2010–2019 (እ.አ.አ)
የተነሳሳ አገልግሎት
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


የተነሳሳ አገልግሎት

የመንፈስ ቅዱስ በተሻለ ለመቀበል የምንችለው ሌሎችን በማገልገል ላይ ስናተኩር ነው። ለዚያም ነው አዳኝን ለማገልገል የክህነት ሀላፊነቶች ያሉን።

ውድ ወድሞቼ፣ በዚህ በታሪካዊ አጠቃላይ ጉባኤ እናንተን ለማነጋገር በመቻሌ ታላቅ ምስጋና አለኝ። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰንን እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 17ኛ ፕሬዘደንት ደግፈናል። ከእርሳቸው ጋር በየቀኑ ለመስራት በረከት ስላለኝ፣ በመንፈስ በኩል ፕሬዘደንት ኔልሰን በእግዚአብሔር የጌታን እውነተኛ ቤተክርስቲያን እንዲመሩ እንደተጠሩ ማረጋገጫ ተሰምቶኛል።

ደግሞም ጌታ ሽማግሌ ጌረት ደብሊው. ጎንግ እና ሽማግሌ ዩሊሰስ ሶሬስ በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ እንደተጠሩም ምስክርነቴ ነው። እነርሱን እወዳቸዋለሁ እናም እደግፋቸዋለሁ። እነርሱም፣ በአገልግሎታቸው፣ በአለም ዙሪያ እና በትውልድ ሁሉ ህይወቶችን ይባርካሉ።

ይህ ጉባኤ ለሌላም ምክንያት ታሪካዊ ነው። ፕሬዘደንት ኔልሰን በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባለው የድርጅት እቅድ የተነሳሳ የወደፊት እርምጃን አስተዋውቀዋል። ያም እቅድ የክህነት ቡድኖች በዎርድ እና ካስማዎች የክህነት ሀላፊነቶቻቸንን በተሻለ እንድናሟላ አዲስ አሰራርን የያዘነው። እነዚያም ሀላፊነቶች ለአባታችን ልጆች የክህነት እንክብካቤ በምናደርግባቸው ጋር የተገናኙ ናቸው።

ጌታ ለቅዱሳኑ ያለው አፍቃሪ እንክብካቤ እቅድ በተለያዩ አመታት ብዙ ቀርጾች ነበሩት። በድሮ ጊዜ በናቩ ውስጥ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ወደ ከፈማው በብዛት ለሚመጡር ደሀ ለሆኑት ተቀያሪዎች የሚንከባከብበት የተደራጀ መንገድ ፈልጎ ነበር። አራቱ የአያቶቼ ወላጆች ከእነዚህ መካከል ነበሩ—አይሪንጎች፣ ቤንየንኖች፣ ሮምኖዎች፣ እና ስሚዞች። ነቢዩ የእነዚህ ቀዱሳን እንክብካቤን በጂኦግራፊ አደራጀ። በኢለኖይ ውስጥ እነዚህ የከተማ ተከፋፋዮች “ዎርድ” ተብለው ይጠሩ ነበር።

ቅዱሳን በሜዳው ተጉዘው ሲሄዱም፣ እርስ በርስ ያላቸው እንክብካቤም “በቡድኖች” ውስጥ ተደራጅቶ ነበር። ከአባቴ አያቶቼ ወላጆች አንዱ አሁን ኦክላሆማ ከሚባለው ቦታ በሚስዮን ካገለገለ በኋላ ሲመለስ ከአንዱ ቡድን ጋር በመንገዱ ተገናኘ። በበሽታ በጣም አቅም ስላጣ እርሱ እና የአገልግሎት ጓደኛው በጋሪው ውስጥ በጀርባቸው ተኝተው ነበር።

የቡድኑ መሪ ሁለት ወጣት ሴቶች በዚያ አሳዛኝ ጋሪው ውስጥ ያሉትን ማንንም ሰው እንዲረዱ ላከ። አንዷም፣ በስዊዘርላንድ የተቀየረች ወጣት እህት፣ ከሚስዮኖቹ አንዱን ተመለከተችና ርህራሄ ተሰማት። በቅዱሳን ቡድን ነበር የዳነው። ተሽሎት ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆም ከአዳነችው ጋር በእግር እየሄደ ነበር የገባው። ተፋቀሩ እናም ተጋቡ። እርሱም ቅድመ አያቴ ሔንሪ አይሪንግ ነበር፣ እና እርሷም ቅድመ አያቴ መሪ ቦሜሊ አይሪንግ ነበረች።

