2010–2019 (እ.አ.አ)
በመፅሐፉ ውስጥ ኃይል አለ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


በመፅሐፉ ውስጥ ኃይል አለ

በእርግጥም፣ የመፅሀፈ ሞረሞን ታላቁ ኃይል እኛን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቅረብ ውስጥ ያለው ተፅእኖ ነው።

ሰኔ  1989 ላይ፣ ስለ ቤተክርስቲያኑ ባለው በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የጋና መንግስት በዛ የአፍሪካ ሀገር ላይ ያለውን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከሁሉም እንቅስቃሴዎች አገደ። መንግሰቱ የቤተክርስቲያን ንብረቶችን ሁሉ ያዘ፣ እናም ሁሉም የምስዮናዊ ስራ ቆመ። መታገድ ብለው ይህንን ጊዜ የሚገልፁት፣ የቤተክርስቲያን አባላት፣ ያለ ቅርንጫፍ ስብሰባዎች ወይም ያለ ምስዮናዊያን እርዳታ ወንጌልን ለመኖር የተቻላቸውን አደረጉ። በቤታቸው ውስጥ በማምለክ እና የቤት ለቤት እና የጉብኝት አስተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን አንዳቸው ለአንዳቸው እንክብካቤ በማድረግ አባላት እንዴት የወንጌል ብርሃንን ማብራቱን እንዳስቀጠሉ የሚያሳዩ ብዙ የሚያነሳሱ ታሪኮች አሉ።

በስተመጨረሻም ያለመግባባቱ ተፈታ፣ እናም ህዳር 30፣ 1990 (እ.አ.አ) ላይ፣ መታገቱ አበቃ እና የተመለዱት የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች እንደገና ጀመሩ።1 ከዛ ሰዓት ጀምሮ፣ በቤተክርስቲያኑ እና በጋና መንግስት መካከል በጣም ግሩም የሆነ የእርስ በእርስ ግንኙነት ኖሯል።

ቤተክርስቲያኑ በታገደበት ወቅት የነበሩ አባላት ከዛ ያልተለመደ ወቅት የመጡትን በረከቶች ለይቶ ለማሳየት ፈጣኖች ናቸው። በተጋፈጡት መከራ ምክንያት የብዙዎች እምነት ተጠናክሮ ነበር። ነገር ግን የመታገዱ አንድ በረከት ባልተለመደ መንገድ መጣ።

ኒኮላስ ኦፎሶ ሄኔ፣ ቤተክርስያኑ በታገደበት ወቅት የኋለኛ ቀን ቁዱሳን ማምለኪያ ቦታን እንዲጠብቅ የተመደበ ወጣት ፖሊስ ነበር። ግዴታው ህንፃውን በለሊት የመጠበቅ ነበር። ኒኮላስ መጀመሪያ የማምለኪያው ቦታ ሲደርስ፣ በወረቀቶች፣ በመፅሀት፣ እናም የቢሮ እቃዎች ስርኣት ባልያዘ መልኩ እቃዎቹ በዙሪያ ተበታትነው አየ። በዚህ ብትንትን ባሉ እቃዎች መካክል፣ መፅሀፈ ሞረሞንን አየ። መፅሀፉን ችላ ሊለው ሞከረ ምክንያቱም ርኩስ እንደሆነ ተነግሮት ስለነበር። ነገር ግን እንግዳዊ በሆነ መልኩ በእሱ ተሳበ። በስተመጨረሻም መፅሀፉን ችላ ሊለው አልቻለም። አነሳው። ማንበብ መጀመር እንዳለበት አስገዳጅ ስሜት ተሰማው። ለሊቱን ሙሉ አነበበ፣ መፅሀፉን በሚያነብበት ጊዜ፣ በጉንጮቹ ላይ እምባዎቹ ፈሰሱ።

