ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 15–21 (እ.አ.አ)፦ “ኑ እና ፍሬውን ተቋደሱ።” 1 ኔፊ 6–10


“ጥር 15–21 (እ.አ.አ)፦ ‘ኑ እና ፍሬውን ተቋደሱ’ 1 ኔፊ 6-10፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ጥር 15–21 (እ.አ.አ)። 1 ኔፊ 6–10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2023 (እ.አ.አ)]

ምስል
የሌሂ የህይወት ዛፍ ራዕይ

የሌሂ ህልም፣ ስቲቭን ሎይድ ኒል

ጥር 15–21 (እ.አ.አ) :- “ኑ እና ፍሬውን ተቋደሱ”

1 ኔፊ 6–10

የሌሂ ህልም—ማለትም የብረቱ ዘንግ፣ የጨለማው ጭጋግ፣ ሰፊው ሕንፃ እና “እጅግ ጣፋጭ” የዛፍ ፍሬ-—የአዳኙን ፍቅር እና የሃጢያት ክፍያ መስዋዕትነት በረከቶችን ለመቀበል የሚያነሳሳ ግብዣ ነው። ይሁን እንጂ፣ ለሌሂ ይህ ህልም ስለ ቤተሰቡም ጭምር ነበር፦ “እናም እነሆ ባየሁት ነገር የተነሳ በኔፊና ደግሞም ስለ ሳም በጌታ የምደሰትበት ምክንያት አለኝ… ነገር ግን እነሆ ላማንና ልሙኤል፣ በእናንተ ምክንያት እጅግ እፈራለሁ” (1 ኔፊ 8፥3–4)። ሌሂ ህልሙን ገልጾ ሲያበቃ ላማንን እና ልሙኤልን “ምናልባት ጌታ ለእነርሱም መሐሪ እንዲሆንላቸው የእርሱን ቃላት እንዲሰሙ” ለመናቸው (1 ኔፊ 8፥37)። ምንም እንኳን የሌሂን ህልም ብዙ ጊዜ ያጠናችሁ ቢሆንም፣ በዚህ ጊዜ ልክ ሌሂ ባሰበበት መንገድ አስቡ—ስለምትወዱት ሰው አስቡ። ይህንን ስታደርጉ የብረት ዘንጉ ደህንነት፣ የሰፊው ሕንፃ አደገኝነት እና የፍሬው ጣፋጭነት አዲስ ትርጉም ይኖራቸዋል። እንዲሁም ይህን ድንቅ ህልም የተቀበለን “[የአፍቃሪ] ወላጅን ሙሉ ስሜት” የበለጠ በጥልቀት ትረዳላችሁ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

1 ኔፊ 7፥6–21

ሌሎችን ይቅር ማለት እችላለሁ።

1 ኔፊ 7፥6–21 ውስጥ ስለ ኔፊ ምሳሌ ምን ያስደንቃችኋል? እርስ በእርስ “በእርግጥ ይቅርታ” ስንደራረግ እንዴት ነው የምንባረከው? “ጌታ ኔፊን ከአመጸኛ ወንድሞቹ አዳነው [The Lord Delivers Nephi from His Rebellious Brothers]” (የወንጌል ቤተ መጽሐፍት) የሚለው ቪድዮ ለጥናታችሁ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

1 ኔፊ 8

የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መያዝ ወደ አዳኜ ይመራኛል እንዲሁም የእርሱ ፍቅር እንዲሰማኝ ይረዳኛል።

የሌሂ ህልም እንደ ክርስቶስ ለመሆን በምታደርጉት በግል ጥረታችሁ ውስጥ የቱ ጋር እንዳላችሁ እንድትመለከቱ ግብዣን ያቀርባል። ፕሬዚዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዲህ አሉ፦ “እናንተ አላችሁበት፣ ሁላችንም አለንበት። የሌሂ የብረት ዘንግ ህልም ወይም ራዕይ … አንድ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ስለ ሕይወት ፈተና ለመረዳት የሚያስፈልገውን ሁሉንም ነገር ይዟል” (“Lehi’s Dream and You(የሌሂ ህልም እና እናንተ)፣” ኒው ኤራ, ጥር. 2015(እ.አ.አ), 2)።

ስታጠኑ እንደዚህ ዓይነት ሰንጠረዥን መሙላትን አስቡ።

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

ዛፍ እና ፍሬው (1 ኔፊ 8፥10–12)

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ሌሎች የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲካፈሉ ለመጋበዝ ምን እያደረኩ ነው?

