ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 12-18፦ “በክርስቶስ እምነት ፈጥነን [መ]ቆም።” አልማ 43–52


“ነሐሴ 12-18፦ “በክርስቶስ እምነት ፈጥነን [መ]ቆም።’ አልማ 43-52፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ነሐሴ 12–18 (እ.አ.አ)። አልማ 43-52፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ሞሮኒ እና የነጻነት አርማ

For the Blessings of Liberty[የነፃነት በረከትን ለማግኘት፣ በስኮት ኤም. ስኖው

ነሐሴ 12-18፦ “በክርስቶስ እምነት ፈጥነን ካልቆምን”

አልማ 43–52

አልማ 43መጀመሪያ ላይ—“እናም አሁን በኔፋውያን እና በላማናውያን መካከል ስለነበረው የጦርነት ታሪክ እመለሳለሁ” የሚሉትን ቃላት ስናነብ በሰሌዳው ላይ የነበረው ቦታ ውሱን ቢሆንም ሞርሞን እነዚህን የጦርነት ታሪኮች ለምን እንዳካተተ መጠየቅ ተፈጥሯዊ ነው ( የሞርሞን ቃላት 1:5 ይመልከቱ)። በኋለኞቹ ቀናት የራሳችን የጦርነት ድርሻ እንዳለን እውን ነው፤ ነገር ግን ከጦርነቱ ስትራቴጂ እና አሳዛኝ ገለጻዎች በላይ በእርሱ ቃላት ውስጥ ዋጋ አለ። የእርሱ ቃላት በእያንዳንዱ ቀን ከክፉ ኃይላት ጋር ለምንዋጋው “ሁላችንም ለተመለመልንበት” (መዝሙር ቁ.250) ጦርነትም ያዘጋጀናል። ይህ ጦርነት በጣም እውን ነው ውጤቱም የዘላለም ህይወታችንን ይነካል። እንደ ኔፋውያን “ሞሮኒ የክርስቲያኖች ጉዳይ” ብሎ በሚጠራው “[በ]አምላካችን፣ [በ]ኃይማኖታችን፣ እናም [በ]ነፃነታችን፣ [በ]ሰላማችን፣ እናም [በ]ሚስቶቻችን፣ [በ]ልጆቻችን አልማ 46:12፣ 16 የተቀደሰ ምክንያት ተነሳስተናል።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 43–52

ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈሳዊ ውጊያዬ ሊረዳኝ ይችላል።

አልማ 43-52 ስታነቡ ኔፋውያንን ውጤታማ(ውጤት አልባ) ያደረጋቸውን ድርጊታቸውን አስተውሉ። ከዚያም የተማራችሁትን መንፈሳዊ ውጊያዎቻችሁን ለማሸነፍ ይረዳችሁ ዘንድ እንዴት ልትጠቀሙበት እንደምትችሉ አሰላስሉ። ሃሳቦቻችሁን ከዚህ በታች መዝግቡ፦

በተጨማሪም ከኔፋውያን ጠላቶች ምን ልትማሩ እንደምትችሉ ተመልከቱ። ሰይጣን እንዴት በተመሳሳይ መንገዶች ሊያጠቃችሁ እንደሚችል አሰላስሉ፦

  • አልማ 43፥8ዛራሄምናህ በእነርሱ ላይ ስልጣን ይኖረው ዘንድ የእርሱን ህዝብ ማስቆጣትን ፈለገ። ሰይጣን በቁጣ እንድሠራ ሊፈትነኝ ይችላል።

  • አልማ 43፥29

  • አልማ 46፥10

  • አልማ 47፥10–19

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን “የወደፊቱን በእምነት ተቀበሉ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 73–76፤ “A Mighty Fortress Is Our God፣” መዝሙር፣ ቁ. 68 ይመልከቱ።

ምስል
ኔፋውያን ከላማናውያን ጋር እየተዋጉ

ሚነርቫ ቴከርት (1888–1976)እ.አ.አ፣ የኔፋውያንን ከተማ መከላከል፣ 1949–1951 (እ.አ.አ)፣ oil on masonite፣/36 × 48 ኢንች። ብሪግም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የአርት ሙዚየም 1969 (እ.አ.አ)።

አልማ 46፧11–2848፧7–17

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
“በክርስቶስ እምነት ፈጥነን [መ]ቆም”

ጠላት በህይወታችሁ ውስጥ የሚኖረውን ጉልበት መቀነስ ትፈልጋላችሁ? አንደኛው መንገድ በአልማ 48፧17 ውስጥ የቀረበውን “እንደ ሞሮኒ” የመሆን ምክር መከተል ነው። በአልማ 46፡11-2848:7–17 ስታነቡ ሞሮኒን የሚገልጹትን ቃላት መዘርዘርን አስቡ። በክርስቶስ እምነት ፈጥ[ኖ] [ስለመ]ቆም ከሞሮኒ ምን ትማራላችሁ? (አልማ 46፥27)።

ሞሮኒ “በክርስቲያኖች ነገር” ሌሎችን እንዴት እንዳነሳሳ ( አልማ 46:11–22 ይመልከቱ) ልታጠኑም ትችላላችሁ። ያንን ነገር እንዴት መግለፅ ትችላላችሁ? በእርሱ ውስጥ ለመሳተፍ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ሌሎችም እንዲሳተፉ እንዴት ልታነሷሷቸው ትችላላችሁ?

