ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 22–28 ፦ “በቅድስና እና በእግዚአብሔር ኃይል መታጠቅ።” 1 ኔፊ 11–15


“ጥር 22–28 ፦ ‘በቅድስና እና በእግዚአብሔር ኃይል.መታጠቅ።’ 1 ኔፊ 11–15፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ጥር 22–28 1 ኔፊ 11–15፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ሰዎች የሕይወት ዛፍን ፍሬ እየበሉ

የእግዚአብሔር ፍቅር፣ በሰብሪና ስክውርስ

ጥር 22–28፦ “በቅድስና እና በእግዚአብሔር ኃይል.መታጠቅ”

1 ኔፊ 11–15

እግዚአብሔር የእርሱ ነቢይ እንዲያደርግ የሚፈልገው አስፈላጊ ስራ ሲኖረው፣ ብዙ ጊዜ ለዚያ ነቢይ ታላቅ ራዕይን ይሰጣል። ሙሴ፣ ዮሐንስ፣ ሌሂ እና ጆሴፍ ስሚዝ ሁሉም እንደዚያ ዓይነት ራዕይ ነበራቸው—ማለትም አዕምሮአቸውን ያሰፋ እና የእግዚአብሔር ስራ ምን ያህል ታላቅ እና አስደናቂ እንደሆነ እንዲመለከቱ የረዳ ራዕይ።

ኔፊ ከእነዚህ ሕይወት የሚቀይሩ ራዕዮች ውስጥ አንዱን አይቷል። የአዳኙን አገልግሎት፣ በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ የሌሂን ትውልዶች እና የእግዚአብሔርን የኋለኛው ቀን ስራን ተመለከተ። ከዚህ ራዕይ በኋላ ኔፊ ወደፊት ላለው ስራ በአግባቡ ተዘጋጀ። እናም ይህን ራዕይ ማንበብ እናንተንም ሊያዘጋጅ ይችላል ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንግሥቱ ውስጥ የምትሰሩት ስራ አለውና። ኔፊ “በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ” ካላቸው “የበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን” መካከል አንዱ ናችሁ (1 ኔፊ 14፥14)።

በተጨማሪም “ኔፊ የወደፊት ክስተቶችን ራዕይ አየ [Nephi Sees a Vision of Future Events]” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍትን ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

1 ኔፊ 11

እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ፍቅሩ መገለጫ ላከው።

ኔፊ መልአኩን በሌሂ ህልም ውስጥ የዛፉ ትርጉም ምን እንደሆነ ሲጠይቀው መልአኩ በቀላሉ “የእግዚአብሔርን ፍቅር ይወክላል” ብሎ ማለት ይችል ነበር። በምትኩ፣ ከአዳኙ ሕይወት ውስጥ ምልክቶችን እና ክስተቶችን ለኔፊ አሳየው። 1 ኔፊ 11ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ እነዚህን ምልክቶች እና ክስተቶች ፈልጉ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ፍቅር መገለጫ እንደሆነ እንድትገነዘቡ የረዳችሁን ምን ታገኛላችሁ?

ኔፊ ካየው ክስተት ጋር የሚዛመዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ቪድዮዎችን በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ውስጥ መመልከትትችላላችሁ። አዳኙ የሰማይ አባትን ፍቅር እንዲሰማችሁ እንዴት ረዳችሁ?

በተጨማሪም፣ “የግዚአብሔር ፍቅር፦ ለነፍስ በጣም አስደሳች የሆነ [God’s Love: The Most Joyous to the Soul]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 33–35 ተመልከቱ።

1 ኔፊ 12–14

በኃይል እና “በጽድቅ [መታጠቅ]” እችላለሁ።

ኔፊ በራዕይ ያያቸውን ብዙ ነገሮች ሲከናወኑ ለማየት አልኖረም። ኔፊ እነዚህን ነገሮች ማወቁ አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? እነሱን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ኔፊ በራዕዩ ውስጥ ያየውን ነገር ባነበባችሁ ቁጥር እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቁ (1 ኔፊ 12–14 ይመልከቱ)። በጌታ “ታላቅ እና አስደናቂ ስራ” ውስጥ ስለ እናንተ ሚና ምን መነሳሳትን ትቀበላላችሁ? (1 ኔፊ 14፥7)። ለእናንተ ያደረገላችሁ አንዳንድ ታላቅ ስራዎች ምንድን ናቸው?

