ እኔ ሁኑ።
፳፰ እናም እንግዲህ ሀወደ አብ እሄዳለሁ። እናም እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማናቸውንም ነገሮች በስሜ ብትጠይቁት ለእናንተ ይሰጣችኋል።
፳፱ ስለዚህ፣ ሀለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ እናም ይከፈትላችኋል፤ የሚጠይቅ ያገኛልና፤ እናም ለሚያንኳኳም ይከፈትለታልና።
፴ እናም እንግዲህ፣ እነሆ፣ በእናንተና ደግሞ በዚህ ትውልድ ምክንያት ሙሉ እስከሚሆን ድረስ ደስታዬ ታላቅ ነው፤ አዎን፣ እናም በእናንተና በዚህ ትውልድ ምክንያት አብና ደግሞ ቅዱስ የሆኑ መላዕክቶች ሁሉ ተደስተዋል፤ ምክንያቱም ከእነርሱም ማንም ሀአልጠፋምና።
፴፩ እነሆ፤ ምክንያቱም ሀበዚህ ትውልድ ለበህይወት ስላሉት ስለእነርሱ እንደተናገርኩ እንድትረዱ እፈልጋለሁ፣ እናም ማናቸውም አይጠፉም፤ እናም በእነርሱ ሙሉ ሐደስታዬን አግኝቻለሁ።
፴፪ ነገር ግን እነሆ፣ ከዚህ ትውልድ ሀአራተኛው ትውልድ ልክ በጥፋት ልጅም እንደሆነው በምርኮ ስለሚወሰዱ፣ እኔን አሳዝኖኛል፤ ምክንያቱም እነርሱ ለብርና ለወርቅ፣ እናም ለበብልም ለሚበላሸውና ሌቦች ሊሰብሩትና ሊሰርቁት ለሚችሉት ይሸጡኛል። እናም በዚያን ቀን ስራቸውንም በራሳቸው ላይ በመመለስ እጎበኛቸዋለሁ።
፴፫ እናም እንዲህ ሆነ ኢየሱስ ይህንን ንግግሩን በጨረሰበት ወቅት ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ ሀበጠበበው ደጅ ግቡ፤ እናም ወደ ህይወት የሚወስደው ደጁ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ስለሆነ፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸውና፤ ነገር ግን ወደ ሞት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነው፣ እናም ምሽቱ እስከሚመጣ ሰዎችም መስራት እስከማይችሉበት ድረስ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙ ናቸው።