2010–2019 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ማገልገል
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ማገልገል

በስሙ፣ በሀይሉ እና በስልጣኑ፣ እናም በእርሱ አፍቃሪ ደግነት እናገለግላለን።

ውድ ወንድሞቼ፣ ለጌታ እና ለቅዱስ ስራው ስላላችሁ ታማኝነት አመሰግናለሁ። ከእናንተ ጋር መሆንም በእውነት አስደሳች ነው። እንደ አዲስ ቀዳሚ አመራር፣ ለጸሎታችሁ እና ለደጋፊ ጥረታችሁ እናመሰግናችኋለን። ለህይወታችሁ እና ለጌታ አገልግሎታችሁ አመስጋኝ ነን። ለሀለፊነት ያለችው ፍቅር እና ራስ ወዳድነት የሌለ አገልግሎታችው በጥሪአችን እንደሆኑት በእናንተም ጥሪ በጣም አስፈላጊ ናቸው። በዚህ ቤተክርስትያን የህይወት ዘመን አገልግሎት ውስጥ፣ አንድ ሰው በየትኛውም ቦታ ብያገለግል ምንም ግድ እንደሌለው ተምሬአለሁ። ጌታ የሚያስብበት እንዴት ሰው እንደሚያገለግል ነው።

ከ50 አመት በላይ ለእኔ ምሳሌ ለነበሩት፣ ለፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ ጥልቅ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ለአማካሪዎቻቸው፣ ለፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እና ለፕሬዘደንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ያለኝን ታላቅ አድንቆት እገልጻለሁ። ለጌታና ለነብያት አገልግሎታቸው አሞግሻቸዋለሁ። ነገር ግን እነዚህ መለኮታዊ አገልጋዮች አዲስ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። በብርታት እና በዝግጁነት በማገልገል ይቀጥላሉ። ሁለቱንም አከብራቻዋለሁ፣ እንዲሁም እወዳቸዋለሁ።

በጌታ ስልጣን እና ሀይል በእውነተኛ እና ህያው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ማገልገል አስገራሚ በረከት ነው። የክህነት ቁልፎችን ጨምሮ፣ የእግዚአብሔር ክህነት በዳግም መመለስ፣ ለብቁ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ከሁሉም በላይ ታላቅ መንፈሳዊ በረከቶች ይከፍታል። እነዚህ በረከቶች በመላው ዓለም ለሚገኙ ሴቶች፣ ወንዶች እና ልጆች ሲፈሡ ተመልክተናል።

በጥሪአቸው እና በመንፈስ ስጦታና በሌሎች የቤተመቅደስ ስርዓቶቻቸው ውስጥ ያለውን ኃይል የሚራዱ ታማኝ ሴቶች እናያለን። እነዚህ ሴቶች ባለቤቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን እና ሌሎች የሚያፈቅሯቸውን ለመጠበቅ እና ለማጠናከር የሰማይ ሀይልን መጥራት ያውቃሉ። እነዚህም በጥሪያቸው በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን ያለፍርሀይ የሚመሩ፣ የሚያስተምሩ፣ እና የሚያገለግሉ መንፈሳዊ ጠንካራ ሴቶች ናቸው!1 ለእነርሱ ምን ያህል ምስጋና አለኝ!

በተመሳሳይ ሁኔታ፣እንደ የክህነት ስልጣን ተሸካሚነታቸው መብቶቻቸው የጠበቁ ታማኝ የሆኑ ወንዶችን እናያለን። በመስዋዕት በጌታ መንገድ የሚመሩት እና የሚያገለግሉት በፍቅር፣ በደግነት፣ እና በትዕግስት ነው። ሌሎችን በሚሸከሙት በክህነት ሀይል ይባርካሉ፣ ይመራሉ፣ ይጠብቃሉ፣ እናም ያጠናክራሉ። የራሳቸውን ጋብቻ እና ቤተሰብ እየጠበቁም ለሚያገለግሉት ታዕምራቶችን ያመጣሉ። ክፉን ይርቃሉ እናም የእስራኤል ታላቅ ሽማግሌዎች ናቸው።2 ለእነርሱም ምስጋና አለኝ!

