ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 16-22 “ራስህን አቅና፤ እናም ተደሰት።” 3 ኔፊ 1–7


መስከረም 16-22 ‘ራስህን አቅና፤ እናም ተደሰት።’ 3 ኔፊ 1–7፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“መስከረም 16–22 (እ.አ.አ) 3 ኔፊ 1–7፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ኔፋውያን ብርሃን ያልነበረበትን ቀን አዩ።

One Day, One Night, and One Day[አንድ ቀን፣ አንድ ምሽት እና አንድ ቀን፣ በጆርጅ ኮኮ

መስከረም 16-22 “ራስህን አቅና፤ እናም ተደሰት።”

3 ኔፊ 1–7

በአንዳንድ መንገዶች የአኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ መሆን አስደሳች ጊዜ ነበር። ትንቢቶች እየተፈጸሙ ነበር—በህዝቡ ፊት እየተፈጸሙ የነበሩት ታላላቅ ምልክቶች እና ተዓምራት አዳኙ በቅርቡ እንደሚወለድ ጠቁመዋል። በሌላ በኩል እነዚያ ሁሉ ተዓምራት የታዩ ቢሆንም የማያምኑ ሰዎች አዳኝ የሚወለድበት “ጊዜ አልፏል” ሲሉ አጥብቀው ይናገሩ ስለነበር ለሚያምኑትም አስጨናቂ ጊዜ ነበር (3 ኔፊ 1–5)። እነዚህ ሰዎች “በምድሪቱ ላይ ታላቅ ረብሻ” አደረጉ (3 ኔፊ 1:7) እንዲሁም በላማናዊው ሳሙኤል የተነበየው ምልክት ይኸውም—ጨለማ የሌለበት ሌሊት—ካልታየ አማኞቹን ሁሉ ለመግደል እንኳን ቀን ቆርጠው ነበር።

በነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ነቢዩ ኔፊ “ወደ አምላኩ ለህዝቡ ድገፋ በሃይል ጮኸ” (3 ኔፊ 1:11)። ስደት ወይም ጥርጣሬ ለገጠመው ለማንኛውም ሰው እንዲሁም ብርሃን ጨለማን እንደሚያሸንፍ ማወቅ ለሚያስፈልገው ሰው የጌታ ምላሽ የሚያነቃቃ ነበር፦“ራስህን አቅና፤ እናም ተደሰት…በቅዱሳን ነቢያቶቼ አንደበት እንዲነገሩ ያደረግሁአቸውን በሙሉ [እፈጽማለሁ]” (3 ኔፊ 1:13)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 1–7

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለወጥ ጥረትን እና ትዕግሥትን ይጠይቃል።

3 ኔፊ 1–7 ወደ ጌታ የተለወጡ እና ሌሎች ያልተለወጡ ሰዎችን ይገልጻል። በእነዚህ ቡድኖች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደረገው ምንድን ነው? እንደሚከተለው አይነት ቻርት ሃሳባችሁን እንድታደራጁ ሊረዳችሁ ይችላል፦

ለውጥን የሚያዳክሙ ነገሮች።

ለውጥን የሚያጠናክሩ ነገሮች።

3 ኔፊ 1፥5–11

የነቢዩን ቃላት አለማመን እና በጻድቅ ሰዎች ላይ መሳለቅ

በነቢዩ ቃላት ማመን እና ለእርዳታ መጸለይ

3 ኔፊ1:29–30

3 ኔፊ 2:1–3

3 ኔፊ 3:12–16

3 ኔፊ 4:8–10, 30–33

3 ኔፊ 6:13–18

3 ኔፊ 7:15–22

በምታጠኑበት ጊዜ የግል ጥያቄዎችን ጠይቁ። ለምሳሌ፣ ይህንን ቻርት በምትሞሉበት ጊዜ “እዚህ ምን ትምህርት እማራለሁ?” የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ልትጠይቁ ትችላላችሁ። ይህ ከመንፈስ ቅዱስ መነሳሳትን ያመጣል።

3 ኔፊ 1፥1–23

ምስል
seminary icon
በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት “ልደሰት እችላለሁ።”

የሰማይ አባታችሁ ሕይወታችሁ አስቸጋሪ የሆኑ ብሎም የሚያስፈሩ ወቅቶችን እንደሚያካትት ያውቃል። ነገር ግን ደስታንም እንድታጣጥሙ ይፈልጋል። ታማኞቹ ኔፋውያን መፍራት ስለነበሩባቸው ምክንያቶች ለመማር 3 ኔፊ 1፥1–23ን አንብቡ። ጌታ “ለመደሰት” ምን አይነት ምክንያት ሰጣቸው?

