2010–2019 (እ.አ.አ)
እነሆ ሰውዬው!
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


እነሆ ሰውዬው!

ሰውን በእውነት ለማየት መንገድ ያገኙት ለህይወት ከሁሉም በላይ ታላቅ ደስታ እና በህይወት በጣም አስቸጋሪ ለሆኑት መድሀኒት ወደሚገኝበት በር ያገኙ ናቸው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ በዚህ አስደናቂ የአጠቃላይ ጉባኤ ከእናንተ ጋር ለመገኘት በመቻሌ ምስጋና አለኝ። ሀሪየት እና እኔ ከእናንተ ጋር  ሽማግሌ ጎንግ እና ሶሬስን እና ታላቅ አዲስ ጥሪዎችን በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ የተቀበሉትን ብዙዎች ወንድሞች እና እህቶችን በመደገፍ እደሰታለሁ።

ውድ ጓደኛዬ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ቢናፍቁኝም፣ ውድ ነቢያችንና ፕሬዘደንታችንን፣ ራስል ኤም. ኔልሰንና አማካሪዎቻቸውን አፈቅራለሁ እናም እደግፋለሁ።

እንደገና ከአስራ ሁለት ሐዋሪያት ወንድሞቼ ጋር በቅርብ ለመስራት በመቻሌ ክብር ይሰማኛል እና ምስጋና አለኝ።

ከሁሉም በላይ፣ በማንኛውም ችሎታ ወይም ጥሪ፣ ባሉበት ቦታ ከፍ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ ብዙ ሚልዮን የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በሚገኙበት በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆኔ ትህትና እና ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።

ዛሬ ቅዱስ ቀን ነው። ይህም የትንሳኤ ሰንበት፣ አዳኛችን የሞትን ሠንሰለት የሰበረበት1 እና ከመቃብር በድል የወጣበት አስደናቂ ጠዋትን የምናከብርበት ቀን ነው።

በታሪክ ውስጥ ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነ ቀን

በቅርብ ኢንተርኔትን እንዲህ ጠየኩኝ፣”ምን ቀን የታሪክን መንገድ ከሁሉም በላይ ቀይሯል?”

መልሶችም ከሚያስደንቅ እና ካልተለመደ እናም አስተያየት ካለው እንዲታሰብበት ወደሚያደርግ የተለያዩ ነበሩ። ከእነርሱ መካከል፣ የጥንት ሚጢጢ ፕላኔት የያከታን ደሴት መምታት፤ ወይም በ1440 (እ.አ.አ)፣ዮሀንስ ጉትንበርግ የማተሚያውን መሳሪያ የፈጸመበት ጊዜ፣ እናም በ1903 (እ.አ.አ) የራይት ወንድሞች ሰዎች ለመብረር እንደሚችሉ ለአለም ያሳዩበት ቀናትም ነበሩ።

እንደዚህ አይነት ጥያቄ ብትጠየቁ፣ ምን ትላላችሁ?

በአዕምሮዬ መልሱ ግልፅ ነው።

ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነውም ቀን ለማግኘት፣ ከ2000 አመት በፊት በገትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥብቅ ጸሎት ተንበርክኮና ራሱን ለእኛ ኃጢያቶች እንደ ክፍያ ወዳቀረበበት መሄድ ያስፈልገናል። ይህም በሰውነት እና በመንፈስ ተመሳሳይ በሌለው ስቃይ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር፣ ከእያንዳንዱ የቆዳ ቀዳዳው ደም ባፈሰሰበት በዚያ ታላቅ እና መጨረሻ በሌለው መስዋዕት ጊዜ ነበር። ፍጹም በሆነ ፍቅር፣ እኛ ሁሉንም እንቀበል ዘንድ ሁሉንም ሰጠ። የእርሱ መለኮታዊ መስዋዕት፣ ለመረዳት አስቸጋሪ፣ በልባችን እና በአዕምሮአችን ሁሉ ለመሰማት ብቻ የሚችል ቢሆንም፣ ለመለኮታዊ ስጦታው ምን አይነት የምስጋና እዳ እንዳለን እንድናስታውስ ያደርገናል።

በዚያም ምሽት በኋላም፣ ኢየሱስ በሀይማኖትና በፖለቲካ ስልጣኖች ፊት ቀርቦ፣ እነርሱም አሳልቀውበታል፣ አስደብድበውታል፣ እናም በሚያሳፍር ሞት እንዲሞት ፈርደውበታል። በመስቀል ላይ በታላቅ ስቃይ ተሰቀለ፣ በመጨረሻም፣ “ተፈጸመ።”2 ህይወት የሌለው ሰውነት በተበደረ መቃብር ውስጥ ተኛ። ከዚያም፣ በሶስተኛው ቀን ጠዋት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የሁሉን ቻይ አምላክ ልጅ፣ ከመቃብር እንደ ግርማዊ፣ ከሞት የተነሳ የወብት፣ የብርሀን፣ እና የግርማ ሰው ወጣ።

አዎን፣ የሀገርን ወይም የህዝብን እጣ ፈንታ የነኩ ብዙ ድርጊቶች በታሪክ ውስጥ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉንም ቢያጣምሩ፣ እና ከዚያ የመጀመሪያ የትንሳኤ ጠዋት ጋር በአስፈላጊነት የሚመዛዘኑ ምንም የሉም።

የኢየሱስ ክርስቶስን መጨረሻ የሌለው መስዋዕት እና ትንሳኤን ከታሪክ ድርጊቶች ሁሉ በላይ—ከአለም ጦርነት፣ ከመአት፣ እና ህይወትን ከሚቀይር የሳይንስ እውቀት በላይ አስፈላጊ የሚያደርግም ምንድን ነው?

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ እንደገና ለመኖር እንችላለን

መልሱ የሚገኘው ለማሸነፍ ከማንችላቸው ሁለት ታላቅ ፈተናዎች ጋር ነው።

መጀመሪያ፣ ሁላችንም እንሞታለን። ምንም ወጣት፣ ቆንጆ፣ ጤነኛ፣ ወይም ጥንቁቅ ብትሆኑም፣ አንድ ቀን ሰውነታችሁ ህይወት የሌለው ይሆናል። ጓደኞች እና ቤተሰቦች ለእናንተ ያዝናሉ። ነገር ግን መልሰው ሊያጧችሁ አይችሉም።

ምንም ቢሆን፣በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ፣ የእናንተ ሞት ጊዜያዊ ብቻ ይሆናል። መንፈሳችሁ አንድ ቀን ከሰውነታችሁ ጋር አንድ ይሆናል። ይህ ከሞት የተነሳው ሰውነት በሞት ተገዢ አይሆንም፣3 እናም በዘለአለም፣ ከህመም እና ከሰውነት ስቃይ ነጻ ሆናችሁ ትኖራላችሁ።4

ይህም የሚሆነው፣ ህይወቱን አሳልፎ ሰጥቶ እንደገና በወሰደው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ነው።

ይህን ያደረገው በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ ነው።

ይህን ያደረገው በእርሱ ለማያምኑት ሁሉ ነው።

ይህን ያደረገው ለተሳለቁበት፣ ለነቀፉት፣ እናም ስሙን ለሰደቡት ነው።5

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንችላለን

ሁለተኛ፣ ሁላችንም ኃጢያት ሰርተናል። ኃጢያቶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር ከመኖር ለዘለአለም ይገድቡናል፣ “በመንግስተ ሰማይ ምንም እርኩስ ነገር ሊገባ አይቻለውም።”6

በዚህም ምክንያት፣ እያንዳንዱ ወንድ፣ ሴት፣ እና ልጅ ከፊቱ ወጥተው እንዲቀሩ ተደርገው ነበር—ያም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንከን የሌለው ጥቦት፣ ህይወቱን እንደ ክፍያ ለኃጢያቶቻችን እስከሚሰጥ ድረስ ነው። ኢየሱስ ለፍትህ ምንም እዳ ስላልነበረው፣ እዳችንን ለመክፈልና ከእያንዳንዱ ነፍስ ፍትህ ለምትፈልገው ለመክፈል ይችላል። ያን እኔን እና እናንተን ይጨምራል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያታችንን ዋጋ ከፈለ።

ለሁሉም።

በታሪክ በጣም አስፈላጊ በሆነበት በዚያ ቀን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን ደጅ ከፈተ እናም ወደ ዘለአለም ህይወት ቅዱስ ምድር እና የተቀደሰ አዳራሽ ለመግባት የሚገድበንን ወረወረው። በጌታችን እና አዳኛችን ምክንያት፣ እኔና እናንተ ውድ እና ዋጋው የለሽ የሆነ ስጦታን ሰጠን—የድሮ ድርገታችን ምንም ቢሆን፣ ንስሀ ለመግባት እና በሰማይ አባት ታማኝ ልጆች ተከብበን ወደ ሰለስቲያል ብርሀንንና ግርማ የሚመራውን መንገድ ለመከተል እንችላለን።

ለምን እንደምንደሰት

ይህም ምን በትንሳኤ ሰንበት የምናከብረው ነው—ህይወትን እናከብራለን!

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት በሞት ተስፋ ከሞቅረጥ ከፍ እንላለን እናም በሚያጥለቀልቅ የደስታ እምባን ምስጋና የምናፈቅራቸውን እናቅፋለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ እንደ ዘለአለማዊ ፍጥረቶች፣ መጨረሻ እንደሌላቸው አለም፣ እንኖራለን።

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ ኃጢያቶቻችን ለመደምሰስ የሚቻሉ ብቻ ሳይሆን፤ ሊረሱም ይቻላሉ።

ለመንጻት እና ከፍ ለመደረግ እንችላለን።

ቅዱስ።

በውድ አዳኛችን ምክንያት፣ ወደ ዘለአለም ህይወት ከምትፈነቅለው ውሀ ለዘለአለም ለመጠጣት እንችላለን።7 በዘለአለም ንጉሳችን ቤት፣ በአዕምሮ አይን ለመመልከት የማይቻል አይነት ግርማ እና ፍጹም ደስተኛነት እያለን፣ ለዘለአለም እንኖራለን።

“ሰውዬውን” እናያለንን?

ይህም ሁሉ ቢሆንም፣ ዛሬ በዚህ አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰጠን ውድ ስጦታ የማያውቁ ወይም የማያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ። ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሰምተው ይሆናል እና እርሱን እንደ ታሪካው ሰው ያውቁታል፣ ግን እርሱን በእውነት ማን እንደሆነ አይመለከቱትም።

ስለዚህ ሳስብ፣ በይሁዳ መሪ ፊት፣ በጲላጦስ ፊት፣ ከሞቱ ከትንሽ ሰዓት በፊት ቆሞ የነበረውን እንዳስታውስ ያደርገኛል።

ጲላጦስ ኢየሱስን በአለም አስተያየት ብቻ ነበር የተመለከተው። ጲላጦስ የሚሰራው ስራ ነበረው፣ እና ይህም ሁለት ታላቅ ስራዎች ነበሩ፥ ቀረጥ ለሮሜዎች መሰብሰብ እና ሰላምን መጠበቅ ነበር። አሁን የይሁዳ ሸንያንዲን በእርሱ ፊት ለእነርሱ እንቅፋት ነው ብለው ያመጡት ሰው ነበር።8

እስረኛውን የቃል ጥያቄ ከሰጠው በኋላ፣ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም”9 አለ። ነገር ግኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሳሾችን ማብላላት እንዳለበት ተሰማው፣ ስለዚህ ጲላጦስ በፋሲካ አንድ እስረኛ የሚለቀቅበትን የክልል በሀልን አስታወሰ። ዘራፊና ገዳይ ከሆነው በርባን ይልቅ ኢየሱስን እንዲለቅላቸው አይፈልጉምን?10

ሁከታማ ሰዎች ጲላጦስ በርባን እንዲለቅ እና ኢየሱስን እንዲሰቅል ጠየቁት።

“ለምን?” ጲላጦስ ጠየቀ። “ምን ክፉ አደረገ?”

ነገር ግን በከፍተኛ ድምጽ ጮሁ። “ስቀለው!”11

ረባሾቹን ለማስረካት በመጨረሻ ጥረት፣ ጲላጦስ ሰዎቹ ኢየሱስን እንዲገርፉት አዘዘ።12 እርሱ በደም እና በጉዳት እስኪሸፈን ይህን አግደረጉ። ተሳለቁበት፣ የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ አደረጉ፣ እናም ቀይ ልብስን አለበሱት።13

ምናልባት ጲላጦስ ረባሾች ደም ለማየት የነበራቸውን ፍላጎት ያረካል ብሎ አስቦ ይሆናል። ምናልባት በዚህ ሰው ላይ ሊያዝኑ ይሆናል። ጲላጦስም እንዲህ አለ “እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ። … እነሆ ሰውዬው!”14