መፅሀፉን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነሳው፣ 1 ኔፊን በሙሉ አነበበ። ሁለተኛው ጊዜ ላይ፣ 2 ኔፊን በሙሉ አነበበ። 2 ኔፊ ምእራፍ 25ላይ ሲደርስ የሚከተለውን አነበበ፥ “እናም ስለ ክርስቶስ እንናገራለን፣ በክርስቶስ እንደሰታለን፣ ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን፣ ስለ ክርስቶስ ትንቢት እንናገራለን፣ በትንቢታችን መሰረት እንፅፋለን፣ ስለዚህ ልጆቻችን ለሀጢያታቸው ስርየት የትኛውን መንገድ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ።”2

በዚያን ሰዓት፣ ኒኮላስ ስቅስቅ ብሎ እስኪያለቅስ ድረስ በጠንካራ ሁኔታ መንፈስ ተሰማው። በማንበቡ ሂደት ውስጥ ይህ ቅዱስ መፅሀፍ እንደሆነ አና አንብቦ ከሚያውቃቸው መፅሀፍ የበለጠ ትክክል እንደሆነ ብዙ መንፈሳዊ መነሳሳትን እንደተቀበለ ተረዳ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ሰምቶት ከነበረው በተቃራኒ መልኩ፣ በጠንካራ ሁኔታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያምኑ ተረዳ። መታገዱ ካበቃ በኋላ ምስዮናውያን ወደ ጋና ተመለሱ፣ ኒኮላስ፣ እና ሚስቱ እና ልጆቹ ቤተክርስቲያኑን ተቀላቀሉ። ያለፈው አመት ሳየው፣ የፖሊስ አዛዥ ነበር እናም የጋና ታማሌ ቤተክርስቲያን እንደ አውራጃ ፕሬዘዳንት ሆኖ ያገለግል ነበር። እንዲህ አለ፣ “ቤተክርስቲያኗ ህይወቴን ለውጣታል። … እኔን ወደ ወንጌል ስለመራኝ ሀያሉ አምላክን አመሰግናለሁ።”3

አልበርት ዴቪስ፣ ሌላኛው ጋናዊ ነው፣ ጓደኛው የአመራር ስብሰባ ወዳለበት፣ ከማምለኪያ ቦታዎቻችን ከሆኑት በአንዱ አብሮት ሄደ። ጓደኛውን እየጠበቀ ሳለ፣ አልበርት በአቅራቢያው ያገኘውን መፅሀፍ አነበበ። ስብሰባው ሲያልቅ፣ አልበርት መፅሀፉን ወደ ቤት መውሰድ ፈለገ። ያንን መፅሀፍ እንዲወስድ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የመፅሀፈ ሞርሞን ቅጅንም እንዲወስድ ተፈቀደለት። እቤት ሲደርስ፣ መፅሀፈ ሞርሞን ማንበብ ጀመረ። ማስቀመጥ አልቻለም ነበር። እስከ ለሊቱ 9 ሰዓት ድረስ በሻማ ብርሃን አነበበ። ይህንንም ለብዙ ምሽቶች አደረገ፣ ባነበበው እና በተሰማው ነገር ተነካ። አልበርት አሁን የቤተክርስቲያን አባል ነው።

አንጄሎ ስካረፑላ፣ በተወለደበት ጣልያን ላይ የ 10አመት ልጅ ሳለ የሀይማኖት ትምህርት ማጥናት ጀመረ። በስተመጨረሻም ቄስ ሆኖ ቤተክርስቲያኑን በታማኝነት አገለገለ። የሆነ ወቅት ላይ እምነቱ ላይ ጥርጣሬን ያሳድር ጀመር፣ እናም ተጨማሪ የትምህርት እድልን ፈለገ አናም አገኝ። ቢሆንም፣ የበለጠ ሲያጠና፣ የበለጠ መጨነቅ ጀመር። ባነበበው እና በተሰማው ስሜት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እና በቀደምት ሐዋሪያት ከተሰጠው ትክክለኛ ትምህርት አጠቃላይ ክህደት እንደነበር አሳመነው። አንጀሎ የእግዚያብሔርን ትክክለኛ ቤተክርስቲን በተለያዩ እምነቶች ውስጥ ፈለገ ነገር ግን ለብዙ አመታት አጥጋቢ ሆኖ አልተሰማውም ነበር።