ከአመታት በኋላ፣ በክፍለ አህጉሩ ተሻግሮ ለመሄድ ታላቅ አስቸጋሪነት ሰዎች ሲናገሩ፣ እንዲህ ትል ነበር፣ “አይደለም፣ ከባድ አልነበረም። በእግር ስንሄድ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ ወንጌል ማግኘታችን እንዴት ታዕምራዊ እንደሆነ እንነጋገር ነበር። ይህም ከማስታውሰው በላይ ሁሉ ደስተኛ ጊዜ ነበር።”

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ ቅዱሳቱን እርስ በራስ የሚረዳዱበት የተለያዩ መንገዶችን ጌታ ተጠቅሟል። አሁን በጥንካሪ እናም በዎርድ እና ካስማ ቡድኖች—ከሁሉም የዎርድ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚሰራው አንድ እንድንሆንበት ባርኮናል።

ሁሉም ዎርዶች፣ ቡድኖች፣ እና የቡድን ጥንካሮዎ ጌታ እርሱ እንደሚንከባከባቸው ቅዱሳኑ እርስ በራስ ለመንከባከብ በሚያስፈልጋቸው መንገድ ውጤታማ እንዲሆን የሚያደርጉ ሁለት የሆኑ አስፈላጊ ነገሮች ነበሯቸው። እነርሱ ውጤታማ የሚሆኑት ቅዱሳን ከራሳቸው በላይ የክርስቶስ ፍቅር ለሌሎች ሲሰማቸው ነው። ቅዱሳት መጽሐፍት “ልግስና … የክርስቶስ ንፁ ፍቅር” ብለው ይጠሩታል (ሞሮኒ 7፥47)። እናም ውጤታማ የሆኑት ለተረጂው ምን መልካም እንደሆነ ጌታ እንደሚያውቅ እርዳታ ሰጪው በመንፈስ ቅዱስ ሲመራው ነው።

በቅርብ ሳምንታት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ በዛሬ እንዲተዋወቅ እንደተደረጉት አይነት፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ጌታ ሊያደርግ ያለውን አስቀድሞው እንደሚያውቁ በአኳኋናቸው በፊቴ ገልጸው ነበር። ሁለት ምሳሌዎች ልስጣችሁ። አንደኛው፣ በጌታ አገልግሎት የክህነት ተሸካሚዎች ምን ማከናወር እንደሚችሉ የተረዳ በአሮናዊ ክህነት ውስጥ የ14 አመት አስተማሪ የሆነ ልጅ ንግግር ነበር። ሁለተኛው፣ የክርስቶስ ፍቅር ያለው የመልከ ጼዴቅ ተሸካሚ ቤተሰብ ለማገልገል የተነሳሳበት ነበር።

መጀመሪያ፣ በዎርዱ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ ወጣቱ ሰው የተናገራቸውን ቃላቶች ልስጣችሁ። በዚያ ነበርኩኝ። በ14 አመታችሁ ምን እንደነበራችሁ ለማስታወስ ሞክሩ እና ወጣት ልጅ ለማወቅ ከሚገባው በላይ የሚለውን ሲናገር ስሙ፥

“14 አመቴ ከሞላሁ ጊዜ ጀምሮ በዎርዴ የአስተማሪዎች ሸንጎ አባል መሆኔን በጣም ነው የምወደው። አስተማሪ የዲያቆን በሙሉ እና ትንሽ ተጨማሪም ሀላፊነቶች አለው።

“አንዳንዶቻችን አስተማሪዎች ስለሆንን፣ ሌሎች አንድ ቀን ይሆናሉ፣ እናም ሁሉም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በክህነት የተባረከ ነው፣ ስለዚህ ሁላችንም ስለአስተማሪ ሀላፊነት በተጨማሪ ማወቅ ያስፈልገናል።

“ከሁሉም በመጀመሪያ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥53 እንደሚለው፣ ‘የመምህሩ ሀላፊነትም ቤተክርስቲያኗን ዘወትር መጠበቅ፣ እና እነርሱን መርዳትና ማጠንከር ነው።’

“ቀጥሎም፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥54–55 እንደሚለው፥

“እናም ምንም ጥፋት በቤተክርስቲያኗ እንዳይኖር፣ እንዲሁም አባላቶቿ እርስ በራሳቸው እንዳይከፋፉ፣ እንዳይዋሹ፣ እንዳይተማሙ፣ ወይም ክፉ እንዳይነጋገሩ መጠበቅ፤

“እናም ቤተክርስቲያንም በየጊዜው እንዲሰበሰቡ ማድረግ፣ እናም አባላቶቿ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ ነው።”

