2010–2019 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔርን ለመገናኘት ተዘጋጁ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


እግዚአብሔርን ለመገናኘት ተዘጋጁ

በጽድቅ, አንድነትና በእኩልነት የተቀበሉትን መለኮታዊ ሃላፊነቶች መከታተል እግዚአብሔርን እንድንገናኝ ያዘጋጅልናል።

ኤሊዛ አር ስኖው፣ (ስለተካፈሉት) የኪርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፥ “የምረቃው ሥነ-ሥርዓቶች ልምምድን ሊያካትቱ ይችላል፣ ነገር ግን ያንን የማይረሳ ቀን የሰማይ መገለጦችን ምንም የሰው ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም። መላእክት ለአንዳንዱ ተገለጡ፣ በተገኙት ሁሉም ላይ የመለኮታዊ መገኘት ተረጋገጠ፣ እናም እያንዲንዱም ልብ መግለጽ በማይቻል እና በክብር ደስታ ተሞልቶ ነበር።”1

በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ የተከናወኑት መለኮታዊ መገለጦች ለተመለሰው የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ዓላማ የሰማይ አባታችን ልጆችን ደህንነት እና ዘለአለማዊነትን ለማምጣት ዋና መሠረት ነበራቸው።2 እግዚአብሔርን ለመገናኘት ስንዘጋጅ፣ መለኮታዊ ሃላፊነቶቻችንን በኪርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ የተመለሰውን የተቀደሱ ቁልፎች በመከለስ እናውቃለን።

በምረቃው ጸሎት፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጌታን “እንድንገነባ ያዘዝከንን ይህን ቤት እንድትቀበል”3 በማለት በትህትና ተማጸነ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ በፋሲካ እሁድ፣ ጌታ በድንቅ ራዕይ ተገለጠ እናም ቤተመቅደሱን ተቀበለ። ይህም የተከሰተው በሚያዚያ  3, 1836(እ.ኤ.አ), በትክክል ከ 182 ዓመታት በፊት ከፋሲካ እሁድ ነበር። የአይሁድም በዓል ነበር ማለትም የፋሲካ በዓል እና የአይሁድ በዓል በተመሳሳይ ቀን የሚከሰትበት ጊዜ ነበር። ራእዩ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ሶስት ጥንታዊ ነብያቶች፣ ሙሴ፣ ኤልያስ እና ኤላይጃ በዚህ ዘመን የተመለሰችውን የጌታን ቤተክርስቲያን ዓላማ ለማሟላት አስፈላጊ የሆኑትን ቁልፎች ገለጡ። ያ ዓላማው በቀላሉ፣ ግን አንደበትን በሚረታ ሁኔታ፣ እስራኤልን የመሰበሰብ፣ ቤተሰቦችን ለማተሚያ እናም አለምን ለጌታ ዳግም ምጽዓት እንደሚያዘጋጅ መግለጹ ነበር።4

ኤሊያስ እና ሙሴ መታየታቸው “በመጨረሻው ዘመን” ሙሴና ኤልያስ በአንድነት እንደሚመጡ “ከአይሁድ ወግ ጋር ተመሳሳይነት አለው”5 በትምህርታችን፣ ይህ መገለጽ “በመጨረሻዎቹ ቀኖች እና በመጨረሻው ጊዜ፣ የአጠቃላዩ ጊዜ ስርአቶች” የተሰጡትን አንዳንድ ቁልፎች መሰረታዊ መመለስን አሟልቷል።6

የከርትላንድ ቤተመቅደስ፣ በመጠኑና በቦታው ፣ በአንጻራዊ ሁኔታ ድብቅ ነበር። ሆኖም ግን ለሰው ልጅ ትልቅ ጠቀሜታው ዘለዓለማዊነትን የሚቀርጽ ነው። የጥንት ነቢያት የክህነት ቁልፎችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዘላለማዊ የማዳን ስርዓቶች መልሰዋል። ይህም ለታማኝ አባሎች ታላቅ ደስታ አስገኝቶላቸዋል።

እነዚህ ቁልፎች በዛን ጌዜ እና አሁን በመለኮት ከተሰጡ ለቤተክርስቲያኗ ዋና ዓላማዎች የሰማይን ሃይል7 ያቀርባሉ።8 በዚያ የከበረ የፋሲካ በዓል ቀን በከርትላንድ ቤተመቅደስ ሶስት ቁልፎች ወደነበሩበት ተመልሰዋል።