ሞሮኒ ሌሎችን ለማነሳሳት ያደረገው አንድ ነገር ኔፋውያንን በሚያነሳሱ መርሆዎች ላይ አፅንዖት የሚሰጥ የነጻነት ዓርማን መፍጠር ነበር። (ቁጥር 12 ይመልከቱ)። የቤተክርስቲያን መሪዎች በዘመናችን አፅንኦት የሚሰጧቸው መርሆች ምንድን ናቸው? በFor the Strength of Youth: A Guide for Making Choices (booklet, 2022 (እ.አ.አ))፣ “ቤተሰብ፦ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ወጣት ሴቶች እና አሮናዊ የክህነት ቡድን ጭብጦች፣ ወይም የቅርብ ጊዜ የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ውስጥ ልትፈልጓቸው ትችላላችሁ። ለአዳኙ እና ለወንጌሉ ታማኝ እንድትሆኑ የሚያሳስባችሁን የራሳችሁን የነፃነት ዓርማ ስለመፍጠር የሚያስተምሩትን ነገሮች ወደ ቀላል ዓረፍተ ነገሮች ልታጠቃልሏቸው ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “Faith in Jesus Christ፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

አልማ 47

ሰይጣን ቀስ በቀስ ይፈትናል እንዲሁም ያታልላል።

ሰይጣን ትልቅ ኃጢአት የመሥራት ወይም ግልጽ የሆኑ ውሸቶችን የማመን ሁኔታችሁ አነስተኛ እንደሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከጽድቅ ሕይወት ከሚገኝ ጥበቃ ያርቃችሁ ዘንድ ትቀበላላችሁ ብሎ የሚያስበውን ያህል በግልጽ የማይታዩ ውሸቶችን እና ትንንሽ ፈተናዎችን ይጠቀማል።

ይህንኑ ተመሳሳይ መንገድ በአልማ 47 ውስጥ ፈልጉ እንዲሁም ሰይጣን እንዴት ሊያታልላችሁ እየሞከረ እንደሆነ አሰላስሉ። የሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስን እነዚህን ግንዛቤዎች አስቡ።

ከሃዲው አማሊቅያ ሌሆንቲ ‘እንዲወርድ’ እና በሸለቆው ውስጥ እንዲያgeኘው ገፋፍቶት ነበር። ሆኖም ሌሆንቲ ከተራራው በወረደ ጊዜ እስኪሞት ድረስ ‘ቀስ በቀስ’ ተመረዘ፤ እንዲሁም ሰራዊቱ በአማሊቅያ እጅ ወደቀ። (አልማ 47 ይመልከቱ)። በክርክር እና በክስ አንዳንድ ሰዎች ከፍ ያለውን ቦታ እንድንለቅ አጠመዱን። ብርሃኑ ያለው በተራራው ላይ ነው።… ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ነው” (“Christian Courage: The Price of Discipleship፣” ሊያሆና፣ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 74)።

“Temptation Fades as We Seek Christ in Every Thought” (ወንጌል ላይብረሪ) ከሚለው ቪዲዮ ፈተናን ለመቋቋም የሚረዳችሁ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ነህምያ 6፥32 ኔፊ 26:2228፥21–22 ይመልከቱ።

አልማ 50–51

ህብረት ደህንነትን ያመጣል።

ኔፋውያን የጦር ትጥቅ እና ምሽጎች የነበራቸው ቢሆንም (አልማ 51:26-27 ይመልከቱ) ላማናውያን ወዲያውኑ ብዙዎቹን ከተሞቻቸውን ያዙ። ያ እንዴት ሊሆን ቻለ? እነዚህን ምዕራፎች ( በተለይ አልማ 51፥1-12 ይመልከቱ) ስታነቡ መልሶችን ፈልጉ። ይህ ዘገባ ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ ምን ማስጠንቀቂያ ሊኖረው እንደሚችል አሰላስሉ?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 43:17–2148:7–849:1–550:1–6