ወጣቱም እንዲህ ቀጠለ፥

“ክርስቶስ ይህች ቤተክርስቲያኑ ስለሆነች እደሚያደርገው እኛም ቤተክርስቲያኗን መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ደግሞም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉትን ሰዎች መንከባከብ ሀላፊነታችእ እንደሆነ ጌታ ይነግረናል። ትእዛዛትን ለመጠበቅ የምንጥር ከሆነ፣ ለእርስ በራስ ደግ፣ ታማኝ፣ መልካም ጓደኛ፣ እና አብረን በመሆን ስንደሰት፣ መንፈስ ከእኛ ጋር እንዲሆን እናስችላለን እናም የሰማይ አባታችን እንድናደርግ እንደሚፈልግ እናውቃለን። ይህን ካላደረግን፣ ጥሪአችንን ለማሟላት አንችልም።”

እንዲህ በማለት ቀጠለ፥

“አስተማሪ ጥሩ የቤት ለቤት አስተማሪ በመሆን፣ አባላትን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰላምታ በመስጠት፣ ቅዱስ ቁርባንን በማዘጋጀት፣ በቤት በመርዳት፣ እና የሰላም ሰሪ በመሆን ትክክለኛውን ምሳሌ ሲያሳይ፣ ክህነቱን ለማክበር እና ጥሪውን ለማሟላት እየመረጠ ነው።

“ጥሩ አስተማሪ መሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ እና በቤተክርስቲያን ተሳትፎዎች ላይ ሀላፊ መሆን ብቻ አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳስተማረው፣ ‘በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን’ (1 ጢማቴዎስ 4፥12)።”

ከዚያም ያ ወጣት ስል እንዲህ አለ፥

“የትም ብንሆን እና ምንም እያደረግን ከሆንን፣ በሁሉም ሂዜ እና በሁሉም ቦታዎች የጽድቅ ጥሩ ምሳሌ ለመሆን እንችላለን።

“አባቴ እና እኔ ለብራውን ቤተሰብን የቤት ለቤት አስተማሪዎች ነን።1 ወደዚህ ሁሌም ስንሄድ፣ እነርሱን በመጎብኘት እና እነርሱን ለማወቅ በመጣር ጥሩ ጊዜ አለን። ስለብራውን ቤተሰብ የምወደው ነገር ቢኖር ወደዚያ ስንሄድ፣ ሁሉም ለማዳመጥ ፈቃደኞች ናቸው እናም ሁልጊዜም የሚያካፈሉት መልካም ታሪክ ነበራቸው።

“በዎርድ ያሉትን ሰዎች በቤት ለቤት ማስተማር ምክንያት በደንብ ስናውቃቸው፣ የሚቀጥለውን የአስተማሪ ሀላፊነት ለማከናወን ቀላል ይሆናል፣ እና ያም የቤተክርስቲያን አባላትን ሰላም ማለት ነው። ሰዎች እንደተፈለጉ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት እንዳላቸው እንዲሰማቸው ማድረግ የዎርድ አባላት በሙሉ ፍቅር እንዲሰማቸው እና ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል እንዲዘጋጁ ያደርጋቸዋል።

“ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡትን አባላት ሰላም ከማለት በኋላ፣ አስተማሪዎች በእያንዳንዱ እሁድ ቅዱስ ቁርባንን በማዘጋጀት ይረዳሉ። በዚህ ዎርድ ቅዱስ ቁርባንን ማዘጋጀት እና ማስተላለፍን በጣም እደሰትበታለሁ ምክንያቱም ሁሉም አምልኮን የሚያሳዩ ስለነበሩ። ቅዱስ ቁርባንን ሳዘጋጅ እና ሳስተላልፍ መንፈስ ሁልጊዜም ይሰማኛል። ይህን በየእሁድ ለማድረግ በመቻሌ ለእኔ ታላቅ በረከት ነው።

“እንደ ቅዱስ ቁርባንን ማስተላለፍ አይነት አገልግሎትን ሰዎች ተመልክተው ይህን በማድረጋችን ያመሰግኑናል፣ ነገር ግን ቅዱስ ቁርባንን የማዘጋጀት አይነትና ሌሎች አገልግሎቶች የሚደረጉት ማንም ሳያዩት ነው። ይህን ሰዎች ማየታቸው ለእኛ አስፈላጊ አይደለም፤ አስፈላጊውም ጌታ እንዳገለገልነው ማወቁ ነው።

