ምዕራፍ ፫
ሽማግሌዎች እጃቸውን በካህናት እናም በመምህራን ላይ በመጫን ሾሙአቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ የቤተክርስቲያኗ ሀሽማግሌዎች ተብለው የሚጠሩት ደቀመዛሙርት ካህናትን እና መምህራንን ለየሚሾሙበት ስርዓት—
፪ ወደ አብ በክርስቶስ ስም ከፀለዩ በኋላ፣ እጃቸውን ጭነውባቸው እንዲህ አሉ፥
፫ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ካህን እንድትሆን (መምህር ከሆነ መምህር እንድትሆን)፣ ንሰሃን እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ሀለኃጢአታቸው ስርየትን በስሙ እስከመጨረሻው በእምነት በመፅናት እንደሚያገኙ እንድትሰብክ እሾምሃለሁ። አሜን።
፬ እናም በዚህ ስርዓት ለሰዎች በእግዚአብሔር ሀስጦታና ጥሪ መሰረት ካህናትን እናም መምህራንን ለይሾሙ ነበር፤ እናም በውስጣቸው ባለው በመንፈስ ቅዱስ ሐኃይልም ሾሙአቸው።