ምዕራፍ ፱
በጭለማው ውስጥ፣ የክርስቶስ ድምጽ በክፋታቸው የተነሳ የብዙ ሰዎችን እንዲሁም የከተሞቹን ጥፋት አወጀ—መለኮታዊነቱንም ደግሞ አወጀ፣ የሙሴ ህግም እንደተሟላም አስታወቀ፣ እናም ሰዎችም ወደ እርሱ እንዲመጡ፣ እናም እንዲድኑ ጋበዛቸው። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ ገጽ ሁሉ ላይ ባሉ ነዋሪዎቹ መካከል አንድ ሀድምፅ መጥቶ እንዲህ ሲል መጮኹ ተሰማ፥
፪ ለዚህ ህዝብ ሀወዮ፣ ወዮ ወዮለት፣ ንሰሃ ካልገቡ በስተቀርም ለምድር ነዋሪዎች በሙሉ ወዮላቸው፤ መልካም የሆኑት የህዝቦቼ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በመገደላቸው ዲያብሎስ ለይስቃል፣ እናም መላዕክቶቹም ይደሰታሉና፤ እናም በክፋታቸውና በእርኩሰታቸው የተነሳ ነው የወደቁት!
፫ እነሆ፣ ታላቋን የዛራሄምላን ከተማ እናም ነዋሪዎችዋን በእሳት አቃጥያቸዋለሁ።
፬ እናም እነሆ፣ ታላቋን የሞሮኒን ከተማና በዚያም የሚገኙትን ነዋሪዎች በባህሩ ጥልቅ እንዲሰጥሙም አድርጌአለሁ።
፭ እናም እነሆ፣ ክፋታቸውንና ርኩሰታቸውን ከፊቴ ለመሸሸግ፣ የነቢያቱ እናም የቅዱሳን ደም ከእንግዲህ በኔ ላይ እንዳይመጣ ታላቋን የሞሮኒሀን ከተማና ነዋሪዎችዋን በመሬት ውስጥ ሸፍኜአቸዋለሁ።
፮ እናም እነሆ፣ የጌልገላ ከተማ እንድትሰጥም እናም በዚያን ስፍራ የሚገኙት ነዋሪዎችም በምድሪቱ ውስጥ እንዲቀበሩ አድርጌአለሁ፤
፯ አዎን፤ እናም የኦኒሀ ከተማና ነዋሪዎችዋ፤ እናም የሞኩም ከተማና ነዋሪዎችዋ፤ እናም የኢየሩሳሌም ከተማና ነዋሪዎችዋ፤ ከእንግዲህ ወዲያ የነቢያቱና የቅዱሳን ደም በእነርሱ ላይ ወደ እኔ እንዳይመጣ ክፋታቸውን እናም ርኩሰታቸውን ከፊቴ ለመሸሸግ በስፍራቸው ሀውሃ እንዲመጣባቸው አደረግሁ።
፰ እናም እነሆ፣ የጋድያንዲን ከተማና፣ የጋድዮምናን ከተማ፣ እናም የያዕቆብን ከተማና፣ የጊምጊምኖን ከተማ፣ በሙሉ እንዲሰምጡ አደረኳቸው፣ እናም በስፍራው ሀኮረብታዎችንና ሸለቆዎችን ሰራሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የነቢያቱና፣ የቅዱሳን ደም በእነርሱም ላይ ወደ እኔ እንዳይመጣ ክፋታቸውን፣ እናም ርኩሰታቸውን ከፊቴ ለመሸሸግ በስፍራው የነበሩትን ነዋሪዎች በመሬት ውስጥ ቀበርኳቸው።
፱ እናም እነሆ፣ ከምድር ኃጢአቶች ሁሉ በላይ በነበረው ኃጢአቶቻቸውና ክፋቶች፤ ሀበሚስጥራዊው ግድያቸው፣ እንዲሁም በህብረታቸው የተነሳ ታላቋ ከተማ የንጉስ ያዕቆብ ህዝብ የሰፈረባት ያዕቆቡጋትን በእሳት እንድትቃጠል አደረግሁ፤ ምክንያቱም እነርሱ ነበሩ የህዝቤን ሠላም እናም የምድሪቱን አገዛዝ ያጠፉት፤ ስለዚህ ከእንግዲህም ወዲያ የነቢያቱምና የቅዱሳን ደም በእነርሱም ላይ ወደ እኔ እንዳይመጣ ከፊቴም ለለማጥፋት እንዲቃጠሉ አደረግሁ።
፲ እናም እነሆ፣ ስለ ኃጢአታቸውና ርኩሰታቸው እንዲናገሩ የላኳቸውን ነቢያት በማስወጣት በሰሩት ክፋትና፣ በድንጋይ ስለወገሩአቸው፣ የላማን ከተማና፣ የኢዮሽ ከተማ፣ እናም የጋድ ከተማና፣ የቂሽቁመንን ከተማ፣ እንዲሁም ነዋሪዎቻቸው በእሳት እንዲቃጠሉ አደረግሁ፤
፲፩ እናም ሁሉንም አስወጥተው ስለወረወሩአቸው፣ በመካከላቸውም ምንም ፃድቅ የሆነ ባለመኖሩ በመካከላቸውም የላኳቸው ነቢያትና፣ ፃድቃኖች ደም ሀከመሬት ወደ እኔ እንዳይጮህ ክፋቶቻቸው፣ እናም ርኩሰታቸው ከፊቴም ይደበቁ ዘንድ ለእሳት ላኩባቸውና፣ አጠፋቸው።