“እንደ አስተማሪዎች፣ የክህነት ሀላፊነቶቻችንን በማሟላት ቤተክርስቲያኗን፣ ጓደኞቻችንን፣ እና ቤተሰቦቻችንን ለማጠናከር መጣር አለብን። ሁልጊዜም ቀላል አይደለም፣ ነገር ግን ‘ያዘዛቸውን ትዕዛዛት [የምናሟላበት] መንገድ ካላዘጋጀ በቀር’ (1 ኔፊ 3፥7) ጌታ ምንም ትእዛዛት አይሰጠንም።”

ወጣት ልጁ ሲጨርስ፣ በእርሱ ጎልማሳነት እና ጥበብ መገረሜን ቀጠልኩኝ። እንዲህም በማለት ገመገሙ፣ “[ኢየሱስ ክርስቶስን] ለመከተል ከመረጥን የተሻለ እንደምንሆን አውቃለሁ።”

ሌላ የክህነት አገልግሎት ታሪክ በዎርድ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ ተነግሮ ነበር። እንደገናም በዚያ ነበርኩኝ። በዚህ ጉዳይ፣ ይህ የሸመገለ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ ሲናገር ጌታ በተጠናከረ የክህነት ሸንጎ ምን እንዲደረግ የፈለገውን እየገለጸ እንደነበረ አያውቅም ነበር። የእርሱ ታሪክ ይህ ነው፥

እርሱ እና የቤተሰብ የቤት ለቤት ትምህርት ጓደኛው ሰባት ቤተሰቦችን ለማገልገል ተመድበው ነበር። በአብዛኛዎቹ ለመጎብኘት አልፈለጉም ነበር። የቤት ለቤት አስተማሪዎች ወደ ቤታቸው ሲመጡ፣ በሩን ለመክፈት እምቢ አሉ። በስልክ ሲደውሉም፣ አላነሱትም። መልእክት ሲተዉም፣ መልሰው አልደወሉላቸውም። ከፍተኛው የትምህርት ጉደኛ በመጨረሻም ወደ ደብዳቤ የመጻፍ አገልግሎት ዞረ። መልስ ለማግኘት ተስፋ ኖሮት የደመቀ ብጫ ፖስታ መጠቀም ጀመረ።

ከሰባት ቤተሰቦች አንዷ ከአውሮፓ የመጣች ተሳታፊ ያልሆነች ያላገባች እህት ነበረች። ሁለት ልጆች ነበሯት።

ከእርሷ ጋር ለመገናኘት ከነበረ ከብዙ ጥረት በኋላ፣ የእጅ ስልክ መልእክት አገኘ። ከቤት ለቤት አስተማሪ ጋር ለመገናኘት ጊዜ እንዳልነበራት ነገረችው። ሁለት ስራ ነበራት እና ውትድርና ውስጥ ነበረች። የመጀመሪያዋ ስራ እንደ ፖሊስ ነበር፣ እናም የስራ እቅዷ መርማሪ ለመሆን እና ከዚያም ወደ ተወለደችበት አገር ለመመለስና ስራዋን በዚያ ለመቀጠል ነበር።

የቤት ለቤት አስተማሪም በቤቷ ሊጎበኛት አልቻለም ነበር። አንዳዴም በእጅ ስልክ መል እክት ይልክላት ነበር። በየወሩ በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ላከላት፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ልጅ የበአል ፖስት ካርድ በተጨማሪ ይልክ ነበር።

ምንም መልስ አላገኘም። ነገር ግን የቤት ለቤት አስተማሪዎቿ ማን እንደነበሩ፣ እንዴት ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት እንደምትችል፣ እና በክህነት አገልግሎታቸው በአቋም እንደሚጸኑ ታውቃለች።

ከዚያም አንድ ቀን ከእርሷ አስቸኳይ መልእክት አገኘ። እርዳታ በታም ያስፈልጋት ነበር። ኤጲስ ቆጶስ ማን እንደሆነ አላወቀችም፣ ግን የቤት ለቤት አስተማሪዎቿን ታውቅ ነበር።

በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ አንድ ወር ውትድርና ስልጠና ከስቴቱ ወጥታ መሄድ ነበረባት። ልጆቻን ይዛ ለመሄድ አትችልም። ልጆቿን ሊያንከባክቡ የነበሩ እናቷም የጤንነት ችግር የነበረውን ባለቤቷን ለመንከባከብ ወደ አውሮፓ ሄዳ ነበር።

ይህች ተሳታፊ ያልነበረች ያላገባች እህት ወደ አውሮፓ የሚኬድበት ትኬት ለመቅዛ ገዘብ የነበራት ለታናሽ ልጇ ብቻ እንጂ ለ12 አመት ወንድ ልጇ፣ ለኤሪክ፣ አልነበረም።2 የቤት ለቤት አስተማሪዋ ልጇን ለ30 ቀን የሚከባከብ መልካም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰብ እንዲያገኝላት ጠየቀች!