ምስዮናውያን ተጨማሪ ሰዎችን አግኝተው እንዲያስተምሩ እያገዙዋቸው የነበሩ ሁለት የቤተክርስቲያን አባላትን አንድ ቀን አገኛቸው። ወደ እነሱ እንደተሳበ ተሰማው እናም በደስታ መንፈስ መልእክታቸውን አዳመጠ። አንጀሎ በፍቃደኝነት የመፅሀፈ ሞርሞን ቅጅን ተቀበለ።

በዛን ቀን ምሽት መፅሀፉን ማንበብ ጀመረ፣ በደስታ እንደተሞላ ተሰማው። በመንፈስ አማካኝነት፣ ለብዙ አመታት ሲፈልግ የነበረውን እውነት በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ እንደሚያገኘው እግዚያብሔር በአንጀሎ ውስጥ ማረጋገጫን ሰጠው። ጣፋጭ ስሜቶች በውስጡ ፈሰሱ። ያነበበው እና ከምስዮናውያን የተማረው አጠቃላይ ክህደት ተከስቶ ነበር ብሎ የሰጠውን ማጠቃለያ አረጋገጠለት፣ ነገር ግን የእግዚያብሔር ቤተክርስቲያን ወደ ምድር እንደተመለሰም ተምሯል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ አንጀሎ ወደ ቤተክርስቲያን ተጠመቀ።4 ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኘው፣ የእኛ ቤተክርስቲያን የሪሚኒ ጣሊያን ቅርንጫፍ ፕሬዘዳንት ነበር።

ከመፅሀፈ ሞርሞን ጋር ኒኮላ እና አልበርት ያገኙት ተሞክሮ የፓርሊ ፒ. ፕራት ልምድ ተምሳሌት ነው፤

“[መፅሀፉን] ለማወቅ በመፈለግ ጉጉት ከፈትኩት። …ቀኑን ሙሉ አነበብኩ፣ መመገብ ሸክም ነበር፣ ለምግብ ምንም ፍላጎት የለኝም ነበር፣ ምሽቱ ሲመጣ … መተኛት ሸክም ነበር፣ ምክንያቱም ከመተኛት ማንበብ መርጬ ነበርና።

በማነብበት ጊዜ፣ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነበር፣ እናም አንድ ሰው በቀላል እና በተገለፀ መንገድ እራሱ በህይወት እንዳለ መረዳት እና ማወቅ ልክ እነደሚችለው ያህል መፅሀፉ እውነት እንደነበር አውቄ እና ተረድቼ ነበር። አንዳንዶች መፅሀፈ ሞርሞንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱት እንደዚህ አይነት ኃይል ያለው ልምድ ሊኖራቸው ይችላል።”5

አንዳንድ ሰዎች መፅሐፈ ሞርሞንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱት ሀያል ተሞክሮን ያገኛሉ፣ ነገር ግን ለሌሎች ደግሞ ሲያነቡት እና ስለ እሱ ሲፀልዩ የበለጠ ቀስ በቀስ የእውነት ሙላት ምስክርነት ይመጣል። ለእኔ እንደዛ ነበር። እንደ ሴሚናሪ ወጣት ተማሪ መፅሀፈ ሞርሞንን ለመጀመሪያ ጊዜ አነበብኩ። ይሄ ያኔ ያነበብኩት የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጅ ነው፣ ይህ የተከሰተበትን ትክክለኛ ጊዜ እና ቦታ ልነግራችሁ አልችልም፣ ነገር ግን በማነብበት ሰዓት ሆነ ቦታ ላይ፣ የሆነ ነገርን መረዳት ጀመርኩ። መፅሀፉን በከፈትኩት ሰዓት ሁሉ የጋለ ስሜት እና መንፈስ ይመጣ ነበር። ማንበቤን ስቀጥል ስሜቱም አብሮ አደገ። ያ ስሜት ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። መፅሀፈ ሞረሞን በከፈትኩ ሰዓት ሁሌም፣ ልክ ማብሪያና ማጥፊያውን እንደማብራት ነው— መንፈስ በልቤ እና በነፍሴ ውስጥ ይፈሳል።