የእግዚአብሔር ልጅ በኢየሩሳሌም ሰው ፊት ቆመ።

ኢየሱስን ያያሉ፣ ግን እርሱን በእውነትም አልተመለከቱም።

ለማየት አይኖች አልነበራቸውም።15

በምሳሌአያዊ አነጋገር፣ እኛም “ሰውዬውን [እንድናይ]” ተጋብዘናል። ስለእርሱ ያለው አስተያየት በአለም ውስጥ የተለያየ ነው። የጥንት እና የዚህ ዘመን ነቢያት እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ይመሰክራሉ። ይህን እኔም አደርገዋለሁ። እያንዳንዳችን ለራሳችን ማወቃችን በጣም ትርጉም ያለው እና አስፈላጊ ነው። ስለዚህ፣ ስለኢየሱስ ህይወት እና አገልግሎት ስታሰላስሉ፣ ምን ታያላችሁ?

ሰውን በእውነት ለማየት መንገድ ያገኙት ለህይወት ከሁሉም በላይ ታላቅ ደስታ እና በህይወት በጣም አስቸጋሪ ለሆኑት መድሀኒት ወደሚገኝበት በር ያገኙ ናቸው።

ስለዚህ፣ በሀዘን ስትከበቡ፣ ሰውዬውን ተመልከቱ።

እንደጠፋችሁ እና እንደተረሳችሁ ሲሰማችሁ፣ ሰውዬውን ተመልከቱ።

ተስፋ ስትቆርጡ፣ ስትተዉ፣ ስትጠራጠሩ፣ ስትጎዱ፣ ወይም ስትሸነፉ፣ ሰውዬውን ተመልከቱ።

እርሱ ያፅናናችኋል።

ይፈውሳችኋል እናም ለጉዞአችሁ ትርጉም ይሰጣል። መንፈሱን በእናንተ ላይ ያፈሳል እናም ልባችሁን ከታላቅ ደስታ ይሞላል።16

እርሱም “ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።”17

ሰውየውን በእውነት ስንመለከት፣ ስለእርሱ እንማራለን እናም ህይወታችንን ከእርሱ ጋር ለማሰለፍ እንፈልጋለን። ንስሀ ለመግባት እና ፍጥረታችንን ለማንጠር እናም በትንሽ ወደ እርሱ በመቅረብ እናድጋለን። በእርሱ እናምናለን። ለእርሱ ያለንን ፍቅር ትእዛዛቱን በማክበር እና በቅዱስ ቃል ኪዳኖቻችን በመኖር እናሳያለን።

በሌሎች ቃላትም፣ የእርሱ ደቀ መዛሙርቶች እንሆናለን፡

የእርሱ የሚያነጥረው ብርሀን ነፍሳችንን ይሞላል። ጸጋውም ከፍ ያደርገናል። ሸከማችን ቀላል ይሆናሉ፣ ሰላአችንም ጥልቅ። ሰውዬውን በእውነት ስንመለከት፣ በህይወት ጉዞ መደናቀፊያዎች እና መጠማዘዣዎች ሁሉ የሚያነሳሳን እና የሚደግፈን የተባረከ ወደፊት እንደሚኖረን ቃል ኪዳን አለን። ወደኋላ በመመልከት፣ መለኮታዊ ንድፍ እንዳለ፣ ነጥቦቹ እንደሚገናኙ፣ እናውቃለን።18

የእርሱን መስዋዕት ስትቀበሉ፣ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ስትሆኑ፣ እና በመጨረሻም የምድር ጉዞአችሁ መጨረሻ ላይ ስትደርሱ፣ በህይወታችሁ ሁሉ የጸናችሁባቸው ሀዘኖች ምን ይሆናሉ?

ይጠፋሉ።

ያጋጠሟችሁስ ብስጭት፣ ክህደት፣ ስደት?

ይጠፋሉ።

ያለፉባችሁስ ስቃይ፣ የልብ ህመም፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ እና ጭንቀትስ?

ይጠፋሉ።

ይረሳሉ።

“እናም ስለ ክርስቶስ እንናገራለን፣ በክርስቶስ እንደሰታለን፣ ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን፣ ስለ ክርስቶስ ትንቢት እንናገራለን፣ … ልጆቻችን ለሀጢያታቸው ስርየት የትኛውን መንገድ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ”19 ማድረጋችን የሚያስገርም ነውን?

