2010–2019 (እ.አ.አ)
ክርስቶስ ጌታ ዛሬ ተነስቷል
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


ክርስቶስ ጌታ ዛሬ ተነስቷል

ይህ የፋሲካ እሁድ ነው። ስለህያው ክርስቶስ፣ “ለሞተው፣ ስለተቀበረው፣ እና በሶስተኛው ቀን ከሞት ስለተነሳው” እርሱም በአምልኮ እመሰክራለሁ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ወንድ ልጆቻችን ትንሽ በነበሩበት ወቅት፣ ስለ ቢግል ቡችላዎች ታሪኮች እነግራቸው እናም “ክርስቶስ ጌታ ዛሬ ተነስቷል”1 የሚለውን መዝሙር እዘምርላቸው ነበር። አንዳንዴም ቃላቶችን እንዲህ እቀይራለሁ፥ “አሁን ለመተኛት ጌዜው ነው—ሀሌሉያ።” በአብዛኛው ጊዜ ልጆቻችን ወዲያው ይተኛሉ፤ ተኝተዋል ብዬ የማስብ ከሆንኩኝ፣ መዘመርን እንደማቆም ያውቃሉና።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ተወዳጇ ሱዛን በአጠገቤ ሆና፣ እጆቼን በፍቅር ይዘው ትንፋሼን የወሰደውንና በእነዚህ ትንሽ ቀናት ውስጥ ለብዛት እንዳለቅስ ላደረገኝ ከጌታ የመጣ ይህን ቅዱስ ጥሪ ሲሰጡኝ ምን አይነት ታላቅ ስሜት እንደነበረኝ ለመግለፅ አልችልም።

በዚህ ፋሲካ ሰንበት፣ በደስታ “ሀሌሉያ” ብዬ እዘምራለሁ። የተነሳው አዳኛችን የቤዛነት ፍቅር መዝሙር2 የቃል ኪዳን ስምምነትን (ከእግዚአብሔር እና ከእርስ በራስ ጋር የሚያገናኘውን) እና የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያን (የፍጥረትን ወንድ እና ሴት ሰው እንድንተውና በመንፈስ ቅዱስ መነሳሻነት እንድንቀበል የሚረዳንን3) ያከብራል።

ዛሬ፣ ቃል ኪዳኖቻችን እና የአዳኛችን የኃጢያት ክፍያ ችሎታ የጣል እናም ያስከብራል። እኛ አብረን እንድንቀጥል እና እንድንተው ይረዱናል። አብረውም ያጣፍጣሉ፣ ይጠብቃሉ፣ ይቀድሳሉ፣ እናም ያድናሉ።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳለው፥ “በምድር ስለሚመዘግብ ወይም እለሚያስተሳስር እና በሰማይ ስለሚያስተሳስር ሀይል መናገራችንን ለአንዳንዶች ደፋር ትምህርት ይመስላቸዋል። ይህም ቢሆን፣ በአለም ሁሉም ዘመናት፣ ጌታ ለማንም ሰው፣ ወይም ማንም ሰዎች፣ የዘመንን ክህነት በራዕይ ሲሰጥ፣ ይህም ሀይል ሁልጊዜም ይሰጣል።”4

ዛሬም እንዲህ ነው። በሌላ ቦታ በምንም የማይገኙትት ቅዱስ ቃል ኪዳኖች እና ስርዓቶች በ43 ሀገሮች በሚገኙት በ159 የጌታ ቅዱስ ቤቶች ውስጥ ይሰጣሉ። ቃል የተገቡ በረከቶችም በዳግም በተመለሱት የክህነት ቁልፎች፣ ትምህርቶች፣ እና ስልጣኖች እምነታችንን፣ ታዛዥነታችንን፣ እና ለእኛ በዚህ ትውልድ፣ በጊዜና በዘለአለም ቃል በሚገባልን መንፈስ ቅዱስ ይንጸባረቃሉ።

በአለም አቀፍ ቤተክርስቲያኗ፣ በሁሉም ሀገሮች፣ ዘመዶች፣ እና አንደበቶች ያላችሁ ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በእያንዳንዱ እርምጃ ላላችሁ ለህያው እምነታችሁ፣ ተስፋችሁ፣ እና ልግስናችሁ አመሰግናለሁ። በዳግም የተመለሰው ወንጌል ምስክሮች እና አጋጣሚዎች ተሰብሳቢ ሙሉነት በመሆናችሁም አመሰግናለሁ።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እኛ የእናንተ እናም እናንተ የእኛ ናችሁ። “ልባቸው በአንድ ላይ በአንድነትና፣ አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር እንዲጣበቁ”5 ይህንንም በሁሉም ቦታዎች እና በሁሉም ነገሮች6 ለማድረግ እንችላለን። እኛም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚጋብዘን፣ የትም ብንሆን፣ ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ “ኑ እና ተመልከቱ።”7

በዚህ ቀን ምንም ቢሆኑ ወይም ምንም ለመሆን ቢችሉም፣ ለውዷ ሱዛንና ለቤተሰቤ፣ ለወንድሞቼ፣ እና ለእያንዳንዳችሁ፣ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ኃይል ሁሉ እናም ያለኝ ችሎታ ሁሉ 8 ለመስጠት ቃል እገባለሁ።

ብቁ የሆነ እና ዘለአለማዊ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር፣ አፍቃሪው የዘለአለም አባታችን፣ እና በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት በተሰጠው በኃጢያት ክፍያው ላይ የተመሰረተ ነው።9 ይህም የፋሲካ ሰንበት ነው።. ስለህያው ክርስቶስ በአምልኮ እመሰክራለሁ—እርሱም “የሞተው፣ የተቀበረው፣ እና እነገናም በሶስተኛው ቀ እንደገና የተነሳው፣ እና ወደ ሰማይ ያረገው”10 ነው። እርሱም አልፋ እና ኦሜጋ11—በመጀመሪያው ከእኛ ጋር የነበረ፣ በመጨረሻም ከከኛ ጋር የሚሆን ነው።

ከጆሴፍ ስሚዝ ጀምሮ፣ ዛሬ በደስታ ከደገፍናቸው፣ እስከ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለኋለኛው ቀን ነቢያት እመሰክራለሁ። መጀመሪያ ክፍል ልጆቻችን እንደሚዘምሩት “ነቢይን ተከተሉ፣ መንገዱን ያውቀዋልና።”12  በቅዱሳት መጻህፍት፣ በተጨማሪውም በመፅሐፈ ሞርሞን፥ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ውስጥ በትንቢት እንደተነገረው፣ ለመሲህ ዳግም ምፅዓት ለመዘጋጀት፣ የጌታ መንግስት እንደገና በምድር ላይ ተመስርታለች።13 በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።