ለሌሎች ደግሞ፣ የመፅሀፈ ሞርሞን ምስክርነት ዝግ ባለ ሁኔታ ነው የሚመጣው፣ ብዙ ካጠኑ እና ከፀለዩ በኋላ። እውነት እንደሆነ ለማወቅ በመፈለግ መፅሀፈ ሞረሞንን ያነበበ ጓደኛ አለኝ። በንፁህ ልባችሁ፣ ከእውነተኛ ስሜት በክርስቶስ ስም አምናችሁ መፅሀፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ መጠየቅ፣የሚለውን በሞሮኒ ውስጥ ያለውን ግብዣ ተገበረ።6 ነገር ግን ወዲያው ቃል የተገባውን መልስ አላገኘም። ቢሆንም፣ አንድ ቀን በመንገድ ወደ ታች እየነዳ፣ በጥልቅ ሀሳብ ውስጥ ሳለ፣ መንፈስ ቅዱስ የመፅሀፈ ሞረሞን እውነትን መሰከረለት። የመኪናውን መስኮት ወደታች አውርዶ፣ ለሆነ ሰው በግል ባይሆንም ለአለም ሁላ መፅሀፈ “እውነት ነው!” ብሎ ሲጮህ በጣም ደስተኛ እና ጥልቅ ስሜት ነበረው።

የመፅሀፈ ሞርሞን ምስክርነታችን መጀመሪያ ስንከፍተው ቢመጣ ወይም ከጊዜ በኋላም ይምጣ፣ ማንበባችንን የምንቀጥል ከሆነ እና ትምህርቶቹን የምንተገብር ከሆነ በጊዜያችን ላይ ሁሉ ተፅእኖ ያመጣል። ኤዝራ ቴፍት ቤንሰን እንዲህ አስተማሩ፤ “መፅሀፉን በቁም ነገር ማጥናት በጀመራችሁ በዛው ሰዓት በህይታችሁ ውስጥ የሚፈስ ኃይል በመፅሀፍ ውስጥ አለ። ፈተናን ለመቋቋም ታላቅ ኃይል ታገኛችሁ። መታለልን ለማስወገድ ኃይልን ታገኛላችሁ። በቀጥተኛው እና በጠባቧ መንገድ ለመቆየት ኃይልን ታገኛላችሁ።”7

ይህንን መልእክት የሚቀበሉትን ሁሉ፣ የመፅሀፈ ሞርሞንን ኃይል ለማግኘት፣ ዛሬ በዚህ ምሽት በዚህ ስብሰባ ላይ በአንድ ላይ የተሰባሰቡትን የአሮን ክህነት ተሸካሚዎችንም ጨምሮ፣ ሁሉንም አበረታታለሁ። ልክ ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳበረታቱን፤ መፅሀፈ ሞርሞንን አንብቡ፣ ትምህርቶቹን አሰላስሉ። እውነት እንደሆነ የሰማይ አባትን ጠይቁ።”8 በዚህ ሂደት ውስጥ የእግዚያብሔርን መንፈስ በህይወታችሁ ውስጥ ይሰማችኋል። መፅሀፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እውነተኛ ነብይ እንደነበር፣ እናም የኃለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዛሬ በምድር ላይ ያለ ትክክለኛ የእግዚያብሔር ቤተክርስቲያን እንደሆነ መንፍስ ቅዱስ የምስክርነታችሁ አካል ይሆናል። ያ ምስክርነት ፈተናን እንድትቋቋሙ ይረዳችኋል።9 “በጌታ የወይን ስፍራ ለመስራት … ለታላቅ የትጋት ጥሪ” ያዘጋጃችኋል።10 እምነታችሁን ለመፈታተን ወቀሳዎች ወይም ሀሜታዊ አረፍተ ነገሮችን እናንተ ላይ ሰዎች ሲጠቀሙ እንደ ማይነቃነቅ መልህቅ ሆኖ ይቆምላችኋል እናም ቢያንስ ወዲያው፣ መመለስ በማትችሉት ጥያቄዎች ስትፈተኑ ጠንካራ የአለት መሰረት ይሆናል። እውነትን ከስህተት ለመለየት ትችላላችሁ፣ እናም በድጋሚ መፅሀፈ ሞርሞንን በህይወታችሁ ውስጥ ሁሉ ማንበብ ስትቀጥሉ ምስክርነታችሁን በድጋሚ የሚያረጋግጥ መንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ ይሰማችኋል።

