ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 8–14፦ “ጌታ ከእኛ ጋር ይሰራል።” ያዕቆብ 5–7


“ሚያዝያ 8–14፦ ‘ጌታ ከእኛ ጋር ይሰራል።’ ያዕቆብ 5–7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ሚያዝያ 8–14፦ ያዕቆብ 5–7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
በወይራ ዛፎች ደን ውስጥ ወንዶች ስራ እየሰሩ

የወይራ ዛፎች ምሳሌያዊ ታሪክ፣ በብራድ ቲር

ሚያዝያ 8–14፦ ጌታ ከእኛ ጋር ይሰራል

ያዕቆብ 5–7

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እስካሁን ያልሰሙ እጅግ ብዙ ሰዎች አሉ። ወደ ጌታ ቤተክርስቲያን እነሱን የመሰብሰብ ግዙፍ ሃላፊነት ካሳሰባችሁ፣ ያዕቆብ በያዕቆብ 5 ውስጥ ስለ ወይራ ዛፍ የተናገረው የሚያረጋጋ ማስታወሻ አለው፦ የወይኑ ስፍራው የጌታ ነው። ለእያንዳንዳችን በእርሱ ሥራ የምናግዝበት ትንሽ ቦታ—ቤተሰባችን፣ በዙሪያችን ያሉ ጓደኞቻችን፣ የእኛ የተፅዕኖ ክልል ሰጥቶናል። አንዳንድ ጊዜ ለመሰብሰብ የምንረዳው የመጀመሪያው ሰው እኛው እራሳችንን ነው። ነገር ግን የወይኑ ስፍራው ጌታ ከአገልጋዮቹ ጎን በመሆን ስለሚሰራ፣ በዚህ ስራ ውስጥ ብቻችንን አይደለንም (ያዕቆብ 5፥72 ይመልከቱ)። እግዚአብሔር ልጆቹን ያውቃል፣ እንዲሁም ይወዳቸዋል። ለእያንዳንዳቸው፣ ከዚህ በፊት እርሱን የተቃወሙትንም ጨምሮ የእርሱን ወንጌል የሚሰሙበትን መንገድ ያዘጋጃል (ያዕቆብ 4፥15–18 ይመልከቱ)። ከዚያም ስራው ሲያበቃ “በወይኑ ስፍራ በትጋት ከእርሱ ጋር የሰሩት … በእርሱ ወይን ስፍራ ደስታ ይኖራቸዋል” (ያዕቆብ 5፥75)።

በተጨማሪም “ያዕቆብ ስለ እስራኤል መሰብሰብ አስተምሯል” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍት ላይ ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ያዕቆብ 5

ኢየሱስ ክርስቶስ የወይኑ ስፍራ ጌታ ነው።

ያዕቆብ 5 ምሳሌያዊ ትርጉም ያለው ታሪክ ነው። ስለ ዛፎችን፣ ፍሬዎችን እና ሰራተኞች ይገልፃል፣ ነገር ግን በእርግጥ መላው ታሪክ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ህዝቦቹ ግንኙነት ነው። ስለዚህ ታሪኩን ስታነቡ በታሪኩ ውሰጥ የተወሰኑ ነገሮች ምንን እንደሚወክሉ አስቡ።

ለምሳሌ፣ የወይኑ ስፍራ ዓለምን እንዲሁም የለሙት የወይራ ዛፎች እስራኤልን (ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን ያደረጉት ያዕቆብ 5፥3 ይመልከቱ) የሚወክል ከሆነ፣ የዱር የወይራ ዛፎቹ ምንን ይወክላሉ? መልካሙ እና መጥፎው ፍሬ ምንን ሊወክል ይችላል? ሌሎች ምን ምሳሌያዊ ምልክቶችንስ ታያላችሁ?

ምንም እንኳን ያዕቆብ 5 የዓለምን ሃገራት የክፍለ ዘመናት ታሪክ ቢያስተምርም፣ ስለ እናንተ እና ስለ ህይወታችሁም ጭምር ነው። በያዕቆብ 5 ውስጥ ለእናንተ ምን መልዕክቶችን ታገኛላችሁ?

ምናልባት ከሁሉ በላይ ያዕቆብ 5 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስታነቡ እርሱን ፈልጉ። ለምሳሌ በቁጥር 40–41፣ 46–47 ውስጥ ስለ እርሱ ምን ትማራላችሁ?

