ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 29–ነሐሴ 4፦ “ወደ እግዚአብሄር ተመልከትና ኑር።” አልማ 36–38


ሐምሌ 29–ነሐሴ 4፦ “ወደ እግዚአብሄር ተመልከትና ኑር።” አልማ 36–38፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ሐምሌ 29–ነሐሴ 4 አልማ 36-38፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
አንዲት ሴት እየጸለየች

Woman[ሴት]፣ በጄን ቶልማን፣ መቅዳት አይቻልም

ሐምሌ 29–ነሐሴ 4፦ “ወደ እግዚአብሄር ተመልከትና ኑር።”

አልማ 36–38

አልማ በዙሪያው ያለውን ክፋት በተመለከተ ጊዜ “ሃዘን፣” “መከራ” እና “የነፍስ ስቃይ” ተሰማው (አልማ 8:14)። ስለዞራማውያን ሲናገር “በእነዚህ ሰዎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ክፋት” “ነፍሴን ያስጨንቃታል” ብሏል (አልማ 31:30)። ከሚስዮን አገልግሎቱ ወደ ዞራማውያን ከተመለሰ በኋላ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ተሰማው—የብዙዎቹ ኔፋውያን ልብ “መጠጠሩን በመመልከቱና በቃሉም ጥብቅነት የተነሳ መናደድ መጀመራቸው[ን]” አይቷል እንዲሁም ልቡ “እጅግ አዝኖ” ነበር (አልማ 35:15)። አልማ ስላየው እና ስለተሰማው ነገር ምን አደረገ? በዓለም ሁኔታ በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ ወይም ተስፋው የሚጨልም አልሆነም። ከዚያ ይልቅ “ልጆቹ በአንድ ላይ እንዲሰባሰቡ አደረገ” ከዚያም “ለፅድቅ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በተመለከተ” አስተማራቸው (አልማ 35:16)። እንዲህ ሲል አስተማራቸው፣ “በክርስቶስ ብቻ ካልሆነ በቀር መዳን የሚቻልበት ሌላ መንገድ እንደሌለ።… እነሆ እርሱ የዓለም ሕይወት እና ብርሃን ነው” (አልማ 38:9)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 3638:5–6

እኔ ከእግዚአብሔር የተወለድኩኝ መሆን እችላለሁ።

ጥቂቶቻችን እንደ አልማ መለወጥ ያለ ፈጣን ተሞክሮዎች ይኖሩናል። ምንም እንኳን ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በሂደት ቢሆንም እያንዳንዱ ሠው “ከእግዚአብሄር መወለድ” አለበት(አልማ 36:23፤ 38:6)። አልማ 36 ስታነቡ ከእግዚአብሔር መወለድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡ። ለምሳሌ፣ ከእግዚአብሔር በመወለድ ሂደት ስለሃጢያት ምን ይሰማችኋል? ስለኢየሱስ ክርስቶስስ? ከእግዚአብሔር መወለድ ለራሳችሁ ስህተቶች ምላሽ ለመስጠት በምታደርጉት ነገር ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል? በእምነታችሁ እና በድርጊቶቻችሁ ላይ ምን ሌሎች ለውጦች ይከሰታሉ? እነዚህን ለውጦች እንዴት እየተለማዳችኋቸው እንደሆነ አሰላስሉ።

በተጨማሪም ሞዛያ 5:727:25–26አልማ 5:1422:15ሄለማን 3:35፤ “Alma the Younger Is Converted unto the Lord” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመፃሕፍት።

አልማ 36፧12–2438፧8–9

ኢየሱስ ክርስቶስ ሃዘንን በደስታ ይለውጣል።

ንስሐ የሀጢያት አስከፊ ቅጣት ነው ብለው ስለሚያስቡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ንስሃ ለመግባት ይፈራሉ። ስለዚያ ነገር አልማ ምን የሚል ይመስላችኋል? ይህን ለማወቅ ንስሐ ከመግባቱ በፊት የአልማ ህይወት ይመስል የነበረውን ( አልማ 36:6–17 ይመልከቱ) ንስሐ ከገባ በኋላ ስለራሱ ከተናገረው ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ። ( 18–27 ይመልከቱ) በአልማ 36:17-18መሠረት አልማ ይቅርታውን የተቀበለው እንዴት ነው?