በመጀመሪያ፣ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ ከአራቱ የምድር ክፍሎች የመሰብሰብ፣ ማለትም የሚሲዮናዊ ስራን፣ ቁልፎች በመገለጥ መለሰ።9

ቀጥሎም፣ ኤልያስ የአብርሃም ወንጌል መመለስን የሚያበስረውን የአብርሃምን ወንጌል ቁልፎች ገለጸ።10 ፕሬዘደንት ራስል  ኤም ኔልሰን የቃል ኪዳኑ ቁልፎች አላማ እግዚአብሔርን መንግስት አባላትን ለማዘጋጀት መሆኑን አስተምረዋል። እሳቸውም “ማን እንደሆንን እና እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ እናውቃለን” ብለዋል።11

ሶስተኛው፣ ኤላይጃ በዚህ ዘመን የማተሚያ ሀይል ቁልፎች፣ የቤተሰብ ታሪክ ስራ በህይወት ያሉትን እና ሙታንን ማዳን የሚያስችል የቤተመቅደስ ቁልፎችን በመገለጽ መለሰ።12

በኬርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ በተመለሱት ቁልፎች ላይ በመመርኮዝ እነዚህን ሶስት የተመለሱ ሃላፊነቶችን በበላይነት የሚቆጣጠሩ ሶስት በቤተክርስቲያኑ ዋና ጽፈት ቤት እና በአስራ ሁለቱ ጉባኤ አመራር ሥር አሉ። የሚስዮን አስፈጻሚ መማክርት፣ የክህነት ስልጣን እና የቤተሰብ አስፈፃሚ መማክርት እና የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ዋና አጣሪ መማክርት ናቸው።

እነዚህ መለኮታዊ ኃላፊነቶችን ለማሟላት በዛሬው ጊዜ የምንቆምበት ቦታ ምንድን ነው?

በመጀመሪያ፣ ሙሴ ለእስራኤላውያን መሰብሰቢያ ቁልፎች አስመልክቶ፣ ዛሬ ወደ 70,000 የሚደርሱ ሚስዮኖች ወንጌልን በመስበክ እጩዎቹ እንዲሰበስቡ ተሰራጭተዋል። ኔፊ የተመለከተው ታላቁና ድንቅ ስራ በአህዛብ እና በእስራኤል ቤት የሚሟላበት ይህ መነሻው ነው። ኔፊ የእግዚኣብሄር ቅዱሳን በምድር ገጽ ላይ የሚሆኑበትን ጊዜያችንን አይቷል፣ ነገር ግን ቁጥራቸው በሃጢያት ምክንያት ትንሽ ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ “በጽድቅ እና በእግዚአብሄር ኃይል እንደሚታጠቁ” በታላቅ ክብር አስቀድሞ ተመልክቷል።13 በዳግም የተመለሰውን ቤተክርስትያን አጭር ታሪክ ስንመለከት ሚስዮናዊ ጥረት በጣም የሚያስደንቅ ነው። የኔፊን ራዕይ መሟላት እየተመለከትን ነው። ምንም እንኳን ቁጥራችን በአንጻራዊነት ጥቂት ቢሆንም፣ የአዳኙን መልዕክት ምላሽ ለሚሰጡ ሰዎች ጥረታችንን እንቀጥላለን።

በሁለተኛ ደረጃ፣ እኛ እና በእኛ ዘር ያሉ ትውልዶች ሁሉ እንዲባረኩ እያወጀ ኤልያስ በመገለጥ የአብራሃም ወንጌልን አቀረበ። በዚህ ጉባኤ ውስጥ፣ ታላቅ ትርጉን ያለው መመሪያ ቅዱሳናትን ፍጹም ለማድረግ እና ለእግዚአብሄር መንግስት ለማዘጋጀት ተቀርቧል።14 ስለሽማግሌዎች እና ስለሊቀ ካህናት በሚመለከት በክህነት ስብሰባ ውስጥ የነበረው ማስተዋወቂያ የክህነት ሀይልን እና ስልጣን ይከፍታል። አሁን “አገልግሎት” የሚባለው የቤት ለቤት ጉብኝት እና የሴቶች የጉብኝት ትምህርት የኋለኛውን ቀን ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ጋር እንደገና እዲገናኙ ያዘጋጃቸዋል።