ስለ ያዕቆብ 5 ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ በዚህ ንድፍ መጨረሻ ላይ ያለውን ስዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

ያዕቆብ 5፥61–75

ጌታ በእሱ የወይን ስፍራ ከእርሱ ጋር እንዳገለግል ይጋብዘኛል።

ወደ ጌታ የወይን ስፍራ የተጠሩት “ሌሎች አገልጋዮች” (ያዕቆብ 5፥70) እንደ እናንተ ዓይነትን ሰዎችን ያካትታሉ። በጌታ የወይን ስፍራ ውስጥ ስለመስራት በያዕቆብ 5፣ በተለይ በቁጥር 61–62 እና 70–75 ውስጥ ምን እውነቶችን ታገኛላችሁ? በእርሱ ስራ ውስጥ በመርዳት ስለ እርሱ ምን ተማራችሁ?

ጌታ በወይን ስፍራው ውስጥ “ለመጨረሻ ጊዜ” መስራቱን ስታነቡ ጌታን “በሃይል” ለማገልገል ምን ያነሳሳችኋል? (ያዕቆብ 5፥71)። ለምሳሌ ወንጌልን በማካፈል፣ በቤተመቅደስ ውስጥ በማገልገል ወይም ሌሎችን በማጠንከር የወይን ስፍራ ጌታን ስታገለግሉ ስለተሰማችሁ ደስታ የግል ልምድ ልታስቡ ትችላላች። እንዲሁም ሽማግሌ ጋሪ ኢ ስቲቨንሰን “በቀላሉ ቆንጆ—በቅለቱ ውብ [Simply Beautiful—Beautifully Simple]” (ሊያሆና ህዳር 2021 (እ.አ.አ) 47–50) በሚለው መልዕክታቸው የተጋሩትን ምሳሌዎች ማሰስ ትችላላችሁ።.

ለ“ማንኛውንም ሰው —በመጋረጃው በሁለቱም በኩል—የሚረዳ ማንኛውንም ነገር ባደረጋችሁ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት እና አስፈላጊ የሆነውን የጥምቀት እና የቤተመቅደስ ስነስርዓቶችን ይቀበል ዘንድ ለማገዝ እርምጃ ስትወስዱ፣ እስራኤልን ለመሰብሰብ እየረዳችሁ ነው። እንደዚህ ቀላል ነው” “የእስራኤል ተስፋ”[አለም አቀፍ የወጣቶች አምልኮ፤ ሰኔ 3፣ 2018 እ.ኤ.አ]፣) ተመልከቱ። ChurchofJesusChrist.org)። እስራኤልን ለመሰብሰብ ምን ማድረግ እንድምትችሉ የሃሳቦችን ዝርዝር ለማውጣት አስቡ። ከእናንተ ዝርዝር ውስጥ፣ ጌታ ዛሬ በወይኑ ቦታው ውስጥ እንድታደርጉ የሚፈልገው ምን እንደሆነ ይሰማችኋል? በቁጥር 75 መሠረት፣ ጌታ በወይኑ ቦታው ውስጥ በማገልገላችን ወሮታውን እንዴት ይከፍለናል?

በተጨማሪም “እስራኤል፣ እስራኤል፣ እግዚአብሔር እየጠራ ነው፣መዝሙር፣ ቁ. 7; “ብሉይ ኪዳን የወይን ቦታ” (ቪዲዮ) ፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፣ የወንጌል ርዕሰ ጉዳዮች፣ “እስራኤልን መሰብሰብ፣” “ሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ መጋበዝ”፣ “በመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ መሳተፍ”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍትን ይመልከቱ።

ትምህርት አስተምሩ። ውይይቶቻችሁ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ባለው መሰረታዊ ትምህርት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን አረጋግጡ። ጥቅሶችን አብራችሁ በማንበብና የምታገኟቸውን እውነቶች እንዲሁም እነዚህን እውነቶች በመኖር ረገድ ተሞክሮዎችን በማካፈል ይህን ማድረግ ትችላላችሁ።

ያዕቆብ 6፥4–5

ጌታ ህዝቡን በፍቅር እና በምሕረት ያስታውሳል።

መጽናት”የሚለው ቃል አንዱ ትርጉም አንድ ነገር ላይ በሃይል፣ በቅርበት እና በማያወላውል ሁኔታ መጣበቅ ማለት ነው። ያ ትርጉም ያዕቆብ 6፡4–5ን በተረዳችሁበት መንገድ ላይ ምን ተጽእኖ አለው? በወይራ ዛፍ ታሪክ ውስጥ፣ የወይኑ አትክልት ቦታ ጌታ “የምሕረት ክንዱን” እንዴት ዘረጋ? (ለምሳሌ፣ ያዕቆብ 5፡47፣ 51፣ 60–61፣ 71–72 ይመልከቱ)። ይህን እንዴት ለእናንተ አደረገ?