የቤት ለቤት አስተማሪውም መልሶ የሚችለውን ያህል እንደሚጥር መልእክት ላከላት። ከዚያም ከክህነት መሪዎቹ ጋር ተነጋገረ። የሊቀ ካህናት መሪ የሆነው ኤጲስ ቆጶስም የዎርድ ሸንጎን፣ እና በተጨማሪም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት፣ ለማነጋገር ፈቃድ ሰጡት።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንትም ወዲያው የኤሪክ እድሜ የሆኑ ልጆች ያሏቸው፣ እና ለሳምንት ያህል በተራ እርሱን የሚንከባከቡ አራት መልካም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰቦች አገኘች። በሚቀጥለውም ወር፣ እነዚህ ቤተሰቦች ኤሪክን መገቡ፣ ብዙ ሰዎች በሚገኙበት አፓርትመንታቸው ወይም ቤታቸው ቦታ አገኙለት፣ በፊት ታቅዶ ወደነበረ የቤተሰብ የገና ሽርሽርም ይዘውት ሄዱ፣ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዱት፣ በቤተሰብ የቤት ለቤት ምሽትም ተሳታፊ አደረጉት፣ እናም ዘወትር።

ቤተሰቦቹ የኤሪክ እድሜ ያላቸው ወንድ ልጆች ነበሯቸው፣ እርሱንም በዲያቆን ቡድን ስብሰባቸው እና ድርጊቶች ተሳታፊ አደረጉት። በ30 ቀናት ውስጥ፣ ኤሪክ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ በየእሁድ ይገኝ ነበር።

እናቱ ከመሰልጠኛዋ ከተመለሰች በኋላ፣ ኤሪክ፣ በአብዛኛው ጊዜ በፈቃደኝነት አብሯቸው እንዲቆይ ካደረጉት ከአራት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰቦች ጋር ወይም ከእናቱ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪ በተጨማሪ፣ከእርሱ ጋር ጓደኞች ከሆኑት ጋር ወደ ቤተክርስቲያን መምጣትን ቀጠለ። ከጊዜም በኋላ፣ እንደ ዲያቆን ተሾመ እናም ቅዱስ ቁርባንን በየጊዜው ማስተላለፍ ጀመረ።

አሁን ወደ ኤሪክ ወደፊት ህይወት እንመልከት። ቤተሰቡ ወደ እናቱ አገር ሲመለሱ በዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪ መሆኑ የሚያስደንቅ አይደለም—ይህም የሚሆነው፣ በኤጲስ ቆጶስ አመራር፣ በአንድነት በመንፈስ ቅዱስ አመራር እና በልባቸው ከነበረው ልግስና ቅዱሳን በማገልገላቸው ምክንያት ነበር።

ልግስና በእግዚአብሔር መንግስት ለመዳን አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን። ሞሮኒ እንደጻፈው፣ “እናንተ ልግስና ከሌላችሁ በእግዚአብሔር መንግስት በምንም መንገድ ልትድኑ አይቻላችሁም” (ሞሮኒ 10፥21፤ ደግሞም ኤተር 12፥34)።

ልግስናም ለማድረግ የምንችለውን ካደረግን በኋላ እንደ ስጦታ የሚሰጠን የመንፈስ ስጦታ እንደሆነ እናውቃለን። “በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ።”(ሞሮኒ 7፥48)።

ለእኔ እንደሚመስለኝ፣ የመንፈስ ቅዱስ በተሻለ ለመቀበል የምንችለው ሌሎች በማገልገል ላይ ስናተኩር ነው። ለዚያም ነው አዳኝን ለማገልገል የክህነት ሀላፊነቶች ያሉን። ሌሎችን ስናገለግል፣ ስለራሳችን ማስብን እንቀንሳለን፣ እናም መንፈስ ቅዱስን ወደ እኛ ወዲያው ይመጣል እናም የልግስና ስጦታ ለመቀበል ያለንን የህይወት ሙሉ ፍላጎትን ለማሟላት ይረዳናል።

ጌታ በክህነት አገልግሎታችን በተጨማሪ የተነሳሳን እና ግልስና ያለን እንድንሆን ለእኛ ባለው እቅድ ወደፊት መግፋትን እንደጀመረ እመሰክራለሁ። ለፍቅሩ ምስጋና አለኝ፣ ይህንንም በልጋስ ይሰጠናል። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።”

ማስታወሻዎች

  1. ስም ተቀይሯል።

  2. ስም ተቀይሯል።