፲፪ እናም በክፋቶቻቸውና በርኩሰታቸው የተነሳም በዚህች ምድር፣ እናም በዚህ ህዝብ ላይ ሀብዙ ታላቅ ጥፋቶች እንዲሆኑ አደረግሁ።
፲፫ አቤቱ ከእነርሱ የበለጠ ፃድቅ በመሆናችሁ እናንተ ሀየተረፋችሁትን ሁሉ ለእፈውሳችሁ ዘንድ ለኃጥያታችሁ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን?
፲፬ አዎን በእውነት እላችኋለሁ፣ ወደ እኔ ሀከመጣችሁ ለዘለዓለማዊ ህይወትን ታገኛላችሁ። እነሆ የምህረት ሐክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ፣ እናም ወደ እኔ የሚመጡ የተባረኩ ናቸው።
፲፭ እነሆ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ የሆንኩኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። ሰማያትንና ምድርን፣ እናም በውስጧ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ሀፈጥሬአለሁ። ከመጀመሪያው ጀምሮ ከአብ ጋር ነበርኩኝ። ለእኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ አለ፤ በእኔም የአብ ስሙን አስከብሯል።
፲፮ የእኔ ወደሆኑት መጣሁና፣ የራሴ የሆኑትም ሀአልተቀበሉኝም። እናም የእኔን መምጣት በተመለከተ ቅዱሳን መጻሕፍት ተፈጽመዋል።
፲፯ እናም ለተቀበሉኝ ሁሉ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሀሰጠኋቸው፣ እናም በስሜ ለሚያምኑትም ሁሉ እንዲህም አደርጋለሁ፣ እነሆም በእኔም ለቤዛነት ይመጣልና በእኔም የሙሴ ሐህግ ተፈፀሟል።
፲፰ እኔ የአለም ሀብርሃንና ህይወት ነኝ። ለአልፋና ኦሜጋ፤ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ነኝ።
፲፱ እናም ከእንግዲህ ደምን በማፍሰስ ሀአታበረክቱልኝም፤ አዎን፣ መስዋእቶቻችሁና የሚቃጠሉት መስዋእቶች ማንኛውንም ስለማልቀበል መስዋእቶቻችሁ እናም የሚቃጠሉት መስዋእቶቻችሁ ይቆማሉ።
፳ እናም ለእኔም ሀመስዋእት የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ ታቀርባላችሁ። እናም ወደ እኔም በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ የሚመጣ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ለአጠምቀዋለሁ፤ ላማናውያንን እንኳን ቢሆን በመለወጣቸው ወቅት በእኔ በነበራቸው እምነት የተነሳ በእሳት እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ እንደተጠመቁት፣ እናም ይህንንም አያውቁም ነበር።
፳፩ እነሆ ዓለምን ከኃጢያት ለማዳን ለዓለም ቤዛነትን ለማምጣት ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
፳፪ ስለዚህ ሀንሰሃ የሚገባን እናም እንደህፃን ለልጅ ወደ እኔ የሚመጣንም እቀበለዋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግስትም እንደነዚህ ላሉት ናትና። እነሆ፣ እንደነዚህ ላሉትም ህይወቴን ሐሰጥቻለሁና፣ እናም በድጋሚም አንስቼዋለሁ፤ ስለዚህ የምድር ዳርቻ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ ወደ እኔም ኑና፣ ዳኑ።