ሦስተኛ፣ ኤልያስ የዚህን የዘመን የማተሚያ ቁልፎች አቀረበ። በዚህ ጊዜ ለእኛ በህይወት ለምንኖረው፣ የቤተመቅደሶች እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ መጨመር በጣም አስገራሚ ክስተት ነው። አዳኙ ዳግም እስኪመጣ ድረስ መላው ምድር “በሚመጣበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዳይጠፋ”15 ይህ በፍጥነት ይቀጥላል እና ይፈጥናል።

ባለፈው ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከሰማይ ከተሰጠው ቴክኖሎጂ አማካኝነት የቤተሰብ ታሪክ ሥራ በጣም ተጨምሯል። ይህን መለኮታዊ ኃላፊነት አክስት ጄን ወይም ሌላ የታመነ ዘመድ ያከናውናሉ ብለን ከገመትን ጠቢብ አይደለንም። ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝን የሚያስገርም አስተያየት ላካፍል፥ “ማንም ከዚህ ትልቅ ግዴታ ነፃ አይደለም።” ከሐዋርያው ​​አንስቶ እስከ ዝቅተኛው ሽማግሌ ወይም [እህት] የሚጠበቅ ነው። ቦታ፣ወይም መታወቅ፣ወይም በቤተክርስቲያኗ ለረጅምጊዜ ማገልገል … ምንም የሙታንን ደህንነት ችላ ለማለት ምንም መብት አይሰጥም።”16

በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ቤተመቅደሶች አሉ እና ከቤተ-መቅደስ ርቀው ለሚገኙ እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል የገንዘብ እርዳታዎች አሉን፡

በግለሰብ ደረጃ፣ የሚሲዮንን፣ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን እና እግዚአብሔርን ለመገናኘት ዝግጅታችንን የምናደርገውን ጥረት ብንገመግም የተሻለ እናከናውናለን።

በጌታ ዘንድ ጽድቅ፣ ህብረት እና እኩልነት እነዚህን ቅዱስ ተግባራት ያጠነክራሉ።

ጽድቅን በተመለከተ፣ ይህ ሕይወት ሁላችንም ጌታን ለመገናኘት እንድንዘጋጅ ነው።17 ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ማክበር ሲያቆሙ መፅሐፈ ሞርሞን በርካታ አሳዛኝ ውጤቶችን ያቀርባል።18

በሕይወቴ ወቅት፣ ዓለማዊ ጉዳዮች እና ጭንቀቶች ከአንዱ አድማስ፣ ከሞኝነት እና ቁም ነገር ካልሆነ ተግባር ወደ ከባድ የሥነ ምግባር መበላሸት ወደ ሌላ ተሸጋግረዋል። ስምምነት የሌለው ሥነ ምግባር የጎደላቸው ሰዎች መጋለጣቸው እና መወገዛቸው የሚደገፍ ነው።19 እንዲህ ዓይነቶቹ ያልተወሳሰቡ የሥነ ምግባር ብልግናዎች የእግዚአብሔርን እና የህብረተሰቡን ሕግጋት ይቃረናሉ። ይሁን እንጂ፣ የእግዚአብሔርን እቅድ የሚያውቁ ሰዎች ስምምነት ያለውን የሥነ ምግባር ጉድለት መቃወም አለባቸው፣ ይህም ደግሞ ኃጢያት ነው።። ቤተሰብ፣ ለአለም አዋጅ የሚለው አንቀጽ እንደሚያስጠነቅቀው “የንጽህናን ህግ ቃልኪዳኖች የሚጥሱ ግለሰቦች፣ የትዳር ጓደኛን ወይም ልጆችን [ወይም ለማንኛውም] የሚያጎሳቅሉ፣ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች ይሆናሉ።”20

ዙሪያችንን ስንመለከት፣ ክፋትንና ሱስን በየአቅጣጫው እናያለን። እንደ ግለሰብ፣ ለአዳኝ የመጨረሻው ፍርድ በእርግጥ ከልብ በማሰብ፣ ንስሀ መግባት አለብን። ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች ከመሆናቸውም በላይ ወደ ቅዱሳት መጻህፍት ወይንም የነቢያት መመሪያን አይሰሙም። እኛ፣ እንደ አንድ ህብረተሰብ፣ በኀጢአት መዘዝ ላይ የምናሰላስል ከሆነ፣ የብልግና ምስሎች እና ሴቶችን ማቃለልን ብዙ ሕዝብ ይቃወሙ ነበር።21 አልማ ለልጁ ኮሪያንተን በመፅሐፈ ሞርሞን እንደገለጸው፣ ክፋት ፈጽሞ ደስታ አይሆንም።22