በተለይ በ1 ኔፊ 14፥14 ውስጥ ያለውን በረከት አስቡ። ጌታ በህይወታችሁ ውስጥ ይህንን ቃል ኪዳን እንዴት ነው የፈጸመው? (ለተወሰኑ ምሳሌዎች የዴቪድ ኤ. ቤድናርን፣ “ከግዚአብሔር ኃይል ጋር በታላቅ ክብር [With the Power of God in Great Glory]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 28–30፣ ይመልከቱ።)

1 ኔፊ 13፥1–914፥9–11

ኔፊ ያያት “ታላቅና … የርኩሰት ቤተክርስቲያን” ምንድን ናት?

ፕሬዝደንት ዳለን ኤች. ኦክስ ኔፊ “ታላቋና … የርኩሰት ቤተክርስቲያን”በማለት የገለጸው “በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነትን የሚቃወም ማንኛውም ፍልስፍና ወይም ተቋምን እንደሚወክል አብራርተዋል። እናም ይህች ‘ቤተክርስቲያን’ ቅዱሳትን ለማስገባት የምትሻው ‘ምርኮ’ አካላዊ እስር ቤት ሳይሆን የሃስተኛ ሃሳቦች ምርኮ ነው (“እንደ የእግዚአብሔር ምስክሮች ቁሙ [Stand as Witnesses of God]፣” ኢንሳይን፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 32)። አዳኙ የሃሰተኛ ሃሳቦች ምርኮን እንድታስወግዱ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

1 ኔፊ 15:1–11

በእምነት ከጠየኩኝ እግዚአብሔር ይመልስልኛል።

የግል መገለጥን እየተቀበላችሁ እንዳልሆነ ማለትም እግዚአብሔር እያናገራችሁ እንዳልሆነ መስሎ ተሰምቷችሁ ያውቃል? የኔፊ ወንድሞች እንደዚህ ዓይነት ስሜት ሲሰማቸው እሱ ምን ምክርን ሰጣቸው? (1 ኔፊ 15፥1–11 ይመልከቱ።) የኔፊን ምክር በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት ነው ተግባራዊ ማድረግ የምትችሉት?

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

1 ኔፊ 15:23–25

የእግዚአብሔርን ቃል መጠበቅ የሴጣንን ተፅዕኖ እንድቋቋም ይረዳኛል።

ኔፊ ብዙ ጊዜ አፋጣኝ ነገሮችን ለወንድሞቹ ይናገራቸው ነበር። ነገር ግን በ1 ኔፊ 15፥23–25 ውስጥ ስለነገራቸው ነገር በጣም ስሜታዊ የሆነ ይመስል ነበር። የኔፊ መልዕክት ምንድን ነው እናም ጠንካራ ስሜት የተሰማው ለምን ይመስላችኋል?

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “የእግዚአብሔር ቃል” ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ በህይወት ያሉ ነቢያት ቃላትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እራሱን እንደሚጠቅስ አስተምረዋል። ቅዱሳት መጽሐፍትን እና በህይወት ያሉ ነቢያት ቃላትን “አጥብቆ መያዝ” ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? ኢየሱስ ክርስቶስን “አጥብቆ መያዝ” ምን ማለት ሊሆን ይችላል? በሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ነገር ግን አንሰማቸውም [But We Heeded Them Not]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 14-16) በተሰኘው መልዕክት ውስጥ መልሶችን ትፈልጉ ይሆናል።

የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መያዝ የሰይጣንን ተፅዕኖ እንድትቋቋሙ እንዴት ይረዳችኋል? እንደሚከተለው አይነት ሰንጠረዥ መሙላት ሃሳባችሁን እንድታቀናጁ ሊረዳችሁ ይችላል፦

 … የፈተናን ጭጋግ እንዳሸንፍ ይረዳኛልን? (1 ኔፊ 12፥17 ይመልከቱ)

 … የዓለምን ከንቱነት እና ኩራት “እንዳልሰማ” ይረዳኛልን? (1 ኔፊ 12፥18)

ቅዱሳት መጽሐፍትን እና በህይወት ያሉ ነቢያት ቃላትን አጥብቆ መያዝ እንዴት ነው …

አዳኙን አጥብቆ መያዝ እንዴት ነው …

እንዲሁም “የብረት ዘንግ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 274፤ ጆርጅ ኤፍ. ዘባሎስ “ከጠላት የሕይወት መከላከያን መገንባት [Building a Life Resistant to the Adversary]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ) 50–52 ተመልከቱ።

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ሕይወት ዛፍ እንድሚመራ የብረት ዘንግ ናቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

1 ኔፊ 11፥16–33

እግዚአብሔር ስለሚወደኝ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከ።

  • ኔፊን የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማስተማር መልአኩ ከአዳኙ ሕይወት ውስጥ ክስተቶችን ለኔፊ አሳየው። ለልጆቻችሁ ተመሳሳይ ነገርን ማድረግ ትችላላችሁ ማለትም ኔፊ በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ያየውን ክስተቶች ስዕል ስጧቸው፦ 1 ኔፊ 11፥20፣ 24፣ 27፣ 31፣ እና 33 (የወንጌል የስነ ጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥሮች 30353942፣ 57 ተመልከቱ)። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ፣ የሚዛመደውን ምስል ልጆቻችሁ እንዲያገኙ እርዷቸው። ከእነዚህ ጥቅሶች እና ምስሎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንማራለን?