አሁን፣ አንድ አሳሳቢ ነገር ልናገር? ይህም ይህ ነው፥ ብዙዎቹ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የክህነት ሀይል እና ስልጣንን በሙሉ አይረዱትም። የእግዚአብሔርን ሀይል ልጆቹን ለመባረክ ከመጠቀም የራስ ወዳጅ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንደሚፈልጉ አይነት ናቸው።

ብዙዎቹ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችን ለእነርሱ የሚሆኑትን መብቶች የሚረዱ እንዳልሆኑ ፍርሀቴ ነው።3 አንዳንድ ወንድሞቻችን፣ ለምሳሌ፣ ክህነት ምን እንደሆነ እና ምን ለማድረግ እንደሚያስችላቸው የማይገባቸው ይመስላሉ። ልዩ ምሳሌዎች ልስጣችሁ።

በቅርብ ጊዜ፣ አዲስ ህጻን ስም እና የአባት በረከት የሚሰጥባት የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። ወጣቱ አባት ውድ ህጻኑን አቅፎ፣ ስም ሰጣት፣ እናም በጣም ቆንጆ ጸሎት አቀረበ። ነገር ግን ለዚህች ልጅ ምንም በረከት አልሰጠም። ይህች ሴት ልጅ ስም አገኘች ግን ምንም በረከት አልተሰጣትም! ውዱ ሽማግሌ በጸሎት እና በክህነት በረከት ምን ልዩነት እንዳለ አላወቀም። በክህነት ስልጣኑ እና ሀይል፣ ህጻን ልጁን ለመባረክ ይችል ነበር፣ ግን አላደረገውም። እንዲህ አሰብኩኝ፣ “ምን ያመለጠ እድል ነው!”

አንዳንድ ሌሎች ምሳሌዎችን ልጥቀስ። እንደ መጀመሪያ ክፍል፣ ወጣት ሴቶች፣ ወይም የሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች እና አስተማሪዎች እህቶችን የሚለዩ ግን ጥሪያቸውን ለማከናወን በሚችሉበት ሀይል ያልባረኳቸው ወንድሞች እንዳሉ እናውቃለን። ማሳሰቢያዎች እና መመሪያዎችን ብቻ ነው የሚሰጡት። የሚያስፈልጋቻው ይህ ሆን ሳለ፣ ለባለቤቱ እና ለልጆቹ የክህነት በረከቶችን የማይሰጥ አንድ ብቁ አባት ይታየናል። የክህነት ሀይል በምድር ላይ በዳግም ተመልሷል፣ እናም በጣም ብዙ የሆኑ ወንድሞች እና ሴቶች እውነተኛ የክህነት በረከትን ሳይቀበሉ በከፍተኛ የፈተናዎች ህይወት ያፋሉ። ይህ እንዴት የሚያሳዝን ነው! ያም ልንወግደው የምንችል አንድ አሳዛኝ ነገር ነው።

ወንድሞች፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ክህነት ነው የምንሸከመው! ህዝቡን ለመባረክም የእርሱ ስልጣን አለን። ጌታ እንዲህ ሲል ስለሰጠን አስደናቂ ማረጋገጫ አስቡበት፥ “ማንንም የምትባርኩትን እኔም እባርከዋለሁ።”4 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ልጆቹን ለመባረክ እድላችን ነው። የካስማ ፕሬዘደንቶች እና ኤጲስ ቆጶሶች፣ በእናንተ ሀላፊነት ስር ያሉ እያንዳንዱ የሸንጎ አባላት የክህነት በረከት እንዴት እንደሚሰጡ፣ በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ሀይል በሙሉ ለመጥራት የሚያስፈልገውን የግል ብቁነት እና መንፈሳዊ ዝግጅትን የተረዱ እንደሆኑ አረጋግጡ።5

ለሁሉም ለክህነት ወንድሞች፣ አባላትን ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲጾሙና እንዲጸልዩ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እንዲያጠኑ፣ በቤተመቅደስ እንዲያመልኩ፣ እና እንደ እግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች በእምነት እንዲያገለግሉ እንድታነሳሷቸው እጋብዛችኋለሁ። ሁሉም ታዛዥነት እና ጻድቅነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያቀርባቸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነትን እንዲደሰቱ በመፍቀድ፣ እና በህይወት ደስታ እንዲያጋጥማቸው በእምነት አይን እንዲያዩት ለመርዳት እንችላለን።