በልባችን ሁሉ ሰውዬውን ለመመልከት መጣራችን የሚያስገርም ነውን?

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነው ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በሙት እና በኃጢያት ላይ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ድድል ያገኘበት ቀን እንደሆነ እመሰክራለሁ። በህይወታችሁ እና በእኔም በጣም አስፈላጊ የሆነው ቀን “ሰዬውን [ለመመልከት]” ስንማር፤ እርሱ ማን እንደሆነ በእውነት የምናይበት፤ በልባችንና በአዕምሮአችን በሙሉ የኃጢያት ክፍያ ሀይሉን የምንካፈልበት፤ በሚታደስ በጕጉት እና በጥንካሬ፣ እርሱን ለመከተል የምንወስንበት ነው። ያም ቀን በህይወታችን በሙሉ ደጋግሞ ይድረስም።

“ሰውዬውን [ስንመለከት]” በዚህ በምድራዊ ህይወት እና በዘለአለም ህይወት ትርጉም፣ ደስታ፣ ሰላም እናገኝ ዘንድ ምስክሬንና በረከቴን እተውላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሞዛያ 15፥23 ተመልከቱ።

  2. ዮሀንስ 19፥30

  3. አልማ 11፥45 ተመልከቱ።

  4. ራእይ 21፥4 ተመልከቱ።

  5. 1 ቆሮንቶስ 15፥21–23 ተመልከቱ።

  6. 3 ኔፊ 27፥19

  7. ዮሀንስ 4፥14 ተመልከቱ።

  8. ሉቃስ 23፥2 ተመልከቱ።

  9. ዮሀነስ 18፥38። ኢየሱስን ላይ ላለመፍረድ፣ ጲላጦስ ጉዳዩን ለሄሮድ ላከው። የመጥምቁ ዮሀንስ ሞትን ያዘዘው (ማቴውስ 14፥6–11 ተመልከቱ) ሄሮድስ ኢየሱስን የሚፈርድበት ከሆነ፣ ጲላጦስ ፍርዱን ወዲያው ተቀብሎ የክልል ጉዳይ እንደሆነ እና ይህን የተቀበለው በክልል ሰላም ለመጠበቅ ለማለት ይችል ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ለሄሮድስ ምንም ቃል አልተናገረም (ሉቃስ 23፥6–12)፣ እናም ሄሮድስ ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው።

  10. ማርቆስ 15፥6–7፤ ደግሞም ዮሀንስ 18፥39–40። አንድ የአዲስ ኪዳን አስተማሪ እንደጻፈው፣ “የሮሜ ገዢ በፋሲካ ውስጥ ለአይሁዳ ሰዎች በሞት የተፈረደበት እስረኛ ሰው የመፍታት ባህል ነበር” (Alfred Edersheim, The Life and Times of Jesus the Messiah [1899], 2:576)። ባራበስ ማለት “የአባት ልጅ” ማለት ነው። የኢየሩሳሌም ህዝቦችን በእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል ርጫ መኖራቸው የሚያስገርም ነበር።

  11. ማርቆስ 15፥11–14 ተመልከቱ።

  12. This scourging was so terrible it was called “the intermediate death” (Edersheim, Jesus the Messiah, 2:579).

  13. ዮሀንስ 19፥1–3 ተመልከቱ።

  14. ዮሀንስ 19፥4–5

  15. Earlier, Jesus had observed that “this people’s heart is waxed gross, and their ears are dull of hearing, and their eyes they have closed; lest at any time they should see with their eyes, and hear with their ears, and should understand with their heart, and should be converted, and I should heal them.” And then with tenderness He said to His disciples, “But blessed are your eyes, for they see: and your ears, for they hear” (Matthew 13:15–16). Will we allow our hearts to be hardened, or will we open our eyes and hearts that we may truly behold the Man?

  16. ሞዛያ 4፥20 ተመልከቱ።

  17. ኢሳይያስ 40፥29

  18. See Dieter F. Uchtdorf, “The Adventure of Mortality” (worldwide devotional for young adults, Jan. 14, 2018), broadcasts.lds.org.

  19. 2 ኔፊ 25፥26