መተባበርን በተመለከተ፣ አዳኝ እንዲ ሲል አወጀ፣ “ አንድ ካልሆናችሁ፣ የእኔ አይደላችሁም።”23 የክርክር መንፈስ የሰይጣን መንፈስ እንደሆነ እናውቃለን።24

በዘመናችን ለአንድነት ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስፈላጊነት በአብዛኛው ችላ ተብሏል፣ እናም ለብዙ ሰዎች አፅንዖት የሚሰጡት በጎሳዊነት ላይ ነው፣25 ብዙውን ጊዜ በቋንቋ፣ በፆታ፣ በዘር እና በሀብት ላይ የተመሠረተ ነው። በበርካታ አገሮች ውስጥ፣ ብዙ ባይሆኑም፣ ሰዎች ባኗኗራቸው ላይ በጥልቅ ይከፋፈላሉ። በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ የምንከተለው እና የምናስተምረው ባህል የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ባህል ነው። አንድነት የምፈልገው ከአዳኝ እና ከእርሱ ትምህርቶች ጋር ነው።26

የቤተክርስቲያኗ ዋና አላማዎችን ስንመለከት፣ ሁሉም በጌታ ፊት እኩልነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው27 እናም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ባህል መከተል ነው። ከሚስዮናዊ ስራ ጋር፣ ለጥምቀት አስፈላጊ የሆኑት መዘጋጃዎች በእግዚአብሔር ፊት ራስን ዝቅ ማድረግ እና የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ መምጣት ነው።28 ትምህርት፣ ሀብት፣ የዘር ወይም የብሄራዊ ማንነት ከግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም።

በተጨማሪም፣ ሚስዮኖች በተጠሩበት ቦታ በትህትና ያገለግላሉ። በአለማዊ ደረጃዎች ወይም ለወደፊት የሙያ ስራዎች በማዘጋጀት ለማገልገል አይሞክሩም። በሙሉ ልባቸው፣ ሃሳባቸው፣ አዕምሮአቸው፣ እና ጥንካሬአቸው በየትኛውም ቦታ ሆነው ያገለግላሉ። እነሱ የሚስዮናዊነት ወዳጆቻቸውን አይመርጡም እናም የክርስቶስን ዓይነት ባህሪያት ለማዳበር በትጋት ይሻሉ፣29 ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ባህል ውስጥ ማእከላዊ ነው።

ቅዱሳት መጻህፍት በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ግንኙነቶቻችን መመሪያ ይሰጣሉ። አዳኝ የመጀመሪያው ትእዛዝ “ጌታ አምላክህን ውደድ” ብሎ አስተማረ። ሁለተኛ ደግሞ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”30

አዳኙ ሁሉም ሰው ባልንጀራችን መሆኑን ጎላ አድርጎ ገልጿል።31 መፅሐፈ ሞርሞንም ምንም ዓይነት ሰዎች፣ ጎሳዎች፣ ወይም ክፍሎች መኖር እንደሌለባቸው ግልፅ አድርጓል። 32 አንድ መሆን እና እኩል መሆን አለብን።

ቅዱስ ስነስርዓቶች እና መለኮታዊ ሃላፊነቶች በዚህ መሰረት ይገነባሉ። በቤተመቅደስ ውስጥ ያላችሁ ልምዶች ከእኔ ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆኑ እጠብቃለሁ። በሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ ያለውን የሥራ ቦታዬን ትቼ ወደ ኦክላንድ ቤተመቅደስ በምጣበት ጊዜ፣ በፍቅር እና በሰላም ስሜት እሞላ ነበር። ከዛው ውስጥ ዋነኛው ክፍል ወደ እግዚአብሄር የተቃረብሁ መሆኔ ስለሚሰማኝ ነበር። የማዳኑ ስነ-ስርአቶች የእኔ ዋነኛ ትኩረት ነበሩ, ግን የእነዚህ ውብ ስሜቶች ዋነኛ ክፍል ቤተመቅደስ ውስጥ ያለ እኩልነትና አንድነት ነበር። ሁሉም ነጭ ልብስ ይለብሳሉ። የሀብት ደረጃ ወይም የትምህርት ደረጃ ምንም አይታይም፤ እኛ ሁላችንም ወንድሞች እና እህቶች በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ያዋረድን ነን።