ያዕቆብ 7፥1–23

ሌሎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለኝን እምነት ሲቃወሙ ጠንክሬ መቆም እችላለሁ።

ኔፋውያን ከሼረም ጋር የነበራቸው ልምድ ዛሬም ላይ ይታያል፣ ሰዎች በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ለማጥፋት እየሞከሩ ነው። ያዕቆብ በእምነቱ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ምን ምላሽ ሰጠ? ከእሱ ምላሾች ምን ትማራላችሁ? በአዳኙ ላይ ያላችሁ እምነት ለሚፈተንበት ጊዜ ለመዘጋጀት አሁን ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ጄፍሪ አር. ሆላንድን፣ “የደቀመዝሙርነት ዋጋ—እና በረከቶች “[The Cost—and Blessings—of Discipleshipኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2014። 6–9፤ “ሼረም ክርስቶስን ይክዳል [Sherem Denies Christ]” (ቪድዮ) የወንጌል ቤተ መጻህፍት ውስጥ ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶችን እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ያዕቆብ 5

ጌታ ለህዝቦቹ ያስባል።

  • ልጆቻችሁ በሚረዱት መንገድ የወይራውን ታሪክ እንዴት ማካፈል ትችላላችሁ? አንደኛው መንገድ፣ ዛፍ ለማየት ወደ ውጭ በእግር መሄድ እና የታሪኩን ዋና ዋና ነጥቦች በአጭሩ መከለስ ነው። የወይኑ ቦታ ጌታ ለዛፎቹ ምን አደረገ? በታሪኩ ውስጥ እንዳሉት ሰራተኞች መሆን እና ሌሎች የአዳኙ ፍቅር እንዲሰማቸው እንዴት መርዳት እንችላለን?

  • ያዕቆብ ሕዝቡ ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ለመጋበዝ የወይራ ዛፎችን ታሪክ አካፍሏል። ለልጆቻችሁ ተመሳሳይ ነገርን ሊያደርግ ይችላል። ምናልባት ታሪኩን እንደ ያዕቆብ 5፡3-4፣ 28–29፣ 47 እና 70–72 ባሉት ቁጥሮች ማጠቃለል ትችላላችሁ (በተጨማሪም “የብሉይ ኪዳን የወይን ቦታ [Old Testament Olive Vineyard]” [ቪዲዮ]፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍትውስጥ ይመልከቱ)። እናንተ ወይም ልጆቻችሁ የወይኑ ስፍራ ጌታ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ለዛፎቹ ምን ያህል እንደሚያስብ የሚያሳዩ ነገሮችን በመፈለግ ያዕቆብ 5:11, 41, 47 እና 72ን ማንበብ ትችላላችሁ። አዳኙ ስለ እኛ እንደሚያስብ ለማሳየት ምን ያደርጋል?

ያዕቆብ 6፥4–5

የሰማይ አባት ይወደኛል እንዲሁም ንስሃ ስገባ ይቅር ይለኛል።

  • ያዕቆብ 6፡4-5 የተሳሳተ ምርጫ ስንመርጥ ለእኛ የሚጠቅም መልእክት አለው። ምናልባት ልጆቻችሁ እንዲያገኙ መርዳት ትችላላችሁ። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ በእግዚአብሔር የማዳን ፍቅር ላይ ተስፋ የሚሰጡን የትኞቹ ቃላት ናቸው? የሽማግሌ አለን ዲ. ሃይኒ “የምንታመንበትን ማስታወስ [Remembering in Whom We Have Trusted]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 121–22) በተሰኘው መልዕክቱ በጭቃ ጉድጓድ ውስጥ ስለመቆሸሸ ያካፈለው ታሪክ ሊረዳ ይችላል። ይህ ታሪክ እና ያዕቆብ 6፡4-5 በእግዚአብሔር መንግስት ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለብን ያስተምረናል?

ያዕቆብ 7፥1–23

እውነት እንደሆነ ለማውቀው መቆም እችላለው።

  • ልክ እንደ ያዕቆብ፣ ልጆቻችሁ ለእውነት እንዲቆሙ እንዴት ልታነሳሱ ትችላላችሁ? ልጆቻችሁ “ምዕራፍ 10፦ ያዕቆብ እና ሼረም” (የወንጌል ቤተ መጽሐፍት) የሚለውን ቪድዮ መመልከት እና ያዕቆብ 7፥1–23ን እንደ መመሪያ በመጠቀም በያዕቆብ እና በሼረም መካከል ያለውን መስተጋብር መተወን ይችላሉ። ያዕቆብ እውነት እንደሆነ ለሚያውቀው ነገር እንዴት ነው የቆመው? ልጆቻችሁ ለእውነት የቆሙበትን ልምድ እንዲያካፍሉ ጋብዙ ወይም የእናንተን ልምድ አካፍሉ። ምናልባት እንደ ያዕቆብ ብርታትን የሚገልጹ እንደ “ለእውነት ቁሙ [Stand for the Right]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 159 ያለ መዝሙርን ሊዘምሩ ይችላሉ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።