አዳኙ “ተደሰቱ” የሚለውን ሃረግ በተለያዩ ሁኔታዎች ተጠቅሟል—ለምሳሌ፣ በማቴዎስ 14:24–27ዮሃንስ 16:33ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61:3678:17–19። ስለነዚህ ግብዣዎችዎች ምን ያስደንቃችኋል? አዳኙ እነዚህን ቃላት የተናገረባቸውን ሁኔታዎች ለመረዳት በዙሪያው ያሉትን ጥቅሶች ልታነቡ ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ሁኔታ ሰዎች ፍርሃታቸውን እንዲጋፈጡ ለመርዳት ምን ምክንያቶችን ሰጠ? ይህንን ለናንተ ያደረገላችሁ እንዴት ነው?

“Joy and Spiritual Survival” የሚለውን የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን መልዕክት ሊያሆና ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 81-84) ማጥናትን አስቡ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ደስታን ስለማግኘት ፕሬዚዳንት ኔልሰን ምን ያስተምሯችኋል? ፕሬዚዳንት ኔልሰን ትኩረት የሚለውን ቃል ለምን ያህል ጊዜ እንደተጠቀሙ ልብ በሉ። ምናልባት የአንድን ካሜራ ወይም የሌላ ነገርን ሌንስ ትኩረት ማስተካከልን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ከማተኮር ጋር ታነጻጽሩ ትችላላችሁ። በእርሱ ላይ የበለጠ ልታተኩሩ የትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም በወንጌል ቤተመፃህፍት ውስጥ “የህይወት እርዳታ” በሚለው ክፍል ሥር “ሃዘን፣” “ተስፋ” “የዓእምሮ ጤና” ወይም ሌሎች ርዕሶችን ይመልከቱ)።

3 ኔፊ 1:4–215:1–3

ጌታ ቃሉን ሁሉ በጊዜው ይፈጽማል።

3 ኔፊ 1:4–7 አንብቡ እና ከአማኞቹ አንዱ ብትሆኑ ኖሮ እንዴት ተሰምቷችሁ ሊሆን እንደሚችል አስቡ። እምነታቸው ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ምን አደረጉ? (3 ኔፊ 1:4–21 እና 5:1–3)። የሣሙኤል ቃል የተፈጸመው እንዴት ነበር?( 3 ኔፊ 1:19–21 ይመልከቱ)። ጌታ በህይወታችሁ ቃሉን የፈፀመው እንዴት ነው?

3 ኔፊ 1:4–155:12–266:10–157:15–26

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነኝ?

ሞርሞን “እነሆ፣የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነኝ” ሲል ተናግሯል (3 ኔፊ 5:13)። ይህ ሃረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት ባህሪያት፣ እምነቶችን እና ተግባራት በመፈለግ 3 ኔፊ 1:4–15፣፣ 5:12–266:10–15፤ እና 7:15–26 ማንበብን አስቡ።

በተጨማሪም “እንደ ኢየሱስ ለመሆን እየሞከርኩ ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79 ይመልከቱ።

3 ኔፊ 2:11–12; 3:1–26

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን እምነት ስጠቀም ፍርሃት አያስፈልገኝም።

ኔፋውያን ከወንበዴዎች ቡድን ጋር የነበራቸው ተሞክሮ መንፈሳዊ አደጋዎች በሚያጋጥሟችሁ ጊዜ ሊረዷችሁ የሚችሉ ትምህርቶችን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። በ 3 ኔፊ 2፥11–12 እና 3፥1–26 ውስጥ እነዚህን ትምህርቶች ፈልጉ። ለምሳሌ የጊዲያንሒን ቃል በ3 ኔፊ 3:2–10 ልትፈልጉ እና ሰይጣን ሊያታልላችሁ ከሚሞክርባቸው መንገዶች ጋር ልታነፃፅሯቸው ትችላላችሁ። ከላኮኔዎስ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

3 ኔፊ 1:4–15፣ 19–21

ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ አዲስ ኮከብ ታየ።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ልጆቻችሁ፣ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ ኔፋውያን ስላዩዋቸው ተዓምራት እንዲማሩ ሊረዳቸው ይችላል። እንዲሁም “Chapter 41: The Signs of Christ’s Birth” (የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 114–16) ይህንን ታሪክ ልታስተምሯቸው—ወይም ለእናንተ ለመንገር እንዲረዳቸው ልትጠቀሙበትም ትችላላችሁ።