ሁልጊዜም የጌታ እውነተኛና ህያው ቤተክርስቲያን ማመልከቻ ቢኖር ለእግዚአብሔር ልጆች በግለሰብ እና ለቤተሰቦቻቸው የማገልገል የተደራጀ፣ የሚመራ ጥረት ነው።6 ይህችም የእርሱ ቤተክርስቲያን ስለሆነች፣ እኛ እንደ እርሱ አገልጋዮች፣ እርሱ እንዳደረገው፣ እያንዳንዱን እናገለግላለን።7 በስሙም በእርሱ ሀይል እና ስልጣን፣ እናም በእርሱ አፍቃሪ ደግነት እናገለግላለን።

ከ60 አመታት በፊት በቦስተን አጋጥሞኝ የነበረው አንድ-ለአንድ-አንድ የማገልገል እድል እንዴት ሀይለኛ እንደሆነ አስተምሮኛል። በዚያ ጊዜ በማሳቹሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የቀዶ ጥገና ሃኪም ነበርኩኝ፣ በዚያም በየቀኑ፣ በየሌሊቱ፣ እናም በሁለት ሳምንት አንዴ በቅዳሜና እሁድ ስራ ላይ ነበርኩኝ። ለባለቤቴ፣ ለአራት ልጆችችን፣ እና ለቤተክርስቲያን ተሳታፊነት የተወሰነ ጊዜ ብቻ ነበረኝ። ህይም ቢሆን፣ የቅርንጫፍ ፕሬዘደንታችን ወንድም ኮክስ በቤተክርስቲያን ተሳታፊ እንዲሆን ተስፋ በማድረግ የዊልበርና ሊዮኖራን ቤት እንድጋብዝ መደቡኝ። እርሳቸው እና ሊዮኖራ በቤተመቅደስ ተሳስረው ነበር።8 ግን፣ ዊልበር ለብዙ አመታት ተሳታፊ አልነበሩም።

ጓደኛዬ እና እነ ወደቤታቸው ሄድን። ፣ ስንገባም፣ እህት ኮክስ ሞቅ ያለ አቀባበል አደረጉልን፣9 ግን ወንድም ኮክስ ወዲያው ወደሌላ ክፍል ሄዱ እና በሩን ዘጉ።

ወደተዘጋው በር ሄድኩኝና አንኳኳሁ። ከጊዜ በኋላ፣ ጸጥ ያለ “ግባ” የሚልን ሰማሁ። በሩን ከፍቼ ወንድም ኮክስ በሙያ ያልሰለጠነ የራድዮ መሳሪያዎች አጠገብ ተቀምጠው አገኘኋቸው። በዚያዝ ትንሽ ክፍል ውስጥ፣ ሲጋራ አነደደ። በግልጽ፣ የእኔ ጉብኝት የማይፈለግ ነበር።

በክፍሉ በመገረም ተመለከትኩኝና እንዲህ አልኩኝ፣ “ወንድም ኮክስ፣ በሙያ ስላልሰለጠነ የራድዮ ድርጊት ለመማር ሁልጊዜም እፈልግ ነበር። ስለዚህ ሊያስተምሩኝ ይችላሉን? በዚህ ምሽት በምንም ለብዙ ጊዜ ለመቆየት አልችልም፣ ነገር ግን በሌላ ጊዜ ለመምጣት እችላለሁን?”

ለትንሽ ጊዜ አመነቱ፣ ከዚይም እሺ አሉ። ያም አስደናቂ የሆነ ጓደኝነት መጀመሪያ ሆነ። ተመለስኩኝ እናም አስተማሩኝ። እርሳቸውን ማፍቀርና ማክበር ጀመርኩኝ። በቀጣይ ጉብኝቶቻችን፣ የዚህ ሰው ታላቅነት ወጣ። በጣም ጥሩ ጓደኞች ሆንን፣ ዘለአለማዊ ጓደኞቻችንም ሆኑ። ከዚያም፣ ጊዜ ካለፈ በኋላ፣ ቤተሰባችን ወደሌላ ቦታ ሄድን በአካባቢው ያሉ መሪዎች የኮክስ ቤተሰብን በመንከባከብ ቀጠሉ።10

ከመጀመሪያው ጉብኝት ስምንት አመት በኋላ፣ የቦስተን ካስማ ተደራጀ።11 የዚያ የመጀመሪያ የካስማ ፕሬዘደንት ማን እንደሆነ ለመገመት ትችላላችሁን? አዎ! ወንድም ኮክስ! በሚቀጥሉት አመታት፣ እንደ ሚስዮን ፕሬዘደንት እና የቤተመቅደስ ፕሬዘደንት አገለገሉ።