በተጨማሪም ማቲው ኤስ ሆላንድ፣ “የልጁ ድንቅ ስጦታ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 45–47 ይመልከቱ።

አልማ 37

ቅዱሳት መፃህፍት “ለብልህ ዓላማ” ተጠብቀዋል።

ዛሬ ቅዱሳት መጻህፍትን የማግኘትን ተዓምር እና በረከት አስቡ! አልማ 37 ስታነቡ ቅዱሳት መጻህፍት ስላሉ የሚመጡትን በረከቶች ፈልጉ ( ለምሳሌ፣ ቁጥር 7፣ 10፣ 18–19፣ 44–45 ይመልከቱ)።

አልማ 37:38-47ውስጥ አልማ “የክርስቶስን ቃላት” ከሊያሆና ጋር አነጻጽሯል። ይህን ንጽጽር ስታሰላስሉ የክርስቶስን ትምህርቶች ተዓምር እና ኃይል “ቀን በቀን” የተለማመዳችሁባቸውን መንገዶች አስቡ (አልማ 37:40)።

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Blessing of Scripture,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)፣ 32–35፤ “As I Search the Holy Scriptures፣” መዝሙር፣ ቁ. 277፤ “Alma Testifies to His Son Helaman” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ቤተመፃህፍት።

ምስል
ሴት ቅዱሳት መጻሐፍትን እያነበበች

ቅዱሳት መጻሐፍት እግዚአብሄርን እንዴት እንደምንከተል ያስተምሩናል።

አልማ 37፥1–14

ምስል
seminary icon
“በትንሽና በቀላል ነገሮች ታላቅ ነገሮች ተፈፅመዋል።”

አንዳንድ ጊዜ ችግሮቻችን በጣም ከባድ እና የተወሳሰቡ እንደሆኑና መፍትሄዎቹም እንደዚያው ከባድ እና የተወሳሰቡ መሆን እንዳለባቸው ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን ያ ሁልጊዜ የጌታ መንገድ አይደለም፡፡ አልማ 37:1–14 ስታነቡ ሥራውን ስለሚሰራበት መንገድ ምን አስደነቃችሁ? ከዚያም ይህን መርህ በህይወታችሁ ውስጥ ያያችሁባቸን መንገዶች ማሰላሰል እንዲሁም መፃፍ fትችላላችሁ።

ይህን መሠረታዊ ሥርዓት ለአንድ ሰው ልታስተምሩ ቢሆን ከተፈጥሮ ወይም ከዕለት ተዕለት ሕይወት ምን ምሳሌዎችን ወስዳችሁ ለማብራራት ትጠቀሙበታላችሁ? ከሽማግሌ ዳልን ኤች. ኦክስ “Small and Simple Things” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ) 89-92) መልእክት ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

ወደሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርቧችሁ አንዳንድ ትንሽና ቀላል ነገሮች ምን ምን ናቸው።

ብዙውን ጊዜ “ትንሽና ቀላል” ምርጫዎቻችን በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ከFor the Strength of Youth: A Guide to Making Choices ውስጥ ርዕስ መውሰድን እና እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎችን ራሳችሁን መጠየቅን አስቡ፦ስለዚህ ነገር የማደርገው ምርጫ እኔን እና በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን የሚነካው እንዴት ነው? ወደ ትልቅ ሰላም እና ደስታ የሚመሩ ምን ትንሽና ቀላል ለውጦች ማድረግ እችላለሁ?

በተጨማሪም ኤ. ደን፣ “One Percent Better፣” ሊያሆና ህዳር 2021(እ.አ.አ)፣ 106-8 ፣ የወንጌል አርዕስቶች፣ “Agency፣” የወንጌል ቤተመፃሕፍት ይመልከቱ።

ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን ተጠቀሙ። በህይወት ውስጥ እንዳሉ ልክ እንደ ሌሎች ነገሮች የወንጌል መማር ማስተማር በትንሽ እና ቀላል መንገዶች ሊከናወን ይችላል። ለምሳሌ፣ ትንሽ ጨው ወይም እርሾ የትንሽ እና ቀላል ነገሮችን ኃይል ለማስተማር እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል? ( ማቴዎስ 5:1313:33 ይመልከቱ)።

አልማ 37፥35–37

“ከጌታ ጋር ተማከር።”

አልማ 37:35-37ውስጥ ለልጁ ለሄለማን ያቀረባቸውን የአልማን ግብዣዎች ፈልጉ። ከእነዚህ ግብዣዎች ውስጥ በየትኞቹ ላይ እርምጃ እንድትወስዱ እንደተነሳሳችሁ ይሰማችኋል? ለምሳሌ “ከጌታ ተማከር” (ቁጥር 37) ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማሰላሰል ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ የሞከራችሁት እንዴት ነው? ወደ በጎ ነገር የመራችሁ እንዴት ነው?