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ መንፈሳዊ ጥበቃን ማግኝት እችላለሁ።

  • በኔፋውያን እና በላማናውያን መካከል ስለተደረገው ጦርነት ለልጆቻችሁ ለመንገር“ Chapter 31: Captain Moroni Defeats Zerahemnah” (የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 85–88) መጠቀምን አስቡ። በአልማ 43:19 ውስጥ ስለኔፋውያን የጦር መሳሪያ በምታነቡበት ጊዜ ሰውነታችንን የሚከላከለውን ትጥቅ እግዚአብሄር መንፈሳችንን ለመከላከል ከሰጠን ነገሮች ጋር ልታነጻጽሩ ትችላላችሁ። ምናልባት እናንተና ልጆቻችሁ የአንድን ልጅ ሥዕል መሳልና ልጆቻችሁ ለሚጠቅሱት በመንፈሳዊ ለሚጠብቃቸው ለእያንዳንዱ ነገር በሥዕሉ ላይ አንድ የጦር መሳሪያ ለመጨመር ትችላላችሁ።

  • እነዚህ ጥቅሶች ኔፋውያን ስለገነቧቸው ምሽጎች ይገልፃሉ፦አልማ 48:7–949:1–950:1–6። እነዚህን ጥቅሶች አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ ልጆቻችሁ እንደ ወንበሮች እና ብርድ ልብሶች ካሉ ነገሮች ምሽግ በመገንባት ይደሰቱ ይሆናል። “ሽማግሌ ስቲቨንሰን ቤተሰብን ስለማጠናከር” (ወንጌል ላይብረሪ) ያቀረቡት ቪዲዮ ቤታችሁን በመንፈሳዊ እንዴት ለማጠናከር እንደምትችሉ ለመወያየት ሊረዳችሁ ይችላል።

አልማ 46፧11–1648፤11–13፣16–17

እንደ ካፒቴን ሞሮኒ “በክርስቶስ እምነት የጸናሁ” ልሆን እችላለሁ።

  • የነጻነት ዓርማን ታሪክ ለመናገር ልጆቻችሁ በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያሉትን ምስሎች ማየት ይችላሉ አልማ 46:11-16ምዕራፍ 32፤ ካፒቴን ሞሮኒ እና የነፃነት አርማ፣” የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 89–90) ይመልከቱ። ሞሮኒ ሕዝቡ ምን እንዲያስታውስ ፈለገ ( ቁጥር 12 ይመልከቱ)። የሰማይ አባት ምን እንድናስታውስ ይፈልጋል? ምናልባት ልጆቻችሁ እነዚህን ነገሮች ሊያስታውሷቸው የሚችሉ ሃረጎች ወይም ምሥሎች ያሉባቸው የራሳቸውን “የነጻነት ዓርማዎችን” ማዘጋጀት ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁን እንደ ሞሮኒ “በክርስቶስ ፅኑ እምነት ስለመኖር” ለማስተማር (አልማ 48:13 ይመልከቱ) አንድን ጠንካራ ነገር እንዲያገኙ እና እንዲዳስሡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። እምነት “ፅኑ” ነው ሲባል ምን ማለት ነው? አልማን ምን በክርስቶስ እምነት የጸና እንዳደረገው ልማወቅ አልማ 48፥11-12 አንድ ላይ አንብቡ። “ጀግና እሆናለሁ ፣” የሚለውን መዝሙር ልትዘምሩም ትችላላችሁ (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣162)። “በክርስቶስ እምነት የፀናን” ለመሆን ምን ማድረግ እንችላለን?

አልማ 47፥4–19

ሰይጣን ቀስ በቀስ ይፈትነናል እንዲሁም ያታልለናል።

አልማ 47፥4-19 ውስጥ የተመረጡ ጥቅሶችን በጋራ አንብቡ። አማሊቅያ ከመጀመሪያው ምን ለማድረግ እንዳቀደ ለሌሆንቲ ነግሮት የነበረ ቢሆን ኖሮ ምን ሊከሰት ይችል ነበር? ሰይጣን ሊያታልለን ስለሚሞክርባቸው መንገዶች እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል?

ልጆቻችሁ በራስ መተማመንን እንዲያሳድጉ እርዷቸው። አንዳንድ ልጆች ወንጌልን በራሳቸው ለመማር ዓቅም እንዳላቸው ላይሰማቸው ይችላል። የልጆቻችሁን በራስ መተማመን ማሳደግ የሚቻልበት አንዱ መንገድ በትምህርቱ ላይ ሲሳተፉ በማመስገን ነው። ይህንን ጥቆማ በዚህ መዘርዘር ውስጥ ካሉ አክቲቪቲዎች ውስጥ በየትኛው ላይ ተግባራዊ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ካፒቴን ሞሮኒ እና የነጻነት አርማ

የነጻነት አርማ

© 2018 በላሪ ኮንራድ ዊንበርግ