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

ወንዝ (1 ኔፊ 8፥13)

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

የብረት ዘንግ (1 ኔፊ 8፥19–20፣ 30)

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

የጨለማ ጭጋግ (1 ኔፊ 8፥23)

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

በሌሂ ህልም ላይ ያለ ምልክት

ትልቅ እና ሰፊ ሕንፃ (1 ኔፊ 8፥26–27፣ 33)

ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ሌሂ ስላያቸው አራት የሰዎች ቡድን ለመማር የሚከተሉትን ጥቅሶች መመርመር ትችላላችሁ፦ 1 ኔፊ 8፥21–23፣ 24–28፣ 30፣ እና 31–33። በእነዚህ ቡድኖች መካከል ምን ልዩነት ታስተውላላችሁ? የተወሰኑ ሰዎች ወደ ዛፉ ከደረሱ እና ፍሬውን ከቀመሱ በኋላ ለምንድን ነው ጥለው የሄዱት (ቁጥሮች 24–28ን ይመልከቱ)? ከዚህ ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ኬቭን ደብሊው ፒርሰን፣ “Stay by the Tree [ከዛፉ ጎን ቁሙ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 114–16፤ “ሌሂ የሕይወት ዛፍ ህልምን አየ [Lehi Sees a Vision of the Tree of Life]” (ቪድዮ)፣ በወንጌል ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ይመልከቱ።

ስለ ሌሂ ህልም ተጽዕኖ በሚያሳድር መልኩ ለመማር እዚህ ይጫኑ

ተማሪዎች የራሳቸውን ግኝቶች እንዲያካፍሉ ፍቀዱ። ተማሪዎቹ ስለሚያገኙት እውነቶች ቅዱሳት መጽሐፍትን በራሳቸው እንዲፈልጉ መጋበዝን አስቡ። ለምሳሌ፣ ሰንጠረዥ ውስጥ የቅዱሳት መጽሐፍትን ማጣቀሻዎች በግላቸው ወይም በትንሽ ቡድኖች እንዲመረምሩ መጋበዝ ትችላላችሁ። የሚያገኙትን እውነቶች ያስታውሷቸዋል እንዲሁም ይወዷቸዋል።

ምስል
ሰዎች ወደ ሕይወት ዛፍ የሚያመራውን የብረት ዘንግ ይዘው

የጋራ ክር [Common Thread]፣ በኬልሲ እና ጀሲ ባሬት

1 ኔፊ 10፥2–16

የጥንት ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ አውቀው ስለ እርሱ መሰከሩ።

1 ኔፊ 10:2–16 ውስጥ የሚገኙትን እውነቶች ጌታ የሌሂ ቤተሰብ እንዲሁም ሁላችንም እንድናውቅ የሚፈልገው ለምን ይመስላችኋል? የምትወዷቸው ሰዎች አዳኙን ወደ ሕይወታቸው እንዲጋብዙ እንዴት እንደምትረዷቸው አስቡ።

1 ኔፊ 10፥17–19

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
እግዚአብሔር እውነትን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይገልጽልኛል።

የማትረዱትን የወንጌል መርህ እንድትኖሩ ስትጠየቁ እንዴት ነው ምላሽ የምትሰጡት? በሚከተሉት ምዕራፎች ውስጥ ለሌሂ ህልም የኔፊን መልስ (1 ኔፊ 10፥17–19፤ 11፥1ን ይመልከቱ) እንዲሁም የላማን እና የልሙኤልን መልስ ልዩነት ልብ በሉ (1 ኔፊ15፥1–10 ይመልከቱ)። ኔፊ እንደዚያ እንዲመልስ ያደረገውን ምን እውነቶች ተረድቷል?

የኔፊን ምላሽ በአእምሮ ውስጥ በመያዝ ይበልጥ ለመረዳት የምትፈልጓቸውን የወንጌል መርሆዎች ዝርዝር አውጡ። ለራሳችሁ ምላሾችን ለማግኝት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (በተጨማሪም “Truth Will Make You Free [እውነት ነፃ ያወጣችኋል]” የሚለውን በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን ለማድረግ መመሪያ ፣ 30–33 ይመልከቱ።)

ልክ ኔፊ የአባቱ ቃላት እውነት እንደሆኑ በራሱ እንዳረጋገጠው፣ የዘመናችን ነቢያትን እና ሐዋርያትን ቃላት ስንሰማ ተመሳሳይ ነገርን ማድረግ እንችላለን። በቅርቡ አጠቃላይ ጉባኤ፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ያስተማሩን ምንድን ነው? እነሱ ስላስተማሩት ነገሮች የግል ምስክርነትን ያገኛችሁት እንዴት ነው?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 2፥11–19ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥1–3፤ “ፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ጸልዩየልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 109፤ የወንጌል ርዕሶችን፣ “ራዕይ፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍትን ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተር የሚረዱ ሀሳቦች