አልማ 38

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን ምስክርነት ማካፈል የምወዳቸውን ሰዎች ሊያጠናክር ይችላል።

አልማ ለልጁ ለሺብሎን የተናገራቸው ቃላት ወንጌልን በመኖር የምንወዳቸውን ሰዎች እንዴት ማጠናከር እና ማበረታታት እንደምንችል የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። አልማ 38ን ማጥናት በኢየሱስ ክርስቶስ ጥንካሬ ያገኙ ዘንድ የቤተሰብ አባላትን እና ጓደኞችን ለመርዳት የሚሆኑ አንዳንድ ሀሳቦችን ሊሰጣችሁ ይችላል። የምታገኟቸውን በጽሁፍ አስፍሩ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶችን ዕትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 36፥6–24

ንስሐ በኢየሱስ ክርስቶስ ደስታን ያስገኝልኛል።

  • ልጆቻችሁ ንስሃ መግባት ደስታ እንደሚያመጣ እንዲገነዘቡ ለመርዳት በአንድ በኩል ደስተኛ ፊት በሌላኛው ደግሞ ያዘነ ፊት ያለበት ወረቀት ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። አልማ 36:13, 17–20ን በምታነቡበት ጊዜ እንዲያዳምጡ ጠይቋቸው እንዲሁም አልማ እየተሰማው የነበረውን ስሜት ለማሳየት ከሁለቱ ፊቶች አንዱን ከፍ አድርጋችሁ ያዙ። ከፍ ከፍ ያሉ ልጆች እንዴት እንደተሰማው የሚገልጹ ቃላትን ወይም ሀረጎችን ሊፅፉ ይችላሉ። አልማን ምን አሳዘነው ምንስ ደስታን አመጣለት። ከዚያም ንስሃ በምትገቡበት ጊዜ ስለሚሠማችሁ ደስታ ልትነግሯቸው ትችላላችሁ።

አልማ 37፥6–7

“በትንሽና በቀላል ነገሮች ታላቅ ነገሮች ተፈፅመዋል።”

  • ልጆቻችሁ ትልቅ ነገሮችን ሊያደርጉ የሚችሉ ትንሽ ነገሮችን በመፈለግ ሊደሰቱ ይችላሉ። እንደ ባትሪ፣ የመኪና ቁልፍ ወይም የሚጫወቱበት አሻንጉሊት የመሳሰሉ ነገሮች ምሳሌዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚያም አልማ 37፥6–7ን አብራችሁ ልታነቡና እግዚአብሄር እንድናደርጋቸው የሚፈልገውን አንዳንድ ትንሽ ወይም ቀላል ነገሮች ልናስብ እንችላለን። እነዚህን ትንሽ ወይም ቀላል ተዕዛዛት ስንጠብቅ ምን ትልልቅ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ?

  • ልጆቻችሁ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ሊሞክሩም ይችላሉ፦በአንድ ጊዜ አንድ ጠብታ በማድረግ አንድን ኩባያ በውሃ መሙላት መጀመር። ይህ ከአልማ 37:6–7 ጋር የሚገናኘው እንዴት ነው? ከዚያም በየዕለቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብን የመሳሰሉ የጌታ “ትንሽ እና ቀላል ነገሮች” እንዴት በኩባያ ውስጥ እንደሚንጠባጠቡ የውኃ ጠብታዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ በቤት፣ በትምህርት ቤት ወይም በቤተክርስቲያን ትልቅ ነገሮችን የሚያመጡባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ እርዷቸው። በተጨማሪም “‘Give,’ Said the Little Stream፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 236) ይህንን መርህ ያብራራል።

አልማ 37፥38–47

ቅዱሳት መጻህፍት በየቀኑ ሊረዱኝ ይችላሉ።

  • አልማ ሄለማንን እንደረዳው ልጆቻችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸውን ፍቅር እንዲያሳድጉ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? ስለእሱ የሚያውቁትን በሚያካፍሉበት ጊዜ የሊያሆናን ምስል (ለምሳሌ Gospel Art Bookቁ. 68) ማሳየትን አስቡ ወይም እንዲስሉት ጋብዟቸው (አልማ 37:38–471 ኔፊ 16:10፣ 28–29 ይመልከቱ)። ቅዱሳት መፃህፍት እንደ ሊያሆና የሆኑት እንዴት ነው?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የ ጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ለአልማ እና ለሞዛያ ልጆች መልአክ ሲገለጥላቸው።

ለአልማ እና ለሞዛያ ልጆች መልአክ ሲገለጥላቸውበክላርክ ቤሪ ፕራይስ