እንዲሁም ይህንን መልእክት የሚሰሙትን ወይም የሚያነቡትን ወላጆች መፅሀፈ ሞርሞንን ጠቃሚው የቤታችሁ አካል እንድታደርጉት አበረታታለሁ። ልጆቻችን በሚያድጉበት ጊዜ፣ ቁርስ እየበላን መፅሀፈ ሞርሞንን እናነባለን። ይህ ስንጠቀም የነበረው የገፅ ማስታወሻ ነው። ከፊት ለፊቱ ላይ ፕሬዘዳንት ቤንሰን መፅሀፈ ሞረሞንን ካነበብን እግዚያብሔር በረከቱን በእኛ ያፈሳል ብለው ቃል የገቡት ጥቅስ አለ።11 ከኋላው ደግሞ ቀደም ብሎ የመጀመሪያው አመራር ላይ አማካሪ የነበሩት፣ ፕሬዘዳንት ማሪኦን ጂ. ሮምኒ የገቡት ቃል አለ “በቤቶቻችን፣ ወላጆች በፀሎት መንፈስ በቋሚነት በመፅሀፈ ሞርሞንን የሚያነቡ ከሆነ፣ እነሱ እና ልጆቻቸው፣ የታላቁ መፅሀፍ መንፈስ ቤታችንን እና በቤት ውስጥ የሚኖሩት ላይ ሁሉ ይጥለቀለቃል። የጠብ መንፈስ ይርቃል። ወላጆች ልጆቻቸውን በታላቅ ፍቅር እና ጥበብ ይመክራሉ። ልጆች ኃላፊነት ይሰማቸውዋል እንዲሁም ለወላጆቻቸው ምክር የበለጠ ይታዘዛሉ። ፅድቅና ይጨምራል። እምነት፣ ተስፋ እና የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር የሆነው—ልግስና፣ በቤታችን እና በህይወታች ውስጥ ይበዛል፣ ሰላምን፣ ሀሴትን፣ እና ደስታን እንደተነሱ ያመጣል።”12

አሁን ልጆቻችን ከቤት ከወጡ ከብዙ አመታት በኋላ፣ እናም የራሳቸውን ቤተሰብ እያሳደጉ ነው፣ የፕሬዘዳንት ሮምኒ ቃል መሟላት በግልፅ ማየት እንችላለን። ቤተሰባችን ፍፁም ከመሆን በጣም የራቀ ነው፣ ነገር ግን የመፅሀፈ ሞርምን ኃይልን እናም እሱን በማንበብ የመጡት በረከቶች እና በመላው ቤተሰባችን ህይወት ላይ በረከት ማምጣቱን ስለመቀጠለ መመስከር እንችላለን።

በእርግጥም፣ የመፅሀፈ ሞረሞን ታላቁ ኃይል እኛን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቅረብ ውስጥ ያለው ተፅእኖ ነው። በእርግጥም፣ የመፅሀፈ ሞረሞን ታላቁ ኃይል እኛን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቅረብ ውስጥ ያለው ተፅእኖ ነው። የእርሱ እና የማዳን ተልእኮው ጠንካራ ምስክርነት ነው።13 በርሱ አማካኝነት የቤዛነቱን ግርማ እና ኃይልን ወደ መረዳት እንመጣለን።14 የእርሱን ትምህርት በግልፅ ያስተምራል።15 እናም የተነሳው ክርስቶስ ኔፋዊያን ጋር አደረገውን ጉብኝት በሚገልፀው እፁብ ድንቅ በሆነው ምእራፍ ምክንያት፣ እናን ሰዎችን ሲወዳቸው፣ ሲባርካቸው፣ እናም ሲያስተምራቸው ያለውን እናያለን እንዲሁም እንለማመዳለን፣ እናም የእሱን ወንጌል በመኖር ወደ እሱ ከመጣን ለእኛም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግልን ወደ መረዳት እንመጣለን።16