1 ኔፊ 8

የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መያዝ ወደ እርሱ ይመራኛል እንዲሁም የእርሱ ፍቅር እንዲሰማኝ ይረዳኛል።

  • 1 ኔፊ 8ን በጋራ ስታነቡ ልጆቻችሁ የሌሂን ህልም ስዕል በመሳል ሊደሰቱ ይችላሉ። ስዕላቸውን እንዲያካፍሉ አድርጉና በህልሙ ውስጥ ያሉት ምልክቶች የሚሚወክሉት ምን እንደሆነ እንዲያውቁ እርዷቸው (1 ኔፊ 11፥21–2212፥16–1815፥23–33፣ 36 እና የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽን ይመልከቱ)። ለሚከተለው ጥያቄ የቻሉትን ያህል መልስ እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው፦ ከሌሂ ህልም ምን እንማራለን?

  • በሌሂ ህልም ውስጥ የብረት ዘንጉን የሚወክል እንደ ቧንቧ ወይም እንጨት ያለ ነገር አላችሁ? በክፍል ውስጥ ወደ አዳኙ ምስል ልጆቻችሁን ስትመሩ የብረት ዘንጉን የሚወክለውን እንዲይዙ አድርጓቸው። በሌሂ ህልም ውስጥ የብረት ዘንጉ የሚጠቅመው ለምንድን ነው ? (1 ኔፊ 8፥20፣ 24፣ 30ን ይመልከቱ)። የብረት ዘንጉ እንዴት ነው የእግዚአብሔርን ቃል የሚወክለው?

  • የተወሰኑ ልጆቻችሁ 1 ኔፊ 8፥10–12ን እንዲያነቡ እና ሌሂ የተመለከተውን እንዲገልጹ ጋብዙ። ሌሎቹን ደግሞ 1 ኔፊ 11፥20–23ን እንዲያነቡ እና ኔፊ የተመለከተውን እንዲገልጹ አድርጉ። መልአኩ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለኔፊ ሊያስተምረው ህፃኑን ኢየሱስ ያሳየው ለምንድን ነው? ልጆቻችሁ በሕይወታቸው ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት እንደተሰማቸው ከእነሱ ጋር ተነጋገሩ። እንደ “የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል፣” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 74–75) መዝሙር ምሳሌዎችን እንዲያስቡ ሊረዳቸው ይችላል።

1 ኔፊ 10፥17–1911፥1

እግዚአብሔር እውነትን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይገልጽልኛል።

  • 1 ኔፊ 10፥19 ውስጥ ኔፊ ያስተማረውን ልጆቻችሁ እንዲረዱ እንዴት ነው መርዳት የምትችሉት? ምናልባት የኢየሱስን ምስል ወይም ሌላ የተለየ እቃን በብርድ ልብስ ውስጥ በመጠቅለል ልጆቻችሁ እንዲገልጡት ልትጋብዙ ትችላላችሁ። 1 ኔፊ 10፥19ን ስታነቡ፣ “[መግለጥ]” እና “መንፈስ ቅዱስ” የሚሉትን ቃላት ሲሰሙ እጃቸውን ማንሳት ይችላሉ። ከዚያም መንፈስ ቅዱስ እውነትን እንድታገኙ የረዳችሁን ልምድ ማካፈል ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ለአንድ ጥያቄ መልሶችን ለማግኘት ምን እንደሚያደርጉ እንዲናገሩ ጠይቋቸው። ስለ ወንጌል ጥያቄ መልሶችን እንዴት እንደሚያገኝ ኔፊን የሆነ ሰው ቢጠይቀው ምን ብሎ ይመልሳል? 1 ኔፊ 10፥17–1911፥1ን በማንበብ እንዲያውቁ ልጆችን አበረታቱ።

  • ልጆቻችሁ የሆነ ነገር እውነት እንደሆነ እንዲያውቁ መንፈስ ቅዱስ እንደረዳቸው ተሰምቷቸው ያውቃል? ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መልሶችን መቀበል እንደማይችል ለሚያስብ ጓደኛ ምን ልንል እንችላለን? በ1 ኔፊ 10፥17–19 እና በ11፥1 ውስጥ ያንን ጓደኛ የሚረዳ ምን እናገኛለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
የሌሂ ህልም

የሕይውት ዛፍ፣ በኤቨን ኦክሰን