ከአመታት በኋላ፣ እኔ፣ እንደ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል፣ ካስማ በሳንፒት አውራጃ፣ ዩታ ለማደራጀት ተመድቤ ነበር። በዚያ የቃል ጥያቄ ጊዜ፣ ውድ ጓደኛዬን ወንድም ኮክስ እንደገና ለመገናኘት ችዬ ነበር። እርሳቸውን እንደ አዲስ የካስማ ፓትሪያርክ ለመጥራት ስሜት መጣልኝ። እርሳቸውን ከሾምኩኝ በኋላ፣ ተቃቀፍን እና አለቀስን። በክፍሉ የነበሩ ሰዎች ለምን እነዚህ ያደጉ ወንዶች እንደሚያለቅሱ ተገርመው ነበር። ነገር ግን እናውቅ ነበር። እናም እህት ኮክስ ያውቁ ነበር። የእኛ የደስታ እምባዎች ነበሩ! በጸጥታ ከሰላሳ አመት በፊት፣ በአንድ ምሽት በእነርሱ ቤት ውስጥ፣ የተጀመረውን አስደናቂ የፍቅር እና የንስሀ መግባት ጊዞን እናስታውስ ነበር።

ታሪኩ በዚህ አያልቅም። የወንድም እና እህት ኮክስ ቤተሰብ 3 ልጆችን፣ 20 የልጅ ልጆችን፣ እና 54 የልጅ ልጅ ልጆችን ጨምረው አድገው ነበር። በብዙ መቶ ሚስዮኖች፣ በቤተመቅደስ ውስጥ ሺሆች፣ እና በተጨማሪም በወንድም ዊልበር እጆች ስር የፓትሪያርክ በረከቶች የተቀበሉት ብዙ መቶዎች ይህን ደምሩት። የእርሳቸው እና ሊየኖራ ተጽእኖ በመላው ዓለም በበርካታ ትውልዶች ውስጥ ይቀጥላል።

ከዊልበርና ሊየሮራ ኮክስ ጋር የነበረ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች በየሳምንቱ—ምናልባት በየቀሉ—በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ይደርሳል። የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ አገልጋዮች ስራውን በእርሱ ሀይል እና ስልጣን ያከናውናሉ።

ወንድሞች፣ የምንከፍታቸው በሮች አሉ፣ ለመስጠት የምንችላቸው የክህነት በረከቶች፣ የምንፈውሳቸው ልቦች፣ የምናነሳቸው ሸከሞች፣ የምናጠናክራቸው ምስክሮች፣ የምናድናቸው ህይወቶች፣ እና በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤቶች ለማምጣት የምንችላቸው ደስታ አለ—ሁሉም የእግዚአብሔርን ክህነት ስለምንሸከም ነው። እኛም “ከዓለም መፈጠር ጀምሮ በእግዚአብሔር በቀደመው እውቀት መሰረት በእምነታችን” ይህን ስራ ለማከናወን የተጠራን ወንዶች ነን።12

በዚህ ምሽት በታላቅ ዘለአለማዊ ወንድምነት ከእኔ ጋር እንድትነሱ አጋብዛለሁ። የክህነት ሀላፊነታችሁን ስጠራ፣ እባካችሁ ተነሱ እና በመቆም ቆዩ። ዲያቆኖች፣ እባካችሁ ተነሱ! አስተማሪዎች፣ ተነሱ! ካህናት! ኤጲስ ቆጶሶች! ሽማግሌዎች! ሊቀ ካህናት! ፓትሪያርኮች! ሰባዎች! ሐዋሪያት!

አሁን፣ ወንድሞች፣ ቆማችሁ ከዘማሪዎች ጋረ “ተነሱ፣ የእግዚአብሔር ወንዶች ሆይ”13 የሚለውን መዝሙር እባካችሁ ለመዘመር ትችላላችሁን? ስትዘምሩም፣ እንደ እግዚአብሔር ሀይለኛ ሰራዊቶች አለምን ለጌታ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት ለመርዳት ስላላችሁ ሀላፊነት አስቡበት። ይህም ሀላፊነታችን ነው። ይህም እድላችን ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።