በቤተመቅደሰ የማተሚያ ክፍል ውስጥ፣ የዘለአለም የጋብቻ ስርዓት ለሁሉም ሰው አንድ አይነት ነው። ዝቅተኛ የሆነ ህይወት ያላቸው ባልና ሚስት እና የበለፀጉት ባልና ሚስት ተመሳሳይ ተሞክሮ የመኖራቸውን እወነታ እወዳለሁ። ተመሳሳይ ዓይነት ልብሶችን ይለብሳሉ እና ተመሳሳይ መስዋዕቶች በአንድ መሠዊያ ላይ ያቀርባሉ። እነሱም ተመሳሳይ የሆነ የዘላለማዊ የክህነት በረከቶችን ይቀበላሉ። ይህም የሚከናወነው በቅዱሳን አስራት አማካኝነት እንደ የተቀደሰ የጌታ ቤት የተገነባ ቤተመቅደስ ውስጥ ነው።

በጌታ ፊት በጻድቅነት፣ በአንድነት፣ እና በእኩልነት የተሰጣቸውን መለኮታዊ ሃላፊነቶች ማሟላቱ የግል ደስታን ያመጣል እና በዚህ አለም እና በሚመጣው አለም ዘለአለማዊ ህይወት ያዘጋጀናል።33 ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ያዘጋጀናል።34

እያንዳንዳችሁ፣ አሁን ያላችሁበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምንም፣ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር ምክክር በማድረግ ለቤተመቅደስ መግቢያ ብቁ መሆን እንድትችሉ እንጸልያለን።35

ብዙ ተጨማሪ አባሎች ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ እየተዘጋጁ ስለመሆናቸው አመስጋኞች ነን። ለበርካታ አመታት ብቁ የአዋቂ ቤተመቅደስ የመግቢያ ፍቃድ ተሸካሚዎች ቁጥር ከፍ ጭማሪ አሳይቷል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለብቁ ታዳጊ ወጣቶች የሚሰጠው ውስን የመግቢያ ፍቃድ ቁጥሩ በሚገርም ሁኔታ ጨምሯል። የቤተክርስቲያኗ ዋና አባላት ጠንካራነት ከዚህ በላይ አለመኖሩ በግልጽ የታወቀ ነው።

በማጠቃለያ፣ መለኮታዊውን ዓላማ የተቀበሉት የቤተክርስቲያን መሪዎችን መለኮታዊ እርዳታ እንደሚቀበሉ እርግጠኛ ሁኑ። ይህ መመሪያ የሚመጣው ከመንፈስ ቅዱስ ሲሆን አንዳንዴም በቀጥታ ከአዳኝ ነው። ሁለቱም አይነት መንፈሳዊ መመሪያዎች ይሰጣሉ። እንዲህ ዓይነቱን እርዳታ በማግኘቴ አመስጋኝ ነኝ። ነገር ግን የጌታ መመሪያ በጌታ ጊዜ፣ ቀስ በቀስ እናም ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ36 “ሁሉን ቻይ ጌታ ሆን ብሎ የእኛን መማር ሲመርጥ ነው።”37 አጠቃላይ ለቤተክርስቲያኑ የሚሰጠው መመሪያ በነቢዩ አማካኝነት ብቻ ነው።

ሁላችንም ፕሬዚዳንት ራስል  ኤም ኔልሰንን በዚህ ጉባኤ ውስጥ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ፕሬዘደንት እንዲሆኑ ደግፈናል። አስራ ሁለታችን፣ እንደ ቡድን እና በግላችን በፕሬዘደንት ኔልሰን እና በፕሬዘደንት ዳለን  ኤች ኦክስ እጃችንን በጫን ጊዜ ጉልህ የሆነ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነበረን። እርሱ አስቀድሞ የተወከለ እና ለዘመናችን የጌታ ነብይ እንዲሆን ህይወቱን በሙሉ እንደተዘጋጀ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።