3 ኔፊ 1:4–21

የነቢያት ቃል ሁልጊዜ ይፈፀማል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ 3 ኔፊ 1:4-10ን ስታነቡ በዚያን ጊዜ ከነበሩት አማኞቹ አንዱ ቢሆኑ ኖሮ ምን ሊሰማቸው ይችል እንደነበር እንዲናገሩ ጋብዟቸው። ከዚያም በ ቁጥር 11–15ውስጥ ያለውን ቀሪውን ዘገባ ሲያነቡ የሚከተለው ዓረፍተ ነገር ሊሟላ ስለሚችልበት መንገድ ሃሳብ ሊሰጡ ይችላሉ፦ “ከዚህ ታሪክ የማገኘው ትምህርት…”

  • ምናልባት ልጆቻችሁ እግዚአብሔር በነቢዩ በኩል የገባቸውን የተስፋ ቃሎች ስለፈፀመባቸው ስለሌሎች ጊዜያት እንድታስቡ ሊረዷችሁ ይችላሉ። በ የወንጌል የአርት መፅሐፍ ውስጥ የእነዚህን ታሪኮች ምስሎች መፈለግን ሊወዱ ይችላሉ (ለምሳሌ ቁጥር 7–8 እና 81ይመልከቱ)። ስለእግዚአብሄር የተስፋ ቃል መፈፀም ጨምሮ ስለነዚህ ታሪኮች የሚያውቁትን ያካፍሉ። 3 ኔፊ 1:20ን አብራችሁ አንብቡ እና ስለእነዚህ እውነቶች ያሏችሁን የራሳችሁን ምስክርነት አካፍሉ።

3 ኔፊ 2:11–123:13–14, 24–26

በአንድነት ስንሰበሰብ ይበልጥ ጠንካራ እንሆናለን።

  • ልጆቻችሁ በ3 ኔፊ 2:11–12 እና 3:13–14, 24–26 ውስጥ ኔፋውያን በአንድነት ለምን እንደተሰበሰቡ እና ስለመጡላቸው በረከቶች እንዲያገኙ እርዷቸው። ዛሬ በቤተሰባችን ውስጥ እና በቤተክርስቲያን መሰባሰብ ለኛ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ስለህብረት ጥንካሬ የሚያስተምር ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገርን ታውቃላችሁ? ምናልባት ልጆቻችሁ በመጀመሪያ አንድን እንጨት ከዚያም አንድ ላይ የታሰሩ እንጨቶችን ለመስበር ሊሞክሩ ወይም አንድን ወረቀት ለመቀደድ እና ከዚያም የተደራረቡ ወረቀቶችን ለመቅደድ ሊሞክሩ ይችላሉ። እንደ እንጨቱ ወይም እንደ ወረቀቶቹ የሆንነው እንዴት ነው?

3 ኔፊ 5:12–266:147:15–26

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነኝ።

  • 3 ኔፊ 5:13 በአንድነት ካነበባችሁ በኋላ ልጆቻችሁ “የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነኝ” የሚለውን ሃረግ እንዲደግሙ ጋብዟቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመማር እነዚህን መሳሌዎች አብራችሁ አንበቡ፦የተለወጡት ላማናውያን (3 ኔፊ 6:14 ይመልከቱ)፣ ሞርሞን (3 ኔፊ 5:12–26 ይመልከቱ) እና ኔፊ ( 3 ኔፊ 7:15–26 ይመልከቱ)። “እንደ ኢየሱስ ለመሆን እየሞከርኩ ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79 በመሳሰሉ መዝሙሮች ውስጥም ሃሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ እጃቸውን ቀርፅ በቁራጭ ወረቀት ላይ እንዲስሉ እና ቆርጠው እንዲያወጡ እርዷቸው። በአንድ በኩል “የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነኝ” የሚል ፃፉ ከዚያም በሌላኛው በኩል የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ሊያደርጉ የሚችሉትን አንድ ነገር እንዲስሉ ጋብዟቸው።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ኔፋውያን ብርሃን ያልነበረበትን ቀን አዩ።

አንድ ቀን፣ አንድ ምሽት እና አንድ ቀን፣ በዋልተር ሬን