ወንድሞች፣ የመፅሀፈ ሞርሞን ኃይልን እመሰክራለሁ። በእንግሊዘኛ፣ በጣሊያንኛ፣ ወይም በፈረንሳይኛ ፣ የታተመውን ወይም በኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ላይ ባነብም፣ ከምእራፎቹ እና ከቁጥሮቹ ተመሳሳይ የሚያስገርም መንፈስ ወደ እኔ ህይወት እንደፈሰሰ ተረድቻለሁ። ወደ ክርስቶስ እንድንቀርብ ስላለው አቅምን መሰክራለሁ። በዚህ አስገራሚ ቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ያለውን ኃይል እያንዳንዳችን ሙሉ ጥቅም እንድንወስድ እፀልያለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “‘You Can’t Close My Heart’: ጋናዊ ቅዱሳ እና እገዳው፣” ጥር 6፣ 2016 (እ.አ.አ)፣ history.lds.org ተመልከቱ።

  2. 2 ኔፊ 25፥26

  3. ከኒኮላስ ኦፎስ-ሄኔ የመጣ ኢሜል፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (እ.አ.አ)።

  4. አንጄሎ ስካርፑላ፣ “My Search for the Restoration፣” Tambuli፣ ሰኔ 1993 (እ.አ.አ)፤ ከኢዚኖ ካራሚያ የመጣ ኢሜል፣ መስከረም 16፣ 2016 (እ.አ.አ)።

  5. Autobiography of Parley P. Pratt, ed. Parley P. Pratt Jr. (1938), 37.

  6. ሞሮኒ 10፥4–5 ተመልከቱ።

  7. Teachings of Presidents of the Church: Ezra Taft Benson (2014), 141.

  8. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Dare to Stand Alone፣” Liahona፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፤ ደግሞም ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Priesthood Power፣” Liahona፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 66 ተመልከቱ፤ A Prophet’s Voice Messages from Thomas S. Monson፣ (2012)፣ 490–94።

  9. ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ አስተማሩ “ሁሉም የክህነት ተሸካሚ የቀን ተቀን ቅዱስ መፅሀፍትን ጥናት መለማለድ አለበት። …የአሮን ወይም የመልከፀዲቅ ክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች ብትሆኑም፣ በትጋት ቅዱሻን መፀሀፍትን ብታጠኑ፣ ፈተናን ለማስወገድ እናም በምታደርጉት ነገር ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ምሬትን ለመቀበል ያላችሁ ኃይል ያድጋል” (“Be Your Best Self፣” Liahona፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 68)።

  10. አልማ 28፥14

  11. “ከዚህ ጊዜ ጀምሮ፣ [ከመፅሀፈ ሞርሞን] ገጾች በየቀኑ የምንመገብ ከሆንን እና በአስተያየቱ ከኖርን፣ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የፅዮን ልጅ ላይ እና በቤተክርስቲያኗ ላይ ከዚህ በፊት የማይታወቅ በረከት ያፈሳል” (Teachings: Ezra Taft Benson፣ 127)።

  12. ማሪዮን ጂ. ሮምኒ፣ “The Book of Mormon፣” Ensign፣ ግንቦት 1980 (እ.አ.አ)፣ 67።

  13. ለምሳሌ የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገጽን፤ 1 ኔፊ 112 ኔፊ 25ሞዛያ 1618አልማ 5 12ሔላማን 53 ኔፊ 9ሞርሞን 7 ተመልከቱ።

  14. ለምሳሌ 2 ኔፊ 22 ኔፊ 9ሞዛያ 3አልማ 734 ተመልከቱ።

  15. ለምሳሌ 2 ኔፊ 313 ኔፊ 11 27 ተመልከቱ።

  16. 3 ኔፊ 11–28 ተመልከቱ።