ኢየሱስ ክርስቶስ
የውሀ ጸሎት


የውሀ ጸሎት

አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣
ይህንን ውሀ የሚጠጡት ነፍሳት ሁሉ ለእነርሱ የፈሰሰውን
የልጅህን ደም በማስታወስ ያደርጉት ዘንድ፣
ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱ ለአንተም፣
አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣
ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ እንዲኖራቸው፣
ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን።
አሜን።