  • እንደ “ልጁን ላከ [He Sent His Son]፣” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 34-35) መዝሙርን መዘመር ልጆች የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማቸው ሊረዳቸው ይችላል። ከዘመራችሁ በኋላ ልጆቻችሁ ከመዝሙሩ ምን እንደተማሩ ጠይቋቸው። ከ1 ኔፊ 11፥22–23 ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ሌላ ምን እንማራለን?

ልጆች እንዲማሩ ለመርዳት ስነ ጥበብን ተጠቀሙ። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክን ለልጆች ስታስተምሩ፣ በምናባቸው እንዲመለከቱት እርዷቸው። ምስሎችን፣ ቪድዮዎችን፣ አሻንጉሊቶችን፣ አልባሳትን እና የመሳሰሉትን መጠቀም ትችላላችሁ።

1 ኔፊ 13፥26–29፣ 35–36፣ 40

መጸሐፈ ሞርሞን ውድ እውነቶችን ያስተምራል።

  • በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ላሉት “ግልጽ እና ውድ” እውነቶች ልጆች ዋጋ እንዲሰጡ ለመርዳት፣ ስዕልን ስላችሁ የተለየ እንዲመስል የስዕሉን አካሎች እንዲቀይሩ ወይም እንዲያስወግዱ ልጆቻችሁን መጋበዝ ትችላላችሁ። በመጽሐፍ ቅዱስት ውስጥ ያሉ ነገሮች እንደተቀየሩ እና ከጊዜ በኋለ እንደተወገዱ ለማስተማር ይህን መጠቀም ትችላላችሁ። 1 ኔፊ 13፥40ን በጋራ አንብቡና መፅሐፈ ሞርሞን (“እነዚህ የመጨረሻ መዝገቦች”) ከመጽሐፍ ቅዱስ (“የመጀመሪያ” መዝገብ) ውስጥ የጠፉ “ግልጽ እና ውድ ነገሮችን” እንዴት እንድንገነዘብ እንደሚረዳን ተነጋገሩ። ከመጽሐፈ ሞርሞን ምን “ግልጽ እና ውድ” እውነቶችን ተምራችኋል?

  • መፅሐፈ ሞርሞን—የእግዚአብሔር መፅሐፍ [The Book of Mormon—a Book from God]” (የወንጌል ቤተ መጽሐፍ) የሚለው ቪድዮ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመፅሐፈ ሞርሞን በአንድ ላይ መኖር ለምን እንደሚያስፈልግ ልጆቻችሁ እንዲያዩ ሊረዳ ይችላል። ከቪድዮው ምስሉን እንደገና በመፍጠር ልጆች ሊደሰቱ ይችላሉ።

ምስል
በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች

መፅሐፈ ሞርሞን በክህደት ወቅት የጠፉ እውነቶችን ይመልሳል።

1 ኔፊ 15፥23–24

የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መያዝ ፈተናዎችን እንድቋቋም ይረዳኛል።

  • ልጆቻችሁ ከሌሂ ህልም የሚያስታውሱትን እንዲያካፍሉ እድሉን ስጧቸው። ባለፈው ሳምንት ዝርዝር ውስጥ እንዳለው አይነት ምስልን መጠቀም ሊረዳ ይችላል። ሰዎች ዛፉ ጋር እንዳይደርሱ ምን አገዳቸው? እንዲደርሱስ ምን ረዳቸው? በምስሉ ውስጥ የብረት ዘንጉን እንዲያገኙ እነሱን መጠየቅ ትችላላችሁ። የብረት ዘንጉ ምንን እንደሚወክል እና እንዴት እንደሚረዳን ለማወቅ 1 ኔፊ 15፥23–24ን በጋር አንብቡ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ተመልከቱ።

ምስል
የኔፊ የማርያም እና የህፃኑ ኢየሱስ ራዕይ

የኔፊ የማርያም ራዕይ፣ በጄምስ ጆንሰን